ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
37.2K subscribers
63 photos
49 videos
19 files
1.66K links
ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
2፥62 ላይ የክርስትና እምነት፣ የአይሁድ እምነት እና የሳቢያን እምነት ትክክል ነው እያለ ሳይሆን ይሁዳውያን፣ ክርስቲያን እና ሳቢያን ግለሰብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመኑ መልካምንም ሥራ የሠሩ ከሆኑ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው። ምክንያቱም አንድ ሰው በአርካኑል ኢማን ካመነ ሙሥሊም ነውና። ግን አህሉል ኪታብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ስለማያምኑ ነው በሙሥሊም አገር ውስጥ ጂዚያህ የሚከፍሉት፦
9፥29 *”ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን”*፣ አላህና መልክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው፡፡ قَاتِلُوا الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَلَا بِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَلَا يُحَرِّمُونَ مَا حَرَّمَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَلَا يَدِينُونَ دِينَ الْحَقِّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حَتَّىٰ يُعْطُوا الْجِزْيَةَ عَن يَدٍ وَهُمْ صَاغِرُونَ

ልብ አድርግ “አለዚነ” الَّذِينَ ማለትም “እነዚያ” ከሚለው አመልካች-ተውላጠ ስም መነሻ ላይ “ሚን” مِن ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድ አለ። ይህ የሚያሳየው ከአህሉል ኪታብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑ እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ከአህሉል ኪታብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ በእነርሱ ላይ ቁርኣን በሚነበብላቸውም ጊዜ “በእርሱ(በቁርኣን) አምነናል፥ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከእርሱ(ከቁርኣኑ) በፊት ሙሥሊሞች ነበርን” ይላሉ። ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሆነውን ቁርኣን የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ፦
28፥52 *”እነዚያ ከእርሱ(ከቁርአን) በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ(በቁርኣን) ያምናሉ”*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُون
28፥53 *”በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ”*፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِين
3፥113 *”የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም፡፡ ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ”*፡፡ لَيْسُوا سَوَاءً ۗ مِّنْ أَهْلِ الْكِتَابِ أُمَّةٌ قَائِمَةٌ يَتْلُونَ آيَاتِ اللَّهِ آنَاءَ اللَّيْلِ وَهُمْ يَسْجُدُونَ

እነዚህ ታዲያ ሙሥሊሞች አይደሉምን? እንዴታ! ናቸው እንጂ። የመጽሐፉም ባለቤቶች በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ቢያምኑ እና በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ከመካድ ቢጠነቀቁ አላህ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ያስተሰርይ እና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ያገባቸው ነበር። ከእነርሱ ውስጥ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፡፡ ከእነሱም ብዙዎቹ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን በመካድ የሚሠሩት ነገር ከፋ፦
5፥65 *”የመጽሐፉም ባለቤቶች ባመኑ እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር”*፡፡ وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَكَفَّرْنَا عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأَدْخَلْنَاهُمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ
5፥66 *”ከእነርሱ ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ!”* مِّنْهُمْ أُمَّةٌ مُّقْتَصِدَةٌ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ سَاءَ مَا يَعْمَلُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐዲድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን፥ *"ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን"*፡፡لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ

አምላካችን አላህ"ﷻ" ወደ ነቢያችን"ﷺ" መጽሐፍ እና ሚዛን አውርዷል፦
42፥17 አላህ ያ *”መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም እንደዚሁ*”፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል? ٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ وَٱلْمِيزَانَ ۗ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٌۭ

ይህም መጽሐፍ እና ሚዛን ቁርኣን ነው፥ መጽሐፍ እና ሚዛን የቁርኣን ስሞች ናቸው። ለምሳሌ ተውራት መጽሐፍ እና ፉርቃንን ተብሏል፦
2፥53 ሙሳንም *”መጽሐፍን እና ፉርቃንንም”* ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ አስታውሱ፡፡ وَإِذْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْفُرْقَانَ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

“ሚዛን” مِيزَان እውነትን ከሐሰት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ሰናዩን ከእኩይ የምንለይበት መመዘኛ ነው። ይህ መመዘኛ አምላካችን አላህ"ﷻ" ወደ መልእክኞቹ አውርዷል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *"መጽሐፎችን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን፥ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን"*፡፡لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ

"ሐዲድ" حَدِيد የሚለው ቃል በቁርኣን 6 ጊዜ የመጣ ሲሆን "ብረት"Iron" ማለት ነው። "ሐዲድ" የ 57ኛው ሱራ ስም ነው፥ ይህ ሱራ ላይ አምላካችን አላህ"ﷻ"፦ "ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን" በማለት ይናገራል። ታዲያ ይህ ብረት ከየት ነው የወረደው? ስንል "አንዘልና" َأَنزَلْنَا ማለትም "አወረድን" የሚለው ቃል "ገለጥን" ወይም "ሰጠን" በሚል ይመጣል፦
7፥26 የአዳም ልጆች ሆይ! *"ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን"*፡፡ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፡፡ ይገሠጹ ዘንድ አወረደላቸው፡፡ يَا بَنِي آدَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَارِي سَوْآتِكُمْ وَرِيشًا ۖ وَلِبَاسُ التَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ ۚ ذَٰلِكَ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ
16፥14 *እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም "የምትለብሱትን ጌጣጌጥ" ታወጡ ዘንድ የገራ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا وَتَرَى الْفُلْكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبْتَغُوا مِن فَضْلِهِ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

ልብ አድርግ "ጌጣጌጥ" ከባሕር የሚወጣ ነገር ሲሆን አላህ ለእኛ ስላገራው "አወረድን" ብሎታል እንጂ ከሰማይ መውረድን አያመለክትም፥ እንዲሁ ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አውርዶታል። የቤት እንስሳ ግመል፣ ከብት፣ ፍየል እና በግ ከእነ ጥንዳቸው ስምንት ሲሆኑ ወርደዋል ይላል፦
39፥6 ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ *"ለእናንተም ከግመልና ከከብት፣ ከፍየል፣ ከበግ ስምንት ዓይነቶችን ወንድና ሴት "አወረደ"*፡፡ خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ الْأَنْعَامِ ثَمَانِيَةَ أَزْوَاجٍ

"አንዘለ" أَنزَلَ ማለት "አወረደ" ማለት ሲሆን ስምንቱ ጥንድ እንስሳ ወርደዋል ማለት ለሰው ልጆች አገልግሎት ተሰጥተዋል ማለት ከሆነ ብረትም ወረደ ማለት መጠቃቀሚያ ያለበት ሲኾን ለሰው ልጆች አገልግሎት ተሰቷል ማለት ነው። "አንዘለ" أَنزَلَ የሚለው ቃል ደመና ከተሸከመው ሰማይ ዝናብን ለማውረድ ተጠቅሞበታል፦
6፥99 *"እርሱም ያ ከሰማይ ውኃን ያወረደ ነው፡፡ በእርሱም የነገሩን ሁሉ በቃይ አወጣን*፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجْنَا بِهِ نَبَاتَ كُلِّ شَيْءٍ

"ሠማእ" سَّمَاء ማለትም "ሰማይ" ከላይ ያለውን "ጠፈር"Space" ለማመልከት ከገባ ብረት እራሱ ከጠፈር ሥነ-ፈለካዊ ክስተት"supernova" የመጣ በውስጡ ብርቱ ኀይል እና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ነው። የብረት ዑደት"cycle" ከአየር ክልል"atmo-sphere" ወደ ውኃ ክልል"hydro-sphere" ከዚያ ወደ ሕይወት ክልል"bio-sphere" በመቀጠል ወደ ዐለት ክልል"litho-sphere" አርጎ በተለያየ ሁኔታ ያልፋል።
ብርቱ ኀይል እና ለሰዎች መጠቃቀሚያ መባሉ ብረት ካርበን ሲገባበት አስተኔ ብረት"steel" ይሆንና ለመሠረተ-ልማት፣ ለግንባታ፣ ለኤሌትሪክ ወዘተ ይሆናል። በሰውነታችን ውስጥ ፕሮቲንን ለቀይ የደም ሕዋስ የሚያጓጉዘው ይህ የብረት ክምሽት"hemoglobin" ነው፥ በዚህም የአንድ ጎልማሳ አካል 4 ግራም ወይም 0.005% ክብደት ብረት አለው። በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርገጠኛ ምልክቶች አሉ፥ ይህንን በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም ውስጥ ያሉትን ምልክቶች ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም የሚያስተነትኑ ምንኛ የታደሉ ናቸው? አላህ ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያርገን! አሚን፦
45፥3 *"በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርገጠኛ ምልክቶች አሉ"*፡፡ إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ
3፥19 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአላህ ዙፋን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

11፥7 ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች የፈጠረው ነው፤ *ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር*። وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍۢ وَكَانَ عَرْشُهُۥ عَلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۗ وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِنۢ بَعْدِ ٱلْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ

መቼም ሚሽነሪዎች የኢስላም ተስተምህሮት ዶግ አመድ ቢሆንላቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነው፤ ሂስ የሙግት አንዱ ክፍል ቢሆንም የሚሽነሪዎች ሂስ ግን ማሸሞር፣ ማነወር እና ስላቅ ነው፤ ይህ ደግሞ ጡዘቱ ጣራ የነካና ዙሪያ ገባ ነው፤ ከእነርሱ ቅንነት የተሞላው መልስ መጠበቅ ማለት ከጅብ አፍ ላይ ስጋ እንደመጠበቅ ነው። እነርሱ የሚሰጡት ትችት እኛ ሙስሊሞችን የሚያፍረከርክ ሳይሆን ከእለት ወደ እለት የሚያጀግን ነው፤ ለማንኛውም የተነሳውን ትችት አብጠርጥረን እና አንጠርጥረን እንመልከት፦ “የአላህ ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ የሰይጣንም ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ ስለዚህ የሁለቱም ዙፋን አንድ ነው” በማለት ሊያምታቱ ይሞክራሉ።

“ዐርሽ” عَرْش ማለት “ዙፋን” ማለት ሲሆን የንግሥና ምልክት እና መገለጫ ነው፤ አንድ ንጉሥ ንግሥናው የሚገለጠለው በዙፋኑ ነው፦
27፥23 እኔ *የምትገዛቸው* የሆነችን ሴት፣ ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ፤ ለእርሷም ታላቅ *ዙፋን* አላት፤ إِنِّى وَجَدتُّ ٱمْرَأَةًۭ تَمْلِكُهُمْ وَأُوتِيَتْ مِن كُلِّ شَىْءٍۢ وَلَهَا عَرْشٌ عَظِيمٌۭ

“የምትገዛቸው” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ተምሊኩሁም” تَمْلِكُهُمْ ሲሆን “ተምሊኩ” تَمْلِكُ በሚለው ግስ ላይ “ሁም” ُهُمْ ተሳቢ ተውላጠ-ስም ሆኖ የመጣ ሲሆን ከዙፋኗ ጋር መጠቀሱ የሴትየዋን ንግሥና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል እንጂ ሁልጊዜ መቀመጫ በሚል አይፈሰርም፤ “መሊክ” مَلِيك ማለት “ንጉሥ” ማለት ሲሆን አላህም እውነተኛ ንጉሥ ስለሆነ የንግሥናውን ምልክት የሚያምር ዙፋን አለው፦
23:116 *እውነተኛም ንጉሥ* አላህ *ከፍተኛነት ተገባው*፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *የሚያምረው “ዙፋን” ጌታ ነው፡፡ فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلْمَلِكُ ٱلْحَقُّ ۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلْعَرْشِ ٱلْكَرِيمِ

አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በነቢያዊ ቃላቸው የአላህ ዐርሽ በውሃ ላይ እንደነበር ተናግረዋል፦
11፥7 ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች የፈጠረው ነው፤ *ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር*፤ وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍۢ وَكَانَ عَرْشُهُۥ عَلَى ٱلْمَآءِ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۗ وَلَئِن قُلْتَ إِنَّكُم مَّبْعُوثُونَ مِنۢ بَعْدِ ٱلْمَوْتِ لَيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 54, ሐዲስ 414
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ በመጀመሪያ ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ፤ ከዚያ ዙፋኑን በውሃ ላይ ነበረ፤ ከዚያ ሁሉን ነገር በመጽሐፍ ጻፈ፤ ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ ‏”‌‏.

ይህ ዙፋኑ ያለበት ውሃ ከሰባቱ ሰማያት በላይ ያለ ውሃ ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 3320
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ከሰባቱ ሰማያት በላይ ውሃ አለ፤ آل الأحنف بن ويس روى: ثم قال رسول الله: “وفوق السماء السابعة هو الماء،

የኢብሊስ ዙፋን በውሃ ላይ ነው፦
ኢማም ሙስሊም፡ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 60
ጃቢር እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የኢብሊስ ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ إِبْلِيسَ يَضَعُ عَرْشَهُ عَلَى الْمَاء

የዚህ ሐዲስ ዐውድ ፍሰት ላይ “ማእ” مَآء ማለትም “ውሃ” ተብሎ የተቀመጠው ውሃ ከሰባቱ ሰማያት በላይ ስላለው ውሃ ሳይሆን ስለ ባህር ውሃ ነው፤ እዚሁ ሐዲስ ላይ “በሕር” بَحْر ማለትም “ባህር” ተብሎ ተቀምጧል፦ “የኢብሊስ ዙፋን በባህር ላይ ነው” በማለት የባህር ውሃን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፦
ኢማም ሙስሊም፡ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 59
ጃቢር ነብዩም”ﷺ” ሲናገሩ ሰምቶ እንደተረከው፤ ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የኢብሊስ ዙፋን *በባህር* ላይ ነው፤ عَنْ جَابِرٍ، قَالَ سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ إِنَّ عَرْشَ إِبْلِيسَ عَلَى الْبَحْرِ
ቆርጦ ቀጥል ስለሆኑ እንጂ ሙሉውን ሐሳብ ቢያነቡት እዛው ዐውድ ላይ መልሱ አለ። እረ ለመሆኑ ምን መስፈት ተይዞ ነው ቁርኣንና ሐዲስን ይዞ ለማምታታት የሚጣረው? ባይብል ላይ ከሰማያት በላይ ውሃ አለ ይላል እኮ፤ ይህም ውሃ ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ ሲሆን በውሃ የተሰራ ነው፦
መዝሙር 148፥4 ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት *የሰማያት በላይም ውኃ*።
2ኛ ዜና መዋዕል 2፥6 ነገር ግን ሰማይና *ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ* ይይዘው ዘንድ አይችልምና፤
መዝሙር 104፥3 *እልፍኙን በውኃ የሚሠራ*፥

“ከሰማያት በላይ ሰማይ አለ” ካለን በተለዋዋጭ ደግሞ “ከሰማያት በላይ ውሃ አለ” ካለን ይህንን ሰማይ በውኃ ሰርቶታል፤ ከሰማያት በላይ ባለው ውሃ ዙፋኑን አዘጋጀ፦
መዝሙር 103፥19 እግዚአብሔር *ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ*፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።

ከባይብል አንጻር የታችኛው ውሃ ባህር ይባላል፤ ምድርንም በውኃ ላይ ነው ያጸናው፦
መዝሙር 136፥6 *ምድርን በውኃ ላይ ያጸና*፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
ዘፍጥረት 1፥10 *የውኃ መከማቻውንም ባሕር አለው*፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።

ይህም የባህር ውሃ ጥልቁ ይባላል፤ በዚህ ጥልቁ ውስጥ ዲያብሎስ ይኖራል፤ እርሱ ደግሞ የጥልቁ ባህር ንጉስ ነው፦፦
ኢሳይያስ 51:10፤ *ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፥ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?
ዮናስ 2፥4 ወደ *ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ*፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ፥
ራእይ 9፥11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም *የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን* ይባላል።

አጊያን ባህር ላይ ያለችውን የጴርጋሞን ከተማ የሰይጣን ዙፋን ተብላለች፦
ራእይ 2፥13 *የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ*፤

ስለዚህ “የእግዚአብሔር ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ የሰይጣንም ዙፋን በውሃ ላይ ነው፤ ስለዚህ የሁለቱም ዙፋን አንድ ነው” በማለት እንሞግትን? ምን ይህ ብቻ ባህሩ ምድር ላይ ካለ ፈጣሪ በምድር ክበብ ላይ ይቀመጣል ይል የለ እንዴ? የሰይጣን ዙፋን ላይ እንዴት ፈጣሪ ይቀመጣል? ምክንያቱም የባህር ጥልቅ የምድር ክበብ ስለሆነ፦
ኢሳይያስ40፥22 እርሱ *በምድር ክበብ ላይ ይቀመጣል*፥

እስልምናን ሁሉም ሰው ይወደዋል ማለት ሞኝነት እንደሆነ ሁሉ በተቃራኒው ሁሉም ሰው ይጠላኛል ማለትም ወፈፌነት ነው፤ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ኢስላም በዓለማችን ላይ በሁሉም የህይወት ዘይቤ ተግዳሮት ብለን ብናገር እብለት ወይም ግነት አሊያም ቅጥፈት አይሆንብንም፤ ለዛም ነው እስልምና የዓለማችን የመጋገሪያ ርዕስ የሆነው፤ ማንም ሰው ምንም ይሁን ርቱዕ ሆነ ኢርቱዕ ሙግት በኢስላም ላይ በጨዋ ደንብ ማቅረብ ይችላል፤ ሙስሊሞች ደግሞ በእማኝነትና በአስረጅነት ምንተ አፍረት ሳይኖርብን በምንተ እዳ ሃላፍትናውን ወስደን ለሚነሱ ትችቶች ሆነ ሂሶች መልስ እንሰጣለን።
ሲጀመር የሚሽነሪ ሃያሲ ስለ ኢስላም በአሉታዊ ሂስ የሚሰጡት በምዕራባውያን እሳቦትና እርዮት ነው እንጂ የራሳቸውን የቀኖና ሆነ የትውፊት መፅሐፍት መሰረት አድርገው አይደለም።
ሲቀጥል ስለ ኢስላም ያልጎረሱትን ነው የሚያላምጡት፤ ስለ ኢስላም ለመረዳት ቅድሚያ ከመሰረቱ ተስተምህሮቱ በተቀመጠበት መዋቅርና መርሃ-ግብር ማጥናት ይፈልጋል።
ሲሰልስ የመጀመሪያዎቹ የነብያችን”ﷺ” ተከታዮች እንዴት ተረድተው ተገበሩት የሚለው መገንዘብ ያስፈልጋል፤ ካልሆነ ግን እናንተ እንዲህ ነው የምታምኑት እንዲህ ነው ማመን ያለባችሁ ብሎ እስልምናን በጥራዝ ነጠቅ ስልት መደስኮር ውሃ የማይቋጥር ስሑት ሙግት ነው።
ሲያረብብ ኢስላም ላይ ሂስ ከመስጠታችሁ በፊት ቅድሚያ ከቤታችሁ ጀምራችሁ አስተካክሉ፦ ቤተክርስቲያን ሰዶማውያንን ማጋባቷን፤ የቅስና መንበሯን ለእነርሱ መስጠቷን፣ በሰዶማውያኑ ሙሉ ክህነታዊ ባርኮት መሰጠትንና ሥርዐተ ቊርባንን መመራት አስቁሙ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውሸት ይፈቀዳልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ ትክክለኛ ንግግር መናገር ነው፥ አንድ አማኝ ትክክለኛውንም ንግግር መናገር እና የሐሰትንም ቃል መራቅ አለበት፦
33:70 እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ *ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

"ባጢል" ْبَاطِل ማለት "ሐሰት" "ውሸት" "ቅጥፈት" ማለት ነው። እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ይናገራል፥ ከእውነተኞችም ጎን ይቆማል፦
2፥111 *እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ* በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
6፥143 *እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ* በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

ባጢል ፍጹም ሐራም ነው። ከዚብ ግን በሦስት ጉዳይ የተፈቀደ ነው። "ከዚብ" كَذِب የሚለው ቃል "ከዘበ" َكَذَّب ማለትም "አስተባበለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እብለት" ማለት ነው፥ እብለት ተቃራኒ ጾታን ለማስደሰት፣ ጠላት ሊጎዳ ሲመጣ እና የተጣሉ ሰዎችን ለማስማማት በስተቀር ክልክል ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 45
አሥማእ ቢንቲ የዚድ እንደተረከችው፦ "የአላህ መልክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ማስተባበል ለሦስት ጉዳይ ካልሆነ ሐላል አይደለም። ባል ሚስቱን ለማስደሰት፣ በጦርነት እና በሰዎች መካከል ሰላም ለማስፈን"*። عَنْ أَسْمَاءَ بِنْتِ يَزِيدَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ يَحِلُّ الْكَذِبُ إِلاَّ فِي ثَلاَثٍ يُحَدِّثُ الرَّجُلُ امْرَأَتَهُ لِيُرْضِيَهَا وَالْكَذِبُ فِي الْحَرْبِ وَالْكَذِبُ لِيُصْلِحَ بَيْنَ النَّاسِ ‏

"ባል ሚስቱን ለማስደሰት"
ባል ሚስቱን፦ "አንቺ ኮከብ ነሽ" ሊላት ይችላል። ግን ኮከብ አይደለችም። ይህ ግነት እንጂ ውሸት አይደለም።

"በጦርነት ጊዜ"
"እብለት" ማለት ጉዳዩን አለመናገር ማለት ሲሆን በመናገር ማሕበረሠብን የሚጎዳ ከሆነ ማበል መፍትሔ ነው፥ ለምሳሌ አንድ ነፍሰ-ገዳይ እህትህን ሊገድል መጥቶ ጓዳ ተደብቃ እህትህ የት አለሽ ቢልህ ጓዳ አለች ትለዋለህን? በፍጹም አትለውም። ይህ እብለት ይባላል።

"በሰዎች መካከል ሰላም ለማስፈን"
ሌላው ሁልጊዜ እውነት መናገር ሰናይ ነው ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም የሚጎዳ እውነት ስላለ። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ተጣልተው ከተጣይው መሃል አንዱ፦ "እርሱ እንዲህ ብሎኝ ነበር" በማለት አሉታዊ ነገር ቢናገር፥ አስታራቂው ግን ጉዳዩ እያወቀ ለማስታረቅ፦ "እኔ አልሰማውም" ቢል ይህ ውሸት ሳይሆን እብለት ነው።

ተገልብጦ ይህ ጥያቄ ባይብል ላይ ይመጣል። አብርሃም ሚስቱን ሳራን ሚስቴ ናት ካለ የግብፅ ሰዎች እንዳይገድሉት ፈርቶ እህቱ ነኝ በይ እንዳላት እና እኅቴ ናት እንዳለ ዘፍጥረት 12፥10-20 ላይ ተዘግቧል።
ይህንን አድራጎቱን አምላኩ ከመገስፅ ይልቅ እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ፤ ይህ ለምን ሆነ ተብለው ምሁራን ሲጠየቁ ጉዳት ያለው ነገር ቢነገር ከሚጎዳ ቢደበቅ የተሻለ ነው ይሉናል፤ ይህንን አድሯጎት በሌላ ጊዜ በአቢሜሌክ ላይ ደግሞታል፤ ይህንን አድራጎቱ ከመገሰፅ ይልቅ እግዚአብሔርም የሰውዬውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ በማለት መለሰለት፥ ዘፍጥረት 20፥1-7 ተመልከት።
ጋለሞታይቱ ረዓብ ኢያሱ የላካቸውን ሁለቱንሰላዮች ደብቃ እንዲህ ስትዋሻቸው ይታያል፦
ኢያሱ 2፥1-5 የነዌም ልጅ ኢያሱ። ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። የኢያሪኮም ንጉሥ። እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ ሲባል ወሬ ሰማ።
የኢያሪኮም ንጉሥ። አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ። ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርስዋም። አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፥ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላወቅሁም፤ በሩም ሲዘጋ ሲጨልምም ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ታገኙአቸውማላችሁ አለች።

ይህ ስራዋ በአዲስ ኪዳን ፅድቅ መሆኑ ተዘክሮላታል፤ ታዲያ ውሸት ይፈቀዳልን?
ያዕቆብ 2፥25 እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ "በሥራ አልጸደቀችምን""?
ዕብራውያን 11፥31 ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም።"

ኢየሱስ ወደተዘጋጀው በዓል እንደማይወጣ ተናግሮ ግን በስውር ተደብቆ ወጣ፤ ይህ ምንድን ነው ውሸት ወይስ ሌላ? መልሱን ለህሊና፦
ዮሃንስ 7፥8 እናንተ ወደዚህ በዓል ውጡ፤ እኔስ ጊዜዬ ገና ስላልተፈጸመ ወደዚህ ""በዓል ገና አልወጣም""።"
ዮሃንስ 7፥10 ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ ከወጡ በኋላ በዚያን ጊዜ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ""ተሰውሮ ወጣ""።

ከላይ የዘረዘርናዘው ጥቅሶች ውሸት ነው? ወይስ አንድ ነገር እውነት ሆኖ ከወጣ ጉዳት ስላለው መደበቅ ነው? "አይ ውሸትማ አይደለም። ግን እውነት ሁሉ አይነገርም" ከተባለ ከላይ ያለውንም እሳቤ በዚህ ስሌት ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፊቅህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

"ፊቅህ" فِقْه‎ የሚለው ቃል "ፈቂሀ" فَقِهَ‎ ማለትም "ተረዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥልቅ መረዳት" ማለት ነው፦
6፥98 እርሱም ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ ነው፡፡ በማሕፀን መርጊያና በጀርባ መቀመጫም አላችሁ፡፡ *"ለሚያወቁ" ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን"*፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ فَمُسْتَقَرٌّ وَمُسْتَوْدَعٌ ۗ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَفْقَهُونَ

“ሚያወቁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የፍቀሁነ” يَفْقَهُونَ ሲሆን “ሚረዱ” ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ነው። "ፊቅህ" فِقْه‎ የሚለው እሳቤ ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ የሥነ-ሕግ ጥናት”the study of law” ማለት ነው። ይህንን ሕግ የሚያጠና ምሁር በነጠላ "ፈቂህ" فَقِيه‎ ሲባል በብዜት "ፉቀሃእ" فُقَهَاء‎ ይባላል። አንድ ዐሊም የሚያጠናው ሕግ "ሸሪዓህ" ይባላል፥ "ሸሪዓህ" شَرِيعَة ማለት "ትክክለኛ ሕግ" ማለት ነው፦
45፥18 ከዚያም ከትእዛዝ *በትክክለኛይቱ ሕግ* ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُون

"ትክክለኛይቱ ሕግ" ለሚለው ቃል የገባው "ሸሪዓህ" شَرِيعَة የሚል ነው፥ ይህም ቃል “ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም "ሕግ" ከሚል ቃል የመጣ ነው፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” مَنْهَج ማለት ነው። አምላካችን አላህ"ﷻ" ለሁሉም መክእክተኞች በዘመናቸው ሸሪዓህ እና መንሃጅ ማድረጉን ያሳያል። “ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን “ሑክም” ለሚለው የግስ መደብ ነው፥ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው። “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን "ሕግጋት" ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።

እነዚህ ሕግጋት ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው መሠረት ብቻ ዒባዳህ ይፈጸማል። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን ዒባዳህ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው። “ኢቲባዕ” اِتِّبَاع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፤ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” اِتِّبَاع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፥ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒሕ ሐዲስ ነው። “ቢድዓህ” بِدْعَة ማለት ደግሞ “ኢብተደዑ” ٱبْتَدَعُ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው፥ ቢድዓህ የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው። ቢድዓ ማለት ከአምስቱ አሕካም ውጪ አዲስ ፈጠራ ማለት ነው።

እነዚህ አምስቱ ሕግጋት የተዋቀረበት ውቅር ደግሞ አራት ናቸው፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ቁርኣን” قُرْءَان የአምላካችን የአላህ"ﷻ" ንግግር ነው።
2ኛ. “ሡናህ” سُنَّة‎ የነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ ነው።
3ኛ. “ቂያሥ” قِيَاس ዐሊሞች የሚያመዛዝኑበት “ማመጣጠን”Analogy” ነው።
4ኛ. “ኢጅማዕ” إِجْمَاع‎ የምሁራን ስምምነት “ሲኖዶስ”acadamic agreement” ነው።
አንድ ነገር ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ፈርድ ነው? ሙስተሐብ ነው? ሙባሕ ነው? መክሩህ ነው? ሐራም ነው? የሚለው ይታያል። እዚያ ላይ ከሌለ በቂያሥ ይታያል፥ ለምሳሌ "ቢራ" የሚለው ቃል ቁርኣን ላይ ባይኖርም ሐራም መሆኑ "ኸምር" በሚል ቂያሥ ይደረጋል። ቂያስ ማድረጉ በግል ደረጃ ከከበደ በኢጅማዕ በያን ይደረጋል።
ምን አለፋን “ፊቅህ” ሰፊ አርስት ነው፥ በውስጡ፦ ኢጅቲሀድ፣ ተቅሊድ፣ ተክሊፍ፣ ተክፊር፣ ፈትዋ፣ ኢሥትድላል፣ ኢሥቲሕሣን የመሳሰሉትን ከባባድ እሳቦት ይዟል። እነዚህን በግርድፉና በሌጣው እንያቸው፦

1. ኢጅቲሀድ
“ኢጅቲሀድ” اِجْتِهَاد‎ ማለት ቁርኣንን እና ሡናን ባማከለ ሁኔታ የሚደረግ "ፍለጋ" "ጥረት" ወይም "ግኝት" ኢጅቲሀድ ይባላል፥ ዐዋቂ ሆኖ የሚጥረው፣ የሚፈልገው፣ የሚያስሰው ሰው ደግሞ “ሙጅተሂድ” مُجْتَهِد ይባላል።

2. ተቅሊድ
‎ “ተቅሊድ” تَقْلِيد ማለት ዐላዋቂ የሆነ ሰው ከዐዋቂዎች የሚወስደው ነገር “ተቅሊድ” ይባላል፤ ይህ ሰው ደግሞ “ሙቀሊድ” مُقَلِّد ይባላል።

3. ተክሊፍ
“ተክሊፍ” تَكْلِيف‎ ማለት ቁርኣንን እና ሐዲስን መመሪያ አድርጎ የሚሠራ፥ በእነርሱ ትእዛዝ አዛዡንም ለይቶ ማወቅ ነው። ለምሳሌ ሶላት ስገድ ከተባለ ሰላት ትእዛዝ ነው ይተገብራል፥ ስለዚህ የታዘዘውን መተግበር እንጂ የራሱን ጥረት አያደርግም ሌላ ተጨማሬ ነገር ለማወቅ።

4. ተክፊር
“ተክፊር” تَكْفِير‎ ማለት ከእሥልምና ማስወጣት ሲሆን የተለያየ ሁጃ ደሊል ሊገኝበት ከቻለ አህሉል ዒልም የሚወስነው እርምጃ ነው። እርምጃውን የሚወስነው አካል “ሙከፊር” مكفر‌‎ ሲባል የካደው ሰው “ካፊር” كَافِر‎ በብዜት “ኩፋር” كُفَّار ይባላል። ድርጊቱ “ኩፍር” كُفْر‎ ይሰኛል።

5. ፈትዋ
“ፈትዋ” فَتْوَى‎ የሚለው ቃል “አፍታ” أَفْتَى ማለትም "አደረሰ" ወይም"ወሰነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መደበኛ ውሳኔ” ማለት ሲሆን ይህንን ብይን የሚሰጥ አካል “ሙፍቲ” مُفْتٍ‎ ይባላል።

6. ኢሥትድላል
"ደሊል" دَلِيل ማለት "ማስረጃ" ማለት ሲሆን ይህ ሂደት "ኢሥትድላል" اِسْتِدْلَال ይባላል። ቁርኣንን እና ሐዲስ ማስረጃ አርጎ ማስረዳት ኢሥትድላል ነው።

7. ኢሥቲሕሣን
“ኢሥቲሕሣን” ‏اِسْتِحْسَان‎ ማለት ደግሞ መዝሀቦችን መርጦ ሐሰን የሆኑትን ነገሮች በቂያሥ ወስዶ እና በጥሩ መልኩው በራሳቸው ማስቀመጥ ነው። የሚያስቀምጡ እነዚህ የመዝሀብ ሰዎች ናቸው። “መዝሀብ” مَذْهَب‎ ማለት በነጠላ ሲሆን በብዜት “መዛሂብ” مذاهب ሲሆን “የድርጊት መንገድ”school of thought” ማለት ነው። ልክ አንድ ጥጃ ከአራት ጡቶች መርጦ እንደሚጠባ ሁሉ ይህም ሰው አንዱን ወስዶ ይቀስማል፥ እነዚህ መዛሂብ፦
1. የኢማም አቡ ሃኒፋን ግንዛቤ የሚከተል “ሐነፊይ” حنفي‌‎ መዝሃብ ነው።
2. የኢማም ኢብኑ ኢድሪስ ሻፊዕ ግንዛቤ የሚከተል “ሻፊዕይ” شافعي‌‎ መዝሃብ ነው።
3.የኢማም ማሊክ ኢብኑ አነሥ ግንዛቤ የሚከተል “ማሊኪይ” مالكي‌‎ መዝሃብ ነው፣
4. የኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ግንዛቤ የሚከተል “ሐንበሊይ” حنبلي መዝሃብ ነው።

ይህንን የፊቂህ እሳቤ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ለማስቀመጥ ሳይሆን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል መሰናዶ ነው። አምላካችን አላህ"ﷻ" እርሱ ባወረደው ሑክም የምንመራና የምፈርድ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሃሩት እና ማሩት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥102 *”ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩት እና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ”*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

ሰማያውያን ፍጥረታት መላእክት እንደ ጂን እና እንደ ሰው የራሳቸው ነጻ ምርጫ የላቸውም። ይህ ነጻ ምርጫ ስለሌላቸው በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *”መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም”*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *”እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም”*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *”አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። እዚህ ድረስ ከተግባባን የሚቀጥለውን አንቀጽ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንይ። በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው። ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 *”ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩት እና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ”*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሃሩትና ማሩት” እንዳመጹ የሚያሳይ ኃይለ-ቃል ወይም ፍንጭ ሽታው የለም። ምናልባት፦ “እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም” የተባለው ስለ ሃሩትና ማሩት መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኃል፦
2፥102 *”እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፥ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ”*፡፡ وَمَاوَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُم

ምክንያቱም ሃሩትና ማሩት ሁለት ስለሆኑ ለእነርሱ የምንጠቀምበት ተውላጠ-ስም በሙተና “ሁማ” هُمَا ነው፥ ነገር ግን “በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም” የተባሉትን ላይ “እነርሱም” ለሚለው የገባው “ሁም” هُم ሲሆን ከሁለት በላይ ጀመዕ መሆኑ “ሸያጢን” شَّيَٰطِين የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሸያጢን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፥ ሰዎች ከሸያጢን የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ።
ሲጀመር እዚህ አንቀጽ ላይ “ወ” وَ የሚለው መስተጻምር ሕዝብን ሲሕር የሚያስተምሩት ሸያጢን እና ሀሩትና ማሩትን የሚያስጠነቅቁበትን ትምህርት ለመለየት የገባ መስተፃምር ነው። ከመነሻው ሸያጢን የሚያስተምሩት ድግምት እና ለሀሩትና ማሩት ተወረደ የተባለው ነገር ሁለት ለየቅል የሆኑ ሀረግ መሆናቸው ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሃሩትና ማሩት፦ “እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ” እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፥ እነርሱ ላይ የተወረደው ስለ ሲሕር አውንታዊነት ሳይሆን አሉታዊነት የሚያስረዳ ትምህርት ነው።

ሲቀጥል “ማ” مَا የሚለው ቃል ሁለት ፍቺ ይኖረዋል፤ አንዱ “ማ” مَا “መውሱላ” ሲሆን ሁለተኛው “ማ” مَا “መስደሪያ” ነው።
1ኛ. “ማ” مَا የሚለውን “መውሱላ” ማለትም “አንፃራዊ ተውላጠ-ስም” ሆኖ ከተቀራ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደ ነገር እንዳለ ያመለክታል፥ ያ ነገር ግን ከላይ ባየነው የሰዋስም ሙግት ከሸያጢን ሲሕር ተለይቶ በመስተፃምር ተቀምጧል።
2ኛ. “ማ” مَا የሚለው መስደሪያ ማለት “አፍራሽ-ቃል” በሚለው ከተቀራ ደግሞ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የሸያጢን ሲሕር አልተወረደም የሚል ፍቺ ይኖረዋል። ምክንያቱም አይሁዳውያን ሚድራሽ በሚባለው መፅሐፋቸው ላይ፦ “ሲሕር በሁለቱ መላእክት በኩል ባቢሎን ላይ ከፈጣሪ የተወረደ ነው” የሚሉትን ቅጥፈት አላህ እያጋለጣቸው ነው። ምክንያቱም አይሁዳውያን አስማት የሰለሞን ጥበብ ነው የሚል እምነት አላቸው፤ ይህንን እሳቤ አንዳንድ ዐበይት ክርስትና በትውፊት ይጋሩታል። ይህንን ነጥብ ኢብኑ ዐባሥ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ ቁርጡቢ ያነሱታል።

ሢሰልስ “ሀሩትና ማሩት” ማንና ምን ናቸው? የሚለውን ነጥብ ሁለት አመለካከቶች አሉት፤ ይህንም ጤናማ የተለያየ አመለካከት ያመጣው ጤናማው የቂርኣት ውበት ነው፥ “መለከይኒ” مَلَكَيْنِ የሚለው ቃል ”መለክ” مَلَك ማለትም ”መልአክ” ለሚለው ቃል ሙተና”dual” ሲሆን “ሁለት መላእክት” የሚል ፍቺ የሚኖረው “ላምን”ل ላም ፈትሓ “ለ” لَ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሌላው “መሊከይኒ” مَلِكَيْنِ የሚለው ቃል “መሊክ” مَلِك ማለትም “ንጉሥ” ቃል ሙተና ሲሆን “ሁለት ነገሥታት” የሚል ፍቺ “ላምን” ل ላም ከስራ “ሊ” لِ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሁለቱም ቂርኣት ከመለኮት የተወረደ እስከሆነ ድረስ በሁለቱም መቅራት ይቻላል። ይህ ነጥብ በጀላለይን፣ በአጥ-ጠበሪ፣ በዛማኽሻሪ፣ በባጋዊ እና በራዚ ተወስቷል። የውይይታችን ዋናውና ተቀዳሚው ሙግት ሀሩትና ማሩት ማንና ምን ናቸው? ሳይሆን መላእክት በፍጹም አምጸው አያውቅም የሚል ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመላእክት ጋብቻ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥14 *ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውኃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ

አምላካችን አላህ"ﷻ" ኑሕ የሚባለውን መልእክተኛ የላከው፥ የኑሕ ሕዝቦች ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም የተባሉትን አማልክት ያመልኩ ስለነበር እና ያንን ሺርክ ትተው እርሱን ብቻ እንዲያመልኩ ጥሪ እንዲያደርግ ነው፦
7፥59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! *"አላህን አምልኩ፡፡ ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም"*፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡» لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
71፥23 አሉም *«አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው*፡፡ وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا

ይህንን ጥሪ አልሰማ ያሉትን እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውኃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው፦
29፥14 *ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውኃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ

ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው ባይብል ላይ የጥፋት ውኃ የመጣው መላእክት እና ሰዎች ዝሙት ስላረጉ ነው ይለናል፦
ዘፍጥረት 6፥2 *"የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ"*።

ኮዴክስ አሌክንሳድሪየስ እና ኮዴክስ ቫቲካነስ ውስጥ የሚገኘው ግሪክ ሰፕቱጀንት "የእግዚአብሔር ልጆች" የሚለውን "አጌሎስ" ἄγγελος ማለትም "መላእክት" ብሎ ተክቶ አስቀምጦታል። በተጨማሪም የሂፓፑ አውግስቲን የአምላክ ከተማ በሚል መጽሐፉ የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሰማይ መላእክት እንደሆኑ ተናግሯል። የአምላክ ከተማ መጽሐፍ 15 ምዕራፍ 22-23 ተመልከት።
የሙት ባሕር ጥቅል ላይ 1ኛ ሄኖክ 7:1-15 እና ጁብሊይ(ኩፋሌ) 7:21-25 ላይ ኤልኦዩድ የተባሉት የመላእክት ዝርያ እንደተወለዱ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 6፥4 በእነዚያ ወራት "ኔፊሊም" በምድር ላይ ነበሩ፤ ደግሞም ከዚያ በኋላ *”የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው”*፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ።

"ኔፊሊም" נְפִילִים ማለት "የወደቁ" ማለት ነው። በዝሙት የወደቁ መላእክት ናቸው። የሄኖክ ንግግር በሚባለው በመጽሐፈ ሄኖክ፦ “የሰማይ ልጆች መላእክትም ለራሳቸውም ሚስቶችን አገቡ” ይለናል፦
መጽሐፈ ሄኖክ 2፥1-3 የሰው ልጆች ከበዙ በኋላ እንዲህ ሆነ፡፡ በእነዚያ ወራት መልክ መልካሞችና ደመ ግቡዎች ሴቶች ተወለዱላቸው፡፡ *”የሰማይ ልጆች መላእክትም እነርሱን አይተው ወደዷቸው፡፡ እርስ በርሳቸው ኑ ለእኛ ከሰው ልጆች ሴቶችን እንምረጥ፤ለእኛም ልጆችን እንውለድ አሉ፡፡ ለራሳቸውም ሚስቶችን አገቡ”*።

ኩፋሌ ”የእግዚአብሔር ልጆች” የተባሉትን ፍጥረታት ”የእግዚአብሔር መላእክት” እንደሆኑ ይናገራል፦
መጽሐፈ ኩፋሌ 6፥9 የአዳም ልጆች በምድር ይበዙ ዘንድ በጀመሩ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። *"የእግዚአብሔር መላእክትም በዚህ በኢዮቤልዩ በአንዲት ዓመት እነዚህን አዩአቸው፡፡ እነዚያ ላዩአቸው መልከ መልካሞች ነበሩና ከመረጡአቸው ጋር ሚስቶች ሊሆኑአቸው ወሰዱአቸው፤ወንዶች ልጆችንም ወለዱላቸው"* እነዚያም ረዓይት ናቸው፡፡

በተጨማሪም መቃቢያን ፈጣሪ ለመላእክት የሰው ስጋ እንደፈጠላቸው፥ ከቃየል ልጆች ሚስት እንደገቡ፣ እነርሱ ግን ሕጉን አልጠበቁም ከአባታቸው ከዲያብሎስ ጋር ወደ ገሃነም እሳት እንደወረዱ ይናገራል፦
1ኛ መቃብያን 18፥5 ስለ ልቦናቸው ትእቢት ያስታቸው ዘንድ ሕጉን እና ትእዛዙንም ይጠብቁ እንደሆነ ይፈትናቸው ዘንድ *"እግዚአብሔር ጥንቱንም የሰው ስጋ ፈጥሮላቸዋልና ከቃየል ልጆች ሚስት አገቡ። እነርሱ ግን ሕጉን አልጠበቁም ከአባታቸው ከዲያብሎስ ጋር ወደ ገሃነም እሳት አወረዳቸው"*።
አንዳንድ የባይብል ምሁራን፦ "መላእክት በሰማይ እያሉ አያገቡም አይጋቡም፥ ግን ምድር ላይ ሲመጡ ሰውና ስጋ ስለሚሆኑ ይበላሉ ይጠጣሉ፥ ያገባሉ ይጋባሉ" ይላሉ። ይሁዳ ሰዶምና ገሞራ ዝሙት ያደረጉት "እንደ እነርሱ" ማለትም መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን "መላእክት" አይነት ነው ይለናል፦
ይሁዳ 1፥6-7 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን *መላእክት* በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።
*እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉ"* እና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።

"እነርሱ" የሚለው "መላእክት" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ተውላጠ-ስም እንደሆነ አስተውል። እነዚህ ዝሙትን ያደረጉት መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ይኖራሉ። ጴጥሮስ በኖህ ጊዜ ኃጢአትን ስላላደረጉት መላእክት ይናገራል፦
2ኛ ጴጥሮስ 2፥4-5 *"እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ"*።

በኖኅ ዘመን ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ በጨለማ ጉድጓድ ጥሎ ከመላእክት ጋር የተጋቡትን ደግሞ የጥፋት ውኃ አወረደባቸው። ቀደምት የቤተክርስቲያን አበት ሰማዕቱ ጀስቲን፣ ኢራኒየስ፣ የአሌክሳንድሪያው ክሌመንት፣ ኦሪገን ወዘተ ዘፍጥረት 6፥2 ላይ "የእግዚአብሔር ልጆች" የተባሉት "የሰማይ መላእክት" እንደሆኑ ተናግረዋል። ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
ouglas, J. D,Tenney, Merrill C, Silva, Moisés (2011). Zondervan Illustrated Bible Dictionary (Revised ed.). Grand Rapids, Mich. Zondervan.

መልካም የምስራች የሚባለው የባይብል ትርጉም"Good News Translation" ሰማያዊ ኑባሬዎች ከሰው ሴቶች ልጆች ጋር ጋብቻ እንዳረጉ" ተናግራል።
የሚገርመው በሱመሪያን፣ በአካዲያን፣ በባቢሎናውያን እና በአሶራዊያን ሥነ-ተረት"mythology" ውስጥ፦ "አን" የተባሉ ሰማያውያን ወንዶች አማልክት "ኪ" ከተባሉት ምድራውያን ሴቶች አማልክት ጋር ተጋብተው "አኑናኪ" የተባሉ ፍጥረት ተወለዱ" ይለናል። ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
Dalley, Stephanie (1989), Myths from Mesopotamia: Creation, the Flood, Gilgamesh, and Others, Oxford, England: Oxford University Press.

የመላእክት ጋብቻ ከእነዚህ ተረት የተቀዳ ነው እንጂ መላእክት ጾታ የላቸውም፥ ወንድም ሴትም አይደሉም። ነጻ ምርጫም የላቸውም። በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *”መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም”*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *”እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም”*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *”አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። ስለዚህ ከላይ ያለው የመላእክት ጋብቻ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ከፓጋን ሲወርድ ሲወራረድ ወደ ባይብል የገባ ስርቅርቅ እሳቤ ነው። አላህ ከአይሁድ እና ከክርስቲያን ፈሳድ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አላህ መለኮት ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥84 *"እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባ፥ በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው"*፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ إِلَـٰهٌ وَفِي الْأَرْضِ إِلَـٰهٌ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ

"ሥነ-መለኮት"theology" በግሪክ "ቴኦ-ሎጂአ" θεολογία ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ቴኦስ" Θεός ማለትም "አምላክ" እና "ሎጂአ" λογία ማለትም "ጥናት" ነው። "ቴኢኦስ" θεῖος የሚለው ቃል "ቴኦስ" θεός ማለትም "አምላክ"God" ለሚለው ቃል ገላጭ ቅጽል"adjective" ሲሆን "አምላክነት"God-head" ወይም "መለኮት"Divine" ማለት ነው፥ ይህም ቃል በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ 5 ጊዜ ተጠቅሷል።
ስለዚህ "መለኮት" ማለት በቋንቋ ደረጃ በቀላሉ "አምላክ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ"ﷻ" "መለኮት" ነው፦
43፥84 *"እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባ፥ በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው"*፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ إِلَـٰهٌ وَفِي الْأَرْضِ إِلَـٰهٌ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ
6፥3 *"እርሱም ያ በሰማያትና በምድር ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው"*፡፡ ምስጢራችሁን ግልጻችሁንም ያውቃል፡፡ የምትሠሩትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ وَهُوَ اللَّهُ فِي السَّمَاوَاتِ وَفِي الْأَرْضِ ۖ يَعْلَمُ سِرَّكُمْ وَجَهْرَكُمْ وَيَعْلَمُ مَا تَكْسِبُونَ

"ኢላህ" إِلَـٰه የሚለው ቃል "መለኮት" ወይም "አምላክ" ማለት ነው። "መለኮት" ማለት "ሁሉን ነገር ማድረግ የሚችል" "ሁሉን ነገር የሚያውቅ" "ሁሉን ነገር የሚያይ" "ሁሉን ነገር የሚሰማ" "በባዶነት መነሻ በሞት መዳረሻ የሌለው ሕያው" ማለት ነው። አንተ ምንድን ነህ? ብባል "ሰው ነኝ" ብዬ የሰው ባሕርያት ተራቢ ነኝ፣ ተጠሚ ነኝ፣ በዪ ነኝ፣ ጠጪ ነኝ ወዘተ እያልኩኝ እናገራለን፥ አላህ ምንድን ነው? ብንባል "አምላክ ነው" ወይም "መለኮት" ነው ብለን የመለኮት ባሕርያትን በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፥ በባዶነት መነሻ በሞት መዳረሻ የሌለው ሕያው ነው እያልን ታላቁ ባሕርይውን እንናገራለን፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው"*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *"አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *"አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
25፥58 *"በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ"*፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

አላህ በሰማያትና በምድር ሊገዙት የሚገባ መለኮት ነው፥ ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ታላቅ ባሕርይ አለው፦
16፥60 *"ለአላህም ታላቅ ባሕርይ አለው"*፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ وَلِلَّهِ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
30፥27 *"ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ታላቅ ባሕርይ አለው"*፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ وَلَهُ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

"ባሕርይ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አል-መሰል"الْمَثَلُ ሲሆን የአል-መሰል ብዙ ቁጥር ደግሞ "አል-አምሳል" الْأَمْثَال ነው። አላህ የእኔ ባሕርይ ይህ ነው ብሎ በቁርኣን የተናገረውን እንጂ እኛ ለእርሱ ምንም አይነት ባሕርይ ማድረግ ተከልክለናል፦
16፥74 *"ለአላህም ባሕርዮችን አታድርጉ፡፡ አላህ መሳይ እንደሌለው ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُون
42፥11 *"የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው"*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

በሰማያትም በምድርም የእርሱን ታላቅ ባሕርይ የሚመስል ምንም ነገር የለም። "ነገር" ማለት "አጠቃላይ ፍጥረት" ነው። እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው፥ የእርሱ መስማት እና ማየት ጊዜና ቦታ አያካብበውም።
የሥነ-ኑባሬ ጥናት”ontology” ምሁራን እንደሚያትቱት “ዛት” ذَات ማለት “ህላዌ”essence” ማለት ሲሆን “ምንድን” ተብሎ የሚጠየቅ "ምንነት" ነው፥ ምንነት የማንነት መሠረት ነው። "ሸኽስ" شَخْص ማለት "እኔነት"person" ማለት ሲሆን "ማን" ተብሎ የሚጠየቅ "ማንነት" ነው፥ ማንነት የምንነት መገለጫ ነው። አላህ የራሱ አንድ ማንነት አለው፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

"አና" أَنَا ማለት "እኔ" ማለት ሲሆን አንድ ነጠላ ማንነትን የሚያሳይ ነጠላ ተውላጠ-ስም ነው፥ ይህም አንድ ማንነት ምንነቱ አምላክ ስለሆነ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለም" በማለት ይናገራል። አላህ የራሱ ማንነት ስላለ “ነፍሲ” نَفْسِي ማለትም “እራሴ” ይላል፦
20፥41 *ለነፍሴም መረጥኩህ*፡፡ وَاصْطَنَعْتُكَ لِنَفْسِي

በዚህ አንቀጽ ላይ “ለነፍሴ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊነፍሢ” لِنَفْسِي ሲሆን “ለራሴ” ማለት ነው፤ የአላህ እራስነት”own self-hood” እንዳለው ያመለክታል።
አላህ ምንነቱን የሚያሳውቀን በሲፋው ነው። “ሲፋህ” صِفَة ማለትም “ባሕርይ”attribute" ማለት ነው፥ የእርሱ ባሕርያት የተሰየሙበት ስም አለው። “ኢሥም” اِسْم ማለት "ስም" ማለት ሲሆን አላህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል “አሥማኡል ሑሥና” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም “መልካም ስሞች” አሉት፦
20፥8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *"ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት"*፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
አላህ ምንድን ነው? ሲባል የምንነት ጥያቄ ስለሆነ የምንነቱ መታወቂያ የሆኑትን ባሕርያት የተሰየሙበትን ስም በመጥቀስ፦
1. "አል-ኻሊቅ" الْخَالِق ማለትም "ፈጣሪ" ነው፦
29፥24 *እርሱ አላህ "ፈጣሪው"፥ ከኢምንት አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ

2. "አስ-ሰመድ" الصَّمَد ማለትም "የሁሉ መጠጊያ" ነው፦
112፥2 *አላህ "የሁሉ መጠጊያ" ነው*፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

3. "አል-ገኒይ" الْغَنِيّ ማለትም "ተብቃቂ" ነው፦
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ *አላህም እርሱ "ተብቃቂው" ምስጉኑ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

4. "አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለትም "ረቂቅ" ነው፦
6፥103 ዓይኖች አያገኙትም፥ እርሱም ዓይኖችን ያያል፡፡ *እርሱም "ረቂቁ"፥ ውስጠ ዐዋቂው ነው*፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

እያልን እንዘረዝራለን። እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያስገኘ ፈጣሪ፣ ፍጥረታት በእርሱ ላይ ጥገኛ የሆኑ የሁሉ መጠጊያ፣ ከፍጥረቱ ምንም የማይገጅል ተብቃቂ፣ የፍጡራም አእምሮ መርምሮ የማይደርስበት ረቂቅ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ችግኝ መትከል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥2 *በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አውሮፓ ላይ ያለው የበረዶ ግግር እየቀለጠ ነው፥ ይህ በረዶ በዚህ ከቀጠለ አውሮፓን ጎርፍ ያጠቃትና ያጠፋታል የሚል ስጋት አለ። ይህ የሆነበት ምክንያት ደኖች በመመንጠራቸው የበረሓ መስፋፋት እየተከሰተ ስላለ ነው። በስፋቱም ከአውሮፓ የማይተናነሰው የሰሐራ በረሓ በፕላኔታችን ላይ የሙቀት መጨመር እያመጣ ነው።
የመሬት ከባቢ አየር በመሬት ዙሪያ የሚገኝ የጋዝ ክምችት ሲሆን የዚህ የከባቢ አየር የላይኛው ክፍል ማለትም ስትራቶስፌር ወደ ምድር ከሚመጣው አልትራቫዮሌት ጨረር ውስጥ 99% የሚሆነውን ውጦ የሚያስቀረውን “ኦዞን”ozone (O3) የተባለ የኦክስጅን ቅንብር ይዟል። ይህ ኦዞን እየሳሳ ያለው በምድሪቱ በረሓ ግለት እና ከሰው ሠራሽ ከሚመጡ የጋዝ ብክለት ነው። ምን ይሆን መፍትሔው?
አምላካችን አላህ”ﷻ” ከምድር የፈጠረን በውስጧ እንድናለማት ነው፦
11፥61ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ *እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም "አደረጋችሁ"*፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ ለለመነው ተቀባይ ነውና» አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيب

ከተፈጠርንበት ንዑስ አላማ አንዱ ምድርን እንድናለማ ነው። አንድ ሙሥሊም በመሠረተ-ልማት"infrastructure" ውስጥ ያለው ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው። ከሰዎች ጋር በሚኖረው ማኅበራዊ እሴት አምላካችን አላህ”ﷻ” በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አይሁን እንጂ በበጎ ነገር እና እርሱን በመፍራት እንድንረዳዳ አዞናል፦
5፥2 *በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ " የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ምድሪቱን ማልማት በጎ ነገር ነው። ምድሪቱን ከምናለማበት ነገሮች አንዱ ችግኝ መትከት ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ማንም ሙሥሊም አንድ ተክል ተክሎ ሰው ሆነ እንስሳ አሊያም አእዋፍ ቢበላው ሰደቃህ ይሆንለታል" ብለውናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 43
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ሙሥሊም የለም አንድ ተክል ተክሎ ሰው ሆነ እንስሳ ቢበላው ሰደቃህ ቢሆንለት እንጂ"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا مِنْ مُسْلِمٍ غَرَسَ غَرْسًا فَأَكَلَ مِنْهُ إِنْسَانٌ أَوْ دَابَّةٌ إِلاَّ كَانَ لَهُ صَدَقَة
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 63
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ማንም ሙሥሊም የለም አንድ ተክል ወይም አዝዕርት ዘርቶ ሰው ሆነ አእዋፍ ቢበላው ሰደቃህ ቢሆንለት እንጂ"*። عَنْ أَنَسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَغْرِسُ غَرْسًا أَوْ يَزْرَعُ زَرْعًا فَيَأْكُلُ مِنْهُ إِنْسَانٌ أَوْ طَيْرٌ أَوْ بَهِيمَةٌ إِلاَّ كَانَتْ لَهُ صَدَقَة

ይህንን ሰደቃ ከአላህ ዘንድ ለማግኘት የችግኝ ተከላው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ይቀጥላል፦
ሙሥነድ አሕመድ ሐዲስ 12491
አነሥ እብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ ውስጥ ችግኝ በእጁ የያዘ የትንሳኤ ቀን ቢደርስበትም ይትከላት"*። ﻋَﻦْ ﺃَﻧَﺲِ ﺑْﻦِ ﻣَﺎﻟِﻚٍ ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺇِﻥْ ﻗَﺎﻣَﺖْ ﻋَﻠَﻰ ﺃَﺣَﺪِﻛُﻢْ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔُ ﻭَﻓِﻲ ﻳَﺪِﻩِ ﻓَﺴْﻠَﺔٌ ﻓَﻠْﻴَﻐْﺮِﺳْﻬَﺎ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የነቢያችን”ﷺ” ነቢይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

"ነቢይ" نَبِيّ የሚለው ቃል "ነበአ" نَبَّأَ ማለትም "የሩቅ ወሬን አወራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ አውሪ" ማለት ነው። የሚወርድለት "የሩቅ ወሬ" ደግሞ "ነበእ" نَبَأ ይባላል፥ ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ነቢይ ከሦስት መንገድ በአንዱ ይወርድለታል፦
42፥51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም"*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

አንደኛው መንገድ አላህ በራእይ የሚያናግረው ነው፥ “ሩዕያ” رُّءْيَا ማለት “ራዕይ” ማለት ሲሆን ይህም ራዕይ ያ ነቢይ በሰመመን ወይም በተመስጦ ውስጥ ሆኖ አላህ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሁለተኛው መንገድ አላህ በቀጥታ የሚያናግረው ነው፥ “ተክሊም” تَكْلِيم ማለት በሁለት ማንነት መካከል የሚደረግ “ምልልስ”conversation” ሲሆን አላህ ያለ ራዕይ ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆኖ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሦስተኛው መንገድ አላህ በመልአክ የሚያናግረው ነው፥ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው።

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አላህ ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ሰው ሲያሳውቀው ያ ሰው ነቢይ ይባላል። አምላካችን አላህ"ﷻ" ነቢያችንን"ﷺ" በሦስተኛ መንገድ በመልአኩ ጂብሪል አናግሯቸዋል። አላህ ወደ እርሳቸው ያወረደላቸው ቁርኣን ደግሞ "አል-ገይብ" ነው። "አል-ገይብ" ٱلْغَيْبِ ማለት "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ሚስጥር" ማለት ሲሆን ከህዋስ ባሻገር ጥንት የተከሰተ፣ አሁን እየተከሰተ ያለ እና ወደ ፊት የሚከሰት ዕውቀት ነው፥ አላህ የሰማያትን እና የምድርን የሩቅ ሚስጥር ያውቃል። ይህንን የሩቅ ሚስጥር ለማንም ዐያሳውቅም፥ ለሚፈልገው መልእክተኛ ቢሆን እንጂ፦
49፥18 *"አላህ የሰማያትንና የምድርን "ሩቅ ሚስጥር" ያውቃል"*። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ
72፥26 *«እርሱ ”የሩቅ ሚስጥር” ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»* عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
72፥27 *ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም*፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

"አል-ገይብ" በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦ አል-ገይቡል ማዲ፣ አል-ገይቡል ሙዷሪዕ እና አል-ገይቡል ሙሥተቅበል ነው። ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"አል-ገይቡል ማዲ"
"አል-ገይቡል ማዲ" ٱلْغَيْب الْمَاضِي ማለት "ኀላፊያት የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ክስተት ነው። ይህንን የሩቅ ወሬ አምላካችን አላህ ለነቢያችን”ﷺ” “ኑሒሂ ዒለይከ” نُوحِيهِ إِلَيْكَ ማለትም “ወደ አንተ እናወርዳታለን” ወይም “ነቁሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ይናገራል፦
12፥102 *"ይህ ወደ አንተ የምናወርደው ሲኾን ከሩቅ ወሬዎች ነው፡፡ አንተም እነርሱ በእርሱ ላይ የሚመክሩ ኾነው ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም"*፡፡ ذَٰلِكَ مِنْ أَنبَاءِ الْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَ ۖ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ أَجْمَعُوا أَمْرَهُمْ وَهُمْ يَمْكُرُونَ
20፥99 *"እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች በአንተ ላይ እንተርካለን"*፡፡ كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ

"ወሬዎች" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አንባእ" أَنبَاء ሲሆን የነበእ ብዙ ቁጥር ነው። ነቢያችን"ﷺ" ከእርሳቸው በፊት ያለው ክስተት ሲከሰት ስላልተፈጠሩ በቦታው የሉም። ነገር ግን በጊዜና በቦታ ዕውቀቱ የማይገደበው አላህ "አስታውስ" በማለት ተርኮላቸዋል፦
38፥71 ጌታህ *«ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» አስታውስ*፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ
ነጥብ ሁለት
"አል-ገይቡል ሙዷሪዕ"
"አል-ገይቡል ሙዷሪዕ" ٱلْغَيْب ٱلْمُضَارِع ማለት "አሁናት የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ ቁርኣን ሲወርድ ከህዋስ ባሻገት እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው። ለምሳሌ ነቢያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው አንዷ ለሆነችው ለሃፍሳ”ረ.ዐ.”፦ "ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዐ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በፍጹም አልጠጣም” ብለው ይህ ወሬ በሚስጥር በመሰጠሯት ጊዜ ሄዳ ለዓኢሻ”ረ.ዐ.” ተናገረች። ነብይ ማለት የሩቅ ዕውቀት የሚገለጥለት ነውና ለዓኢሻ”ረ.ዐ.” በተናገረች ጊዜ የተናገረችውን ከፊሉን ዐሳውቀዋት ከፊሉን ችላ ብለው ሲተዉት፥ በዚያ በነገሯት ነገር ሃፍሳ”ረ.ዐ.”፦ ይህን ማን ነገረህ? ብላ አለቻቸው፤ ነቢያችንም”ﷺ”፦ «ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አሏት። ይህንን ጉዳይ አምላካችን አላህ እንዲህ ይነግረናል፦
66፥3 *"ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ፥ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት"*። وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው። "አንበአከ” أَنْبَأَكَْ ሆነ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ የሁለቱም ግስ ርቢ "ነበአ" نَبَّأَ ነው። ስለዚህ "ነቢይ" ማለት ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው። ከዚያም ባሻገር መመሪያው እራሱ በራሱ የነቢይነት መደብ ውስጥ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

"ንገራቸው" نَبِّئْ ለሚለው አሁንም "ነበእ" نَبِّئْ ሲሆን "ነበአ" نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። 66፥3 ላይ "ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ" ማለቱ የሚያጅብ ነው፥ በሁለተኛ መደብ "አስታውስ" እያለ በሦስተኛ መደብ ለራሳቸው "በመሰጠርክ ጊዜ" ሳይሆን "በመሰጠረ ጊዜ" ይላል። ሁሉን ዐዋቂው፥ ውስጠ ዐዋቂው አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር ስለሚያውቅ አወረደው፦
25፥6 *«ያ "በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር" የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

ነጥብ ሦስት
"አል-ገይቡል ሙሥተቅበል"
"አል-ገይቡል ሙሥተቅበል" ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለት "መጻእያት የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ መጪው ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚከሰት ነው። ለምሳሌ ስለ ጀነት እና ጀሃነም ያለው የሩቅ ወሬ ነው፦
3፥15 *«ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው"*፡፡ እርሱም «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም፣ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ
22፥72 *«ከዚህ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን» በላቸው"*፡፡ «እርሱም እሳት ናት፡፡ አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች ቀጥሯታል፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكُمُ ۗ النَّارُ وَعَدَهَا اللَّهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

"ልንገራችሁ" ለሚለው ቃል የገባው "ነበኡኩም" نَبِّئُكُم ሲሆን "ነበአ" نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ይህንን እንዲናገሩ አላህ "ቁል" قُلْ የሚል ትእዛዝ ያወርዳል። ቁርኣን ላይ ብዙ ቦታ በትንሳኤ ቀን ምን እንደሚከሰት ለማሳወቅ "አስታውስ" እያለ ይናገራል፦
54፥6 *"ከእነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ"*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ

ይህንን ትንቢት አምላካችን አላህ፦ "በእርግጥ ከጊዜ በኋላ ወደፊትም ታውቁታላችሁ" ይለናል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ
“ኢዝ” إِذْ በሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ ውስጥ “ፈዘከር” فَذَكِّرْ ማለትም “አስታውስ” የሚል ትእዛዝ አለ፥ አላህ ያለፈውን፣ ያሁኑን እና የሚመጣውን የሩቅ ወሬ እየነገራቸው "አስታውስ" ይላቸዋል። ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ “ሙዘከር” مُذَكِّرٌ ማለትም “አስታዋሽ” ናቸው። ነቢያችን”ﷺ” የሚያሳታውሱት በተወረዳቸው “ዚክር” ብቻ ነው፥ ይህም "ዚክር" ذِكْر ማለትም "ማስታወሻ" ቁርኣን ነው፦
88፥21 *አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና*፡፡ فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ
21፥50 *ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ “ዚክር” ነው*፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን? وَهَـٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَاهُ ۚ أَفَأَنتُمْ لَهُ مُنكِرُونَ
50፥45 ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው *በቁርኣን አስታውስ*፡፡ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

አምላካችን አላህ"ﷻ" ነቢያችንን"ﷺ"
በሁለተኛ መደብ፦ "አንተ ነቢዩ ሆይ" በማለት እራሱ እንደላከ ለማመልከት "ላክንህ" በማለት "ለሰዎች ሁሉ" እንደተላኩ ይናገራል፦
33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا
4፥79 *"ለሰዎችም ሁሉ መልክተኛ ኾነህ ላክንህ"፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ*፡፡ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا
45፥6 *እነዚህ በአንተ ላይ በውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህ እና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?* تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَ اللَّهِ وَآيَاتِهِ يُؤْمِنُونَ

መስካሪም በአላህ በቃ። ከላይ የተጠቀሱት አናቅጽ አላህ በነቢያችን"ﷺ" ላይ ያወረዳቸው የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፥ ከአላህ እና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ? ይህንን የሩቅ ሚስጥር ከተረዱ በኃላ እኚህን ነቢይ ማስተባበል ይቻል ይሆን? አላህ ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እንስሳት እና ነፍሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥26 *"አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

አምላካችን አላህ እኛም ለማስተማር የቤት እንስሳትን፣ የዱር እንስሳትን በራሪ ፍጥረትን፣ ነፍሳትን በቅዱስ ቃሉ አውስቷል። ከትንሿ ትንኝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ዝሆን ድረስ ምሳሌ እያደረገ አውስቷል፦
2፥26 *አላህ ማንኛውንም ነገር "ትንኝንም" ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

ሀ. የቤት እንስሳት

1. ፈረስ
38፥32 አለም «እኔ ፀሐይ በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ *ፈረስን*! መውደድን መረጥኩ፡፡» فَقَالَ إِنِّي أَحْبَبْتُ حُبَّ الْخَيْرِ عَن ذِكْرِ رَبِّي حَتَّىٰ تَوَارَتْ بِالْحِجَابِ

2. አህያ
62፥5 የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት ያልሠሩባት ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም *አህያ* ብጤ ነው፡፡ የእነዚያ በአላህ አንቀጾች ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ከፋ፡፡ አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ حُمِّلُوا التَّوْرَاةَ ثُمَّ لَمْ يَحْمِلُوهَا كَمَثَلِ الْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًا ۚ بِئْسَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

3. በቅሎ
16፥8 ፈረሶችንም፣ *በቅሎዎችንም*፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

4. ላም
2፥69 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ *ላም* ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا لَوْنُهَا ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ صَفْرَاءُ فَاقِعٌ لَّوْنُهَا تَسُرُّ النَّاظِرِينَ

5. ግመል
88፥17 ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ *ግመል* እንዴት እነደተፈጠረች! أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ

6. ከብት(በሬ)
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ *የከብት*፣ የበግና የፍየል እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

7. በግ
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ *የበግ* እና የፍየል እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

8. ፍየል
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በቃል ኪዳኖች ሙሉ፡፡ በእናንተ ላይ የሚነበበው ብቻ ሲቀር፡፡ የግመል፣ የከብት፣ የበግና *የፍየል* እንስሳዎች እናንተ በሐጅ ሥራ ላይ ኾናችሁ ማደንን የተፈቀደ ሳታደረጉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈርዳል፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ أُحِلَّتْ لَكُم بَهِيمَةُ الْأَنْعَامِ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّي الصَّيْدِ وَأَنتُمْ حُرُمٌ ۗ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيدُ

9. ውሻ
7፥176 በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ *ውሻ* ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡ وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَاهُ بِهَا وَلَـٰكِنَّهُ أَخْلَدَ إِلَى الْأَرْضِ وَاتَّبَعَ هَوَاهُ ۚ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ الْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ ذَّٰلِكَ مَثَلُ الْقَوْمِ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا ۚ فَاقْصُصِ الْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ
ለ. የዱር እንስሳት

1. ዝሆን
105፥1 *በዝሆኑ* ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ

2. አንበሳ
74፥51 *ከአንበሳ* የሸሹ፡፡ فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍ

3. ተኩላ
12፥13 «እኔ እርሱን ዩሱፍን ይዛችሁ መሌዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡ እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ *ተኩላ* ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ» አላቸው፡፡ قَالَ إِنِّي لَيَحْزُنُنِي أَن تَذْهَبُوا بِهِ وَأَخَافُ أَن يَأْكُلَهُ الذِّئْبُ وَأَنتُمْ عَنْهُ غَافِلُون

4. የሜዳ አህያ
74፥50 እነርሱ ልክ ደንባሪዎች *የሜዳ አህዮች* ይመስላሉ፡፡ كَأَنَّهُمْ حُمُرٌ مُّسْتَنفِرَةٌ

5. እባብ
7፥107 በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ *እባብ* ኾነች፡፡ فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ

6. ዝንጀሮ
7፥166 ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች *ዝንጀሮች* ኹኑ አልን፤» ኾኑም፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ

7. አሳማ
16፥115 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ *የአሳማንም* ስጋ፣ ያንንም በመታረድ ጊዜ በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ አመጸኛም ወሰን አላፊም ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ ۖ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

8. አሳ
37፥142 እርሱም ተወቃሽ ሲሆን *አሳው* ዋጠው፡፡ فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ
ሐ. በራሪ ፍጥረት

1. ሁድሁድ
27፥20 በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም *«ሁድሁድን* ለምን አላየውም! በእውነቱ ከራቁት ነበርን፡፡ وَتَفَقَّدَ الطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِيَ لَا أَرَى الْهُدْهُدَ أَمْ كَانَ مِنَ الْغَائِبِينَ

2. ወፍ
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ *ወፍ* ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡» وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

3. ቁራ
5፥31 የወንድሙንም ሬሳ እንዴት እንደሚሸሽግ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር *ቁራን* ላከለት፡፡ «ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡ ከጸጸተኞችም ኾነ፡፡ فَبَعَثَ اللَّهُ غُرَابًا يَبْحَثُ فِي الْأَرْضِ لِيُرِيَهُ كَيْفَ يُوَارِي سَوْءَةَ أَخِيهِ ۚ قَالَ يَا وَيْلَتَىٰ أَعَجَزْتُ أَنْ أَكُونَ مِثْلَ هَـٰذَا الْغُرَابِ فَأُوَارِيَ سَوْءَةَ أَخِي ۖ فَأَصْبَحَ مِنَ النَّادِمِينَ

4. ቢራቢሮ
101፥4 ሰዎች እንደ ተበታተነ *ቢራቢሮ* በሚኾኑበት ቀን። يَوْمَ يَكُونُ النَّاسُ كَالْفَرَاشِ الْمَبْثُوث

5. ንብ
16፥68 ጌታህም ወደ *ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

6. ዝንብ
22፥73 እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው ጣዖታት *ዝንብን* ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን ለመፍጠር ቢሰበሰቡም እንኳን አይችሉም፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَن يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ

7. አንበጣ
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ *አንበጣንም* ነቀዝንም እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

8. ትንኝ
2፥26 አላህ ማንኛውንም ነገር *ትንኝንም* ኾነ ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا

መ. ነፍሳት

1. ነቀዝ
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም *ነቀዝንም* እንቁራሪቶችንም ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

2. ሸረሪት
29፥41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን ጣዖታትን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች *ሸረሪት* ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

3. ጉንዳን
27፥18 በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ *ጉንዳኖች* ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች፡፡ حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

4. እንቁራሪት
7፥133 ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም *እንቁራሪቶችንም* ደምንም የተለያዩ ተዓምራት ሲኾኑ በነሱ ላይ ላክን ኮሩም ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ፡፡ فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ الطُّوفَانَ وَالْجَرَادَ وَالْقُمَّلَ وَالضَّفَادِعَ وَالدَّمَ آيَاتٍ مُّفَصَّلَاتٍ فَاسْتَكْبَرُوا وَكَانُوا قَوْمًا مُّجْرِمِينَ


ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom


ወሠላሙ ዐለይኩም