ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.7K subscribers
75 photos
80 videos
19 files
1.77K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
Audio
ሙታን ሰዎች ዱዓችንን ይሰማሉን?

16፥20 እነዚያም ከአሏህ ሌላ የምትጠሯቸው ምንንም አይፈጥሩም፡፡ እነርሱም ይፈጠራሉ። وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَا يَخْلُقُونَ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
16፥21 ሕያው ያልኾኑ ሙታን ናቸው፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም፡፡ أَمْوَاتٌ غَيْرُ أَحْيَاءٍ ۖ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ
35፥13 እነዚያም ከእርሱ ከአሏህ ሌላ "የምትጠሯቸው" የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡ ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ
7፥194 እነዚያ ከአሏህ ሌላ "የምትጠሯቸው" እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እስቲ ለእናንተ ይመልሱላችሁ። إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

በሸይኽ ኢልያሥ አሕመድ
ተሶዉፍ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

91፥9 ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا

"ነፍሥ" نَفْس ማለት "እራስነት"Own self" ማለት ነው፥ "ኑፉሥ" نُفُوس‎ ወይም "አንፉሥ" أَنْفُس‎ ደግሞ "ነፍሥ" نَفْس ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "ነፍሳት" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ የሚመለከተው ልባችንን እና ሥራችንን እንጂ ቅርጻችንን እና ገንዘባችንን አይደለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 42
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ወደ ቅርጻችሁ እና ገንዘባችሁ አይመለከትም፥ ነገር ግን ወደ ልባችሁ እና ሥራችሁ ይመለከታል"፡፡  عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ ‏"‏

ልብ የምንነይትበት የኒያህ መቀመጫ ነው፥ ሥራ የሚለካው በኒያህ ስለሆነ ሥራችን የልባችን ውጤት ነው። ጽድቅ መልካም ሥነ ምግባር"Ethics" ሲሆን በግልጠተ መለኮት በኩል ከሥነ መለኮት የሚመጣ ነው፥ በተቃራኒው ኃጢአት በልብህ ውስጥ የሚሸረብ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ, 45, ሐዲስ 16
አን ነዋሥ ኢብኑ ሠዕማል አል አንሷሪይ እንደተረከው፦ "እኔም "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ጽድቅ እና ኃጢአት ጠየኳቸው፥ እርሳቸውም፦ "ጽድቅ መልካም ሥነ ምግባር ነው፥ ኃጢአት በልብህ ውስጥ የሚሸረብ ነው" አሉ"።  عَنِ النَّوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنِ الْبِرِّ وَالإِثْمِ فَقَالَ ‏ "‏ الْبِرُّ حُسْنُ الْخُلُقِ وَالإِثْمُ مَا حَاكَ فِي صَدْرِكَ ‏"‏ ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ, 45, ሐዲስ 17
አን ነዋሥ ኢብኑ ሠዕማል አል አንሷሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጽድቅ መልካም ሥነ ምግባር ነው፥ ኃጢአት በነፍስ ውስጥ የሚሸረብ ነው"።  عَنِ النَّوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْبِرُّ حُسْنُ الْخُلُقِ وَالإِثْمُ مَا حَاكَ فِي نَفْسِكَ ‏"‏ ‏

"ልብ" እና "ነፍስ" በአንድ ዐውድ ላይ ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ መምጣቱ በራሱ ነፍስ ውሳጣዊ ልብን ያመለክታል፥ ልብ ይህን ያክል በሰው ሕይወት ላይ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው። በነፍስ ውስጥ ያለው ዝንባሌ ደግሞ "ነፍሢያህ" نَفْسِيَّة‎ ይባላል፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር ”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

አሏህ ነፍስን በተሶዉፍ ካላጠራት በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናት። “አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”Inclination” ማለት ነው፥ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው "ዝንባሌ" ነው። ዝንባሌ ደግሞ ቦታ ከተሰጠው ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፦
25፥43 ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?። أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

"ዙህድ" زُهْد ማለት "መላቀቅ"Detachment" ማለት ሲሆን ነፍስን ከዝንባሌ መላቀቅ ነው። በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ ያላቀቀ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ ያላቀቀ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

"ተዝኪያህ” تَزكِية የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጥራራት" ማለት ነው። ነፍሱን ከዝንባሌ ያጠራት በእርግጥ ዳነ፥ በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ፦
91፥9 ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا
91፥10 በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ፡፡ وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا

"ያጠራት" ለሚለው የገባው ቃል "ዘካ-ሃ" زَكَّاهَا ነው፥ "አፍለሐ" أَفْلَحَ ማለት "ዳነ" ማለት ሲሆን ተዝኪያ ነፍስን ከዝንባሌ የምናድንበት ነው። ነፍስን ከዝንባሌዋ ማጥራት "ተዝኪያህ" تَزكِية ሲባል ኢብራሂም እና ልጁ ኢሥማዒል ወደ አሏህ "ከክህደት የሚያጠራቸውን ላክ" ብለው ዱዓእ አርገው ነበር፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልእክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን፣ መጽሐፍን እና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን፣ "ከክህደት የሚያጠራቸውን ላክ! አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚያጠራቸውን" ለሚለው የገባው ቃል "ዩዘኪ-ሂም" يُزَكِّيهِمْ ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ዘካ" زَكَىٰ ነው፥ ጊዜው ሲደርስ አምላካችን አሏህ ከክህደት የሚያጠራቸው መልእክተኛ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" ልኳል፦
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና "ከክህደት "የሚያጠራችሁ"፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልእክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚያጠራችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ዩዘኪ-ኩም” يُزَكِّيكُمْ ነው። ዓይነ ስውሩ ከኀጢአቶቹ ሊጥራራ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የመጣው ይህንን ዋቢ እና ታሳቢ አርጎ ነው፦
80፥3 ምን ያሳውቅሃል? ከኀጢአቶቹ "ሊጥራራ" ይከጀላል፡፡ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّىٰ

ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከክህደት የሚያጠሩት በተዕሊም፣ በተርቢያህ እና በተዕዲል ነው፥ "ተዕሊም” تَعْلِيم‎ ማለት “ትምህርት” ማለት ሲሆን፣ “ተርቢያህ” تَرْبِيَة ማለት “እድገት” ማለት ሲሆን፣ “ተዕዲል” تَعْدِيل‎ ማለት ደግሞ “ግብረገብ” ማለት ነው።
"ሶፋእ" صَفَاء የሚለው ቃል "ሶፋ" صَفَا ማለትም "ነጻ" "ጠራ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽሕና" "መጥራራት" ማለት ነው፥ "ተሶዉፍ" تَّصَوُّف የሚለው ቃል "ተሶወፈ" تَصَوَّفَ ማለትም "ተነጻ" "ተጥራራ" "ተማለለ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መንጻት" "መጥራራት" "ተማልሎአዊነት"Mysticism" ማለት ነው፥ "ሙተሶዉፍ" مُتَصَوُّف‎ ማለት "ተማልአዊ" ማለት ሲሆን ነፍስን በአርምሞ ለማጥራት የሚደረገ ተሟልሏዊነት መሠረቱ ቁርኣን እና ሐዲስ ነው፦
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 3
ፈዷላህ ኢብኑ ዑበይድ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ "ከራሱ ነፍስ ጋር የታገለ ሙጃሂድ ነው"። فَضَالَةَ بْنَ عُبَيْدٍ، وَسَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ

እዚህ ሐዲስ ላይ "የታገለ" ለሚለው የገባው ቃል "ጃሀደ" جَاهَدَ መሆኑን አስምርበት! “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَاهَدَ‎ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው፥ ነፍሱን ከዝንባሌ ለማጥራት "ጁሁድ" جُهْد ላይ ያለ ሙተሶዉፍ "ሙጃሂድ” ْمُجَاهِد ይባላል። ሸይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ ስለ ጂሃዱ አን ነፍሥ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦
ረውደቱል ሙሒቢን 1/478
"ከነፍስ እና ከስሜት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ከኩፋር እና ከሙናፊቂ ጋር ለሚደረግ ጂሃድ መሠረት ነው። እርሱ(ሙሥሊም) እነርሱን ከመታገሉ በፊት ቅድሚያ ነፍሱ እና ስሜቱን መታገል ይቀድማልና"። جِهَادُ النَّفْسِ وَالْهَوَى أَصْلُ جِهَادِ الْكُفَّارِ وَالْمُنَافِقِينَ فَإِنَّهُ لَا يَقْدِرُ عَلَى جِهَادِهِمْ حَتَّى يُجَاهِدَ نَفْسَهُ وَهَوَاهُ أَوَّلًا حَتَّى يَخْرُجَ إلَيْهِمْ

እንግዲህ ከነፍስ ጋር ጂሃድ ማድረግ ውስጣዊ ትግል ሲሆን እውነተኛ ተሶዉፍ ይህ ነው፥ ከአሏህ ዲን ጠላቶች ጋር ጂሃድ ማድረግ ውጫዊ ትግል ነው። የዲን ሦስት ደረጃዎች ኢሥላም፣ ኢማን እና ኢሕሣን ናቸው፥ "ኢሕሣን" إِحْسَان የሚለው ቃል "አሕሠነ" أَحْسَنَ ማለትም "አስዋበ" "አሳመረ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ማስዋብ" "ማሳመር" "መልካም ሥራ" ማለት ነው። ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን "ኢሕሣን" إِحْسَان ሸሪዓዊ ፍቺው "አሏህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አሏህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው" ማለት ነው፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 47 , ሐዲስ 6
ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፣ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፥ ወደ ነቢዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ "ስለ ኢሕሣን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ "አሏህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አሏህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው" አሉ"። قَالَ حَدَّثَنِي عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ، قَالَ بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى جَلَسَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ ثُمَّ قَالَ فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِحْسَانِ قَالَ ‏"‏ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ

ጀነት ወደ አሏህ በንጹሕ ልብ ለመጣ ትቀረባለች፥ ለምሳሌ፦ ኢብራሂም ወደ ጌታው በንጹሕ ልብ የመጣ ሰው ነው፦
50፥33 አልረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራ እና "በ-ንጹሕ ልብ" ለመጣ ትቀረባለች፡፡ مَّنْ خَشِيَ الرَّحْمَـٰنَ بِالْغَيْبِ وَجَاءَ بِقَلْبٍ مُّنِيبٍ
37፥84 ወደ ጌታው "በ-ንጹሕ ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 ወደ አሏህ "በ-ንጹሕ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጂ፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ንጹሕ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሠሊም" سَلِيم ነው፥ አንድ በኢሥላም ልቡን ሢያሠልም ልቡ ውስጥ "ሠላም" سَلَام ስላለ ልቡ ሠሊም ስትሆን እርሱ ደግሞ "ሣሊም" سَالِم‎ ይሆናል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 17027
ዐምር ኢብኑ ዐባሣህ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! ኢሥላም ምንድን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ እርሳቸውም"ﷺ"፦ "ልብህን ለአሏህ ዐዘ ወጀል ማሥለም ነው" አሉት"። عَنْ عَمْرِو بْنِ عَبَسَةَ قَالَ قَالَ رَجُلٌ يَا رَسُولَ اللَّهِ مَا الْإِسْلَامُ قَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ يُسْلِمَ قَلْبُكَ لِلَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

"ረህባኒያህ" رَهْبَانِيَّة የሚለው ቃል "ረሂበ" رَهِبَ ማለትም "መነኮሰ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምንኩስና"Monasticism" ማለት ነው፥ ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱት የዒሣ ተከታዮች ዒሣ እና ሐዋርያቱ ያላስተማሩትን "ምንኩስና" ፈጠሩ፦
57፥27 "የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም" وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠሩ" ለሚለው የገባው ቃል "ኢብተደዑ" ابْتَدَعُو መሆኑን አንባቢ ልብ ይበል! ምንኩስና የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፦
57፥27 ግን የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፥ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም፡፡ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا

ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም፥ ምንኩስና አሥሉ ቢድዓህ ሲሆን በተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ሸሪዓህ ግን ሐራም ነው። እንግዲህ እውነተኛ ተሶዉፍ ወደ አሏህ በንጹሕ ልብ መምጣት፣ ከነፍስ ጋር የሚደረግ ጂሃድ፣ ነፍስን ከዝንባሌ ማጥራት እና ኢሕሣን ነው፥ ተሶዉፍ በስርዋጽ እና በቅሰጣ ድንበር ሲታለፍ ረህባኒያህ ነው። አምላካችን አሏህ በእርሱ መንገድ ተሶዉፍ ከሚያደርጉ ሙተሶዉፍ ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር፦ "በግ ስናርድ ስለቱ የተሳለ በሆነ ቢላዋ መሆን አለበት"

ያያ ዘልደታ፦ "ጉዳችን ፈላ እረ ሊያርዱን ነው"

ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር፦ "እረ እኔ ያወራሁት እኮ ስለ በግ ነው"

ያያ ዘልደታ፦ "እኮ! እኛ ክርስቲያኖች እኮ በጎች ነን፥ ጥቅስ ማቅረብ እችላለው"
እረዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 ያቺንም አሏህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

ቁርኣን ሙሉ ለሙሉ የአምላካችን የአሏህ ንግግር ነው፥ በቁርኣን ላይ አሏህ "ሰውን እረዱ" ያለበት ቃል በቀጥታ ሆነ በተዋዋሪ አናገኝም። ከዚያ በተቃራኒው ባይብል ስለ ሰው መታረድ የሚናገር መጽሐፍ  ነው፦
1 ነገሥት 18፥40 ኤልያስም፦ ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ፡ አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ "አሳረዳቸው"። וַיֹּאמֶר֩ אֵלִיָּ֨הוּ לָהֶ֜ם תִּפְשׂ֣וּ ׀ אֶת־נְבִיאֵ֣י הַבַּ֗עַל אִ֛ישׁ אַל־יִמָּלֵ֥ט מֵהֶ֖ם וַֽיִּתְפְּשׂ֑וּם וַיֹּורִדֵ֤ם אֵלִיָּ֙הוּ֙ אֶל־נַ֣חַל קִישֹׁ֔ון וַיִּשְׁחָטֵ֖ם שָֽׁם׃

"አሳረዳቸው" ለሚለው የገባው ቃል "ዪሻተም" יִּשְׁחָטֵ֖ם ሲሆን ሥርወ ቃሉ "ሻሃት" שָׁחַט ነው፥ "ሻሃት" שָׁחַט ማለት "አረደ" ማለት ነው። ኤልያስ ነቢይ ሆኖ የበአል ነቢያትን 450 ሰዎች ማሳረዱ ከቄራ ባለቤት ልዩነቱን ትነግሩኝ? ሲያሳርድ በውስጠ ታዋቂነት "እረዱ" የሚል መርሕ አለ። እንቀጥል! የያዕቆብ ልጆች ገለዓዳውያን የአፍሬምን ሰው ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገሪያ አረዱት፦
መሳፍንት 12፥6 እነርሱ፦ አሁን ሺቦሌት፡ በል አሉት፤ እርሱም አጥርቶ መናገር አልቻለምና፦ ሲቦሌት፡ አለ፤ ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገሪያ "አረዱት"፥ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ።

የቄራው ሥርዓት በዚህ አላበቃም። የሰማርያ ሽማግሌዎች የኢዩን ልጆች እና ሰባ ሰዎች አርደዋል፦
2ኛ ነገሥት 10፥7 ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው "አረዷቸው"፤ ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ። וַיְהִ֗י כְּבֹ֤א הַסֵּ֙פֶר֙ אֲלֵיהֶ֔ם וַיִּקְחוּ֙ אֶת־בְּנֵ֣י הַמֶּ֔לֶךְ וַֽיִּשְׁחֲט֖וּ שִׁבְעִ֣ים אִ֑ישׁ וַיָּשִׂ֤ימוּ אֶת־רָֽאשֵׁיהֶם֙ בַּדּוּדִ֔ים וַיִּשְׁלְח֥וּ אֵלָ֖יו יִזְרְעֶֽאלָה׃

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "ገደሏቸው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዪሻቱ" יִּשְׁחֲט֖וּ ሲሆን "አረዱ" ማለት እንጂ "ገደሉ" ማለት አይደለም። ንጉሥ ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል ቦታ አረዳቸው አሳረዳቸው፦
2ኛ ነገሥት 10፥11 ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል "አረዳቸው"። וַיַּ֣ךְ יֵה֗וּא אֵ֣ת כָּל־הַנִּשְׁאָרִ֤ים לְבֵית־אַחְאָב֙ בְּיִזְרְעֶ֔אל וְכָל־גְּדֹלָ֖יו וּמְיֻדָּעָ֣יו וְכֹהֲנָ֑יו עַד־בִּלְתִּ֥י הִשְׁאִֽיר־לֹ֖ו שָׂרִֽיד׃
2ኛ ነገሥት 10፥14 እርሱም፦ በሕይወታቸው ያዙአቸው፡ አለ። ያዙአቸውም፥ በበግ ጠባቂዎችም ቤት አጠገብ ባለው ጕድጓድ አርባ ሁለቱን ሰዎች "አረዷቸው"፤ ማንንም አላስቀረም። וַיֹּ֙אמֶר֙ תִּפְשׂ֣וּם חַיִּ֔ים וַֽיִּתְפְּשׂ֖וּם חַיִּ֑ים וַֽיִּשְׁחָט֞וּם אֶל־בֹּ֣ור בֵּֽית־עֵ֗קֶד אַרְבָּעִ֤ים וּשְׁנַ֙יִם֙ אִ֔ישׁ וְלֹֽא־הִשְׁאִ֥יר אִ֖ישׁ מֵהֶֽם׃ ס

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "ገደሏቸው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዪሻቱም" יִּשְׁחָט֞וּם ሲሆን "አረዷቸው" ማለት እንጂ "ገደሏቸው" ማለት አይደለም። ዳዊት ነቢይ እና ንጉሥ ሲሆን ፍልስጥኤማዊ ጎልያድን አንገቱን ከማረድም አልፎ ቆርጦታል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥51 ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ "ራሱንም ቈረጠው"።

በተጨማሪ ሬካብ እና ወንድሙ በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ገብተው ኢያቡስቴን ገድለዉት እራሱን ቆረጡት፥ ዳዊትም ሬካብን እና ወንድሙ በዓናን አስገድሎ እጃቸውን እና እግራቸውን እንዲቆረጥ አድርጓል፦
2 ሳሙኤል 4፥7 ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ እርሱ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት።
2ኛ ሳሙኤል 4፥12 ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፤ እጃቸውን እና እግራቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው።

ኢዮአብ እና ሠራዊቱ በአሞን ከከተማ ይኖሩ የነበሩትን የአሞን ልጆች አውጥተው በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው። ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ፦
1ኛ ዜና መዋዕል 20፥3 በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥተው በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው። ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። καὶ τὸν λαὸν τὸν ἐν αὐτῇ ἐξήγαγε καὶ διέπρισε πρίοσι καὶ ἐν σκεπάρνοις σιδηροῖς καὶ ἐν διασχίζουσι· καὶ οὕτως ἐποίησε Δαυὶδ τοῖς πᾶσιν υἱοῖς ᾿Αμμών. καὶ ἀνέστρεψε Δαυὶδ καὶ πᾶς ὁ λαὸς αὐτοῦ εἰς ῾Ιερουσαλήμ.

"ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ" በማለት ዳዊት ልክ እንደ ኢዮአብ የአሞን ልጆችን በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው፥ ግሪክ ሰፕቱአጀንት በዚህ ልክ ያስቀመጡት ሲሆን የ 2 ሺህ የኦርቶዶክስ ባይብል እና King James Version በዚህ አግባብ ተርጉመውታል፦
1 Chronicles 20፥3 KJV And he brought out the people that were in it, and cut them with saws, and with harrows of iron, and with axes. Even so dealt David with all the cities of the children of Ammon. And David and all the people returned to Jerusalem.

ባሻዬ "በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ "ሃይማኖቴ ተነካብኝ" ብሎ ሊያርድ ሰይፍ የመዘዘ ግለሰብ የለም" ላልክበት ዐላዋቂነት በቁና ከላይ ተቀምጦልካል። ከማረድም አልፎ እንደ ዶሮ ለአሥራ ሁለት መቆራረጥም አለ፦
መሣፍንት 19፥29 ወደ ቤቱም በመጣ ጊዜ ካራ አነሣ፥ ቁባቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ሰደደ።

ቁርኣን ስለ መግደል ምን ይላል? ለሚለው ከዚህ በፊት የጻፍኩት ስላለ ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦ https://t.me/Wahidcom/2708

አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሸፍጥ የተሠራበት ሐዲስ ይህ ሐዲስ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 9
ሸዳድ ኢብኑ አውሥ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ዐዘ ወጀል በሁሉ ነገር ላይ መልካምነት ደንግጓል፥ እንስሳት በገደላችኃቸው ጊዜ አገዳደላችሁን አሳምሩ! በአረዳችኃቸው ጊዜ አረዳዳችሁን አሳምሩ። ከእናንተ አንዱ ቢላውን ይሳለውና ለሚያርደው እንስሳ ስቃይ ይተው"። عَنْ شَدَّادِ بْنِ أَوْسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ كَتَبَ الإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَىْءٍ فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ وَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ ‏"‏

ይህንን ሐዲስ የማያውቅ ሙሥሊም ያለ አይመስለኝም። እንስሳትን ለመብላት በእርድ ጊዜ እንዳይሰቃዩ ስለታም ቢላ እንጂ ዱልዱል ሆኖ የሚዘገዝግ መሆን የለበትም።
ሎሬት ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ በኢትዮጵያ የታሪክ ምሁር እና የታሪክ ተመራማሪ ሲሆኑ በአገራችን የታሪክ ሸውራራ ትርክትን በማቃናት ጉልህ ሚና ያደረጉ ሐራዊ ምሁር"Liberal Scholar" ናቸው፥ በተለይ ኢማም አህመድ አልጋዚ ረሒመሁሏህ ላይ የተቃጣውን የሐሰት ትርክት እንኩትኩት ያረጉ ገለልተኛ ምሁር ናቸው። ዛሬ ወደማይቀረው አኺራህ ሄደዋል፥ ለቤተሰባቸው፣ ለዘመድ አዝማዳቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው አምላካችን አሏህ ጽናቱን፣ መጽናናቱን፣ ትእግስቱን ይስጣቸው! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥርጣሬ

ጠርጣሪው ተጠርጣሪን በተጠርጣሪ ጥርጣሬ መጠርጠሩ "የማያጠራጥር ነው" ሲል ጠርጣሪ ኮሚቴ በጥርጣሬ ያለ ጥርጣሬ ተናግሯል፥ ተጠርጣሪው ደግሞ ጠርጣሪውን ጠርጥሮ ቢያስጠረጥረው ያልተጠረጠረ ተመነጠረ የተጠረጠረ አስመነጠረ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ! ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፦
49፥11 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ! ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ጦም ማለት ሥጋን በረሃብ መቅጣት ሳይሆን ነፍስን በሥጋ ላይ የበላይ ማድረግ ነው፥ የጦም ወር፦
1. ተቅዋእ የምናገኝበት
2. ዚክር የምንዘክርበት
3. ቁርኣን የምንቀራበት
4. በዱዓእ የምንዘወተርበት
5. ቀልባችንን የምንሰትርበት
6. ለዓመት የሚሆን መንፈሳዊ ጉልበት የምንቀበልበት
7. በረሃብ አለንጋ የሚለበለቡ ሰዎችን የምናስብበት ነው።

ሁለት ጥግ እርማት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ፥ አንዱ ጦም ማለት ከሥጋ አስተዋጽዖ ተከልክሎ የጥራጥሬ ነገር መብላት ነው ብሎ አስቦ ጦምን የሥጋ መቅጫ አለንጋ አርጎ ማሰብ የኦርቶዶክስ የአስታሰብ ውቅር"Mindset" ነው። ሁለተኛው ረመዷን የጦም ወር እንጂ የምግብ ወር ስላልሆነ በዚህ ወቅት እናትን፣ እኅትን፣ ሚስትን በምግብ ሥራ እንዲወጠሩ አርጎ ከአምልኮ ማዘናጋት ሲሆን ይህ የጦምን ዓላማ እና ዒላማ ካለመረዳት የመጣ የተጠናገረ እና የተንሸዋረረ አሳብ ነው።

አሏህ ያስተካክለን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ነጃሺይ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥83 ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

“አል ሐበሻህ” الْحَبَشَة ማለት “አሰባሳቢው” ማለት ሲሆን የመን ከሚኖሩ በመህራህ ሕዝቦች መካከል ሲኖሩ “የዕጣን አሰባሳቢዎች” ይባሉ የነበሩ ናቸው። “አል ሐበሻህ” የመን ከሚኖሩ ከመህራህ ሕዝቦች ወደ ሰሜኑ ክፍል የተሰበሰቡ ሴማዊ ሕዝቦች መጠሪያ ነው። ስለ አል ሐበሻህ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ቁርኣን ሲወርድ በአል ሐበሻህ ውስጥ ስለ ነገሠው ንጉሥ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ እንዳስሳለን።
“ነጃሺይ” نَّجَاشِيَّ ማለት “ንጉሥ” ማለት ሲሆን ወደ ጠቃሽ አመልካች መስተአምር “አል” ال ተደርጎ ሲነበብ “አን ነጃሺይ” النَّجَاشِيَّ ሲሆን “ንጉሡ”The king” ማለት ነው፥ ይህ ስም የማዕረግ ስም ነው። ይህ ንጉሥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠት ከ 614–631 ድኅረ ልደት በአክሱም መንግሥት የነገሠ ንጉሥ ነው፥ የተጸውዖ ስሙም በዐረቢኛ አነባነብ “አስሐማህ” أَصْحَمَة ሲባል፥ በአገራችን “አርማህ” ይባላል። “ንጉሥ አርማህ” በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ በጥቅሉ “አስሐማህ አን ነጃሺይ” أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ ይባላል። ይህ ንጉሥ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች ከ 615–616 ድኅረ ልደት ተቀብሎ አስተናግዷል፥ እንዲሁ እርሱ እና ሹማምንቱ ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ሱረቱል መርየምን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን አንብተዋል፦
5፥83 ወደ መልእክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

የንጉሡ መሥለም የኢሥላም ጠል”Islamophobia” አቀንቃኝ የሆኑት ጭፍን ተከታዮች እንደዋሹት የአክራሪዎች ፈጠራ ሳይሆን “ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን” ብለው በቁርኣኑ ማመናቸውን አምላካችን አሏህ በቅዱስ ቃሉ የነገረን ነው። ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአሏህ ፈሪዎች በአሏህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ እነ ነጃሺይ እና ሹማምንቱ በአሏህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፦
3፥199 ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአሏህ ፈሪዎች በአሏህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአሏህ እና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው፥ በዚያም ወደ እነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አሏህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

በአሏህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ካመኑ ሠልመዋል ማለት ነው። በነቢያችንም”ﷺ” ሐዲስ ላይ ነቢያችን”ﷺ” ነጃሺይ ከመሥለምም አልፎ ጻዲቅ ሰው እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 103
ጃቢር እንደተረከው፦ “አን ነጃሺይ በሞተ ጊዜ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ዛሬ ጻዲቅ ሰው ሞቷል፥ ተነሱ! ለወንድማችሁ ለአስሐማህ የግንዘት ጸሎት አድርጉ!። عَنْ جَابِرٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم حِينَ مَاتَ النَّجَاشِيُّ ‏ “‏ مَاتَ الْيَوْمَ رَجُلٌ صَالِحٌ، فَقُومُوا فَصَلُّوا عَلَى أَخِيكُمْ أَصْحَمَةَ
“ሷሊሕ” صَالِح ማለት “መልካም” ወይም ጻዲቅ” ማለት ሲሆን የሷሊሕ ብዙ ቁጥር “ሷሊሒን” صَّالِحِين ማለትም “መልካሞች” ወይም “ጻድቃን” ማለት ነው፦
3፥114 በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያምናሉ፣ በጽድቅ ነገርም ያዛሉ፣ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ፣ በበጎ ሥራዎችም ይጣደፋሉ፡፡ እነዚያም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَأُولَـٰئِكَ مِنَ الصَّالِحِينَ
2፥130 ከኢብራሂምም ሕግጋት እራሱን የበደለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? ማንም የለም። በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው፥ በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መልካሞች" ለሚለው የገባው ቃል “ሷሊሒን” صَّالِحِين ነው፥ ስለዚህ አስሐማህ አን ነጃሺይ “ሷሊሕ” መባሉን ከመሥለም አልፎ ሷሊሕ ሰው መሆኑን በቂ ማሳያ ነው። ከዚያ በመቀጠል እርሱ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች የሃይማኖት ወንድም ስለሆነ እሳቸው “አኺኩም” أَخِيكُمْ ማለትም “ወንድማችሁ” ብለውታል። ምእመናን ደግሞ ወንድማማቾች ናቸው፦
49፥10 ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 106
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ለባልደረቦቻቸው ስለ ስለዚያ ቀን ስለሞተበት ስለ ሐበሻው አን ነጃሺይ ሞት እንደነገሯቸው፦ ”ለወንድማችሁ ኢሥቲግፋር አርጉ!”። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَخْبَرَهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم نَعَى لَهُمُ النَّجَاشِيَّ صَاحِبَ الْحَبَشَةِ فِي الْيَوْمِ الَّذِي مَاتَ فِيهِ، وَقَالَ ‏ “‏ اسْتَغْفِرُوا لأَخِيكُمْ ‏”‌‏

“ሶላቱል ጀናዛህ” صَلَاة الجَنَازَة ማለት “የግንዘት ጸሎት” ማለት ሲሆን በኢሥላም የግንዘት ጸሎት የሚደረገው ለሙሥሊም ብቻ ነው። ለንጉሥ አርማህ ደግሞ የሶላቱል ጀናዛህ ክፍል የሆነው “ሶላቱል ጋኢብ” صَلَاة الغَائِبٌ ማለትም “የሩቅ ጀናዛህ” ተደርጓል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 105
ጃቢር አብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ *”ነቢዩም”ﷺ” አስሐማህ አን ነጃሺይ ላይ የግንዘት ጸሎት አድርገዋል፥ አራት ተክቢራህ በእርሱ ላይ አድርገዋል”። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم صَلَّى عَلَى أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ، فَكَبَّرَ عَلَيْهِ أَرْبَعًا‏

ከላይ የተዘረዘሩት ሐዲሳት ንጉሥ አርማህ የአላህ ጥሪ ተውሒድን እንደተቀበለ ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያሉ። ስለዚህ የኢሥላም ጠል አቀንቃኝ የሆኑት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ የነዙት ጨባጣ እና ለማጣ ወሬ እንዲህ ድባቅ ይገባል። አስሐማህ አን ነጃሺይ መሥለሙ በዓለም የሚገኝ መላው ሙሥሊም ሁሉ የሚቀበለው እውነታ ነው። ይህን እውነታ አለመቀበል ትችላለክ፥ ግን ይህ ትርክት የአክራሪዎች እንጂ የሁሉም ሙሥሊም እንዳይደለ ለመቅጠፍ የሞከራችሁት ቅጥፈት ለዛሬ አልተሳካላችሁም። በአፈ ጮሌነት ቤተ መንግሥት እንደገባከው በአፈ ጮሌነት ጀነት አትገባም። ግልባጩን ለመምህር አባይነህ ካሴ አድርሱልኝ!
አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ ኦንሊይ ጂሰስ የሚባሉት "አካል" የሚለውን ቃል ሁልጊዜ የሚረዱት "ተክለ ሰውነት"Body" "ሶማ" σῶμα "ጀሠድ" جَسَد በሚል እንጂ "አካል" የሚለውን "ቀዋሜ ማንነት"Person" "ፕሮሶፓን" πρόσωπον "ሸኽስ" شَخْص በሚል አይረዱትም፥ "አካል" የሚለው የግዕዝ ቃል "አካለ" ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ" "መታወቂያ" ማለት ነው። አንድ ማንነት "እኔ" የሚል ቀዋሜ ማንነት ካለው "አካል" ይባላል፥ ይህንን ሥነ ማንነት ጥናት"Metaphysics" ስላላጠኑ ውይይት ላይ ሲቸገሩ እያየን ነው።

እኛ ሙሥሊሞች እና አይሁዳውያን "አሏህ አንድ ማንነት ነው" ስንል የሥላሴ አማንያን ደግሞ "ሦስት ማንነት ነው" ይላሉ፥ አምላክ ማንነት ከሌለው ኦንሊይ ጂሰሶች "ሦስት ነው" የሚለውን ተቃውመው "አንድ ነው" ሲሉ ምኑን ነው "አንድ ነው" የሚሉት? "አምላክነቱን" ካሉን አምላክነት "ምንነት" ነው። የሥላሴ አማንያንም "በምንነት አንድ ነው" ብለው እኮ ያምናሉ፥ የኦንልይ ጂሰስ ሙግት ወጥነት የሌለው እና ጥናት ላይ ያልተመሠረተ የውኃ ላይ ኩበት ነው።

"እግዚአብሔር ማንነትም አይደለም" "እግዚአብሔር ኢ ማንነትም"Matter" አይደለም" የሚል ምናባዊ አጣብቂኝ አረጉት፥ "እኔ" ብሎ የሚናገር አንድ አምላክ እንዳለ እኮ ብዙ ቦታ በባይብል ተጠቅሷል።

የኦንሊይ ጂሰስ ትምህርት ዛሬ ከሥላሴ የባሰ ውስብስብ ትምህርት እየሆነ ነው።

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
የበደለኛዋን እና የጉልበተኛዋን አሜሪካ መጨረሻ አሏህ በዕድሜዬ ሳያሳየኝ አይውሰደኝ! አሚን።

أَلَا لَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ
ዒድ አደባባይ

"አብዮት አደባባይ" የመንግሥት አደባባይ ሲሆን ይህ አደባባይ መስቀለኞች ክርስቲያን በዓመት አንዴ የመስቀል ደመራ ስለሚያረጉበት ለእነርሱ "መስቀል አደባባይ" ነው፣ ዋቄፈታዎች ዓመታዊ በዓላቸው በዚያ ስለሚያከብሩ "ኢሬቻ አደባባይ" ነው፣ እኛም ሙሥሊሞች ደግሞ በዓመት ሁለት ጊዜ የዒድ ጊዜ ዒዳችንን የምናከብርበት ሲሆን ለእኛ "ዒድ አደባባይ" ነው።

ኢንሻ አሏህ በዒድ ቀን "ዒድ አደባባይ" እንገናኝ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom