ከአሜሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ተባረረ‼
የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ተቋም ፋኖን በ"ደረጃ 3 አሸባሪነት" በመጥቀስ አንድ ኢትዮጵያዊን አባረረ
የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ማስከበሪያ (ICE) ሰለሞን ቦጋለ የተባለ ኢትዮጵያዊን የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመሃል በሚል ከመጋቢት 5 ቀን ጀምሮ ከአሜሪካ አባሮ ወደ ኢትዮጵያ መለሰ።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ራሱን የፋኖ አባል አድርጎ እንደሚገልጽና ፋኖን ደግሞ "የደረጃ 3 (Tier III) አሸባሪ ቡድን" ሲል በሪፖርቱ ጠቅሶታል።
ግለሰቡ በትግራይ ተወላጆች ላይ የጥቃት ቅስቀሳ በማድረጉ የኢሚግሬሽን መብቱ እንዲነጠቅ መደረጉን ICE አስታውቋል።
ምንም እንኳን "ደረጃ 3" የሚለው ምደባ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በይፋ የተሰጠ የሽብርተኝነት ፍረጃ ባይሆንም፣ የኢሚግሬሽን ተቋሙ ግን ለቪዛና ለጥገኝነት ክልከላ ሲል ፋኖን ያልተሰየመ የታጣቂ ቡድን (Undesignated group) በሚል መፈረጁ በዲያስፖራው ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
NB:-ፍረጃው በኢሚግሬሽን ህግ ደረጃ እንጂ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ደረጃ ገና መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

❤3👍2😁1
በኢድሊብ የተፈጸመው ዘግናኝ ግድያና የማህበራዊ ሚዲያ ስህተት
በሶሪያ ዳና ከተማ በቅርቡ የተፈጸመውና በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ የሆነው አሰቃቂ ግድያ መላውን ዓለም አስደንግጧል።
ኑራ ኢብራሂም የተባለችው ግለሰብ ባለቤቷን አህመድ መሐመድ ፎዚን ከገደለች በኋላ አስከሬኑን ወደ 30 ቁርጥራጮች በመከፋፈል መደበቋ በምርመራ ተረጋግጧል።
ይህ ክስተት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መጀመሪያ አካባቢ "ባል የምትፈልግ መበለት" በሚል የፌዝ ጽሑፍ ታጅቦ ሲሰራጭ የነበረ ቢሆንም፣ እውነታው ግን ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል መሆኑ ታውቋል።
ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን ሳያጣሩ ከመቀበልና ካልተገባ ቀልድ መቆጠብ እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል።

❤3👏1
ለነዳጅ አዲስ መመሪያ‼
የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎልን ለመቋቋም አዲስ የቁጠባ መመሪያ ወጣ‼
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመቋቋም የሚያስችል አዲስ ጥብቅ መመሪያ አወጣ።
በመመሪያው መሠረት የነዳጅ አከፋፋዮች ለፀጥታ ተቋማት፣ ለልማት ፕሮጀክቶች፣ ለፋብሪካዎችና ለሕዝብ ትራንስፖርት ቅድሚያ እንዲሰጡ ታዘዋል።
መመሪያው ተጨማሪ የነዳጅ ማጠራቀሚያ (ሰልቫቲዮ) አስገጥመው የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ በጥብቅ የከለከለ ሲሆን፣ ማደያዎች መሰል ድርጊቶችን ለፀጥታ አካላት እንዲጠቁሙ አዟል።
በተጨማሪም የነዳጅ ቦቴዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መድረሳቸው እንዲከታተሉና ብክነት እንዳይኖር ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። ባለሥልጣኑ መመሪያውን በማያከብሩ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

❤2
ጥናት፡ ዊግ እና 'ሂውማን ሄር' ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ ኬሚካሎች ተገኙባቸው
በቅርቡ የወጣ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደጠቆመው፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚጠቀሙባቸው ዊግና ሰው ሠራሽ ፀጉሮች (Human Hair) ለከፍተኛ የጤና እክል የሚዳርጉ ከ50 በላይ መርዛማ ኬሚካሎች ተገኝተውባቸዋል።
በአሜሪካ ኬሚካል ሶሳይቲ ጆርናል ላይ የታተመው ይህ ምርምር፣ በ43 ናሙናዎች ላይ ባደረገው ፍተሻ ካንሰር አመጪ፣ የሆርሞን መዛባትና የሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግር የሚያስከትሉ ንጥረ ነገሮችን ለይቷል።
ዋና ዋና የምርምር ግኝቶች፡-
48 የሚሆኑት በተባበሩት መንግሥታት "አደገኛ" ተብለው የተመደቡ ሲሆኑ፣ 17ቱ ደግሞ በቀጥታ ከጡት ካንሰር ጋር የተያያዙ ናቸው።
ዊጎች ከቆዳ ጋር ለረጅም ጊዜ (ለሳምንታት ወይም ለወራት) ንክኪ ስላላቸው፣ ኬሚካሎቹ ወደ ሰውነት የመግባት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
እሳትን ለመከላከል የሚረዱ (Organotin)፣ ፕላስቲኮችን ለማለስለስ የሚያገለግሉ (Phthalates) እና ለእንጨት ማጣበቂያነት የሚውለው ፌኖል (Phenol) በናሙናዎቹ ውስጥ ተገኝተዋል።
የጥናቱ መሪ ዶ/ር ኢሊሺያ ፍራንክሊን፣ በቢሊዮን ዶላር የሚንቀሳቀስበት የዊግ ኢንዱስትሪ ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት ሊዘረጋለትና ለተጠቃሚዎችም ግልጽ መረጃ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን አወጀች‼
ዘ ኢንዲፔንደንት ከደቂቃዎች በፊት ሰበር ዜና ሲል ባጋራው መረጃ፤ ሆርሙዝ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን ዘግቧል፡፡
ቴሂራን ይህን ውሳኔ ያሳለፈችው ከአሜሪካ ጋር ድርድር ሊጀመር ይችላል የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ ባለበት ወቅት ነው፡፡

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪዲዬ:-ባለፈው ዓመት በዋሽንግተን ዲሲ ሰማይ ላይ በአሜሪካን ኤርላይንስ አውሮፕላን እና በጦር ኃይሉ ሄሊኮፕተር መካከል የደረሰውን አሰቃቂ ግጭት የሚያሳይ አዲስ ምስል ዛሬ ይፋ ሆነ።
67 ሰዎችን ለህልፈት የዳረገው የዚህ አደጋ አዲስ ምስል፣ ለብሔራዊ የትራንስፖርት ደኅንነት ቦርድ (NTSB) ምርመራ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ተገልጿል።
አደጋው በዋና ከተማዋ ሰማይ ላይ ከተከሰቱ እጅግ አስከፊ የአቪዬሽን አደጋዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።

❤3
ጃፓን፤ ከውኃ እና ከካርቦን ዳይኦክሳይድ (CO₂) ነዳጅ ማምረት ቻለች። የጃፓኑ ኢኔኦስ (ENEOS) እና ሌሎች ኩባንያዎች ሰው ሠራሽ የሆኑ "ኢ-ፊውል" (e-fuels) ማምረቻ የሙከራ ጣቢያዎችን ገንብተዋል።
ይህ ቴክኖሎጂ፤ ከአየር ላይ የተያዘን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ከውኃ ውስጥ የተከፈለ ሃይድሮጅንን በማቀናጀት በታዳሽ ኃይል አማካኝነት የሚሠራ "ሃይድሮካርቦን" ነው። በአሁኑ ወቅት በዮኮሃማ (Yokohama) በሚገኘው የሙከራ ጣቢያ በቀን 1 በርሜል ገደማ ብቻ እየተመረተ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በጥቅምት 2025 (እ.ኤ.አ) በከፍተኛ ወጪ ምክንያት ለጊዜው ቢቆምም፣ ግኝቱ ግን ካርቦን-አልባ ነዳጅን ወደ መጠቀም የሚያሸጋግር ትልቅ እምርታ ነው።

የጭነት መርከቦች የሆርሙዝ ሰርጥን
መሻገር ጀመሩ! ፈረንሳይ ቀዳሚ ሆናለች
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ቢሆንም፣ በፈረንሳዩ ሲኤምኤ ሲጂኤም የሚተዳደር አንድ ግዙፍ የጭነት መርከብ፣ ሶስት ከኦማን ጋር ግንኙነት ያላቸው ታንከሮችና አንድ የጃፓን የጋዝ ጫኝ መርከብ የሆርሙዝ ሰርጥን በሰላም ተሻግረዋል። ይህ እርምጃ አንዳንድ መርከቦች በጥንቃቄ ጉዟቸውን መጀመራቸውን የሚያሳይ ሲሆን፣ የፈረንሳዩ መርከብ ኢራን በሩን ከዘጋች ወዲህ ሰርጡን የተሻገረ የመጀመሪያው የምዕራባውያን መርከብ መሆኑ ተረጋግጧል።
እንደ "ማሪን ትራፊክ" መረጃ ከሆነ፣ የፈረንሳዩ መርከብ አርብ ዕለት ጉዞውን ያከናወነ ሲሆን ይህም የባህር ላይ ትራንስፖርቱን ዳግም ለማንቀሳቀስ እየተደረገ ያለውን ጥረት ያሳያል። ምንም እንኳን አካባቢው አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ቢሆንም፣ እነዚህ መርከቦች ያደረጉት ስኬታማ ጉዞ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ ሆኗል።

❤8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አለምን እያነጋገረ ያለው ኢራናዊቷ አዛውንት ጥያቄና መልስ
🇮🇷 ጋዜጠኛ፡ “አያቴ፣ እዚህ ምን እያደረጉ ነው?”
እማማ፡ “መሪዬን ለመደገፍ ነው የመጣሁት።”
ጋዜጠኛ፡ “ታዲያ እርሶ ድጋፍ ለመስጠት ይቻልዎታልንዴ?”
እማማ፡ “አዎ።”
ጋዜጠኛ፡ “እንዴት?”
እማማ፡ “እዚህ በመገኘት አደባባዩ ባዶ ባለማድረግ..”
ጋዜጠኛ፡ “አያቴ፣ የእርሶ መገኘት የሚጥረው ተጽዕኖ ይኖራል?
እማማ፡ “አዎ።”
ጋዜጠኛ፡ “እሺ ምንድን ተጽእኖው?
እማማ፡ “አሜሪካ ትፈራለቻ.. (አሜሪካ አደባባዮቹን ያጥለቀለቁ ሰዎችን ትፈራለች!”

❤5🤣1
በኢትዮጵያ በጂቡቲ መካከል ሲደረግ የነበረው የወደብ ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁ ተሰማ
የጂቡቲ መንግሥት በታጁራ ወደብ ላይ ያቀረበው የ60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በኢትዮጵያ መንግሥት ተቀባይነት አለማግኘቱን የጂቡቲ የወደቦችና የነፃ ቀጣና ባለሥልጣን አስታውቋል። እንደ ባለሥልጣኑ ሰብሳቢ አቡበከር ኦማር ሀዲ ገለጻ፣ ድርድሩ ሊሰናከል የቻለው ኢትዮጵያ ከባለቤትነት ድርሻው በተጨማሪ የራሷ የሆነ የኮሪደር ጥያቄ በማቅረቧ ነው።
ጂቡቲ ይህንን አማራጭ ያቀረበችው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በቀጣናው የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ቢሆንም፣ የኮሪደር ጥያቄው ግን ስምምነቱን አፋርሶታል። ይሁን እንጂ ጂቡቲ አሁንም ለኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ ክፍት መሆኗንና በተለይም ለማዳበሪያና መሰል ስትራቴጂካዊ ጭነቶች ቅድሚያ መስጠቷን እንደምትቀጥል አረጋግጣለች።

በድግምት ሰዎችን ለመጉዳት የሞከሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ‼
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ “በድግምት ሰዎችን ለመግደል እና ለማሳበድ” የተስማሙ ሁለት ግለሰቦች በ8 ወራት ቀላል እስራት ተቀጡ።
ተከሳሾቹ ኦልያ ሱፊ (መድኃኒት ቀማሚ) እና ኡስማን መሀመድ (አሰሪ) ሲሆኑ፣ ኡስማን በግል ቅራኔ ምክንያት አንደኛው ተበዳይ እንዲሞት፣ ሁለተኛው ደግሞ እንዲያብድ ለኦልያ 10 ሺህ ብር ለመክፈል ተስማምቷል።
ለጥንቆላው የሚሆን የቅንድብ ፀጉር ከአንዱ ተበዳይ ላይ አዘናግቶ ለመውሰድ ሲሞክር እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ፣ በፖሊስ ምርመራ ወንጀሉ ተረጋግጦበት የበደኖ ወረዳ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱንም በስምንት ወራት ቀላል እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።

❤4