𝑬𝒏𝒐𝒓 𝒎𝒖𝒔𝒍𝒊𝒎𝐬 𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂
437 subscribers
112 photos
10 videos
2 files
124 links
Download Telegram
ወሳኝ መልእክት ለእውቀት ፈላጊዎች
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
🔹ግልፅ ያለውንና ፍንትው ብሎ የሚታየውን የሀቅ መንገድ ማንም ሰው ሊያዳፍነው አይችልም

🔹 በተምይእ ሽፋን የሰለፍያን ዳእዋ ለመበታተን አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ የሱና ተጣሪዎችን ስም ያለ አግባብ ያጠፋችሁ ደረሳዎች ኢልምን እንዳይማሩ ብሎም ከኢልም ገበታቸው እንዲበታተኑ ይብዛም ይነስም እጃችሁ ያለበት ሰዎች ይህን ድምፅ ደጋግማችሁ አድምጡትና ከስህተታችሁ ተመለሱ ይህ ወንድማዊ ማስታወሻዬ ነው ።

#please_share_and_visit
#_join_our_channel
👉@voice_of_enor_muslims
ስለ ፎቶና ቪድዮ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ከአሁን በፊት የሰጠው ሙሐደራ
<unknown>
ፎቶና ቪድዮን በተመለከተ‼
===================
«በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ የምለቀው ሃሳብ!»
||
✍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልፎ አልፎ አንዳንድ ፎቶዎችን ስለቅ፤ ከፊል ወንድምና እህቶች ግራ እየተጋባችሁ መሆኑን አስተውያለሁ።
በዚህም የተነሳ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ከአሁን በፊት ፎቶ እና ቪድዮን በተመለከተ የሰጠው በቂ ማብራሪያ ስላለ ያንን ላጋራችሁ ወደድኩ‼
★
✔ አስውላችሁ ከሆነ ከአሁን በፊት ባለኝ አቋም መሠረት፤ ፎቶ ስለቅ ዓይናቸውን በሆነ ቀለም ነገር አጥፍቼ ነው። ይህን የማደርገው አንዳንዶቻችሁ እንደምታስቡት በምነቅፋቸው ግለሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን ራሱ የሸይኽ ኢልያስን ፎቶ መልቀቅ ካለብኝም ዓይኑን በቀለም ነገር አጥፍቼ ነበር።
ነገር ግን በቅርቡ ወሎ ላይ በደሴ ከተማ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቆ የሰጠውን ማብራሪያ በሚገባ በአካል ተከታትዬው ነበር። ያቀረባቸው የዑለማዎች ማስረጃም አሳማኝና ሎጂካል ናቸው።
ብዙዎቻችን በፊት ፎቶንም ቪድዮንም እንቃወም ነበር።
ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን በቪድዮ ጉዳይ ለዘብ ብለን ፎቶን መቃወማችንን ቀጠልን።
ኢንሻ አላህ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለንም አረዳድ ቀስ በቀስ ሊለዝብ ይችላል።
★
√ እግረ መንገዴን ልጠቁማችሁ የምፈልገው ይህ ጉዳይ የፊቅህ መስኣላ ነው። በዑለማዎች መካከል የልዩነት ርዕስ ተስተናግዶበታል። ስለዚህ ከኛ መካከል አንዱ በዚህ ጉዳይ ላይ የፈለገውን ዑለማ አቋም ቢከተል ሊወቀስ አይገባውም። በነገራችን ላይ ከምናውቃቸው ታላላቅ ዑለማዎች ውስጥ ራሱ መጀመሪያ አካባቢ ከልክለው በኋላ ግን የፈቀዱ አሉ። በክልከላ አቋማቸው ላይም ጸንተው የሞቱ አሉ። ግና በአሁኑ ወቅት በህይዎት ካሉት እንቁዎቻችን ውስጥ በክልከላ አቋማቸው ጸንተው ያሉ በርካታ ዑለማዎች የሉም። ብዙዎቹ ፈቅደዋል።
||
t.me/MuradTadesse
የጥያቄዎች መልስ
በኡስታዝ ሐሰን አብዱልሐሚድ
በወራቤ ከተማ áŠ á‰Ąá‰ áŠ­áˆ­  መስጅድ በተካሄደው ሃገር አቀፍ የኢጅቲማዕ ፕሮግራም ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ።


🎙 በኡስታዝ ሐሰን አብዱልሐሚድ (ሐፊዘሁሏህ)

-------
#please_share_and_visit
#_join_our_channel
👉@voice_of_enor_muslims
Audio
↪️ የጊዜ አጠቃቀም

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
ሐፊዘሁሏህ

#please_share_and_visit
#_join_our_channel
👉@voice_of_enor_muslims
"በሰራሁት ወንጀል ምክኒያት ለአምስት ወራት የለይል ስግደትን ተከለከልኩ"
'ምን አይነት ወንጀል ነው ?' ተብለው ተጠየቁ
የሆነ ሰው ሲያለቅስ አየሁትና በውስጤ "ይህ ለእዩልኝ ነው ሚያለቅሰው" አልኩኝ።
ሱፍያን አሰውሪ

ውስጥ አዋቂ አይደለህም።የሰወችን ልብ የመበርበር ችሎታውም የለህም።ያንተን የውስጥ መሻት ሌላው እንደማያውቀው ሁሉ አንተም የሌላውን ማወቅ አትችልም።በህዝብ መሀል ተነስቶ ገንዘቡን የሚሰጥ ሁሉ እዩልኝ እያለ አይደለም።በህዝብ መሀል ስቅስቅ ብሎ የሚያለቅስ ሁሉ ፈሪሀ አላህ ተብሎ እንዲሞካሽ አይፈልግም።
በቃ ምን አገባህ።
Š
#please_share_and_visit
#_join_our_channel
👉@voice_of_enor_muslims
ከጠየቅኩት በላይ ሰጥቶኛል፣ ከጥረቴ በላይ ሸልሞኛል፣ ከለመንኩት በላይ ለግሶኛል። ርቄው አልተወኝም፣ ሸሽቼው አልጣለኝም፣ ረስቼዉም አልረሳኝም። ካሰብኩት በላይ አድርጎልኛል ፣ አይታሰብም ያልኩትን አሳክቶልኛል፣ ጥፋቴን እያየ አልፎኛል፣ ዉርደቴን እያወቀ ሰትሮኛል፣ ለኔ በማይገባኝ መልኩ ተንከባክቦኛል፣ ጠብቆኛል፣  በዙርያዬ ባሉት ዘንድ አሳምሮኛል። ሥሜን ጠብቆልኛል።
እዝነቱና ችሮታው ባይኖርልኝ ኖሮ መቸ ቆሜ እሄድ ነበር።
አላህ ሆይ! በሁሉም ሁኔታዬ ዉስጥ ምስጋና ላንተ ይሁን። በመሸ በነጋ ቁጥር ሥምህ ዘወትር ከፍ ይበል።
Š
#please_share_and_visit
#_join_our_channel
👉@voice_of_enor_muslims
ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!

“ሁል ጊዜ እንደተሳሳትኩ ነው … አንድ ቀን ትክክል ሆኜ አላውቅም … አመለካከቴ የተሳሳተ ነው … ብቃት የለኝም ... ሰዎች ወደፊት ሲገሰግሱ እኔ ግን ኋላ ቀርቻለሁ … አልቻልኩበትም … ዓላማየን አላውቀውም … እና የመሳሰሉት ስሜቶች ብዙ ሰዎችን የሚያጠቁ ስሜቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በተገቢው መንገድ ካልተያዙ ማንነትህን የማኮሰስና ወደኋላ የማስቀረት አቅም አላቸው፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ. እነዚህ ስሜቶች ሁሉም ሰው የሚጋራቸው ስሜቶች ናቸው፡፡ ሆኖም፣ እንደ መንቂያ ደወል ከተጠቀምክባቸው መልካም ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እነዚህን ስሜቶች ለተስፋ መቁረጥ ከተጠቀምክባቸው ወደ ኋላ ይጎትቱሃል፡፡

በብልሽት ምክንያት ልክ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የቆመ (አናሎግ) ሰዓትን ተመልከተው፡፡ ይህ ሰዓት ምንም እንኳን የቆመና ትክክል ያልሆነ ሰዓት ቢሆንም፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የቆመ ሰዓት በቀ ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል - ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ እና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ፡፡ አየህ የተበላሸ ሰዓት እንኳን በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል፡፡ አንተ ደግሞ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!

የቆመ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ከሆነ፣ ምንም ያህል ስህተት የሰራህ ሰው ብትሆን፣ ምንም ያህል ወደፊት መራመድ እንዳቃተህ ብታስብ፣ ምንም ያህል የመሻሻል ነገር እንዳልታየብህ ብታምን፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!! የዛሬ አስር አመት፣ የዛሬ አምስት አመት፣ የዛሬ ሶስት አመት፣ የዛሬ አመት . . . የነበርክበትን አስብ፡፡ በትንሹም ቢሆን አሁን ከዚያ ትሻላለህ፡፡

ምናልባት፣ “እኔ ባለሁበት የቆምኩ ሰው ነኝ” ልትል ትችላል፡፡ ምናልባትም፣ “እኔ ባለፉት አመታት ከነበርኩበት ደረጃ የወረደ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት” በማለት ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ እንኳን የተማርከውን ትምህርት አስበው፡፡ ሁኔታህ አለመሻሻሉ እየሰጠህ ያለውን የመንቂያ ደውል አስታውሰው፡፡ ማሰብ፣ ራስን መገምገም፣ ያለፈውንና የወደፊቱን ማስላት የመቻልህን ብቃት አስበው፡፡

ከዚህ አመለካከት ለመውጣት ከፈለክ፣ ከተሳሳትከው፣ ከማትችለው፣ ካልተሳካውና ካልሆነው አትነሳ፡፡ ምንም እንኳን ትንሽ ነው ብለህ ብታስብም፣ ከትክክለኛነትህ፣ ከተሳካልህና ከሆነልህ ነገር ተነሳ፡፡ በዚህ ስሜት ጫና ውስጥ ሆነህ ዘንግተኸው ነው እንጂ፣ ሌሎች ማድረግ የቻሏቸው ለአንተ ግን ያቀቱህ በርካታ ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ ሌሎች ሰዎች ያቃታቸው አንተ ግን ማድረግ የምትችላቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ አትርሳ፡፡

ያም ሆነ ይህ፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
Š
#please_share_and_visit
#_join_our_channel
👉@voice_of_enor_muslims
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ

ነገ ሐሙስ ነው ኢንሻአላህ  ከቻልን እንፁም ካልቻልን እህት ወንድሞቻችንን እናስታውሳቸውና የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!

- عَنْ عَبْدِاللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ : قَالَ لَنَا رَسُولُ اللَّهِ : ŮŠŮŽŘ§ مَعْشَرَ الشَّبَابِ، مَنِ اسْتَطَاعَ مِنْكُمُ الْبَاءَةَ فَلْيَتَزَوَّجْ، فَإِنَّهُ أَغَضُّ لِلْبَصَرِ، وَأَحْصَنُ لِلْفَرْجِ، وَمَنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَعَلَيْهِ بِالصَّوْمِ؛ فَإِنَّهُ لَهُ وِجَاءٌ. مُتَّفَقٌ عَلَيْهِ.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☑️ የጁሙአ ቀን ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ በውዱ ነብያችን ላይ ሰለዋት ማውረድ ነው። በስራም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ ውዱእ ቢኖረንም ባይኖረንም ሰለዋት ማውረድ ትልቅ ምንዳ ያስገኛል።

▪️የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

♦️በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ ሰው፦
🔹በአስር እጥፍ አላህ በሱ ላይ ያወርድበታል
🔹አስር መጥፎ ሰራዎች ይሰረዝለታል
🔹አስር ደረጃዎች ከፍ ይደረጋል


📚الباني (صحيح النسائي) جـ1 ص415

◾️اللہم صلے علی محمد وعلے آل محمد کما صلیت علے إبراھیم و علے آل إبراھیم إنک حمید مجید وباعڊ علی محمد وعلے آل محمد  کما باعڊت علے إبراھیم و علے آل إبراھیم إنک حمید مجید
Š
@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
ሰበር ዜና

ለ3 ወር በእስራት ላያ ስገኙ የነበሩ ወንድሞቻችን አባቶቻችን ዛሬ እንደሚፈቱ ተነግሮዋል‼

ትላንት ሀሙስ 4/12/2015 በተደረገው የሽማግሌዎች ስብሰባ ላይ የታሰሩ ወንድሞቻችንና አባቶቻችን እያንዳንዳቸው በ4000 ብር ቅጣትና በዋስ ዛሬ እንደሚለቀቁ ተወሰነ።

ለሁለት አመት እያንዳንዱ ሙስሊም በጋራ በአንድነት ሲታገልለት የነበረው የኒቃብ ጉዳይ በአላህ ፍቃድ ተሳክቶ ይኸው ሙተነቂብ እህቶቻችን የክረምት ትምህርት እንዲማሩ ተፈቅዶላቸው በጉንችሬ ሀይስኩል ትምህርት ቤት የክረምት ትምህርት በመማር ላይ ይገኛሉ!

@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
➲ትእግስት
〰〰〰〰

➥ሶብር(ትእግስት) በ 3 ይከፈላል።

➢አላህ ያዛዘውን በመስራት ላይ ትእግስት ማድረግ

➢አላህ ከከለከለው ነገር በመራቅ ላይ ትእግስት ማድረግ

➢አላህ በወሰናቸው ቀደር(ውሳኔ) ላይ ትእግስት ማድረግ

➮ትእግስት እስልምና ላይ ትልቅ ቦታ አለው። ሁሉም የእስልምና ስራዎች ውስጥም ይገባል።
አላህ ዘንድም ትእግስተኞች በጣም ትልቅ ምንዳ አላቸው።
إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُمْ بِغَيْرِ حِسَابٍ

አላህ ከታጋሾች ያድርገን
@voice_of_enor_muslims
🤍አጋርነትዎን በተግባር ያረጋግጡ

ነሲሓ ቲቪን በ CBE ንግድ ባንክ ለመርዳት የማይረሳው የአካውንት
ቁጥራችን 444 ነው

_
የአካውንቱ ባለቤት
ibnu Masoud islamic Center

@Nesihatv
ዛሬ ይፈታሉ ተብሎ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የተሳሩ ወንድሞቻችን አባቶቻችን ሳይፈቱ ቀረ።

በትላንትና በሽማግሌዎች ውይይት ውሳኔ መሰረት የተሰሩ ወንድምና አባቶች ይፈታሉ ብሎ በጉጉትና በደስታ ሲጠብቁ የነበሩ የታሳሪ ቤተሰብና የከተማው ሙስሊም ጀመዓ ቅስማቸው ተሰብሮ ውሎዋል። እንዲሁም እስሮኞች ትፈታለቹ ተብሎ ስለተነገራቸው ሙሉ ስንቃቸውን ወደ ቤተሰብ በጠዋቱ ልከው በሆንም ዛሬ እንደማይፈቱ ሲያረጋግጡ በደረጋሚ የላኩትን ስንቃቸው እንዲመለስ ተደርጎዋል።

ዛሬ ያለመፈታቸው ምክንያት እንደተባለው ከሆነ የዞን አቃቢ ህግ አቶ ተስፋዬ በስብሰባ ምክንያት ዛሬ ወደ ጉንችሬ መምጣት ባለመቻሉ የእስረኞች መፈታት ጉዳይ እንዳስተጓጎለው ተነግሮዋል።

@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
የታሳሪ ቤተሰብና የጉንችሬ ጀመዓዎች በሙሉ አብሽሩ የትግላችን ውጤት ፍሬ አፍርቶ እህቶቻችንን በነፃነት ከነኒቃባቸው እንዲማሩ እንዲፈቀድላቸው ከአላህ ቀጥሎ ከዛም ሰበብና ምክንያት ሆነናል።

ኢንሻአላህ በመታገሳች ብዙ ነገር አትርፈናል። ትዕግስት መራራ ብትሆንም ውጤቷ ያማረ ነው። ሁለት አመት በትግስት ያሳለፍን አንድና ሁለት ቀን በትዕግስት መጠበቅ አያቅተንም።
@voice_of_enor_muslims
በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅፈት ቤት ከወሸ ሽማግሌዎች ጋር በጋራ የተዘጋጀው የሰላምና የእርቅ ፕሮግራም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የፊታችን እሁድ 7/12/2015 እስቲፋኖስ አጠግብ በሚገኘው በቂርቆስ ክ/ከተማ መሰባሰቢያ አደራሽ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

ውድ የእኖር ተወላጅ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆናቹ ሙስሊሞች በሙሉ እስከ አሁን ስንታገልልት የነበረው የዲናችን ጉዳይ ፣ ሸሪዓችንን ለማስጠበቅና የእህቶቻችንን የአለባበስ ስርዓት ለማስከበር ሲደረግ የነበረው ትግል በአላህ ፍቃድ ፍሬ አፍርቶ ጫፍ ላይ እንገኛለን። ስለዚህ ትግሉ ስላልተቋጨ ቀጠይ እሁድ ላይ በሚደረገው ውይይት እንድትገኙ በአላህ ስም አጥበቀን ጥሪ አድርገንላቹሀል።

@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims
ጽንፈኛ ብሔርተኝነት ከዲናችን መንገድ እንዳያስወጣን‼
=====================================
✍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሃገራችን ፖለቲካ ጋር ተያይዞ የመጣው የብሔር ፖለቲካ ባመጣው ጦስ ሳቢያ ጥቂት የማይባለው ሙስሊም ከእስልምና የትስስር ገመድ (ኢስላማዊ ወንድማማችነት) ይልቅ የብሔር ትስስር በልጦበት እያዬን ነው።

በተለያዩ የኢስላም ጠላቶች ሙስሊሙ ላይ ጥቃት ሲሰነዘር፤ አጥፊው ማንም ይሁን ማን ኢስላምና ሙስሊሞች ስለተደፈሩ ብቻ ማውገዝ ሲገባን ቀድመን የአጥቂውንና የተጠቂውን ማንነት ስናጣራ እንታያለን።
አጥቂው የኛ ብሔር ተወላጅ ከሆነ ጥፋቱን ቀለል ለማድረግ አለፍ ሲልም ጀስቲፋይ ለማድረክ ሲሞከር ታዝበናል። ይህ እንደ ሙስሊም አደገኛ አካሄድ ነው። እምነታችን ከብሔራችን፣ ከአባታችን፣ ከእናታችን፣ ከነፍሳችን… ከሁሉ ነገራችን በላይ ነው።

√ ሞጣ ላይ ወይም ጎንደር ላይ መስጂዶች ላይ፣ ሙስሊሞችና ንብረታቸው ላይ ጥቃት ሲፈጸምና ሲገ'ደሉ ጥቃቱ ሲወገዝ፤ ከእምነቱ ብሔሩ በልጦበት አጥፊዎችን ከማውገዝ ይልቅ ከጽንፈኛ የአማራ ብሔርተኞችና ጸረ ሙስሊም አሐዳውያን ጋር ወግኖ «ለምን ጉዳዩ ይካበዳል? አማራ ክልል ስለሆነ ነው?…» ብሎ ለመሸፋፈን የሚፈልግ ሙስሊም አይተናል።

√ ወለጋ ላይ ሙስሊሞች በጅምላ ሲገ'ደሉ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ላይ መስጂዶች ሲፈረሱ… ጥቃቱን ሲኮነን፤ ከጽንፈኛና ሙስሊም ጠል የኦሮሞ ብሔርተኞች ጋር ወግኖ «አማራ ክልል መስጂድ ሲቃጠል የት ነበርክ፣ ሙስሊሞች ሲገ'ደሉ የት ነበርክ፣ የኛን ለኛ ተውልን፣ የኦሮሞ ጥላቻ ስላለባችሁ ነው…» ወዘተ የሚል ጸያፍ ሙስሊም መኖሩን አይተናል።

✔ በዚሁ ከቀጠልን፦ «ከአንተ ብሔር ጥፋተኛ የኔ ብሔር ጥፋተኛ ይሻላል!» በሚል ፉክክር ውስጥ ገብተን ከዲናችን መደፈር ይልቅ የብሔራችን ተወላጅ ወንጀለኛ መነካቱ ቆርቁረን በአደራ ከቀደምቶች የተቀበልነውን ዲናችንን እንዳንተወው ያሰጋል። እኛ ባንተወውም ዲናችን ይተወናል።
ምክንያቱም በተግባርም ጭምር እንጂ በአፍ ብቻ ሙስሊም ነኝ በማለት ሙስሊምነት አይገኝም።

√ እርግጥ ነው አማራ ክልል ላይ በሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲፈጸም፤ ይህን እንደ አጋጣሚ ተጠቅሞ ትግሉን ከፊት ልምራው የሚል አስመሳይ የአማራ ጥላቻ ያለበት ኦሮሞ አይጠፋም። ግን የዚህ ሰው ትክክለኛ ምንነት (የእውነት እየታገለ ያለው በተፈጸመው ጥቃት ተቆርቁሮ ነው ወይንስ የአማራ ጥላቻ ስላለበት? የሚለው) የሚገለጠው፤ ራሱ ክልል ላይ በሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲፈጸም ከልቡ ከተቃወመ ነው። ግን እንኳን ሊቃወም ጭራሽ ጀስቲፋይ የሚያደርግ ከሆነ ያኔ ይገኛል።

√ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲፈጸም፤ ትግሉን ከፊት ልምራው የሚል የኦሮሞ ጥላቻ ያለበት ጽንፈኛ አማራ ሊኖር ይችላል። የዚህም አካል ትክክለኛ ማንነቱ የሚገለጠው አማራ ክልል ውስጥ ጥቃት ሲፈጸም ከልቡ ያወግዛል ወይንስ «አማራ ክልል ሲሆን ብቻ ነው?…» እያለ ወንጀልን ከወንጀል እያነፃፀረ ያድበሰብሳል?» የሚለው ሲታይ ነው።


✔ መውጫ፦
እኔ በግሌ እንደ ሙስሊም፤
√ በተወለድኩበት ክልል በሙስሊሞችም ላይ ሆነ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም በጥብቅ አወግዛለሁ። በዚህም ጽንፈኛ የአማራ ብሔርተኞች «ኦነግ ነህ፣ አማራን ከድተሃል…» ወዘተ ሲሉኝ መስሚያዬ ጥጥ ነው። ሞጣና ጎንደር ይመስክሩ!

√ ኦሮሚያ ክልልም ላይ ሆነ በሌላው አካባቢ ሙስሊሞችና ንጹሐን ላይ ጥቃት ሲፈጸም በጥብቅ አወግዛለሁ። ወለጋና ሸገር ሲቲ ምስክሬ
በዚህም ሳቢያ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች «አንተ ነፍጠኛ፣ የራስህን ክልል ጥቃት ባወገዝክ…» ወዘተ ቢሉኝም መስሚያዬ ጥጥ ነው። ምክንያቱም መለኪያዬ ሁለንተናዊው እምነቴ እንጂ መንደሬ አይደለም።

ሙስሊም በብሔር ሳይታጠር አጥፊ የየትም ብሔር ቢሆን ዲኑን አስቀድሞ ለዲኑ ዘብ መቆም አለበት።
አላህ ወደ ዲኑ ትክክለኛ መመለስን ይመልሰን።

||
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
ነሐሴ 06, 2015  E.C.
ሙሐረም 25, 1445 H.C.
ኦገስት 12, 2023 G.C.

♠
በርካታ የምለቃቸውን መልዕክቶች በቀላሉ ማገኘት ከፈለጋችሁ ይህን የቴሌግራም ቻነሌን መቀላቀል ትችላላችሁ።
⇓⇓⇓
Join: t.me/MuradTadesse
ቤት ውስጥ መሆን ለሴት ልጅ ራሱን የቻለ ዒባደህ ነው። ተገዳ ወይም አማራጭ አጥታ ካልሆነ በስተቀር ሙስሊም ሴት ወጣ-ገባ ማለት ልታበዛ አይገባም።
ከደጋግ ቀደምት ሴቶች መካከል አንዷ የሆኑት ፋጢመህ ቢንቱልዓጣር በህይወታቸው 3 ጊዜ ብቻ እንጂ ከቤት ወጥተው አያውቁም ነበር፤
1- ያገቡ ቀን፣
2- ሐጅ ያደረጉ ቀንና
3- የሞቱ ቀን ብቻ!::

አንቺስ እህቴ! በቀን ስንቴ ነው የምትወጪው!?
Š
@voice_of_enor_muslims
ለማስታወስ ያክል👌
ዛሬ የሚመቻቹህ አዲስ አበባ የምትገኙ የእኖር ተወላጅ ሙስሊሞች በሙሉ እስቲፋኖስ አጠግብ በሚገኘው በቂርቆስ ክ/ከተማ መሰባሰቢያ አደራሽ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚካሄደውን የሰላምና የእርቅ ፕሮግራም ለመገኘት ሞኩሩ።
@voice_of_enor_muslim
@voice_of_enor_muslims
@voice_of_enor_muslims