ሎሬት ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ በኢትዮጵያ የታሪክ ምሁር እና የታሪክ ተመራማሪ ሲሆኑ በአገራችን የታሪክ ሸውራራ ትርክትን በማቃናት ጉልህ ሚና ያደረጉ ሐራዊ ምሁር"Liberal Scholar" ናቸው፥ በተለይ ኢማም አህመድ አልጋዚ ረሒመሁሏህ ላይ የተቃጣውን የሐሰት ትርክት እንኩትኩት ያረጉ ገለልተኛ ምሁር ናቸው። ዛሬ ወደማይቀረው አኺራህ ሄደዋል፥ ለቤተሰባቸው፣ ለዘመድ አዝማዳቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው አምላካችን አሏህ ጽናቱን፣ መጽናናቱን፣ ትእግስቱን ይስጣቸው! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥርጣሬ
ጠርጣሪው ተጠርጣሪን በተጠርጣሪ ጥርጣሬ መጠርጠሩ "የማያጠራጥር ነው" ሲል ጠርጣሪ ኮሚቴ በጥርጣሬ ያለ ጥርጣሬ ተናግሯል፥ ተጠርጣሪው ደግሞ ጠርጣሪውን ጠርጥሮ ቢያስጠረጥረው ያልተጠረጠረ ተመነጠረ የተጠረጠረ አስመነጠረ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ! ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፦
49፥11 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ! ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡

ጦም ማለት ሥጋን በረሃብ መቅጣት ሳይሆን ነፍስን በሥጋ ላይ የበላይ ማድረግ ነው፥ የጦም ወር፦
1. ተቅዋእ የምናገኝበት
2. ዚክር የምንዘክርበት
3. ቁርኣን የምንቀራበት
4. በዱዓእ የምንዘወተርበት
5. ቀልባችንን የምንሰትርበት
6. ለዓመት የሚሆን መንፈሳዊ ጉልበት የምንቀበልበት
7. በረሃብ አለንጋ የሚለበለቡ ሰዎችን የምናስብበት ነው።
ሁለት ጥግ እርማት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ፥ አንዱ ጦም ማለት ከሥጋ አስተዋጽዖ ተከልክሎ የጥራጥሬ ነገር መብላት ነው ብሎ አስቦ ጦምን የሥጋ መቅጫ አለንጋ አርጎ ማሰብ የኦርቶዶክስ የአስታሰብ ውቅር"Mindset" ነው። ሁለተኛው ረመዷን የጦም ወር እንጂ የምግብ ወር ስላልሆነ በዚህ ወቅት እናትን፣ እኅትን፣ ሚስትን በምግብ ሥራ እንዲወጠሩ አርጎ ከአምልኮ ማዘናጋት ሲሆን ይህ የጦምን ዓላማ እና ዒላማ ካለመረዳት የመጣ የተጠናገረ እና የተንሸዋረረ አሳብ ነው።
አሏህ ያስተካክለን! አሚን።

ነጃሺይ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
5፥83 ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ
“አል ሐበሻህ” الْحَبَشَة ማለት “አሰባሳቢው” ማለት ሲሆን የመን ከሚኖሩ በመህራህ ሕዝቦች መካከል ሲኖሩ “የዕጣን አሰባሳቢዎች” ይባሉ የነበሩ ናቸው። “አል ሐበሻህ” የመን ከሚኖሩ ከመህራህ ሕዝቦች ወደ ሰሜኑ ክፍል የተሰበሰቡ ሴማዊ ሕዝቦች መጠሪያ ነው። ስለ አል ሐበሻህ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ቁርኣን ሲወርድ በአል ሐበሻህ ውስጥ ስለ ነገሠው ንጉሥ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ እንዳስሳለን።
“ነጃሺይ” نَّجَاشِيَّ ማለት “ንጉሥ” ማለት ሲሆን ወደ ጠቃሽ አመልካች መስተአምር “አል” ال ተደርጎ ሲነበብ “አን ነጃሺይ” النَّجَاشِيَّ ሲሆን “ንጉሡ”The king” ማለት ነው፥ ይህ ስም የማዕረግ ስም ነው። ይህ ንጉሥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠት ከ 614–631 ድኅረ ልደት በአክሱም መንግሥት የነገሠ ንጉሥ ነው፥ የተጸውዖ ስሙም በዐረቢኛ አነባነብ “አስሐማህ” أَصْحَمَة ሲባል፥ በአገራችን “አርማህ” ይባላል። “ንጉሥ አርማህ” በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ በጥቅሉ “አስሐማህ አን ነጃሺይ” أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ ይባላል። ይህ ንጉሥ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች ከ 615–616 ድኅረ ልደት ተቀብሎ አስተናግዷል፥ እንዲሁ እርሱ እና ሹማምንቱ ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ሱረቱል መርየምን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን አንብተዋል፦
5፥83 ወደ መልእክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ
የንጉሡ መሥለም የኢሥላም ጠል”Islamophobia” አቀንቃኝ የሆኑት ጭፍን ተከታዮች እንደዋሹት የአክራሪዎች ፈጠራ ሳይሆን “ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን” ብለው በቁርኣኑ ማመናቸውን አምላካችን አሏህ በቅዱስ ቃሉ የነገረን ነው። ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአሏህ ፈሪዎች በአሏህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ እነ ነጃሺይ እና ሹማምንቱ በአሏህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፦
3፥199 ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአሏህ ፈሪዎች በአሏህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአሏህ እና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው፥ በዚያም ወደ እነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አሏህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ
በአሏህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ካመኑ ሠልመዋል ማለት ነው። በነቢያችንም”ﷺ” ሐዲስ ላይ ነቢያችን”ﷺ” ነጃሺይ ከመሥለምም አልፎ ጻዲቅ ሰው እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 103
ጃቢር እንደተረከው፦ “አን ነጃሺይ በሞተ ጊዜ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ዛሬ ጻዲቅ ሰው ሞቷል፥ ተነሱ! ለወንድማችሁ ለአስሐማህ የግንዘት ጸሎት አድርጉ!። عَنْ جَابِرٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم حِينَ مَاتَ النَّجَاشِيُّ “ مَاتَ الْيَوْمَ رَجُلٌ صَالِحٌ، فَقُومُوا فَصَلُّوا عَلَى أَخِيكُمْ أَصْحَمَةَ

“ሷሊሕ” صَالِح ማለት “መልካም” ወይም ጻዲቅ” ማለት ሲሆን የሷሊሕ ብዙ ቁጥር “ሷሊሒን” صَّالِحِين ማለትም “መልካሞች” ወይም “ጻድቃን” ማለት ነው፦
3፥114 በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያምናሉ፣ በጽድቅ ነገርም ያዛሉ፣ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ፣ በበጎ ሥራዎችም ይጣደፋሉ፡፡ እነዚያም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَأُولَـٰئِكَ مِنَ الصَّالِحِينَ
2፥130 ከኢብራሂምም ሕግጋት እራሱን የበደለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? ማንም የለም። በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው፥ በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ
ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መልካሞች" ለሚለው የገባው ቃል “ሷሊሒን” صَّالِحِين ነው፥ ስለዚህ አስሐማህ አን ነጃሺይ “ሷሊሕ” መባሉን ከመሥለም አልፎ ሷሊሕ ሰው መሆኑን በቂ ማሳያ ነው። ከዚያ በመቀጠል እርሱ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች የሃይማኖት ወንድም ስለሆነ እሳቸው “አኺኩም” أَخِيكُمْ ማለትም “ወንድማችሁ” ብለውታል። ምእመናን ደግሞ ወንድማማቾች ናቸው፦
49፥10 ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 106
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ለባልደረቦቻቸው ስለ ስለዚያ ቀን ስለሞተበት ስለ ሐበሻው አን ነጃሺይ ሞት እንደነገሯቸው፦ ”ለወንድማችሁ ኢሥቲግፋር አርጉ!”። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَخْبَرَهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم نَعَى لَهُمُ النَّجَاشِيَّ صَاحِبَ الْحَبَشَةِ فِي الْيَوْمِ الَّذِي مَاتَ فِيهِ، وَقَالَ “ اسْتَغْفِرُوا لأَخِيكُمْ ”
“ሶላቱል ጀናዛህ” صَلَاة الجَنَازَة ማለት “የግንዘት ጸሎት” ማለት ሲሆን በኢሥላም የግንዘት ጸሎት የሚደረገው ለሙሥሊም ብቻ ነው። ለንጉሥ አርማህ ደግሞ የሶላቱል ጀናዛህ ክፍል የሆነው “ሶላቱል ጋኢብ” صَلَاة الغَائِبٌ ማለትም “የሩቅ ጀናዛህ” ተደርጓል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 105
ጃቢር አብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *”ነቢዩም”ﷺ” አስሐማህ አን ነጃሺይ ላይ የግንዘት ጸሎት አድርገዋል፥ አራት ተክቢራህ በእርሱ ላይ አድርገዋል”። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم صَلَّى عَلَى أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ، فَكَبَّرَ عَلَيْهِ أَرْبَعًا
ከላይ የተዘረዘሩት ሐዲሳት ንጉሥ አርማህ የአላህ ጥሪ ተውሒድን እንደተቀበለ ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያሉ። ስለዚህ የኢሥላም ጠል አቀንቃኝ የሆኑት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ የነዙት ጨባጣ እና ለማጣ ወሬ እንዲህ ድባቅ ይገባል። አስሐማህ አን ነጃሺይ መሥለሙ በዓለም የሚገኝ መላው ሙሥሊም ሁሉ የሚቀበለው እውነታ ነው። ይህን እውነታ አለመቀበል ትችላለክ፥ ግን ይህ ትርክት የአክራሪዎች እንጂ የሁሉም ሙሥሊም እንዳይደለ ለመቅጠፍ የሞከራችሁት ቅጥፈት ለዛሬ አልተሳካላችሁም። በአፈ ጮሌነት ቤተ መንግሥት እንደገባከው በአፈ ጮሌነት ጀነት አትገባም። ግልባጩን ለመምህር አባይነህ ካሴ አድርሱልኝ!
አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ ኦንሊይ ጂሰስ የሚባሉት "አካል" የሚለውን ቃል ሁልጊዜ የሚረዱት "ተክለ ሰውነት"Body" "ሶማ" σῶμα "ጀሠድ" جَسَد በሚል እንጂ "አካል" የሚለውን "ቀዋሜ ማንነት"Person" "ፕሮሶፓን" πρόσωπον "ሸኽስ" شَخْص በሚል አይረዱትም፥ "አካል" የሚለው የግዕዝ ቃል "አካለ" ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ" "መታወቂያ" ማለት ነው። አንድ ማንነት "እኔ" የሚል ቀዋሜ ማንነት ካለው "አካል" ይባላል፥ ይህንን ሥነ ማንነት ጥናት"Metaphysics" ስላላጠኑ ውይይት ላይ ሲቸገሩ እያየን ነው።
እኛ ሙሥሊሞች እና አይሁዳውያን "አሏህ አንድ ማንነት ነው" ስንል የሥላሴ አማንያን ደግሞ "ሦስት ማንነት ነው" ይላሉ፥ አምላክ ማንነት ከሌለው ኦንሊይ ጂሰሶች "ሦስት ነው" የሚለውን ተቃውመው "አንድ ነው" ሲሉ ምኑን ነው "አንድ ነው" የሚሉት? "አምላክነቱን" ካሉን አምላክነት "ምንነት" ነው። የሥላሴ አማንያንም "በምንነት አንድ ነው" ብለው እኮ ያምናሉ፥ የኦንልይ ጂሰስ ሙግት ወጥነት የሌለው እና ጥናት ላይ ያልተመሠረተ የውኃ ላይ ኩበት ነው።
"እግዚአብሔር ማንነትም አይደለም" "እግዚአብሔር ኢ ማንነትም"Matter" አይደለም" የሚል ምናባዊ አጣብቂኝ አረጉት፥ "እኔ" ብሎ የሚናገር አንድ አምላክ እንዳለ እኮ ብዙ ቦታ በባይብል ተጠቅሷል።
የኦንሊይ ጂሰስ ትምህርት ዛሬ ከሥላሴ የባሰ ውስብስብ ትምህርት እየሆነ ነው።
አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ዒድ አደባባይ
"አብዮት አደባባይ" የመንግሥት አደባባይ ሲሆን ይህ አደባባይ መስቀለኞች ክርስቲያን በዓመት አንዴ የመስቀል ደመራ ስለሚያረጉበት ለእነርሱ "መስቀል አደባባይ" ነው፣ ዋቄፈታዎች ዓመታዊ በዓላቸው በዚያ ስለሚያከብሩ "ኢሬቻ አደባባይ" ነው፣ እኛም ሙሥሊሞች ደግሞ በዓመት ሁለት ጊዜ የዒድ ጊዜ ዒዳችንን የምናከብርበት ሲሆን ለእኛ "ዒድ አደባባይ" ነው።
ኢንሻ አሏህ በዒድ ቀን "ዒድ አደባባይ" እንገናኝ!

ሆሣዕና
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
3፥49 በአሏህ ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን እና ለምጸኛን አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ
"ሆሣዕና" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሆሣና" ὡσαννά ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ነው፥ "ሆሣና" ὡσαννά የሚለው የግሪክ ቃል "ሆሻና" הוֹשַׁע נָא ከሚል የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ነው። "ሆሻና" הוֹשַׁע נָא የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "የሻ" יָשַׁע ማለት "አድን" ማለት ሲሆን "ና" נָא ማለት "አሁን" "እባክህ" ማለት ነው። እስራኤላውያን ለዳስ በዓል በቀረበ መዝሙር ላይ "አና ዮድ-ሄ-ቫቭ-ሄ ሆቮሲአህ ና" אָנָּ֣א יְ֭הוָה הֹושִׁ֘יעָ֥ה נָּ֑א ብለው ይዘምሩ ነበር፥ ትርጉሙ "ያህዌህ ሆይ! እባክህ፥ አሁን አድን" ማለት ነው፦
መዝሙር 118፥25 ያህዌህ ሆይ! እባክህ፥ አሁን አድን። אָנָּ֣א יְ֭הוָה הֹושִׁ֘יעָ֥ה נָּ֑א
"ያህ" יָהּ የሚለው ቃል "ያህዌህ" יהוה ለሚለው ምጻረ ቃል ሲሆን "ያሻ" יָשַׁע ማለት "አዳነ" ማለት ነው፥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ ማለት "ያህዌህ አዳኝ ነው" ማለት ሲሆን መሢሑ የያህዌህ መሢሕ ሲሆን የሚመጣው በያህዌህ ስም ነው፦
መዝሙር 118፥26 በያህዌህ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው። בָּר֣וּךְ הַ֭בָּא בְּשֵׁ֣ם יְהוָ֑ה
ኢየሱስ "እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም" ሲል የአብ ስም ያህዌህ መሆኑን ያስረዳል፦
ዮሐንስ 5፥43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም።
ዮሐንስ 12፥13 የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ “ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው” እያሉ ጮኹ። ἔλαβον τὰ βαΐα τῶν φοινίκων καὶ ἐξῆλθον εἰς ὑπάντησιν αὐτῷ, καὶ ἐκραύγαζον Ὡσαννά, εὐλογημένος ὁ ἐρχόμενος ἐν ὀνόματι Κυρίου, καὶ ὁ Βασιλεὺς τοῦ Ἰσραήλ.
ብሉይ ላይ "ዮድ-ሄ-ቫቭ-ሄ" יְהוָ֑ה ተብሎ የተቀመጠው ቴትራግራማቶን አዲስ ኪዳን ላይ "ኩርዮስ" κύριος በሚል ስም መቀየሩ ለማምታታት ነው እንጂ "በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" ሲባል እውነታው "በያህዌህ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው" ለማለት ነው። ዳዊት በያህዌህ ስም የመጣ የእስራኤል ንጉሥ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥45 ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን፦ "አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ በሠራዊት ጌታ በያህዌህ ስም እመጣብሃለሁ" አለው። וַיֹּ֤אמֶר דָּוִד֙ אֶל־הַפְּלִשְׁתִּ֔י אַתָּה֙ בָּ֣א אֵלַ֔י בְּחֶ֖רֶב וּבַחֲנִ֣ית וּבְכִידֹ֑ון וְאָנֹכִ֣י בָֽא־אֵלֶ֗יךָ בְּשֵׁם֙ יְהוָ֣ה צְבָאֹ֔ות אֱלֹהֵ֛י מַעַרְכֹ֥ות יִשְׂרָאֵ֖ל אֲשֶׁ֥ר חֵרַֽפְתָּ׃
ዳዊት በያህዌህ ስም ስለመጣ "ዳዊት" የሚለው ስም "የአብ ስም ነው" እንደማንል ሁሉ ኢየሱስ በያህዌህ ስም ስለመጣ "ኢየሱስ" የሚለው ስም "የአብ ስም ነው" አንልም። በያህዌህ ስም የሚመጣው የዳዊት ልጅ ብቻ ሳይሆን የዳዊትም መንግሥት ናት፦
ማርቆስ 11፥10 በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም፡” እያሉ ይጮኹ ነበር።
የኢየሱስ አስገኚ ያህዌህ ኢየሱስን መሢሕ አርጎ ሲልከው ያ መሢሕ ሲመጣ በአብ ስም ነው፥ ያህዌህ አምላክ ጐብኝቶ ለሕዝቡ አዳኝ አድርጎአልና፥ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ በባሪያው በዳዊት ቤት መሢሑን አስነስቶልናል፦
የሐዋርያት ሥራ 5፥31 ይህን አምላክ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ "ራስ" እና መድኃኒትም "አድርጎ" በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው። τοῦτον ὁ Θεὸς Ἀρχηγὸν καὶ Σωτῆρα ὕψωσεν τῇ δεξιᾷ αὐτοῦ τοῦ δοῦναι μετάνοιαν τῷ Ἰσραὴλ καὶ ἄφεσιν ἁμαρτιῶν.
"አድርጎ" የሚለው ቃል አምላክ አድራጊ ሲሆን ኢየሱስ ተደራጊ መሆኑን ያመላክታል፥ አምላክ ኢየሱስን መድኃኒት ካረገው ኢየሱስ መድኃኒትነቱ የባሕርይ ገንዘቡ ሳይሆን በመደረግ ላይ የተመሠረተ የጸጋ ብቻ እና ብቻ ነው። አምላክ ከዳዊት ዘር ከማርያም እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ እንጂ እራሱ አልመጣም፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 ከዚህም ሰው ዘር አምላክ እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።
"ሆሣዕና" ማለት "ምስጋና" በሚል ይመጣል፥ አምላክ ከዳዊት ዘር ላመጣው ለዳዊት ልጅ ሕዝቡ "ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ" ሲሉ ኢየሱስ በአብ ስም የመጣ መሢሕ እንደሆነ ገብቷቸው ነው እንጂ ሕዝቡ “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው" በማለት የሚመጣው መሢሕ በማንነቱ ነቢይ መሆኑን በቅጡ እና በአግባብ አበጥረው እና አብጠርጥረው ተረድተዋል፦
ማቴዎስ 21፥9 የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ማቴዎስ 21፥11 ሕዝቡም፦ “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው” አሉ።
"ክርስቶስ" የሚለው ቃል "ኽሪስቶስ" χριστός ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "መሢሕ" የሚለው ቃል ደግሞ "ማሺያኽ" מָשִׁיחַ ከሚል የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ነው፥ ኢየሱስ በጌታ አምላክ የተቀባ የጌታ ቅቡዕ"The Lord's Christ" የአምላክ ቅቡዕ"The Christ of God" ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 ክርስቶስ የአምላክ ነው።
ሉቃስ 2፥26 የጌታን ቅቡዕ ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።
ሉቃስ 9፥20 “እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ “የአምላክ ቅቡዕ ነህ” አለ።
በዕብራይስጥ "ማሺያኽ" מָשִׁיחַ ወይም በግሪክ "ኽሪስቶስ" χριστός አሊያም በግዕዝ "ቅቡዕ" ማለት "የተቀባ" ማለት ነው፥ ስለዚህ "ኢየሱስ" የአብ ስም ወይም ያህዌህ ሳይሆን የያህዌህ መሢሕ ነው። አንዱ ጌታ አምላኩ ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እና በኃይል በመቀባት መሢሕ አደረገው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 አምላክ ኢየሱስን ጌታ እና "ክርስቶስ እንዳደረገው" የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።
የሐዋርያት ሥራ 10፥38 አምላክ የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም “ቀባው”።
ዕብራውያን 1፥9 አምላክ አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ።
በዲኑል ኢሥላም ኢየሱስ "አል መሢሕ" ነው፥ አምላካችን አሏህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች ላይ 11 ጊዜ ኢየሱስ "መሢሕ" مَسِيح መሆኑን ነግሮናል። ኢየሱስ በአሏህ ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን እና ለምጸኛን አድኗል፦

ክርስቲያኖች ሆይ! የመሢሑን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ሠለስቱ አማልክት
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
"ሥሉስ" ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን መደበኛ ቁጥር"Cardinal Number" ነው፥ "ሣልስ" ማለት "ሦስተኛ" ማለት ሲሆን ተረኛ ቁጥር"Ordinal Number" ነው። "ሠለስቱ" ማለት "ሥሉስ" ለሚል ውስን ጠቃሽ አመልካች ሲሆን "ሦስቱ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ አናንያ፣ ሚሳኤል እና አዛርያን ወይም በቤተ መንግሥት ስማቸው ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብደናጎ "ሦስቱ ሰዎች" ተብለዋል፦
ዳንኤል 3፥23 እነዚህም "ሦስቱ ሰዎች" ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ።
አናንያ፣ ሚሳኤል እና አዛርያን በምንነት አንድ ናቸው፥ አናንያ ሰው ነው፣ ሚሳኤል ሰው ነው፣ አዛርያን ሰው ነው። ግን በማንነት ሦስት ስለሆኑ "ሦስት ሰዎች" ናቸው፥ እያንዳንዳቸው ሙሉ ሰው ናቸው። በተመሳሳይ በሥላሴ እሳቤ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት ስለሆኑ "ሦስቱ አማልክት" ይባላሉ፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22
"ሠለስቱ አማልክት ልዑላን አሐዱ ሥልጣነ ምልክናሆሙ"
ትክክለኛ ትርጉሙ "የአምላክነታቸው ሥልጣን አንድ የሆነ ሦስቱ አማልክት ልዑላን ናቸው" የሚል ነው፥ ዐማርኛው ላይ "የገዥነታቸው ሥልጣን አንድ ሲሆን ሦስቱ ልዑላን ገዥዎች ናቸው" ብሎ ቢያስቀምጥም "ሠለስቱ አማልክት" ማለት "ሦስቱ አማልክት" ማለት ነው። ሰው የማያነብ ይመስላችኃል? "አማልክት" የሚለውን ቃል ስታፍሩበት በዐማርኛ "ገዥዎች" ብላችሁ ብትደበቁ ከአንባቢ የምታመልጡ ይመስላችኃል? "አማልክት" የሚለው ቃል "አምላክ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን በጸያፍ ርቢ "አምላኮች" ማለት ነው። አንድ ሰው ይህንን እያወቀ በሥላሴ ትምህርት ውስጥ ይዘልቅ ይሆን?
"ነገሥታት" የሚለው ቃል "ንጉሥ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን በጸያፍ ርቢ "ንጉሦች" ማለት ነው፥ በሥላሴ እሳቤ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት ስለሆኑ "ሦስት ነገሥታት" ይባላሉ፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 26
"ሦስት ነገሥታት አንድ አገዛዝ ናቸው"
በአንድ መንግሥት ውስጥ ሦስት ነገሥታት ሲመሩ አይታያችሁም? በዚህ ቢበቃ ይገርም ነበር። "እግዚእ" ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ "አጋእዝት" ማለት "ጌቶች" ማለት ሲሆን በሥላሴ እሳቤ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት ስለሆኑ "ሦስት ጌቶች" ይባላሉ፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 26
"ሠለስቱ አጋእዝት አሐዱ ትእዛዞሙ"
ትርጉሙ "ትእዛዛቸው አንድ የሆነ ሦስቱ ጌቶች ናቸው" የሚል ነው። ነቢያት እና ሐዋርያት "አንድ አምላክ" "አንድ ጌታ" ብለው ባስተማሩበት አንደበት ውልብ ብሎባቸው "ሦስት" የሚለውን ቃል አንድ አምላክ ጋር ድርሽ አርገውት አያውቁም። አምላካችን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ የሥላሴ አማንያን ሆይ! «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፦

የማንበቡ ክህሎት እና የማወቁ ክጃሎት ያለው ሰው ይህ እውነት ሲገባው ይሠልማል፥ ወደ ኢሥላም ከመጣችሁ በለሆሳው እና በደምሳሳው የኢሥላም ጭብጡ ተውሒድ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ሦስት እግዚአብሔር

"ጸባዖ" ማለት "ሣር" "ጭፍራ" ማለት ነው፥ "ጸባዖት" ማለት "ጸባዖ" ለሚል ብዙ ቁጥር ሲሆን "ሠራዊት" "ጭፍሮች" ማለት ነው። "ጸባዖ" ማለት ሁለተኛው ትርጉም "አሸናፊ" "ኃያል" ማለት ነው፥ "ጸባዖት" ማለት "ጸባዖ" ለሚል ብዙ ቁጥር ሲሆን "አሸናፊዎች" "ኃያላን" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ በዘወትር ጸሎት ላይ "ጸባዖት" የሚለው ቃል "አሸናፊ" በሚል መጥቷል፦
የዘወት ጸሎት ቁጥር 7
"ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያት ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ"
ትርጉሙ "አሸናፊ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሠገናለህ፥ ምስጋናህም በሰማይ በምድር የመላ ነው" ማለት ነው፥ "መንበረ ጸባዖት" ማለት እራሱ "የጸባዖት መቀመጫ" ማለት እዚህ ዙፋን ላይ የሚቀመጡት ሦስት አሸናፊዎች ናቸው፦
ድርሳነ መስቀል ዘሰኔ ምዕራፍ 28 ቁጥር 33
"ሥሉስ ጸባዖት"
"ሥሉስ" ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ሥሉስ ጸባዖት" ማለት "ሦስት ጸባዖት" ማለት ነው። በሥላሴ እሳቤ ሦስት ኃያላን እግዚአብሔር አሉ፦
ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምዕራፍ 11 ቁጥር 11
"ሥሉስ እግዚአብሔር ጸባዖት"
"ሥሉስ እግዚአብሔር" ማለት "ሦስት እግዚአብሔር" ማለት ሲሆን እነዚህ እግዚአብሔር የሚባሉት ሦስቱ እግዚአብሔር፦
፨ እግዚአብሔር አብ አንዱ እግዚአብሔር
፨ እግዚአብሔር ወልድ ሁለተኛው እግዚአብሔር
፨ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስተኛው እግዚአብሔር ናቸው።
ሐምሌ 7 ለሚከበረው የሥላሴ ዓመታዊ በዓለ ዋዜማ ሐምሌ 6 ላይ እንዲህ የሚል ዜማ አለ፦
1. "ነአምን ወናመልክ በአሐዱ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ"
ትርጉም፦ "ከዓለም በፊት በነበረው በአንዱ እግዚአብሔር እናምናለን እናመልካለን"
2. "ወነአምን በካልኡ እግዚአብሔር ዘበምልክናሁ ለአብ ይመስሎ"
ትርጉም፦ "በአምላክነቱ አብን በሚመስለው በሁለተኛው እግዚአብሔር እናምናለን።
3. "ወነአምን በሣልሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘይመልዕ ኲሎ"
ትርጉም፦ "ሁሉን በሚመላ መንፈስ ቅዱስ በሦስተኛው እግዚአብሔር እናምናለን"
ይህንን ዚቅ የደረሰው በ 570 ድኅረ ልደት ቅዱስ ያሬድ እንደሆነ ይታሰባል፥ ያሬድ መድብለ አማልክት አምላኪ ነበርን? መለኮት ሦስትነት እንዳለው እና በሦስት አካላት ታውቃ የምትመለከው ሦስትነት ማን ናት?
ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት ምዕራፍ 7 ቁጥር 68
"ለመለኮት ሦስትነት ምስጋና ይገባል"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘቀዳሚት ምዕራፍ 7 ቁጥር 75
"ለሥላሴ ሦስትነት ምስጋና ይገባል"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 99 ቁጥር 5
"ልዩ የምትሆን ሦስትነት በሦስት አካላት ታውቃ የምትመለክ ናት"።
"አንድ እግዚአብሔር" ብላችሁ ሕዝቡን ትሸውዱት ይሆን? በእርግጥ ነቢያት እና ሐዋርያት "አንድ እግዚአብሔር" ብለው እንጂ "ሦስት እግዚአብሔር" "ሁለተኛው እግዚአብሔር" "ሦስተኛው እግዚአብሔር" ብለው አላስተማሩም፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።
አምላካችን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ የሥላሴ አማንያን ሆይ! «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፦

በአንድነቱ ሁለትነት ሦስትነት የሌለበት እና በምንነት በማንነት አንድ የሆነው አንዱ አምላክ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

አንኽ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ
"ሒሮግልይፊኮስ" ἱερογλυφικός ማለት "ቅዱስ ቅርፅ" ማለት ሲሆን የግብፃውያን የፊደል ገበታ"Hieroglyphs" በድንጋይ ላይ አሊያም በደንገል"Papyrus" ላይ የተጻፈ ነው፥ ይህ የፊደል ገበታ ከ 3250 ቅድመ ልደት እስከ 400 ቅድመ ልደት የነበረ ሲሆን ከግብፃውያን የፊደል ገበታ አንዱ አንኽ"Ankh" ነው።
በግብፃውያን "አንኽ" ꜥnḫ ማለት "ሕይወት" ማለት ሲሆን ምልክቱ "ቶ" ነው፥ በግብፃውያን ሥነ ተረት ጥናት"Egyptian mythology" "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ የተመሳቀለ መስቀል "ሆረስ" የተባለው አምላክ "ለዳግማዊ ራምሴ ንጉሥ የሰጠው ሕይወት ነው" ተብሎ ይታመናል። "ሆረስ" የተባለው ጣዖት የመራባት፣ የእርሻ፣ የሞት እና የትንሣኤ አምላክ ከተባለው "ኦስሪስ" አባቱ እና የኦስሪስ ሚስት ከሆነችው ሴት አምላክ "አይሲስ" እናቱ የተወለደ ነው" ተብሎ ይታመናል።
"ቶ" ምልክት ያለው አንኽ የእናትየው የአይሲስ የእጅ እንጥልጥ ነው፥ አንኽ በተለይ የግብፅ የሕይወት ምልክት እና ከሞት በኋላ ስለሚኖረው ሕይወት የሚያመለክት የጥንታዊ ግብጻውያን የጣዖት ምልክት ሲሆን የግብፃውያን አማልክት ብዙውን ጊዜ በቀኝ እጅ ይይዙት ነበር፡፡
"ቶ" ምልክት ያለው አንኽ ወደ ክርስትና ስርዋፅ ሆኖ የገባው በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደት ሲሆን "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ በኃላ ላይ የአዲስ ኪዳን ብጥስጣሾች"Fragments" በሆኑት ደንገሎች ላይ ተጽፎ ይገኛል፥ ለምሳሌ፦ 66 በ 150 ድኅረ ልደት ገደማ፣ ደንገል 45 በ 250 ድኅረ ልደት ገደማ እና ደንገል 75 250 ድኅረ ልደት ገደማ ልባሶቻቸው ላይ የመስቀል ምልክት"Staurogram" ተደርጓል። ዋቢ ምንጭ ይመልከቱ፦
የብሪታኒካ መድብለ ዕውቀት(ኢንሳይክሎፔድያ) (1946)፣ ጥራዝ 6፣ ገጽ 753
"ቶ" ምልክት ያለው አንኽ ወደ ክርስትና ሰርጎ ገብ በመሆን ዘው ብሎ ሲገባ በድርሳነ ዑራኤል፣ በፍካሬ ኢየሱስ፣ በራእየ ሲኖዳ፣ በራእየ ሳቤላ፣ በመጽሐፈ ምሥጢር እና በገድለ ፊቅጦር "ይመጣል" ተብሎ የሚጠበቀው "ቶ" የተባለው ንጉሥ "ቴዎድሮስ" ሲሆን ምልክቱ "ቶ" ነው። የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 14 አንድምታ ላይ ስለ ቴዎድሮስ መምጣት ይመልከቱ!
በግሪክ "ቴዎስ" θεός ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ድሮስ" δῶρος ማለት "ስጦታ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ቴዎ ድሮስ" θεό δῶρος ማለት "የአምላክ ስጦታ" ማለት ነው። በግሪክ ሥነ ተረት "ሲቡላ" Σίβυλλα መጻዒ ጊዜን የሚተነትን "ትንቢት" ሲሆን ግሪካውያን በግሪክ አማልክት መንፈስ፦ "ጥቁር ንጉሥ ከጥቁር አገር ይመጣል፥ ስሙም "ቴዎድሮስ" ነው" ብለው የተናገሩትን ምናባዊ ንጉሥ ነው፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ይህንን አስተምህሮት የቀየጠችው ከእነዚህ ዐረማዊ"Pagan" አስተምህሮት ነው።
፨ በመጀመር እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" አቆጣጠር ከ 1413 ድኅረ ልደት እስከ 1416 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የቀዳማዊ አጼ ዳዊት እና የንግሥት ጽዮን መንገሻ ልጅ "ወልደ አንበሳ" እራሱ "ያ ይጠበቀው ቴዎድሮስ ነኝ" ብሎ ትንቢቱ ሳይሳካ የቀረው ቀዳማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ነው።
፨በመቀጠል እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ አቆጣጠር ከ 1811 ድኅረ ልደት እስከ 1860 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የደጅ አዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ እና የአትጠገብ ወንድ ወሰን ልጅ "ካሳ ኃይሉ" በፈረስ ስሙ "አባ ታጠቅ" በወታደራዊ ስሙ "መይሳው ካሳ" እራሱ "ያ ይጠበቀው ቴዎድሮስ ነኝ" ብሎ ትንቢቱ ሳይሳካ የቀረው ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ነው።
፨ በመሠለስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ "ሣልሳዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ይመጣል፣ ኢትዮጵያ የዓለም ገዥ ትሆናለች፣ የዓለም መንግሥታት በሙሉ ይታዘዙታል" ብለው ዛሬ ላይ ብዙኃኑ እየጠበቁ ነው።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት እየሰማናቸው ካሉ የቆረፈዱ የምኞት ተረቶች መካከል "ቶ ንጉሥ የተባለ ኢትዮጵያን የሚገዛ ንጉሥ ይነግሣል" የሚለው ትርክት ከማኅበረ ቅዱሳን እስከ ፋኖ፣ ከጴጥሮሳውያን እስከ ሞዐ ተዋሕዶ፣ ከባልደራስ እስከ ኢትዮ 360 ያሉት ደሴታውያን የሚጠብቁት ይህንን ተስፋ ነው።
ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የ "ቶ" መስቀል እሳቤ ከግብፅ ሥነ ተረት የተወሰደ ከንቱ ዝንባሌ ሲሆን የ "ቴዎድሮስ" እሳቤ ከግሪክ ሥነ ተረት የተወሰደ ከንቱ ዝንባሌ ነው። እናንተ እነዚህ እሳቦት የምታራምዱ፣ የምታቀንቅኑ እና የምታስቀነቅኑ ክርስቲያኖች ሆይ! ከእናንተ በፊት በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ፦

አምላካችን አሏህ የየተሳሳቱን የዐረማዊ ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች ከመከተል ይጠብቀን! አሚን።