በብእሮቹ ጫፍ ስሜን አንከርፍፎ
ስፅፈኝ ይውላል
አመል መልኬን ሁሉ በወረቀት ፅፎ
ስጦታም ላከልኝ የእጁን ብራስሌት
ጥሩ ሰው ነው ብሎ አፌ እንዲያወራለት
ስለደግነቱ ልቤ እንዲሰብክለት
አይ እመነኝ እመነኝ !
ሠጠኸኝ ብዬኳ ጭራሽ አላየሁት
ከኪስ ነው እንጂ ከልብህ እንዳልህነ እኔ መች አጣሁት
እውነቱን ልንገርህ ?
አደለም ወረቀት ድንጋይ ላይ ብስለኝ
በደመናው ፈትለህ ልበሽው ብትለኝ
ፍፁም አታስበው ግና እኔ የምልህ
ብትሞትም ግድ የለኝ
ርካሽ ገላህን ስለምቀብርልህ እንዲያው አመስግነኝ
(kati 16)
@WAS143
@WAS143
ስፅፈኝ ይውላል
አመል መልኬን ሁሉ በወረቀት ፅፎ
ስጦታም ላከልኝ የእጁን ብራስሌት
ጥሩ ሰው ነው ብሎ አፌ እንዲያወራለት
ስለደግነቱ ልቤ እንዲሰብክለት
አይ እመነኝ እመነኝ !
ሠጠኸኝ ብዬኳ ጭራሽ አላየሁት
ከኪስ ነው እንጂ ከልብህ እንዳልህነ እኔ መች አጣሁት
እውነቱን ልንገርህ ?
አደለም ወረቀት ድንጋይ ላይ ብስለኝ
በደመናው ፈትለህ ልበሽው ብትለኝ
ፍፁም አታስበው ግና እኔ የምልህ
ብትሞትም ግድ የለኝ
ርካሽ ገላህን ስለምቀብርልህ እንዲያው አመስግነኝ
(kati 16)
@WAS143
@WAS143
❤7👍7🤣2
"አይደለም ምኞቴ"
አይደለም ምኞቴ....
ለምለም አንገትሽ ላይ፣ ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ፣ ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ፣ ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ፣ ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም፣ ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት፣ ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም።
ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ፣ ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ፣ ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ፣ ትዝታ መጋራት
የጨለመ ፊቴን፣ ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን፣ በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን፣ ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ፣ ዝምታሽን መስማት።
[ በእዉቀቱ ስዩም ]
@WAS143
@WAS143
አይደለም ምኞቴ....
ለምለም አንገትሽ ላይ፣ ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ፣ ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ
ከንፈርሽን ማለብ፣ ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ፣ ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም፣ ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት፣ ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም።
ምኞቴን ልንገርሽ?
ካለሺበት ቦታ፣ ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ፣ ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ፣ ትዝታ መጋራት
የጨለመ ፊቴን፣ ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን፣ በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን፣ ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ፣ ዝምታሽን መስማት።
[ በእዉቀቱ ስዩም ]
@WAS143
@WAS143
👍31❤24👌5🥰2😍1
ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)
ጀርመን በገባሁ በሁለተኛ ቀኑ ማካፋት ጀመረ፤ ዝናብ ያረጠበው አፈር ሽታ ናፈቀኝ ፤ እዚህ ደግሞ መሬቱ እንዳለ በኮብል ተሸፍኗል፤ ደግነቱ ከኢትዮጵያ ስወጣ አፈር በያይነቱ ቆጣጥሬ ነው የወጣሁት፤ ቀይ አፈር - ደባይ አፈር - የመቃብር አፈር- በርበሬ እንዲበረክት የሚያረግ አፈር- ሙሉቀን መለሰ ምነው ባደረገኝ ብሎ የተመኘው “የሚነፈራፈር አፈር”፤
ከሁሉም አፈር አይነት ቆነጣጥሬ፥ በጀርመን ዝናብ ለውሼ ማግ ሳደረገው እልል ያለ አጭሬ ግጥም መጣልኝ፥
“እንዴት ነሽ አገሬ
ከነገ አንጻር ሲታይ ደግ ቀን ነው ዛሬ
ስንት ገባ ይሆን የውጭ ምንዛሬ ?
ከጀርመን ከተማዎች ባንዱ እየተርመሰመስሁ ነበር ፤የሆነ መጸዳጃ ቤት ገብቼ ስሙኒ ከፍየ እጄን ታጠብሁ፤ አለንጋ ጣቶቼን ሳራግፍ ወለሉ ላይ ጥቂት ነጠብጣብ አረፉ፤ ወለል ጠራጊው ሽማግሌ ፈረንጅ ይሄን ሲያይ እንደማበድ አረገው፤
“ቫሩም?” ብሎ ቀወጠው፤ “ ጀርመንኛ ብዙ ባላውቅም፥ “ ምን ነካህ? እንዴት ልፋቴን መና ታደርገዋለህ?” ምናምን ማለት እንደሆነ ቀልቤ ነግሮኛል፤( እምገርመው ። ቀልቤ ከኔ የተሻለ ጀርመንኛ ያውቃል)
ጌታ ሆይ ! ብዙ ሺህ ማይል አቆራርጬ ፥ አውሮፓ ገብቼ ፥ ፈረንጅ የማናድድበት ሐይል የሰጠኸኝ እኔ ማን ነኝ? ብየ ተደነቅሁ፤
መልሼ ሳስበው ግን ተጸጸትሁ፤ ያንጠባጠብሁትን የውሀ ርጋፊ ላጸዳ መጥረጊያውን ብድግ ሳረግ ሰውየው እንደገና ተንደቀደቀ፤
ከውጭ የሚጠብቀኝን ዲያስፖራ ሰለሞን ሞገስን “ምንድነው የሚለው” ብየ ጠየቅሁት፤ ተረጎመልኝ፤
ጠራጊው ሽማግሌ እንዲህ ነው ያለኝ፤
“ውሀ ስታንጠባጥብ ታግሼሀለሁ፤ መጥረጊያየን ስትሰርቀኝ ግን እፋረድሀለሁ”
ሳያሳፍሰኝ አመለጥኩ፤
የሆነ ሰአት ብቻየን እየተራመድኩ አንድ ሀውልት አገኘሁ፤ ሀውልት ከማይሰምርበት አገር ስለመጣሁ ሀውልት ብርቄ ቢሆን አይገርምም ፤ ከሀውልቱ ስር ፎቶ ለመነሳት ፈለግሁ፤ አንድ ፈረንጅ ባጠገቤ ሲያልፍ ተከትየ በጀርመንኛ አንሳኝ አልሁት፤ ዝም ብሎኝ ሄደ፤ በላቲን ሳይቀር ጠየቅሁት፤ ገላምጦኝ ርምጃውን አፋጠነ፤
አይ ፈረንጅ! ከላይ ሲታዩ የተማሩ ይመስላሉ! ፎቶ በሞባይል እንዴት እንደሚነሳ እንኳ አያውቁም ፤ “ብየ ራሴን ለማጥናናት ሞከርኩ፤
አማራጭ ሳጣ ፥ሰልፊ ፊቴ ላይ ደገንኩ፤ ካሜራው የኔን ፊት እየዘለለ ሀውልቱን መቅረጽ ጀመረ፤ አጥብቆ ሆድ ባሰኝ! ሆድ ለባሰው ሞባይል አታውሰው! ድንገት ስልኬ ከመዳፌ ላይ ሲንሸራተት ይታወቀኛል፤ ቷ! ስልኬ በግንባሩ ክንብል ካለበት አንስቼ ሳየው ስክሪኑ የሸረሪት ድር ሪልስቴት መስሏል፤
በመጨረሻ ወደ ማረፊያ ቤቴ ስመለስ ሁለት ደጋግ ያገሬ ልጆችን አገኘሁ፤
ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁዋላ፤
“ የምትፈልገው ካለ ንገረን ?” አሉኝ ፤
“ ባስቸኳይ ወደ አገሬ መልሱኝ "

🤣18❤15👌7👏4
ተስፋ
*
አንት የአይሁድ ጠቦት
ፀረ ሽንፈት ንግርት
ደምህ እንደ መለኮት
ይጋርዳል ከሞት
ገፅህ ገራገር ጦር የሚደልል
ፍርጥም ትከሻህ ጋራ ሚከልል
የልብህ ስፋት አገር ሚያስጠልል
ሀሞትህ ሲመር መብረቅ የሚጥል
አንት ገብርዬ
ያልተምታታብህ ውልህ የለዬ
ጓደኝነትህ የአብራክ ክፋይ የወንድም ዘዬ
ባንተ ስመካ እንኳን ዘሮቼን እራሴን ጥዬ
ጥምዝም አታውቅ ቀጥ እንደማገር
አቋም ስትይዝ አታንገራግር
ሰው ስትደግፍ እስክትሰበር
ሰው ስትደገፍ ሳትጠራጠር
ፍፁም ገራገር
ፍፁም ወታደር
አንተ የልጅ ነፍስ
የጠላህ እንደው አታድበሰብስ
አታመነታም አፈር ስታለብስ
የወደድክ እንደው ስትተናነስ
ለታናሽ ቁጣ መልስ የማትመልስ
እንደ ባልጩት ስል እንደላባ ስስ
ላመንከው ስትሰጥ አትተምንም
እጣህን ሽሽት አትለምንም
እንደ ፈላስፋው አንስተህ ግጥም
አንተን መሆን ነው የወንድ ልጅ ጥም
@WAS143
@WAS143
*
አንት የአይሁድ ጠቦት
ፀረ ሽንፈት ንግርት
ደምህ እንደ መለኮት
ይጋርዳል ከሞት
ገፅህ ገራገር ጦር የሚደልል
ፍርጥም ትከሻህ ጋራ ሚከልል
የልብህ ስፋት አገር ሚያስጠልል
ሀሞትህ ሲመር መብረቅ የሚጥል
አንት ገብርዬ
ያልተምታታብህ ውልህ የለዬ
ጓደኝነትህ የአብራክ ክፋይ የወንድም ዘዬ
ባንተ ስመካ እንኳን ዘሮቼን እራሴን ጥዬ
ጥምዝም አታውቅ ቀጥ እንደማገር
አቋም ስትይዝ አታንገራግር
ሰው ስትደግፍ እስክትሰበር
ሰው ስትደገፍ ሳትጠራጠር
ፍፁም ገራገር
ፍፁም ወታደር
አንተ የልጅ ነፍስ
የጠላህ እንደው አታድበሰብስ
አታመነታም አፈር ስታለብስ
የወደድክ እንደው ስትተናነስ
ለታናሽ ቁጣ መልስ የማትመልስ
እንደ ባልጩት ስል እንደላባ ስስ
ላመንከው ስትሰጥ አትተምንም
እጣህን ሽሽት አትለምንም
እንደ ፈላስፋው አንስተህ ግጥም
አንተን መሆን ነው የወንድ ልጅ ጥም
@WAS143
@WAS143
❤26👏4😢1
ቀብዲ
(በእውቀቱ ስዩም)
በዚህ ዓለም ላይ እንደ ዘፋኝ የታደለ የለም፤ አንድ ነጠላ ዜማ ሰርተህ ድርብርብ ህይወት ትኖራለህ፤ ስቴድየም ሙሉ ታዳሚ ታስጨፍራለህ፤ ታዋቂ ዘፋኞች ባንድ መድረክ የሚያገኙት ገንዘብ የኢትዮጵያን ህዝብ አመታዊ በጀት ያክላል ቢባል ማጋነን ይሆናል፤ ዘፋኝ መንግስተ ሰማያት አይገባም የሚባለው አለምክንያት መስሎሀል? ዘፋኞች የመንግስተ ሰማያት ድርሻቸውን እዚህ ምድር ላይ ጨርስዋል፤ ሁለቴ መንግስተ ሰማያት የለም፤
ይብላኝ ለገጣሚ! እውነተኛ ሰማእታት ማለት እኛ ነን ፤ እልም ባለው ወበቅ “ስካርፍ” እምንለብሰው ወደን አይደለም፤ ሆድ ቢብሰን ለመታነቅ እንዲያመቸን ነው፤
ይህ በእንዲህ እያለ፥ ባለፈው ግሪንላንድ ሚባል አህጉር ውስጥ የሚኖር አንድ ዲያስፖራ የግጥም ምሽት እንዳዘጋጅ ጋበዘኝ ፤
“ የፕሌን ትኬት ታሰናዱልኛላችሁ?”
“በጀት የለንም ! እንደ ፍራሽ የሚነፋ ጀልባና የሚያሻግሩህ ሰዎችን አዘጋጅተናል” ሲለኝ ሙያየን ጠላሁት፤
ባለፈው ደግሞ “አላስካ” የተባለ ጠቅላይ ግዛት ሄድኩ፤ አላስካ ማለት ሩሲያዎች “ብርድ ያስመታናል “ብለው ለአሜካኖች የሸጡላቸው ያገር መስኮት ነው፤
ካውሮፕላን ስወርድ አንድ ብርቱ ዲያስፖራ ተቀበለኝ፤ “አበባ ይዘው የሚጠብቁኝ ቆነጃጅት ጠብቄ ነበር ’ አልሁት፤
‘ወገኛ ነህ ባክህ! እዚህ አገር አመቱን ሙሉ ክረምት ነው፤ ካገራችን ከወጣን ወዲህ አበባ አይተን አናውቅም ፤ “ አለና የምጎትተውን ሻንጣ ብድግ አርጎ አሸከመኝ፤
“እሺ አበባውስ ይቅር፤ የቆነጃጅቱስ ነገር? “ አልሁት፤
“ሲጀመር ቆነጃጅት ከሆኑ ስንት እድል እያላቸው እዚህ፥ የግዜር ፍሪጅ የሆነ አገር ለምን ይመጣሉ? እኛም ካናዳ የለመግባት ስንሞከር ተቆርጠን ቀርተን ነው” አለኝና መኪናው ውስጥ ገፍትሮ አስገባኝ ፤
በጥሩንባና በነጋሪት ተቀስቅሶ ለዝግጅቴ የመጣው ዲያስፖራ አስራ ሁለት አይሞላም፤ ፕሮሞተሩ ለዶዶራንት መግዣ የሚበቃ ቀብድ ሰጠኝ ፤ ዝግጅቴን ለመታደም ከመጡት ሰዎች ፥ልጅ ሚካኤል ሲያትል ላይ ሲዘፍን ያጀቡት ፖሊሶች በቁጥር ይበልጣሉ፤ አብዛኞቹ አሳ ሲያጠምዱ፥ ለዶልፊን አክሮባት ሲያለማምዱ፥ ሻርክ ሲበልቱ ውለው ስለመጡ ከፍተኛ ድካም ይነብባቸዋል ፤
የገቡት አብዛኞቹ እኔ እያነበብሁ እንደ ሰነፍ ተማሪ ዴስካቸው ላይ ተኝተዋል፤
ከዝግጅቱ በሁዋላ አዘጋጁን ካጠገቤ አጣሁት ፤ በስንት ፍለጋ ከአዳራሹ ጀርባ ባለው ባር ውስጥ ጅን በበረዶ እየጣጣ ሲያለቅስ አገኘሁትና፥ ለበረዶው ከፍየ አጽናንቼው ዞር ስል፤
“በውቄ “ አለኝ ፤
“ወየ”
“ ቅድም ከሰጠሁህ ቀብድ ላይ ትንሽ ልታበድረኝ ትችላለህ? “

❤17😁17🤣11🤩2🥰1
እማኝ
(በእውቀቱ ስዩም)
በትህትና ጎንበስ ሳልል ፤ በእብሪት ሳልንጠራራ
ሳልወድቅ እንደዋንዛ ፍሬ ፤ ሳልመጥቅ እንደ ባቢሎን ህንጻ ጣራ
ባንቺ ጉዳይ ስወቀስ፥ ራሴን ነው እማኝ ምጠራ::
እኔ ነኝ አመት ባልሽ፥ እኔ ነኝ የድል ቀንሽ
የደረሰ ምርቃትሽ፥ የከሸፈ ርግማንሽ
ዓይንሽን የገለጥሽበት ባውዛ
አፍሽን የፈታሽበት ፊደል፤ አፍንጫሽን የከፈተ መአዛ
ላስለቅስሽ የምችል፤ ላስቅሽም የማይሳነኝ
ሲሻኝ ሆድ አባባሽሽ፥ ስፈልግ አጫዋችሽ ነኝ፤
የመርዶሽ ቀን እንባም ነበርሁ ፤ የምስራችሽ እልልታ
የተሳሳተ ውሳኔሽ፥ቁማር የተበላሽበት ካርታ
የለመድሽው እንቅፋት ፥እግርሽን እንደ ማግኔት ጎታች
ደጋግሞ የዘረረሽ፥ ከውድቀት ወለል በታች
መቀነትሽ ሁኘ አድሬ፤ ሲነጋጋ የጎን ውጋት
አንዳንዜ ድክመትሽ ነኝ፤ አንዳንድዜ ደሞ ብርታት
የከበረ ህመምሽ ነኝ ፤የዘውድ ስር ራስ ምታት፤
የገነትሽ አበባ ነኝ፤ የገሀነምሽ ቁራጭ ፍም
መጠኔ ከዚህ አያንስም፤ ድርሻየ ከዚህ አያልፍም፡ ፡
@WAS143
@WAS143
(በእውቀቱ ስዩም)
በትህትና ጎንበስ ሳልል ፤ በእብሪት ሳልንጠራራ
ሳልወድቅ እንደዋንዛ ፍሬ ፤ ሳልመጥቅ እንደ ባቢሎን ህንጻ ጣራ
ባንቺ ጉዳይ ስወቀስ፥ ራሴን ነው እማኝ ምጠራ::
እኔ ነኝ አመት ባልሽ፥ እኔ ነኝ የድል ቀንሽ
የደረሰ ምርቃትሽ፥ የከሸፈ ርግማንሽ
ዓይንሽን የገለጥሽበት ባውዛ
አፍሽን የፈታሽበት ፊደል፤ አፍንጫሽን የከፈተ መአዛ
ላስለቅስሽ የምችል፤ ላስቅሽም የማይሳነኝ
ሲሻኝ ሆድ አባባሽሽ፥ ስፈልግ አጫዋችሽ ነኝ፤
የመርዶሽ ቀን እንባም ነበርሁ ፤ የምስራችሽ እልልታ
የተሳሳተ ውሳኔሽ፥ቁማር የተበላሽበት ካርታ
የለመድሽው እንቅፋት ፥እግርሽን እንደ ማግኔት ጎታች
ደጋግሞ የዘረረሽ፥ ከውድቀት ወለል በታች
መቀነትሽ ሁኘ አድሬ፤ ሲነጋጋ የጎን ውጋት
አንዳንዜ ድክመትሽ ነኝ፤ አንዳንድዜ ደሞ ብርታት
የከበረ ህመምሽ ነኝ ፤የዘውድ ስር ራስ ምታት፤
የገነትሽ አበባ ነኝ፤ የገሀነምሽ ቁራጭ ፍም
መጠኔ ከዚህ አያንስም፤ ድርሻየ ከዚህ አያልፍም፡ ፡
@WAS143
@WAS143
❤22👏5🥰2🤣1
ምክክሩ
(በእውቀቱ ስዩም)
የሆነ ጊዜ ላይ እኔ ፥ ምኡዝ መና እና ካሳ በጠረጴዛ ዙርያ እየመከርን ነው፤ የምክሩ ምክንያት ካሳ ነበር፤ ካሳ በሙያው መሀንዲስ ሲሆን በትርፍ ጊዜው ፖለቲካዊ ግጥም ይጽፋል፤ ግጥሙ ብዙ ወዳጅም ጠላትም አፈራበት፤
ከጊዜ በሁዋላ ካሳ ጭንቀት ውስጥ ወደቀ፤ ከኛ ከወዳጆቹ መፍተሄ ፈለገ፤
“ መንግስት ቤቴ ውስጥ ስውር ካሜራ ያስገጠመ ይመስለኛል፤ ከሴቶች ጋር ስጫወት ቀርጸው፥ ገመናየን ለህዝብ ለመበተን እንዳቀዱ ጠርጥርያለሁ፤ ምከሩኝ” አለ ካሳ፤
“ካሜራ እንዳለ በምን አረጋገጥክ”? ስል ጠየቅሁት፤
“ካሜራው ስውር ስለሆነ ያይሀል እንጂ አታየውም፤ ደሞ አምፖል ራሱ ካሜራ ሊሆን ይችላል፡ ባሁኑ ጊዜ ዘመናዊ አምፖሎች የኤሌክትሪክ ለምድ የለበሱ ካሜራዎች ናቸው" ሲል መለሰ፤
“በቃ አምፖል መጠቀም አቁም! በርከት ያለ ጧፍ ገዝተን እናበረከትልሀለን”
አልኩት እየሳቅሁ፤
መና ኮስተር ብላ “ በማይቀለድበት አትቀልድ “ ብላ ከገሰጸችኝ በሁዋላ ወደ ካሳ ዞራ እንዲህ አለችው፤
“ ያንተ ችግር ምን መሰለህ፤ ብዙ ሴቶችን ትወዳለህ፤ ብዙዎችን ቤትህ ትጋብዛለህ፤ ለወንድ ልጅ ትልቁ ደስታ በሴት መታቀፍ መሆኑን አውቃለሁ፤ በሌላ በኩል ታጋይ እና የህዝብ ነጻ አውጭ የመሆን ፍላጎት አለህ፤ ግን ማወቅ ያለብህ አንድ ነገር አለ! ባንድ ጊዜ ጀግና እና ደስተኛ መሆን አይቻልም፤ የፖለቲካ ትግል መስዋእት የሚጠይቅ ነገር ነው፤ መስዋእት የግድ ህይወትን ማጣት ላይሆን ይችላል፤ ግን የምትወደውን ነገር ማጣት፤ ከስጋ ደስታ መቆጠብ ፥ ምቾትህን መቀነስ ግዴታህ ነው! አንድ ቋሚ ፍቅረኛ ያዝ፤ አግባ! ይህን ስታደርግ ፥ጠላቶችህ አንተን የሚያጠቁበትን አንድ መሳርያ አሳጣሀቸው ማለት ነው”
ከመና ቀጥሎ የተናገረው ምኡዝ ነው፤
“ ስማኝ ካሳ-ኖቫ” አለ ምኡዝ፤ “ በስውር ካሜራ እየቀረጹኝ ነው ብለህ ካሰብህ አይቀርጹህም ብየ ላጽናናህ አልችልም ፤ የመናን ምክር መቀበል የምትችል ሰውም እንዳልሆንክም አውቃለሁ፤ አለሌ መሆንህ አሌ የሚባል ነገር አይደለም፤ ካንተ ጋራ ስነጻጸር እኔ ያልተጎመደብኝ ስልብ ነኝ ማለት እችላለሁ፤ ሴቶችን ተው ከምትባል ፖለቲካውን ተው ብትባል ይቀልሀል፤ ሰለዚህ እኔ እምመክርህ ከሴቶች ጋር ስትናዳ ጥሩ አርገህ ንዳ !(ንዳ የሚለውን ቃል በዋናው ተክተው ያንብቡት -ደራሲው ) ፤
እንደ ተቆረጠ የእንሽላሊት ጅራት እየተላወስህ፤ ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተቅመደመድህ አንገታችንን እንዳታስደፋን አደራ ! በካሜራ እየተቀረጽህ እንደሆንክ እያሰብክ ፥ ለታሪክ የሚቀመጥ ስርያ እያበረከትህ እንደሆነ በማሰብ፥ ባለ በሌለ ጉልበትህ ንዳ ! በሁዋላ ቪድዮው ወጥቶ ሲታይ ህዝቡ” አጅሬ! ለካ ፖለቲካው ላይ ብቻ ሳይሆን አልጋ ላይም ጀግና ነው ብሎ እንዲያደንቅህ ያስፈልጋል! “
ምክሩ ፤ በመና ረጅም ሳቅ ተቁዋረጠ::

❤18🤣9😍1
እረ ጎበዝ ! ሰው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ትግስት እየቸገረው ነው፤ በአንድ ደቂቃ የሚጠናቀቅ ዘፈን ተጭኖ አላያችሁም? እኔ አብሬ ለመዝፈን ጉሮሮየን ስጠርግ ዘፈኑ ተጠናቋል !
ባንጻሩ “ ስቅ አለኝ” የሚለውን ፥ በየአመት በአሉ የሚከፈተውን የሰለሞን ደነቀን ቆንጆ ዘፈን አስቡት ! ያ ዘፈን ከልቡ ረጅም ነው! በጉን ገዝተን ፥ አርደን፥ ቆዳውን ሸጠን ስንመለስ እንኳ ዘፈኑ ገና “መሀረሜን አያችሁ “ Season ላይ ነው፤
ምኡዝ እንደሚለው -
“የዘመናችን ሰው ሰላሳ ደቂቃ የሚፈጅ ድንቅ ዶክመንተሪ ለማየት ትግስት የለውም፤ እያንዳንዳቸው፥ አንድ ደቂቃ የሚፈጁ ሰላሳ ስድድቦችን ቲክቶክ ላይ ለማየት ግን ጊዜ አያጣም”
ሰሙኝማ ! የእንቁላልን ችግር ለመቅረፍ ተጨማሪ ዶሮ እናርባ ወይስ ብሄራዊ ጦም እናውጅ በሚለው ዙርያ ሊቃውንት በሚወዛገቡበት በዚህ ቀውጢ ሰአት ፤ ቲክቶክ ላይ ወጣቱ ፤ "ሴጋ እንምታ ወይስ አንምታ?" በሚል አጀንዳ ላይ ተጠምዷል ፤ እምደንቅ ነው!
ዠለስ እነደኔ እንደኔ፤ በባዶ ኪስ ወልደህ ፥ ልጅህን ከምትመታ -
እያረፍህ ምታ !
መቼም መላ አትመታ!

🤣10❤9😁2
የሚያይና የሚያሳይ
(በእውቀቱ ስዩም)
ለእናት አገሬ ወይ ቦንድ አልገዛሁ፥ ወይ ቦንብ አልወረወርሁ፥ እንዲችው ስማስን እድሜን ገፋሁት፤
ከሁሉ የሚቆጨኝ የሆነ ጊዜ ላይ፥ ሰፈራችን ውስጥ ሳምንቱን ሙሉ ውሀ እልም ብላ ጠፋች ፤ ሆድ ቢብሰኝ “ ከመሀል ከተማ ወስደው ነው እንዴ የሚገድቡት ?“ ብየ ያማረርሁትን ሳስበው እስካሁን ይጠጥተኛል ፤ በውነት ግሳጼ የሚገባኝ ግም-ጃ ለባሽ ሰው ሰው ነኝ ፤
አድምጡኝማ ! ቲክቶክ ላይ፥ አንድ ሰው፥ በእንካስላንትያ መዝገበቃላት ውስጥ ለማካተት የሚከብድ ስድብ ተሳድቦ “አንበሳ ይወርድለታል” ፤ በባንጻሩ እኛ ፌስቡል ላይ የምንቸከችክ ሰዎች “ አንበሳው !“ “አንበሲት” ከሚል ቃል ያለፈው ደመወዝ የለንም፤ ለነገሩ ተመስጌን ነው ! ይህንንስ ማን አየብን !
በቀደም አንድ ወጣት ፥ አገር አማን ነው ብሎ የእግረኛ መንገዱ ዳር የተተከለውን ሳር በዘመናዊ ማጭድ ሲያጭድ ፥ ያንድ ክፍለከተማ ህዝብ ከበብ አድርጎ ሲመሰጥበት የሚያሳይ ቪድዮ” Sura ገጽ ላይ አይቼ ነበር፤ መቼም አታምኑኝ ግን በቦታው ነበርኩ፤
"ጊዜው ካፍያ ነበር ትንሽ ጨለም ብሎ
‘አባቴ ሲጠራኝ እያለ ና ቶሎ !”
አንድ ጎብዝ ወጣት ፤ አገር አማን ብሎ-
-በዘመናዊ ማጭድ እያጨደ እያለ ቀና ሲል ሰው ሰፍ ብሎ ይሾፈዋል፤ መጀመርያ ምን አጠፋሁ ብሎ ተደናገረ፤ የህዝቡ አስተያየት የወቀሳ ሳይሆን የጉጉት መሆኑን ለመገንዘብ ጊዜ አልፈጀበትም፤ ወድያው ወጣቱ ከወዛደርነት ወደ ሰርከስ ባለሙያነት ተቀየረ፤ ማጭዱ የገጠር ወፍጮ ድምጽ ያወጣ ነበር፥ ወጣቱ ሂሊኮፍተር ሞድ ላይ አደረገው፤ ማጭዱን በእግሩ መሀል አድርጎ እንደ ማጂክ መጥረጊያ እየጋለበ ማጨድ ጀመረ፤
ተሰብስበው ከሚያዩት ሰዎች አንዱ “ ሞራል ያንሳል ወገን “ ብሎ ካስጨበጨበለት በሁዋላማ ፥ማን ይቻለው?! ከታጨደው ሳር ዘግኖ አድቦልቡሎ ጢባጢቤ መጫወት ጀመረ፤
ጭራሽ ቪድዮው ሶሻል ሚድያ ላይ ሲለጠፍ ብዙ ሺ ሰው ማየቱን አስተውያለሁ፤
ባለፈው ፥ “አዝናኝና አስተማሪ ቪድዮ ሰርቼ ፥ ጭኜ ተመልካች አጣሁ” እያልህ ስታንቧቅስ የነበርከው ዠለሴ ! ለምን አጨዳ አትጀምርም?
እንግዲህ፥ አጫጁ ሰሞኑን ስልካችን ላይ ይከሰትና፥
“ያጨዳውን ትእይንት ተመልክታችሁ የወደዳችሁት ከታች አንድ ቁጥር ጻፉልኝ፤ ነገ ደግሞ ስከምርና ስወቃ የሚያሳየውን እለጥፋለሁ፤ ላይክ ሼር ኮፒሊንክ ማድረጉ እንዳይረሳ “

❤26😢3👍1
'ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት፤ ቡሄ ካለፈ የለም ክረምት “የሚል አባባል ቢኖርም ፥ክረምት የቡሄን ድንበር ይሻገራል፤ በሊቃውንት ምደባ፤ ክረምት በሰኔ ሀያ ስድስት ይጀምርና፥ መስከረም ሀያ አምስት ላይ ያልቃል፤ ዘመን መለወጫን የምናከብረው ከክረምት ሳንወጣ ነው፤
በነባሩ አማርኛ ፥ክረምቱን እንዴት አሳለፋችሁ ለማለት “ አንዴት ከረማችሁ? ይባላል ፤ በጋውን እንዴት አሳለፋችሁ ለማለት ደግሞ” እንዴት ባጃችሁ “ ይባላል፤
አውሮፓ እና አሜሪካ ውስጥ ባሉት ብዙ ቦታዎች ዘመን ሲለወጥ፤ አየሩ ዳፍንታም ነው፤ በብዙ ስፍራ ሰውነትን የሚቆረጥም በረዶ ይፈላል፤ ዓመት በአሉን ፥ ከአዘቦት ለመለየት ይቸግረኛል፤
ባንጻሩ፥ በኢትዮጵያ ዘመን ሲለወጥ ሌላ ነው ፤ ዙርያ ገባው በውበት በህያውነት ይሞላል፤ የሰው ልቦና በመደነቅ እና በምስጋና ይጠመዳል ” ሰማይን በኮከብ ፤ ምድርን በአበባ አስጌጠ’ የሚል ይዘት ያለው የያሬድ መዝሙር ያለ ይመስለኛል ፤ ጸሀፌ ትዝዛዝ ገብረስላሴ “ መስከረም እና መንግስት ሁሌ አዲስ ነው “የሚል ፈሊጥ ነበራቸው፤
በዘመን መለወጫ ላይ የስሜት ህዋሶቻችን ልዩ ድግስ ይቀርብላቸዋል -አበባ ! ችቦ! እጣን! ቄጤማ ! አዲስ ልብስ፥ አዲስ ዜማ!
ወንዶች 'ኢዮሀ' ሴቶች 'እልል' በማለት በውስጣቸው ያለውን ፍስሀ ይገልጻሉ፤
የኢትዮጵያ ህዝብ በአል ማክበር የሚያውቅ ህዝብ ነው፤ አብሮ ይበላል፤ ተቸግሮ ሳለ፥ የባሰ ለቸገረው ከበረከቱ ያካፍላል ፤
ለቅድስና የምንሰጠው ትርጉም እንደየ አመለካከታችን እንደየእምነታችን ይለያያል፤
ለኔ፥ ህይወትን፥ ፍጥረትን፥ ውበትን ፥ ኪነትን ፥ ፍቅርን ርህራሄን የሚያከብር ሁሉ ቅዱስ ነው፤
እንኳን ኖርን !
እንኳን አደረሰን !

❤16🥰2
እየለመንኳት ነበር ።
"አሞኝ ስነቃ አጠገቤ አልነበርክም" አለችኝ ። "አይኔን እንደገለጥኩ አንተን ነበር የጠበኩት" አለችኝ ። "የኔ ስቃዬ ላንተ አያሳስብህም" አለች።
የገጠመኝን ትብታብ አስረዳኋት !! ይቅርታ ጠየኳት !
"ውሰጤ ላንተ ያለው ነገር ቀንሷል" አለች። "እኔ እንደዚህ ነኝ" አለችኝ። "ሞከርኩ ውስጤ እምቢ አለ" እያለች ገፋችኝ ።
እንዴት እንደለመንኳት ፣እንዴት እንደተፀፀትኩ ስንት አማላጅ እንደላኩ ፤ብዙ ዱካካም ቀን ውስጥ ቆየው
"እኔ እንዲ ነኝ..." እያለች ፣ ግዜያዊ ስሜቷን እየቀነሰች እየደመረች ተለየችኝ ፤
ተፋታን!!
ሁሉን አውቃላሁ ባይነትን የሚያህል ከባድ ደዌ የቱ ነው??
ዙሪያዋ ላሉ ሰዎች ቆራጥ መሆኗን ለማስመስከር ፣
ዙርያዋ ያሉ ሰዎች ስላጋጋሉት ዙሩን አከረረችው " እንለያይ" አለችኝ።
ተለያየን !!
ሰነፍ ሰው የከበበው ሰውን እንዳገባ አይነት አደገኛ የሆነግዜ ፈንድቶ ልበ ጎዶሎ አንደሚያደርግ ከባድ ወጥመድ የታጠረ አይነት ምስኪን ሰው የለም !!
ስናጠፋ የማይቆጣን ፣ አስቡበት የማይለን፣ መንገድ የማይጠቁመን ፣ ማዘንበላችንን የማይነግረን የሌለን ሰው በዝናብ በነጭ ልብስ ዘንጦ ጭቃማ ሰፈር እንሚንጎራደድ አይነት ነው
ቀን ሄደ ......
ለሷ የነበረኝ ስሜት፤ ለኔ የነበራት ስሜት እንደተቀየረ አይነት ተቀየረ ..... ግዜ አከመኝ ።
ለኔ የነበራት ስሜት ዳግም ወደ ጥሩ እንደተቀየረ ምልክት ፍላጎት አሳየችኝ ......
"ጎጆ በስሜት በጀብድ እንደማይፀና ገባኝ " አለች ......አርፍዳ ነበር.....
©Adhanom Mitiku

❤23👍6👌3👎1👏1
"ቀኑ እንዴት ይመሻል ያንን ሳናነሳ"
(በእውቀቱ ስዩም)
አዝማሪ ወርቄ (ሻምበል ወረቀት) እንዲህ ይል ነበር፤
“ቢናገሩ አፈኛ፤
ዝም ቢሉ ሞኝ
ቢወፍሩ ዝሆን፥ ቢቀጥኑ ትንኝ ‘
አወይ ሰው! አወይ ሰው! ሰው አስቸገረኝ”
ካዝማሪው የተረፈውን እነዲህ መዘርዘር ይቻላል-
ብትጋብዝ “ አባካኝ “ ትባላለህ- ብትቆጥብ “ ቁዋጣሪ” - ብታሞግስ “ አሽቃባጭ፥- ብትተች” አቃቂረኛ- ብትቀመቅም “ሰካራም” ባትቀመቅም “ አብሿም”- ሴቶች ቢቀርቡህ “አተራማሽ -የሴት ድሮን” ‘ - ሌጣህን ብትሆን “ስልብ “ ወይም “ ጌ”
ሸሸግ ብትይ “ ምነው ጠፋሽ “ - ብቅብቅ ብትይ” ምነው እዩኝ እዩኝ አበዛሽ “ - ባያምርብሽ “አመዳም “ -ቢያምርብሽ “ፊልተራም” ወይም “ዱቄታም” -ብትጨምቺ “ አንገት ደፊ አገር አጥፊ፤ “ ነጻ ብትሆኝ ‘ ሸሌ”
እንደ መካሪ ሲቃጣኝ እንዲህ እላለሁ-
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትገኝ ከሰዎች ምዘና እና ካስተያየት አታመልጥም፤ የሚመዝን ማጉደሉ አይቀርም፤ ዠለስ! እንዳመጣጡ ኑር፤ ዠለሲት እንደፍጥርጥሩ ኑሪ፤ ልብሽን ተከተይ፤ ህግ እስካልጣስህ ድረስ ፥ ሰዎችን እስካልጎዳህ ድረስ ማድረግ የሚገባህን ከማድረግ አትቆጠብ፤
የሆነ ዘመን ላይ አንድ ባላባት ካድዋ ዘመቻ ተመልሰው በህዝብ ፊት ሲፎክሩ ደመቅ ያለ ፈስ አመለጣቸው ፤ ነዋሪውም በታላቁ ዘመቻ ላይ፥ አራት ጣልያን መግደላቸውን ቸል ብሎ ለአራት ሰኮንዶች ያክል አየር ላይ በቆየው ፈሳቸው ዙርያ በማውራት ተጠመደ ፤ ባላባትየው ለህዝቡ ጥሩ ነገር በመስራት ገጽታቸውን ለመገንባት ወሰኑ ፤ አስር በሬ አርደው የአገሩን ሰው ጠርተው አበሉት፤ "እኒያ አስር በሬ ያበሉት ጌታ" እየተባሉ እንዲነሱ ተመኝተዋል፤
ከተበላ ከተጠጣ በሁዋላ አንዱ አዝማሪ ብድግ አለና እንዲህ አቀነቀነ፥
“እንኩዋን አስር በሬ ቢታረድ ሰላሳ
ቀኑ እንዴት ይመሻል ያንን ሳናነሳ 🙂

🤣16❤14😁8👏3🤬1
እየተቀራረጽን
(በእውቀቱ ስዩም)
ዘጠና የጎረመስኩበት እንጂ የተወለድኩበት ዘመን አይደለም፤ ግን የዘጠናዎቹ ሰው ነኝ ለማለት አላቅማማም ፤” የኔ ዘመን የምንለው የተወደድንበትን እንጂ የተወለድንበትን አይደለም “ ይል ነበር ምኡዝ::
ዘጠና እውነትም ገራሚ ዘመን ነበር፤ ለመጀመርያ ጊዜ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ መጣጥፍ ጽፌ ሰላሳ ብር ተከፍሎኛል፤ ስነጽሁፍን ሙያየ ብየ የያዝኩት በይሁዳ በጀት ነው ማለት ነው፤ ያኒ ገንዘቡ አላልቅ ብሎኝ፥ማስቀመጫ ሁሉ ቸግሮኝ ትከሻየ ላይ ሳይቀር ተጨማሪ ኪስ ለመሰፋት ተገድጃለሁ፤
የምር በጊዜው ገንዘቡ በረከት ነበረው፤ የሚገርመው ያኔ የመዝናኛ ጊዜ እጥረት እንጂ የብር እጥረት ስላልነበረ “ይደገም ቅዳሜ “ የሚል ዘፈን ሁሉ ተዘፍኖ ነበር፤ አሁን ቅደሜ ሲመጣ በጀታችንን ቁርሳችን ላይ ጨርሰን ቅዳሜ ራሱ ከወረፋው ቀድሞ የገባ እሁድ እየሆነብን ተቸግረናል :;
ድሮ ደመበራድ ሰው ነበርሁ፤ አሁን ኑሮው ነው መሰል ሳር ቅጠሉ ያበሳጨኛል፤ ባለፈው አንድ ወዳጄ ከወገን ተደብቄ ቁርስ ከምበላበት ምግብ ቤት ፥ በፓራሹት ይሁን በአምባሳል ማር ቆራጭ ገመድ አላወቅሁም -ዱብ አለ፤ ከዚያ ቀለል ያለ ሳምቡሳ ያዝዛል ብየ ስጠብቅ ፤ በከፍተኛ ጭካኔ፤ ሁለት ተጨማሪ እንቁላል ያለው እንቁላል ፍርፍር ፤በማዘዝ ቀልቤን ገፈፈው፤
ጭራሽ አስተናጋጁን ጠርቶ “ እንቁላሉ ግን የፈረንጅ ነው ያበሻ ?” ብሎ ሲመራመር ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም፤
“ አንት የሰላቢ ልጅ ! ቅርፊት እና አስኩዋል ይኑረው እንጂ እንቁላሉ የአፍጋኒስታንስ ቢሆን ምን አባህ አገባህ? አሁን አንጥሬ ሳላዳምጥህ የቀረበልህን በልተህ፥ የጀጎል ግንብ ግንባርህን እስኪመታህ ድረስ ሽሽ “ ብየ ገሰጽሁት፤ አኩርፎ ጥሎ ይሄዳል ብየ ጠብቄ ነበር፤ እሱ ግን አኩርፎ መብላቱን ቀጠለ፤
የኑሮ ውድነቱ ያልቀየረው ነገር ቢኖር የመረዳዳት ባህላችንን ነው፤ ባለፈው አንድ አንጋፋ ተዋናይ ምኒባስ አባርረው ሲሳፈሩ የሚያሳይ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ተለቅቅቆ ህዝቡ አዝኖላቸው የመኪና መግዣ እያዋጣላቸው ነው፤
ይህንን የተመለከተ አንድ ድህረ- አንጋፋ ተዋናይ ጉዋደኛየ፥ ከቀበና ወደ መገናኛ የሚሄደውን ሀይገር አውቶብስ አስቁሞ ሲሳፈር የሚያሳይ ቪድዮ አስቀረጸ ፤ ባለሙያ ቀጥሮ ፥ ድሮን ሳይቀር ተከራይቶ በተለያየ አንግል ተቀርጾ ቪድዮውን ወንድሙ አካውንት ላይ ጣደው ፤
አሁን የንግሊዝ ኢምባሲን መንገድ ዘግተህ የዲፐሎማሲ ጫና ፈጥረህብናል ብሎ ፖሊስ በግር በፈረስ እና በታንክ እያፈላለገው ነው፤

❤23🤣12🤩4
አደራ
(የሚያስተክዝ ገጠመኝ)
(በእውቀቱ ስዩም)
እኛ ሰፈር የጀበና ቡና እሚያፈሉ ሴትዮ አሉ፤ ጠና ያሉ አሮጊት ናቸው፤ ቡናቸው ገብስ ይበዛዋል፤ ያረረ በሶ እንደመጠጣት ነው፤ ደሞ በቡና ማንኪያው ቂጥ ጆሮዋቸውን መጎርጎር ይወዳሉ፤ ግን ስለሚያሳዝኑኝ፤ ይሄን ሁሉ ተቁዋቁሜ ቡና መሰሉን ነገር እጠጣላቸዋለሁ፤
በቀደም ያንን የቦንዳ ቡና እየተጋትሁ፥ በስልኬ ፖድካስት እጨፈጭፋለሁ፤ አንድ አንጋፋ አርቲስት የሌለ እየተፈላሰፉ ነው፤ እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው፤
“ ከሰውነታችን ክፍሎች ሁሉ የቱ ይበልጣል ብትለኝ ፤ ከእግር ከእጅም ከአእምሮም ቂጥ ይበልጣል፤ ቂጥን የሚወዳደር ነገር የለም” እያሉ ስለ ቂጥ ወሳኝነት ማተት ጀመሩ::
እኔም ቡና መሳዩን ፉት እያልሁ ባካል ከፊትለፌቴ የተቀመጡ ይመስል እንደቀደቅባቸው ጀመር፤ ” አባ ! ምን ቅምው ነው ቂጥን ከአአምሮ ያስበለጡት? አሁን እርስዎን ለሚያክል ሰውየ ፥ አእምሮ የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ማስተማር አለብኝ ? ለምሳሌ ቂጥዎ ምድጃ ላይ ቁጭ ከማለት በርጩማ ላይ ቁጭ ማለት እንዲመርጥ ያደረገው አእምሮ ነው፤ የከተማ እብድ፥ መሀል አስፓልት ዳር የሚጸዳዳው አምእምሮው ስለማይሰራ ነው፤ እርሶዎ እንደሚሉት ቂጥ ያን ያህል ቀዳሚነት ቢኖረው ኖሮ ፈጣሪ የአካላችንን ክፍሎች ሲያበጅ አናታችን ላይ ያደርገው ነበር ፤ ለማንኛውም ያንድ ሀሙስ ትኩረት ለማግኘት እንዲህ ቂጥአምባሩ የጠፋ ነገር ባንናገር ጥሩ ነው”
የሰውየውን ንግግር በዚህ መልክ አፈር ድሜ ካስጋጥሁ በሁዋላ ከፍተኛ እርካታ ተሰማኝ፤ አባቴ ድሮ አስራ አምስት እንጀራ መጋገር የሚያስቸል እንጨት ፈልጦ ሲጨርስ ያደርገው እንደነበረው ኮራ ብየ፥የመዳፌን አቧራ በመዳፌ አራግፌ በረጅሙ ተነፈስኩ፤
ወድያ ሽንቴ ስለመጣ “ ማዘር ቦርሳየን እዩልኝ “ አልኩዋቸው፤ ራሳቸውን በ እሽታ ነቀነቁ፤
የድሮ ሰው አደራ ጠባቂ ነው፤ ገጣሚ ሙሉጌታ ተስፋየ የሆነ ጊዜ ላይ ኮካ ጠጥቶ የተረፈውን ግማሽ ለባለሱቁ አስቀምጥልኝ ብሎት ሄደ፤ ከወራት በሁዋላ ሲመለስ ባለሱቁ ባደራ የሰጠውን ግማሽ ጠርሙስ ኮካ መለሰለት፤ አያ ሙሌም በዚህ ተገርሞ ‘ ላንተ ነበር አገርን ባደራ መስጠት “ አለው ይባላል፤ በርግጥ፥ አያ ሙሌ ለባለሱቁ በኮካ ፈንታ ‘ብሉ ሌብል ውስኪ’ በአደራ ሰጥቶት ቢሆን ኖሮ? ውስኪውን መልሶ ያገኘው ነበር ? አያ ሙሌ ራሱ ጨክኖ ውስኪ ባደራ ያስቀምጥ ነበር?
እንዲህ እየተወዛገብሁ ፥ከሽንት ስመለስ ቦርሳየ በቦታው የለም፤
“ ማዘር ቦርሳየስ? “ አልኩዋቸው፤
“ አንዱ ይዞት ወደታች ወረደ “
“እዩልኝ አላልኮትም እንዴ? “ አልኩ ንዴቴ እንደ ኮርዲሩ መብራት እየተንቦገቦገ፤
“ ምን ያንጨረጭርሀል? እዩልኝ እንጂ አባረው ያዙልኝ አላልኸኝ ፤ “
አሉና ማንኪያው ስላላረካቸው፥ ጆሯቸውን በቡና መቁያው መጎርጎራቸውን ቀጠሉ::

❤23🤣6
በለስ ፍሬ ባትሰጥ
ሎሚ መሽተት ቢሳናት
ዔሊ ላባ ብትለብስ
ወፌን ድንጋይ ቢጫናት
ሰማይ እንደ አለት ቢወቀር
ጊዜ ደክሞት ቆሞ ቢቀር
ጨረቃ አመድ ብትቅም
ፀሃይ ጥርሷን ብትለቅም
ስልጣኔን ነቀዝ በልቶት
ኦና ቢሆን ሃገር ምድሩ
ፒራሚዶች ባንድ ለሊት
የኩበት ክምር ሆነው ቢያድሩ
ተፈጥሮ ለህዝብ ቅነሳ
ሰው በሰው ላይ ብታስነሳ
አንዱ ካንዱ ቢተራረድ
ጠፈር በቀን ቢጋረድ
ሙሴን ባህር ቢበላው
የኖህ መርከብ ቢሰጥም
ህይወት ሚስጥር ባትገልጥም
የድል ድርሻዬን ጥዋ
ጭላጭ ሳይቀር እስካጣጥም
የምሻውን እስከማገኝ
ለመሸነፍ እጅ አልሰጥም
እንኳን ተስፋ ጢም አልቆርጥም
በእውቀቱ ስዩም
@WAS143
@WAS143
ሎሚ መሽተት ቢሳናት
ዔሊ ላባ ብትለብስ
ወፌን ድንጋይ ቢጫናት
ሰማይ እንደ አለት ቢወቀር
ጊዜ ደክሞት ቆሞ ቢቀር
ጨረቃ አመድ ብትቅም
ፀሃይ ጥርሷን ብትለቅም
ስልጣኔን ነቀዝ በልቶት
ኦና ቢሆን ሃገር ምድሩ
ፒራሚዶች ባንድ ለሊት
የኩበት ክምር ሆነው ቢያድሩ
ተፈጥሮ ለህዝብ ቅነሳ
ሰው በሰው ላይ ብታስነሳ
አንዱ ካንዱ ቢተራረድ
ጠፈር በቀን ቢጋረድ
ሙሴን ባህር ቢበላው
የኖህ መርከብ ቢሰጥም
ህይወት ሚስጥር ባትገልጥም
የድል ድርሻዬን ጥዋ
ጭላጭ ሳይቀር እስካጣጥም
የምሻውን እስከማገኝ
ለመሸነፍ እጅ አልሰጥም
እንኳን ተስፋ ጢም አልቆርጥም
በእውቀቱ ስዩም
@WAS143
@WAS143
❤47👌8🥰3👏3🤩2🤣2
በእርግጥ መፈቀር ላንቺ የሚያንስሽ ነሽ! አዎ ውበት ይፈቀራል! እኔም ላንቺ ያለኝ ፍቅር ከሚገባሽ በታች ቢሆንም ከምችለው በላይ መሆኑንም አውቃለሁ። አንጃ ብቻ ድንገት ልቤን ተቆጣጥረሽዋል።ብዙ አልከፋኝም!
አረማመድ ጌጥ እንዳለው ለመጀመሪያ ጊዜ ባንቺ ታዘብኩ። እያንዳንዱ ውበትሽን ለመዘርዘር አልሞክርም ፣ የሚሸከሙት ቃላቶች አልተፈበረኩም። በደፈናው የውበት ሚዛኑ ነሽ ማለት ይቀለኛል....(ይኼኛው ገለፃዮም ቢሆን ለዛ የለውም)...እንዴት ያለ ሁለመናው የተረጋጋ ውበት ነው..!?

❤5🥰3👌2