𝑬𝒏𝒐𝒓 𝒎𝒖𝒔𝒍𝒊𝒎𝐬 𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂
439 subscribers
112 photos
10 videos
2 files
123 links
Download Telegram
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

بسم الله الرحمن الرحيم

ነገ እለተ ማክሰኞ በኛ በሙስሊሞች አቆጣጠር አያመል ቢዕድ የሚጀመርበት ቀን ይሆናል

ማክሰኞ(ሰፈር 13)
ረቡዕ(ሰፈር 14)
ሐሙስ(ሰፈር 15)


እናም እነዚህን 3ቀናቶች እንፁም መፆም ካልቻልን እንኳ እህት ወንድሞቻችንን ወደዚህ ኸይር ስራ እንጋብዛቸው ኢንሻአላህ ወደ ኸይር ያመላከተ ልክ እንደ ሰሪው ይሆናልና ምንዳው


ስለ አያመል ቢዕድ በጥቂቱ...


ከ እያንዳንዱ ወር 3ቀን መፆም

👉ይህ ፆም በ1 ወር ውስጥ ያሉ 3 ቀናቶች ሲሆን በወሩ በየትኛውም ቀን ብንፆም እንችላለን ቀኑንም ማከታተል የግዴታ አይደለም ነገርግን አያመል ቢዕድ በመባል ሚታወቁት በእስልምና አቆጣጠር 13,14 እና 15ተኛው ቀን ቢሆን ይበልጥ ይወደድልናል::


👌ይህን 3 ቀን የፆመ ወሩን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠርለታል ምክንያቱም 1መልካም ስራ በ10 ስለሚባዛ ስለዚህ በየወሩ 3,3 ቀን የምንፆም ከሆነ አመቱን ሙሉ እንደፆምን ይቆጠራል ማለት ነው::
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ

ነገ ሐሙስ ነው ኢንሻአላህ  ከቻልን እንፁም ካልቻልን እህት ወንድሞቻችንን እናስታውሳቸውና የአጅሩ ተካፋይ እንሁን
ቢድዐ የተከለከለበት 4 ጥበቦች
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
🎯 ቢድዐ የተከለከለበት 4️⃣ ጥበቦች

🎙 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ (ሐፊዘሁሏህ)
https://t.me/yeilyaswedaje
አዲስ ነገር 🎉🎉🎉🎉
የለውጥ ፌርማታ
🎉🎉🎉🎉

አንደኛ አመት ተማሪ ነህ/ነሽ?
ለወደፊት ምን መሆን እንዳለብን መወሰን ከብዶናል?
ምን መማር እንዳለብን ግራ ገብቶናል?
አላማችንን ፣ ተስጦአችንን ፣ ግባችንን እና ህልማችንን ለመቅረፅ ተቸግረናል?


የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ጀመዐ በተለየ መልኩ ለአንደኛ አመት ተማሪዎች የህይወት ግብን ስለመቅረፅ በጣም ልዩ ስልጠና አዘጋጅቷል።የአላህ ፍቃዱ ከሆነ ስልጠናው በተግባሮች የተደገፈ ፤ ደካማና ጠንካራ ጎናችንን የምንለይበት ፤ ተስጦአችንን የምናውቅበት ፤ ግባችንን አውቀን ወደየት መሄድ እንዳለብን የምንወስንበት የህይወታችን መሪ ቀያሪ ክስተት ይሆናል።


ለወንዶችና ለሴቶች በወንድና በሴት አሰልጣኞች የሚሰጠው ይህ ልዩ ስልጠና እንዳያመልጥዋ ከወዲሁ ቀንዎን ከፕሮግራም ነፃ ያድርጉ።
ከSpecial ሻይ ቡና 🍰🍪🫖 ጋር እንጠብቅዎታለን።

የአሁኑ እሁድ September 3

ጠዋት ከ2:15-6:00 ለወንዶች በልዩ አሰልጣኝ
ከሰዐት ከ7:00-11:00 ለሴቶች በልዩ ሴት አሰልጣኝ

ቦታ:-አል-አቅሳ መስጅድ ቂረዐት ቦታ

ማሳሰቢያ:- ለዚህ Special ስልጠና ያለን ቦታ የተወሰነ በመሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ። ለሚወዱት ሰው በማጋራት ለሂወቱ መለወጥ የበኩልዎን ይወጡ።

ለመመዝገብ በ @Jemzuri ስም እና ስልክ ቁጥር ይላኩ።
አሰላም አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ  ውድ  የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  የመጀመሪያ አመት ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ የዛሬው የስልጠና ፕሮግራማችን በዚህ መልኩ አሰናድተንላቹሀለን።

የፕሮግራሙን አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሰን እናንተን ብቻና ብቻ በመጠበቅ ላይ እንገኛለን።

ውድ ተማሪዎች ፕሮግራሙን በሰዓት እንዲጀመር ሁላቹሁም በሰዓቱ እንድትገኙ በአላህ ስም እናሳስባለን።

ፕሮግራሙ የሚጀመረው 2:30 ጀምሮ ነው።
የፕሮግራሙ ቦታ አል አቅሳ መስጂድ መድረሳ።

Note:- አሁን 2:30 የሚጀመረው የወንድች ፕሮግራም ነው። የእህቶች ከዙሁር በሃላ 7:00 ላይ ይጀምራል።
Forwarded from أبو ماهر
   የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎች ስራ ለሌሎች አረአያ የሚሆን ነው ።

      በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ላይ ከወራት በፊት በጉንችሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ጉዳዩ ከሮ የአካልና ንብረት ጉዳት እስከማድረስ መድረሱ የሚታወቅ ነው ። ይህ ጉዳይ አድማሱ እያሰፋ ሄዶ በወረዳው ውስጥ ውጥረት እንዲነግስ አድርጎ ቆይቷል ። የተኛውም ሰላም ፈላጊ ከመጎዳት በስተቀር በማያተርፍበት ብጥብጥ የማህበረሰቡ የዘመናት አብሮነት ታሪክ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ ያደረገ ሁኔታ የተከሰተ ቢሆንም የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎች በጣም አስደናቂና ብዙዎች ያልቻሉትን ስራ በመስራት ወረዳውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ በመመለስ ታሪካዊ ስራ ሰርተዋል ።
    ይህ የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ ታሪካዊ የሆነው " መጥፎን ነገር ለትውልድ እንዳይሸጋገር እናጥፋው " የሚለውን እሴት መርህ አድርጎ የተነሳው የሽማግሌ ስብስብ እሴቱን ጠብቆ መርሁን እውን አድርጎታል ። የሚገርመው የሽማግሌው ስብስብ ይህን መርህ እውን ሲያደርግ ምንም አይነት ከሸሪዓ ጋር የሚጋጭ ባህላዊ ነገር ሳይኖር መሆኑ ነው ።
     የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የዛሬው ቀን ላይ ደርሶ ይህን ታሪካዊ ሰላም ሲያስመዘግብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀንና ለሊት በእግር ሩቅ ቦታ በመጓዝ  ከገጠር እስከ ከተማ ከሚመለከተው አካል ጋር በመገናኘትና ነገሩን ከስር መሰረቱ በመረዳት ቂምና በቀል እንዳይኖር በሁሉም ልብ ውስጥ የተከሰተው ነገር  አስተማሪ ሆኖ ያለፈ ክስተት ሆኖ እንዲቀር በማድረግ ነው ።
    ይህ የሀገር ሽማግሌ የሰላም ውጤት ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በአላህ እርዳታ የአንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው ወንድማችን ልፋት ውጤት ነው ። ይህ ወንድማችን ሁኔታው ተከስቶ በሁለቱም ጎራ ሁሉም ስሜታዊ ሆኖ ነገሩ ወደ ሀይማኖት ግጭት ሊቀየር እየሄደ ባለበት ወቅት በዋነኝነት ሙስሌሞቹን በማረጋጋት በአስተዋይነታቸውና ሚዛናዊነታቸው የሚያውቃቸውን ክርስቲያን የከተማ ነዋሪ የእነሞር ተወላጆችን  በየግል የሁኔታው አደገኝነትና የሚያስከትለው ውጤት ምን ሊሆን እነደሚችል እንዲያዩትና እነርሱ ባሉበት ዘመን እንዲህ አይነት ክስተት ተክስቶ ለትውልድ የተበላሸ ታሪክ መተው እንደሌለበት በመንገር ነበር ። እነዚህ አስተዋይና ሚዛናዊ የሆኑ ክርስቲያን የእነሞር ተወላጆች ከእነርሱ በፖዚሽንም ሆነ በትምህርት ደረጃ የሚያንሰው ወንድማቸው ያቀረበላቸውን ሀሳብ በቅል ልቦና በመቀበል ወደ ተግባራዊነቱ መገባት እንዳለበት ወሰኑ ።
     የጀመሩት ተገናኝቶ በጋራ በመነጋገር ሲሆን ቀጥሎ ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም ተጨማሪ የከተማ ነዋሪ ጋር የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ውይይት በማድረግ ሲሆን ውይይት ካደረጉ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሀገር ሽማግሌ ማድረስ እንዳለባቸውና ይህንኑ ሀሳብ ለደቡብ ክልል ፕሬዝዳት አቶ እርስቱ ይርዳው አቅርበው እሱም ባለበት በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ላይ ከህብረተሰቡና ሀገር ሽማግሌ ጋር ውይይት እንዲደረግ ወሰኑ ። በዚሁ መንገድ ቀጥለው ጉዳዩ ወደ ፕሬዝዳቱ አቀረቡት ። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ እርስቱ ይርዳው በጣም በሚገርም ሁኔታ ሀሳቡን ተቀብሎ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ አመቻቸ !!!!! ።
    ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ጉንችሬ ከተማ ላይ በጣም አሳዛኝ ነገር ተከሰተ ። ብዙ ንብረት ወደመ ብዙ ሰውም ተጎዳ ። ምናልባትም በተያዘው የሰላም ሂደት የሚከስሩ አካላት ምክንያት ሆነው ሊሆን ይችላል ። ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰው ታሰረ ። ወረዳው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ሆነ ።
    ይሁን እንጂ እነዚያ ሰላም ወዳድ የሆኑ ብርቅዩ የእነሞር ተወላጆችም ሆነ የክልሉ ፕሬዝዳንት ነገሩን ያሰቡበት ከማድረስ አላገዳቸውም ። እዚያ ወንድሞች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተነጋግረው ጉንችሬ ላይ ቀጠሮ ተያዘ ። በተባለው መልኩ የክልሉ ፕሬዝዳንት ወደ ጉንችሬ በማቅናት ለህዝብና ለሀገር ያለውን አክብሮት በተግባር አሳየ ። የህዝቡን ሀሳብ ከሀገር ሽማግሌው ጋር አዳምጦ የሀገር ሽማግሌው የጉዳዩን ሀላፊነት ወስዶ እንዲያስተካክል ሀላፊነት በመስጠት ለተግባራዊነቱ ከጎን እንደሚቆም ገለፀ ። 
    እነዚያ ወንድሞች በዚህ መልኩ ለሀገር ሽማግሌ ጉዳዩን አስረክበው ከጎን በመሆን እስከ ፍፃሜው አብረው ሄዱ ። በዚህም የሀገር ሽማግሌው ከቅድመ አያቶቻቸው በወረሱት " መጥፎ ነገር ለትውልድ እንዳይተላለፍ እናጥፋው " በሚለው መርህ መሰረት ብዙ ዋጋ ከፍለው ችግሩ ከስር መሰረቱ እንዲቀረፍ በማድረግ ሰላም አሰፈኑ ።
     በዚህም መሰረት ንብረታቸው ለተጎዳ ተወላጆች ሁሉም ማህበረሰብ የሚችለውን በማድረግ እንዲዶጉም , ተጎጂዎችም ምርቃት ተደርጎላቸው የተሰጣቸውን ተቀብለው አውፍ እንዲሉ , ከሁለቱም በኩል በዳዮች በባህሉ መሰረት በድለናል አውፍ በሉን ብለው እንዲቀርቡ  በማድረግና ለበደላቸው የሚመጥን ባይሆንም ሽማግሌም ሆነ ተበዳይ ሙሉ በሙሉ አውፍ እንዲላቸው የተወሰነ የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ጨርሰው የታሰሩት እንዲፈቱና ሁሉም ተስማምተው እንዲማሩ በማድረግ እርቀ ሰላም እንዲወርድ አደረጉ ። ይህን ስምምነት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ይዘው በመሄድ የሰሩትን ስራ በማስረዳት የታሰሩት እንዲፈቱላቸውና ለደረሱበት የሰላም ስምምነት እውቅና እንዲሰጥላቸው ጠየቁ ።
    ፍትህ ሚኒስቴርም የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የሰራውን ስራ ትልቅ ቦታ በመስጠት ባጭር ጊዜ በአካል እነሞር ድረስ ባለሞያ በመላክ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በሟሟላት እስረኞቹ እንዲፈቱና የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የሰራውን ስራ እውቅና ሰጥቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አደረገ ። !!!!!
     የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ በሚቀጥሉት 15 ቀናት አጠቃላዩን የእነሞር ህዝብ አገናኝቶ አውፍ ለማስባልና እርቁ ዘላቂ እንዲሆን ቀጠሮ ይዟል ። በመሆኑም የተኛውም ሰላም ወዳድ የእነሞር ተወላጅ ለዚህ ታሪካዊ እርቀሰላም ፍፃሜ የሚችለውን በማድረግ አብሮነቱን ሊያሳይ ይገባል ።
በመጨረሻም ታላቅ ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ አላህ የተገባ ይሁን በማለት ቀጥሎ : –
🔹  ለደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ እርሱ ይርዳው
ላሳዩት ህዝብና ሀገር አክባሪነትና ለሰላሙ እውን መሆን ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፆ
🔹  ለጉራጌ የሀገር ሽማግሌ
ለዘመናት የዘለቀውን የዞኑ ማህበረሰብ የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴት ተጠብቆ እንዲቆይና መጥፎ ነገር ለትውልድ እንዳይተላለፍ እናጥፋው የሚለውን መርህ እውን በማድረግ ሰላም ላሰፈኑት
🔹 ለፍትህ ሚኒስቴር
የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎችን ስራ እውቅና ሰጥቶ በአካል ወደ እነሞር ባለሞያ በመላክ የሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚ እንዲሆን ላደረገው
🔹ለአስገራሚው ወንድማችን
በብጥብጡ ውስጥ አሻግሮ ያ ው የነበረውን የአብሮነትና መደጋገፍ የሰላም መስፈን በአላህ ፈቃድ እውን እንዲሆን የራሱን አእምሮ አቅልጦ ለሌሎች ብርሀን ሆኖ ለማየት ለበቃው
🔹ለእነዚያ አስተዋይና ሚዛናዊ የእነሞር ተወላጅ ክርስቲያን ወገኖች
🔹 ከመጀመሪያ ጀምሮ ለህዝቡ አብሮነትና ሰላም እንዲመጣ ጥረት ላደረጉ ለጉንችሬ ክ/ከተማና ለእነሞር ወረዳ የስራ አመራሮች ምስጋና ይገባቸዋል እላለሁ ።

    ወንድማችሁ ባህሩ ተካ

እንኳን ደስ ያለን ።

https://t.me/bahruteka
Forwarded from أبو ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ(01)
____
ባህሩ ተካ የጉንችሬ እርቅ በተመለከተ በፃፈው ፁሁፍ ላይ ያሉ ስህተቶችን ከስር የራሱ ፁሁፍ እያስገባሁ ማስተካከያ የምሰጥበት ይሆናል።ራሱ ከስህተቱ እንዲመለስና ሌሎችንም እንዳያሳስት የተሰጠ ማስተካከያ።
___
በህሩ ተካ=>"   የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎች ስራ ለሌሎች አረአያ የሚሆን ነው "።አለ።

መልስ=>ይህ አባባል በጉራጌ የጆካ ሽማግሌዎች ላይ ድንበር ማለፍ ነው።የሰሩት መልካም ነገር ካለ እሱን ነጥሎ ማመስገን አንድ ነገር ነው እንጂ እንዲህ በድፍኑ" አራአያ ናቸው" ማለት የተሳሳተ እይታ ነው።የጆካና ወሸ  ሽማግሌዎች መተዳደሪያ (ቂጫ) ሸሪዓ አይደለም።

ይህ የጆካ ባረቅ(የጉራጌ የሽምግልና ስነስርአት) አመጣጡና የቦታ አሰያየሙ መመልከት ብቻውን በቂ ምስክር ነው።

የቦታው የተመረጠበት ምክንያት እንዲህ እያሉ ያስረዳሉ:-"በስፍራው አንድ ትልቅ ዛፍ የሚገኝ ሲሆን ይህ ዛፍ መሬት አርፎ አንድ ቅርንጫፉ ወደ ላይ አደገ ።ቅርንጫፉ መሬት ላይ ያረፈ ስለሆነ በጉራጊኛ ኧጅ ወካ የሚል ስያሜ ተሰጠው።ቦታውም ባህላዊ የሀይማኖት ስነ ስርአቶች (Cultural religious ceremonie)ይካሄድበት ነበር። ወገበቻ ፣ሞኬረረ፣የድሟሚት መንፈስ በአቅራቢያው ነበሩ።እዚህ ቦታ ላይ የምንሰጠው ውሳኔ በነሱ ይፀናል።ይሰማሉ ያያሉ ሞቄ ያያል፣ድሟሚንት ትሰማለች፣ይሰማሉ።ሌላው ሰው ደግሞ እነሱ ባሉበት ቦታ የተደረገ ነገር ስለ ሆነ አይጥሰውም።ከዚህ አንፃር የተመረጠ ቦታ ነው።"የድምፁን ማስረጃውን ለማግኘት ሊንኩ ይጫኑ።https://t.me/Rremedan/2405

ይህ ህግ ወይም ቂጫ ከሽርክና ከባእድ አምልኮት ጋር ተያያዥነት እንዳለው ግልፅ ነው።

       እኛ ሙስሊሞች አራያችን ነብያችን صلى الله عليه وسلم ናቸው።አሏህም ያዘዘን ነብያቶችን አራአያ አድርገን እንድንከተል እንጂ በቄሶችና ሸሪዓን በማያውቁ አባቶች  የሚመራውን ባህላዊ ዳኝነትና አምልኮትን አይደለም።

ማንን አራአያ አድርገን መያዝ እንዳለብን ሸሪዓ በሚገባ አብራርቶልናል።ወዴትም መፋረድ እንዳለብን ኢስላም ግልፅ አድርጎልናል።እኛ ሙስሊሞች ባህላዊ ከሸሪዓ ህግ ውጪ ያሉ መተዳደሪያዎችና መዳኛዎችን  ወደን ተቀብለን ለሌሎችም አራአያ ይሆናል ብለን የምናሞካሸውና የምናስተዋውቅ አይደለም።

    የጆካ የሽምግልና ሂደት በዝርዝርና በጥልቀት ተመልከተው እስቲ ምኑን ነው አራአያችን የሚሆነው?

ምን አልባት የጆካ ሽማግሌ አላልኩም ልትል ትችላለህ ። ይህ አባባል ግን ከመሰረቱ ተቀባይነት የለውም።ምክንያቱም የጉራጌ ሽማግሌ በመባል የሚታወቁትና በጉንችሬ ጉዳይም ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች እነሱ ስለሆኑ።

"ጉንችሬ በተፈጠረው ችግር ነው ለማመለት የፈለግኩት "ካልክ ደግሞ የጉችሬ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ በተመለከተ ምንም ያደረጉት ነገር የለም።የጥሉ መንስኤ የኒቃብ ጉዳይ ነበር።አሁንም ኒቃብ እንደተከለከለ ነው ።ኒቃብ የለበሱ ተማሪዎች በጠቅላላ ከትምርት ገበታ ውጪ ተደርገዋል። የችግሩ መንስኤ፣ወረዳይቷዋ እንድትረበሽ ያደረጋት፣ወንድሞች ለእስር የዳረጋቸው፣ከፊሎች ደግሞ የተባረሩበት፣ሙሉ ሙስሊሞች ከት/ት ገበታ ውጪ የሆኑበት እና የንብረት ውድመት ያስከተለው ኒቃብ በመከልከሉ ምክንያት  ነበር ።አሁንም ኒቃብ በተመለከተ  ምንም ያመጡት አዲስ የመፍትሄ አካሄድ የለም።እናም ምን አድርገው ነው? አራአያችን የሚሆኑት?

እስረኞች አስፈቱ ወረዳው ሰላም አሰፈኑ ካልከኝ።መጀመሪያም ሰላም ሆና ማንም ሳይታሰር ተመሳሳይ እርቅ በተደጋጋሚ ጠይቀው ነበር ።ግን የሙስሊሙ ፅናት ኒቃብ ሳይፈቀድ አንታረቅም ነበር ያልነው።በዚህ ሽማግሌ አማካኝነት ለሙስሊሙ ምንም የመጣ ውጤት የለም ።ይህ በሆነበት እነሱን አራአያችን ብሎ መቆለል አጉል ልወደድ ባይነት ነው።
____
Forwarded from أبو ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ 02
-----------------------------
በህሩ ተካ =>"በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ላይ ከወራት በፊት በጉንችሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ጉዳዩ ከሮ የአካልና ንብረት ጉዳት እስከማድረስ መድረሱ የሚታወቅ ነው ።"አለ
____

መልስ=>ሁለት አመት ያለፈው ጉዳይ  "ከወራት በፊት"ብሎ መግለፅ በራሱ ነገሩን ማቅለልና ድንገት ትላንትና የተፈጠረ ማስመሰል ይሆናል።አንተ እንዳልከው ከወራት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ሳይሆን ለዘመናት ሲያቅዱት የኖረና የስልጣን ሰልሰለቱ ከወረዳ አስተዳደርነት እስከ ክልል ፕሬዝዳንትነት በእጃቸው ባደረጉ ጊዜ እውን ያደረጉት ህልምና ሴራ ነው።

ሌላው ችግሩ የተፈጠረው ጉንችሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ብቻ አይደለም።ኧገዜ፣ተርሆኘ፣ጋርባዶና ሌሎች ት/ቤት ላይ ነው።የችግሩም መንስኤ አንተ እንዳልከው "ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት"ብቻ ሳይሆን ቀድሞውንም የተለያዩ ትንኮሳዎች የነበሩ ቢሆንም የነገራቸው ማሳረጊያ ያደረጉት በርካታ ቁጥር ያላች ኢስላማዊ አለባበስ የለበሱ ተማሪዎችን አንቀበልም በሚል መነሻ ነው።

  ይህ አገላለፅህ እጅጉን ያሳዝናል።ያ ሁሉ ሙስሊሙ ላይ የደረሰውን እንግልትና መከራ ወረዳይቷዋ ለሙስሊሞች የእሳት ባህር ሆና ቆይታ ሙስሊሙን በልዩ ሀይል ሲደበደብ ሌሊት ከቤቱ ተነጥሎ እየወጣ እስር ቤት ሲወረወር፣ከህፃን እስከ አዋቂው ከወጣት እስከ አዛውንቱ ያሳለፈውን ስቆቃ ድፍን ሀገር የተጨነቀበት፣ሙሉ ሙስሊም ተማሪዎች ከት/ት ገበታ የተፈናቀሉበት በርካቶች የተሰደዱለት ፣ከቀዬያቸው የተፈናቀሉበት፣ሙሉ ህይወታቸውን መሰዋትነት የከፈሉለትን ጉዳይ እንዲህ የመንደር ልጆች ያስነሱት ፀብ አስመስሎ መሳልና ለህዝብ መግለፅ በጣም የሚያሳዝን ከዳተኝነት ነው።

አንተ እንዳልከው "ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት"ሳይሆን ለዘመናት የዘለቀውን ሙስሊም ጠልነትና የጥላች ብትራቸውን ማሳረፍ የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሲደርሱ ወደ ተግባር የገቡበት ተጨባጭ ነው።
   "(ዋ ዌራድ ሚሽተነ ታናዋአነ)ይህ መጥፎ አረም ካልመዘዝነው ሰላማችን አናገኝም "እና መሰል የጥላቻ ሰበካዎች የፈጠሩት ጥላቻ ነው።

እነዚህን ክርስቲያን ተማሪዎችን ቤተ_ ክርስቲያን ላይ በተደረጉ ውይይቶች መሰረት ለፀብና ተልእኮ ለማሳካት እንደ ግብአት የተጠቀሟቸው እንጂ የችግሩ መሰረት ሆነው አይደለም።

አንተ እንዳልከው ከሆነ ኧገዜና ተርሆኘ ያሉ እህቶቻችንን ከትምህርት ገበታ ውጪ ማድረግ ለምን አስፈለገ?ኒቃብ የለበሰች መምህርት ማባረርስ ለምን አስፈለገ?,,,,,,,,,,,,,,,,,ይህ አገላለፅ ጉዳዩን አቅልሎ ማየትና የተከፈለውን መሰዋትነት መናቅ ይሆናል።
___
03
በህሩ ተካ=>" ይህ ጉዳይ አድማሱ እያሰፋ ሄዶ በወረዳው ውስጥ ውጥረት እንዲነግስ አድርጎ ቆይቷል ። የተኛውም ሰላም ፈላጊ ከመጎዳት በስተቀር በማያተርፍበት ብጥብጥ የማህበረሰቡ የዘመናት አብሮነት ታሪክ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ ያደረገ ሁኔታ የተከሰተ ቢሆንም የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎች በጣም አስደናቂና ብዙዎች ያልቻሉትን ስራ በመስራት ወረዳውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ በመመለስ ታሪካዊ ስራ ሰርተዋል ። "አለ
__
መልስ=>ይህ አገላለፅ በራሱ እጅጉ አሳፋሪ ስንኞችን ያቀፈ መላምንት ነው።ሙስሊሞች ከሰብአዊ መብታቸው ተገፈው መብት መጠየቃቸውን ነው " የትኛውም ሰላም ፈላጊ ከመጎዳት በስተቀር በማያተርፍበት ብጥብጥ"ብለህ የምትገልፀው።የቃረደ ፖለቲከኛ ለመሆን ዳዴ ማለት አያስመስልብህም።ያ ሁሉ መሰዋትነት "ብጥብጥ "ብለህ ትገልፀዋለህን?እስቲ አንተ የመፍትሄ ሃሳብ አምጣ ሙስሊሞች ምን ማድረግ ነበረባቸው።አንተ የወረዳው ዳዕዋ በኔ ስር ካላለፈ የምትል ራስህን የእነሞር ተወካይ አድርገህ የምትስል ሰው የወረዳው ሙስሊሞች እንዲህ ተጨንቀው ምጥ ውስጥ በገቡበት ጊዜ ምን አደረግክ?ምን ታየልህ? ይህ ነገር ግፍ ነው አግባብ አይደለም ብለህ አንዲት ያደረግካት እንቅስቀሴ አለችህን?እርቅ ሲባል ነገሩ የተጠናቀቀ መስሎህ ከፊት ለመሰለፍና ፖለቲከኞች ዘንድ ለመወደድ ያደረግከው ጥረት ማንነትህና በነፈሰበት ለመንፈስ የምታደርገውን የሞኝ ባቴሌነትህን አሳይቶብሃል።
Forwarded from أبو ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ04
__
 
በህሩ ተካ=>"   ይህ የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ ታሪካዊ የሆነው " መጥፎን ነገር ለትውልድ እንዳይሸጋገር እናጥፋው " የሚለውን እሴት መርህ አድርጎ የተነሳው የሽማግሌ ስብስብ እሴቱን ጠብቆ መርሁን እውን አድርጎታል ። የሚገርመው የሽማግሌው ስብስብ ይህን መርህ እውን ሲያደርግ ምንም አይነት ከሸሪዓ ጋር የሚጋጭ ባህላዊ ነገር ሳይኖር መሆኑ ነው ። "
__
إنا لله وإنا إليه راجعون
በጣም ያሳዝናል ይህ አባባል እንኳን የወረዳው ሼይኽ ነኝ ከሚል ሰው አይደለም ምንም ያልቀራ ተራ ሙስሊም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። እንኳን ሙሉ ስምምነቱና የእርቅ ሂደቱ አይደለም ይህ ፁሁፍህ እራሱ ከሸሪዓ ጋር ይጋጫል።
1/ " መጥፎን ነገር ለትውልድ እንዳይሸጋገር እናጥፋው "ይህ አባባል ታምንበታለህን?ይህ ማለት በአጭሩ በጉራጊኛ በርቸ የሚባለው ነገር ነው።በርቸ ማለት ደግሞ በአጭሩ በምሳሌ ለማስረዳት _እቤት ውስጥ ጀበና እንኳን ቢሰበር በርቸው (ክፋቱ ለትውልድ እንዳይተላለፍ )እናውጣ ተብሎ ሌላ ጀበና ተገዝቶ ይቀየራል።ካልሆነ ለወደፊቱ መጥፎ ክስተቶች ይከሰትብሀል የሚል አመለካከት አለ።ምንም ነገር ይጥፋ ተመሳሳይ ሂደቶች ይኬዳል።እንዲሁም የሆነ አካባቢ ተመሳሳይ ችግሮች በተደጋጋሚ ሚከሰት ከሆነ "(በርቸ ንስድድነ)ወይም ከዚህ በፊት የተሰራ መጥፎ ነገር አለ እሱን እናጥራ" በሚል ባህላዊ አካሄድ ወግ አዋቂ ብለው ወደ ሚያምኑት ጠንቋይ ቤት በመሄድ ጉዳዩን ምን እንደሆነ ጠንቋዩን ጠይቀው የሚፈፅሙት የሽርክ ተግባር የተቀላቀለበት መጥፎ ባህላዊ ልምድ ነው።

የትኛውንም የተውሂድ አስተማሪ ግንባር ቀደም ትኩረት ከሚሰጣቸው እርሶች ውስጥ አንደኛው አድርጎ የሚያስተምረውን ጉዳይ ወረዳው ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና ሽማግሌዎች ዘንድ እውቅና ለማግኘት ይህን የተውሂድ እርዕስ ገደል መክተት ክፉኛ አሳዛኝ ክስተት ያለፈበት ታሪክ አስመዝግበሀል።

ሙስሊሞች የሚያምኑት:-
1/ነገራቶች የሚከሰቱት በአላህ ውሳኔ ነው
يؤمنون بقضاء الله وقدره
በአላህ ውሳኔ ማመን ከኢማን አርካኖች ውስጥ አንዱ መሆኑና በሱ የካደ ከኢስላም እንደሚወጣ እናምናለን።ስለዚህ የሆነ ጊዜ ላይ የሆነ አካባቢ  ችግር ቢፈጠር ቀድሞ የነበሩ ሰዎች በሰረት ጥፋት ነው አንልም።እኛ የሰራነውንም ለትውልድ በርቸ ይቀመጣል የሚል እምነት የለንም።

2/ሌሎች በሰሩት ያልሰሩትን አይጠየቁም።

مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا

የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡

3/ጥፋት ለትውልድ እንዳይቀመጥ የሚለው አባባል በራሱ የተሳሳተ ሆኖ እያለ ጥፋት ማረሚያ መንገድ የተስተካከለ መሆን አለበት።ጥፋቱ ወይም ወንጀሉ በሰውየውና በጌታው መካከል ከሆነ መስፈርቶቹ አሟልቶ ወደ አላህ መመለስ ነው ያለበት።ተጨማሪ የሰው ሐቅ ካለበት ሀቁን መመለስ ወይም ይቅር ማስባል አለበት።የዚህ ሁሉ ግንባር ቀደሙ መስፈር ደግሞ እስልምና ነው።ያለ እስልምና የትኛውንም አይነት ተውበት ሊገኝ አይችልም።

ኩፍር፣ሽርክ፣ቢዳዓ፣ከባባድ ወንጀሎች በተስፋፋበት ሀገር ውስጥ እንዲህ አይነት የአላዋቂ ቀልድ እየቀለዱ ወደ ዲን ማላከክ አግባብ አይደለም።ራስህንም ሙፍቲ አድርጎ መሳል ተገቢ አይደለም።የዚህ ሁሉ እህቶቻችን እንባ ባልታበሰበት ምኑን ነው ለትውልድ መጥፎ ነገር አናስቀምጥ በሚል መርህ ሰሩ የሚባለው?አሏህን በበደል አይነቶች ሁሉ እየታመፀ (በርቸ ንስድድነ)በሚል መርህ ሌላ ሽርክ በሚሰራበት ተጨማሪ "ምንም ከሸሪዓ ጋር የሚጋጭ የለውም" ብለህ ምስክርነት ትሰጣለህን?ይህ ካላደረግን ትውልድ ላይ ለወደፊቱ የሚቀመጥና የሚፈጠር ችግር ይኖራል እያሉህ እኮ ነው አልገባህም?

      እንደ ሰሃቦች አባት በደል የሰራ አለ እንዴ?የዒክሪማህ رضي الله عنه አባት እኮ አቡ ጀህል ነው።የኻሊድ رضي الله عنه አባት እኮ ወሊድ ኢን ሙጊራህ ነው።የሰፍዋን رضي الله عنه አባት እኮ ኡመየተ ኢብኑ ኸለፍ ነው።,,,,,,,,,,እነዚህ ሰዎች ማለት ነብያችንን صلى الله عليه وسلم በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ያደረጉ። ሲሰገዱ የእንግዴ ልጅ የደፉ፣መልእክታቸውን እንዳያደርሱ የከለኩ፣ከሀገር ያባረሩዋቸው፣ተከትለውም በመሄድ የተዋጉዋቸው፣የፈነከትዋቸው፣ያ ሁሉ ሰሃባን የገደሉ አረመኔዎች ናቸው።

ይህ ሁሉ ወደር የሌለው የአባቶች ክፋት እንቁ በሆኑ ሰሃቦች ላይ የፈጠረው ችግር አለን?።ወይስ መጥፎን ነገር ለልጆቻችን እንዳይተርፍ ብለው ያደረጉት ባህለዊ ሸንጎ ነበራቸው?በርቸ እያልክ ከባህላዊ እና ከሽርክ አመለካከት ያልተላቀቁ ሰዎች የሚያዜሙት የሽርክ ዜማ አብረኽ ባትዘምር የተሻለ ነው።

"የእርቅ ሂደቱ ራሱ ከሸሪዓ ጋር አይጋጭም" የምትለው።ኒቃብ እንዳይለበስ መወሰኑን ነው፣ወይስ የቂጫና የጉርዳ (ቂጫ=የጉራጌ ሽማግሌዎች መተዳደሪያ ሲሆን ጉርዳ ማለት ደግሞ ባህላዊ የቃልና የመሀላ ሂደት ነው።) ሂደቱ ነው?
ይህ የተሳሳተ ብይንህን ወደ ጎን ተወውና ዳኝነት ከሸሪዓ አይጋጭም ለመባል በሸሪዓ መዳኘት ይፈልጋል።ከሸሪዓ ውጪ ያሉ ፍርዶች ወደን ተቀብለን ፣ከሸሪዓ አስበልጠንና አማራጭ እያለን ወደ ሌሎች የምንዳኝ ከሆን ብይኑ ምን እንደሆነ ጠፍቶህ አይመስለኝም።ጥቂት ግለሰቦች ዘንድ ለመወደድ መሰረታዊ የዲን ነጥቦችን መናድ እጅጉን የሚያሳዝን ውርድት ነው።


ይህን በተመለከተ ለህዝበ ሙስሊሙ ማስተላለፍ ምፈልገው መልእክት:-በርቸ የሚባል ነገር የለም።ስህተት የሰራ መስፈርቱን አሟልቶ ተውበት ካደረገ አላህ ወንጀሉን ይምረዋል።ድንገት በህይወት ዘመናችን የሚከሰቱ አደጋዎች ካሉ አንድም በአላህ ውሳኔ ነው ሌላም እጃችን በሰራው መጥፎ ስራና ወንጀል  እንጂ ሌላ አይደለም።
Forwarded from أبو ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ 05
_
=>
በህሩ ተካ    " የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የዛሬው ቀን ላይ ደርሶ ይህን ታሪካዊ ሰላም ሲያስመዘግብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀንና ለሊት በእግር ሩቅ ቦታ በመጓዝ  ከገጠር እስከ ከተማ ከሚመለከተው አካል ጋር በመገናኘትና ነገሩን ከስር መሰረቱ በመረዳት ቂምና በቀል እንዳይኖር በሁሉም ልብ ውስጥ የተከሰተው ነገር  አስተማሪ ሆኖ ያለፈ ክስተት ሆኖ እንዲቀር በማድረግ ነው ። "አለ

መልስ=>ጉዳዩ ከላይ እንዳየነው ሆኖ እያለ እነዚህን ሰዎች በዚህ ልክ እያደነቅክ ወረዳው ላይ ተውሂድን ለማንገስና ሸርክን ለማጥፋት ብቸኛው የህይወት ግባቸው አድርገው የሚተጉ ዱዓቶችን በአንዳንድ ቅርንጫፋዊ ነጥቦች ካንተ ጋር ስላልተስማሙ ብቻ  በዚህ ልክ ለመጎንተልና የዳዕዋ ጠላቶች በሚል ለመወረፍ ብእርህን ስታሾል ማየት እጅጉን ይገርማል።


  በህሩ ተካ=>"  ይህ የሀገር ሽማግሌ የሰላም ውጤት ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በአላህ እርዳታ የአንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው ወንድማችን ልፋት ውጤት ነው ። ይህ ወንድማችን ሁኔታው ተከስቶ በሁለቱም ጎራ ሁሉም ስሜታዊ ሆኖ ነገሩ ወደ ሀይማኖት ግጭት ሊቀየር እየሄደ ባለበት ወቅት በዋነኝነት ሙስሌሞቹን በማረጋጋት በአስተዋይነታቸውና ሚዛናዊነታቸው የሚያውቃቸውን ክርስቲያን የከተማ ነዋሪ የእነሞር ተወላጆችን  በየግል የሁኔታው አደገኝነትና የሚያስከትለው ውጤት ምን ሊሆን እነደሚችል እንዲያዩትና እነርሱ ባሉበት ዘመን እንዲህ አይነት ክስተት ተክስቶ ለትውልድ የተበላሸ ታሪክ መተው እንደሌለበት በመንገር ነበር ። እነዚህ አስተዋይና ሚዛናዊ የሆኑ ክርስቲያን የእነሞር ተወላጆች ከእነርሱ በፖዚሽንም ሆነ በትምህርት ደረጃ የሚያንሰው ወንድማቸው ያቀረበላቸውን ሀሳብ በቅል ልቦና በመቀበል ወደ ተግባራዊነቱ መገባት እንዳለበት ወሰኑ ። "አለ።

መልስ=>እንዲህ አይነት ፁሁፍ በመፃፍ አንዱ ወንድማችን ብቻው ባታሳቅቀው ጥሩ ነው።ሌሎችም የሚታዘቡት እውነታ የብዙዎች ልፋት ወደ አንድ ግለሰብ ስትጠቀልለው እሱም ወዶ የተቀበለውና ብቸኛ የድል ባለቤትነትን ለመጎናፀፍ ያደረገው ጥረት አታስመስልበት።ሞኝ ባያፍር የሞኝ ባለቤት ያፍር እንደተባለው።

ሌላው ሰላም ወዳዱ የመላው ሙስሊም ሰፊ ጥረትና ውጣ ውረድ ለአንድ ግለሰብ ብቻ በስጦታ መልክ ማቅረብ  ምን ያህል ለውለታ ስግብግብ መሆንህን ያሳያል።

ደግሞም አስተዋይና ሚዛናዊ እያልክ በፍትሃዊነት ጥግ እየገለፅካቸው ያሉ ግለሰቦች እውነትህ ነው? በልበ ሙሉእነት ትገልፀዋለህን?(ሙመይዓነት)አይሆንብህምን?
06
     በህሩ ተካ =>"የጀመሩት ተገናኝቶ በጋራ በመነጋገር ሲሆን ቀጥሎ ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም ተጨማሪ የከተማ ነዋሪ ጋር የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ውይይት በማድረግ ሲሆን ውይይት ካደረጉ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሀገር ሽማግሌ ማድረስ እንዳለባቸውና ይህንኑ ሀሳብ ለደቡብ ክልል ፕሬዝዳት አቶ እርስቱ ይርዳው አቅርበው እሱም ባለበት በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ላይ ከህብረተሰቡና ሀገር ሽማግሌ ጋር ውይይት እንዲደረግ ወሰኑ ። በዚሁ መንገድ ቀጥለው ጉዳዩ ወደ ፕሬዝዳቱ አቀረቡት ። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ እርስቱ ይርዳው በጣም በሚገርም ሁኔታ ሀሳቡን ተቀብሎ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ አመቻቸ !!!!! ። "አለ።

መልስ=>ወላሂ ሳቄን ነው የመጣው أستغفرالله  "በጣም በሚገር ሁኔታ አላለም"?ደግነቱ እርስቱ ማን አንደሆነ ድፍን የደ/ብ/ብ/ህ/ጠንቅቀው ስለሚያውቁት እነሱ ቢመሰክሩ የተሻለ ነው።ለማንኛውንም በትውልድ ቀዬው ያ ሁሉ ትርምስ ሲፈጠር የችግሩ ተዋናይ ሆኖ ለዚህ ሁሉ ውድመትና በደል ማእከል በሆነችበት ወረዳ እርስቱን ለማድነቅ ምንም አይነት ሞራል አይኖረኝም።እውነታው ደግሞ የገፈቱ ቀማሽ የሆነው ህዝብ ይፍረድ።



 በህሩ ተካ=>"   ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ጉንችሬ ከተማ ላይ በጣም አሳዛኝ ነገር ተከሰተ ። ብዙ ንብረት ወደመ ብዙ ሰውም ተጎዳ ። ምናልባትም በተያዘው የሰላም ሂደት የሚከስሩ አካላት ምክንያት ሆነው ሊሆን ይችላል ። ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰው ታሰረ ። ወረዳው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ሆነ ። "አለ

መልስ=>ጥሩ ጥንቅር ነው።ሪፖርተራችን ከፉሪ

    በህሩ ተካ=>"ይሁን እንጂ እነዚያ ሰላም ወዳድ የሆኑ ብርቅዩ የእነሞር ተወላጆችም ሆነ የክልሉ ፕሬዝዳንት ነገሩን ያሰቡበት ከማድረስ አላገዳቸውም ። እዚያ ወንድሞች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተነጋግረው ጉንችሬ ላይ ቀጠሮ ተያዘ ። በተባለው መልኩ የክልሉ ፕሬዝዳንት ወደ ጉንችሬ በማቅናት ለህዝብና ለሀገር ያለውን አክብሮት በተግባር አሳየ ። የህዝቡን ሀሳብ ከሀገር ሽማግሌው ጋር አዳምጦ የሀገር ሽማግሌው የጉዳዩን ሀላፊነት ወስዶ እንዲያስተካክል ሀላፊነት በመስጠት ለተግባራዊነቱ ከጎን እንደሚቆም ገለፀ ።  "አለ።

መልስ=>ፁሁፉ ስለረዘመ እየሰለቸኝ መጣሁ።ግን ወገኔ "ብርቅዬ "ማለት ገብቶሀል?ስሙን ማይጠቀሰው ወንድሙና ሌሎች ክርስቲያን ሰላም ወዳዶቹ ብቻ ነው"።

የኛ ብርቂዬዎች ግን ትምርታችን ከሂጃባችን አይበልጥብንም ያሉ እንቁ እህቶቻችን፣እስልምናዬ ተነክቶ ተኝቼ አላድርም፣ሱቄንም ከፍቼ አነግድም።ያሉ ጀግኖቻችን ናቸው።እድሜያቸውና አባወራነታቸውን ከልጆቼ ጎን ከመቆም አያግደኝም ብለው የተንገላቱና የታሰሩ ጀግና አባቶቻችን።መኖር ተከልክለው የተሰደዱ አንበሶቻችን ለዲናቸው የተንገበገቡ በሀገሪትዋና ከሀገር ውጪ ያሉ የእኖር ልጆችና ኢትዮጵያውን ለኛ ብርቅዬ ናቸው።


    =>በህሩ ተካ "እነዚያ ወንድሞች በዚህ መልኩ ለሀገር ሽማግሌ ጉዳዩን አስረክበው ከጎን በመሆን እስከ ፍፃሜው አብረው ሄዱ ። በዚህም የሀገር ሽማግሌው ከቅድመ አያቶቻቸው በወረሱት " መጥፎ ነገር ለትውልድ እንዳይተላለፍ እናጥፋው " በሚለው መርህ መሰረት ብዙ ዋጋ ከፍለው ችግሩ ከስር መሰረቱ እንዲቀረፍ በማድረግ ሰላም አሰፈኑ ። "አለ

መልስ=>የበርቸ ጉዳይ ደገመው።"ከስር መሰረቱ እንዲቀረፍ በማድረግ ሰላም አሰፈኑ።"እውነት ከስር መሰረቱ ነው።ይህ አንባቢና ተጨባጩ የእርቅ ሂደት የሚያውቁ ሰዎች ይፍረዱት።እኛ ግን ሙስሊሞች ሂጃባቸውን ለብሰው እስካልተማሩ ሁሌም ልባችን እንደቆሰለ ነው።የደም እንባ ያፈሳል።አንተ ተደስተህ ሊሆን ይችላል።


     በህሩ ተካ=>"በዚህም መሰረት ንብረታቸው ለተጎዳ ተወላጆች ሁሉም ማህበረሰብ የሚችለውን በማድረግ እንዲዶጉም , ተጎጂዎችም ምርቃት ተደርጎላቸው የተሰጣቸውን ተቀብለው አውፍ እንዲሉ , ከሁለቱም በኩል በዳዮች በባህሉ መሰረት በድለናል አውፍ በሉን ብለው እንዲቀርቡ  በማድረግና ለበደላቸው የሚመጥን ባይሆንም ሽማግሌም ሆነ ተበዳይ ሙሉ በሙሉ አውፍ እንዲላቸው የተወሰነ የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ጨርሰው የታሰሩት እንዲፈቱና ሁሉም ተስማምተው እንዲማሩ በማድረግ እርቀ ሰላም እንዲወርድ አደረጉ ። ይህን ስምምነት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ይዘው በመሄድ የሰሩትን ስራ በማስረዳት የታሰሩት እንዲፈቱላቸውና ለደረሱበት የሰላም ስምምነት እውቅና እንዲሰጥላቸው ጠየቁ ።
    ፍትህ ሚኒስቴርም የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የሰራውን ስራ ትልቅ ቦታ በመስጠት ባጭር ጊዜ በአካል እነሞር ድረስ ባለሞያ በመላክ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በሟሟላት እስረኞቹ እንዲፈቱና የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የሰራውን ስራ እውቅና ሰጥቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አደረገ ። !!!!!"አለ


መልስ=>እሺ በቃ ጥሩ ጥንቅር ነው።ሪፖርተራችን ከፉሪ
አላሁ አክበር አላሁ አክበር አልሀምዱሊላህ ከጉንችሬ ከ12ኛ ክፍል ካፊር ተማሪዎች እሰከ አሁን ባለን መረጃ ከተፈተኑቱ ምንም ተማሪ ያለፈ የለም

እስከ አሁን ከፍተኛ ውጤት 264 ነው።
የጉንችሬ ሰቃዮች
=============
እነዚህ የሞኣ አንበሳ ዩኒፎርም እያሠሩ በመልበስና ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ይሄዱ ይመስል ነጠላ ለብሰው ት/ቤት በመመላለስ ኒቃብስቶች እንዳይማሩ ሴራ በመጠንሰስ እህቶቻችንን ከትምህርት ገበታቸው አፈናቀሉ እንጂ ቀድሞውኑ እየተማሩ አልነበረም።

ለመሆኑ ፈተናው ከ25 ነበር እንደ?
ሰው እንደት ህይዎት እያለው ማትስን ከ100 ዜሮና አንድ ያመጣል?
ምርጫ የሌለው workout ፈተና ነበር እንደ?

እነዚህ ልጆች በዚህ የማትስ ዕውቀታቸው የበፊቱን የሽንኩርት ዋጋ ከአሁኑ ላይ ቀንሱና ውጤቱን ንገሩኝ ብንላቸው ካልኩለስ የሚሆንባቸው ይመስለኛል¡ አሰዳቢ!

እኔን ዓይኔን ጨፍኜ ምንም ሳልሠራ ከ A-D ካሉት ምርጫዎች መካከል ለሁሉም ጥያቄ አንዱን ፊደል ብቻ መርጨ ብሞላ በትንሹ ከ10 በላይ አመጣለሁ¡

ምድረ ደነዝ! ምቀኝነትና ድግምት ብቻ እንጂ ዕውቀት'ማ ባዶ ናቸው።

ኢንሻ አላህ! የጉንችሬዋ እንቁ ግን ተምራ አንድ ቀን ታኮራናለች።

||
t.me/MuradTadesse