𝑬𝒏𝒐𝒓 𝒎𝒖𝒔𝒍𝒊𝒎𝐬 𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂
488 subscribers
112 photos
10 videos
2 files
123 links
Download Telegram
Forwarded from ŘŁŘ¨Ůˆ ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ 02
-----------------------------
በህሩ ተካ =>"በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ላይ ከወራት በፊት በጉንችሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ጉዳዩ ከሮ የአካልና ንብረት ጉዳት እስከማድረስ መድረሱ የሚታወቅ ነው ።"አለ
____

መልስ=>ሁለት አመት ያለፈው ጉዳይ  "ከወራት በፊት"ብሎ መግለፅ በራሱ ነገሩን ማቅለልና ድንገት ትላንትና የተፈጠረ ማስመሰል ይሆናል።አንተ እንዳልከው ከወራት በፊት የተከሰተ ጉዳይ ሳይሆን ለዘመናት ሲያቅዱት የኖረና የስልጣን ሰልሰለቱ ከወረዳ አስተዳደርነት እስከ ክልል ፕሬዝዳንትነት በእጃቸው ባደረጉ ጊዜ እውን ያደረጉት ህልምና ሴል ነው።

ሌላው ችግሩ የተፈጠረው ጉንችሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ብቻ አይደለም።ኧገዜ፣ተርሆኘ፣ጋርባዶና ሌሎች ት/ቤት ላይ ነው።የችግሩም መንስኤ አንተ እንዳልከው "ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት"ብቻ ሳይሆን ቀድሞውንም የተለያዩ ትንኮሳዎች የነበሩ ቢሆንም የነገራቸው ማሳረጊያ ያደረጉት በርካታ ቁጥር ያላች ኢስላማዊ አለባበስ የለበሱ ተማሪዎችን አንቀበልም በሚል መነሻ ነው።

  ይህ አገላለፅህ እጅጉን ያሳዝናል።ያ ሁሉ ሙስሊሙ ላይ የደረሰውን እንግልትና መከራ ወረዳይቷዋ ለሙስሊሞች የእሳት ባህር ሆና ቆይታ ሙስሊሙን በልዩ ሀይል ሲደበደብ ሌሊት ከቤቱ ተነጥሎ እየወጣ እስር ቤት ሲወረወር፣ከህፃን እስከ አዋቂው ከወጣት እስከ አዛውንቱ ያሳለፈውን ስቆቃ ድፍን ሀገር የተጨነቀበት፣ሙሉ ሙስሊም ተማሪዎች ከት/ት ገበታ የተፈናቀሉበት በርካቶች የተሰደዱለት ፣ከቀዬያቸው የተፈናቀሉበት፣ሙሉ ህይወታቸውን መሰዋትነት የከፈሉለትን ጉዳይ እንዲህ የመንደር ልጆች ያስነሱት ፀብ አስመስሎ መሳልና ለህዝብ መግለፅ በጣም የሚያሳዝን ከዳተኝነት ነው።

አንተ እንዳልከው "ኒቃብ ከለበሱ ሴት ተማሪዎች ጋር አንማርም ባሉ የተወሰኑ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት"ሳይሆን ለዘመናት የዘለቀውን ሙስሊም ጠልነትና የጥላች ብትራቸውን ማሳረፍ የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሲደርሱ ወደ ተግባር የገቡበት ተጨባጭ ነው።
   "(ዋ ዌራድ ሚሽተነ ታናዋአነ)ይህ መጥፎ አረም ካልመዘዝነው ሰላማችን አናገኝም "እና መሰል የጥላቻ ሰበካዎች የፈጠሩት ጥላቻ ነው።

እነዚህን ክርስቲያን ተማሪዎችን ቤተ_ ክርስቲያን ላይ በተደረጉ ውይይቶች መሰረት ለፀብና ተልእኮ ለማሳካት እንደ ግብአት የተጠቀሟቸው እንጂ የችግሩ መሰረት ሆነው አይደለም።

አንተ እንዳልከው ከሆነ ኧገዜና ተርሆኘ ያሉ እህቶቻችንን ከትምህርት ገበታ ውጪ ማድረግ ለምን አስፈለገ?ኒቃብ የለበሰች መምህርት ማባረርስ ለምን አስፈለገ?,,,,,,,,,,,,,,,,,ይህ አገላለፅ ጉዳዩን አቅልሎ ማየትና የተከፈለውን መሰዋትነት መናቅ ይሆናል።
___
03
በህሩ ተካ=>" ይህ ጉዳይ አድማሱ እያሰፋ ሄዶ በወረዳው ውስጥ ውጥረት እንዲነግስ አድርጎ ቆይቷል ። የተኛውም ሰላም ፈላጊ ከመጎዳት በስተቀር በማያተርፍበት ብጥብጥ የማህበረሰቡ የዘመናት አብሮነት ታሪክ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንዲገባ ያደረገ ሁኔታ የተከሰተ ቢሆንም የጉራጌ የሀገር ሽማግሌዎች በጣም አስደናቂና ብዙዎች ያልቻሉትን ስራ በመስራት ወረዳውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ በመመለስ ታሪካዊ ስራ ሰርተዋል ። "አለ
__
መልስ=>ይህ አገላለፅ በራሱ እጅጉ አሳፋሪ ስንኞችን ያቀፈ መላምንት ነው።ሙስሊሞች ከሰብአዊ መብታቸው ተገፈው መብት መጠየቃቸውን ነው " የትኛውም ሰላም ፈላጊ ከመጎዳት በስተቀር በማያተርፍበት ብጥብጥ"ብለህ የምትገልፀው።የቃረደ ፖለቲከኛ ለመሆን ዳዴ ማለት አያስመስልብህም።ያ ሁሉ መሰዋትነት "ብጥብጥ "ብለህ ትገልፀዋለህን?እስቲ አንተ የመፍትሄ ሃሳብ አምጣ ሙስሊሞች ምን ማድረግ ነበረባቸው።አንተ የወረዳው ዳዕዋ በኔ ስር ካላለፈ የምትል ራስህን የእነሞር ተወካይ አድርገህ የምትስል ሰው የወረዳው ሙስሊሞች እንዲህ ተጨንቀው ምጥ ውስጥ በገቡበት ጊዜ ምን አደረግክ?ምን ታየልህ? ይህ ነገር ግፍ ነው አግባብ አይደለም ብለህ አንዲት ያደረግካት እንቅስቀሴ አለችህን?እርቅ ሲባል ነገሩ የተጠናቀቀ መስሎህ ከፊት ለመሰለፍና ፖለቲከኞች ዘንድ ለመወደድ ያደረግከው ጥረት ማንነትህና በነፈሰበት ለመንፈስ የምታደርገውን የሞኝ ባቴሌነትህን አሳይቶብሃል።
Forwarded from ŘŁŘ¨Ůˆ ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ04
__
 
በህሩ ተካ=>"   ይህ የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ ታሪካዊ የሆነው " መጥፎን ነገር ለትውልድ እንዳይሸጋገር እናጥፋው " የሚለውን እሴት መርህ አድርጎ የተነሳው የሽማግሌ ስብስብ እሴቱን ጠብቆ መርሁን እውን አድርጎታል ። የሚገርመው የሽማግሌው ስብስብ ይህን መርህ እውን ሲያደርግ ምንም አይነት ከሸሪዓ ጋር የሚጋጭ ባህላዊ ነገር ሳይኖር መሆኑ ነው ። "
__
إنا لله وإنا إليه راجعون
በጣም ያሳዝናል ይህ አባባል እንኳን የወረዳው ሼይኽ ነኝ ከሚል ሰው አይደለም ምንም ያልቀራ ተራ ሙስሊም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። እንኳን ሙሉ ስምምነቱና የእርቅ ሂደቱ አይደለም ይህ ፁሁፍህ እራሱ ከሸሪዓ ጋር ይጋጫል።
1/ " መጥፎን ነገር ለትውልድ እንዳይሸጋገር እናጥፋው "ይህ አባባል ታምንበታለህን?ይህ ማለት በአጭሩ በጉራጊኛ በርቸ የሚባለው ነገር ነው።በርቸ ማለት ደግሞ በአጭሩ በምሳሌ ለማስረዳት _እቤት ውስጥ ጀበና እንኳን ቢሰበር በርቸው (ክፋቱ ለትውልድ እንዳይተላለፍ )እናውጣ ተብሎ ሌላ ጀበና ተገዝቶ ይቀየራል።ካልሆነ ለወደፊቱ መጥፎ ክስተቶች ይከሰትብሀል የሚል አመለካከት አለ።ምንም ነገር ይጥፋ ተመሳሳይ ሂደቶች ይኬዳል።እንዲሁም የሆነ አካባቢ ተመሳሳይ ችግሮች በተደጋጋሚ ሚከሰት ከሆነ "(በርቸ ንስድድነ)ወይም ከዚህ በፊት የተሰራ መጥፎ ነገር አለ እሱን እናጥራ" በሚል ባህላዊ አካሄድ ወግ አዋቂ ብለው ወደ ሚያምኑት ጠንቋይ ቤት በመሄድ ጉዳዩን ምን እንደሆነ ጠንቋዩን ጠይቀው የሚፈፅሙት የሽርክ ተግባር የተቀላቀለበት መጥፎ ባህላዊ ልምድ ነው።

የትኛውንም የተውሂድ አስተማሪ ግንባር ቀደም ትኩረት ከሚሰጣቸው እርሶች ውስጥ አንደኛው አድርጎ የሚያስተምረውን ጉዳይ ወረዳው ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና ሽማግሌዎች ዘንድ እውቅና ለማግኘት ይህን የተውሂድ እርዕስ ገደል መክተት ክፉኛ አሳዛኝ ክስተት ያለፈበት ታሪክ አስመዝግበሀል።

ሙስሊሞች የሚያምኑት:-
1/ነገራቶች የሚከሰቱት በአላህ ውሳኔ ነው
يؤمنون بقضاء الله وقدره
በአላህ ውሳኔ ማመን ከኢማን አርካኖች ውስጥ አንዱ መሆኑና በሱ የካደ ከኢስላም እንደሚወጣ እናምናለን።ስለዚህ የሆነ ጊዜ ላይ የሆነ አካባቢ  ችግር ቢፈጠር ቀድሞ የነበሩ ሰዎች በሰረት ጥፋት ነው አንልም።እኛ የሰራነውንም ለትውልድ በርቸ ይቀመጣል የሚል እምነት የለንም።

2/ሌሎች በሰሩት ያልሰሩትን አይጠየቁም።

مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا

የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡

3/ጥፋት ለትውልድ እንዳይቀመጥ የሚለው አባባል በራሱ የተሳሳተ ሆኖ እያለ ጥፋት ማረሚያ መንገድ የተስተካከለ መሆን አለበት።ጥፋቱ ወይም ወንጀሉ በሰውየውና በጌታው መካከል ከሆነ መስፈርቶቹ አሟልቶ ወደ አላህ መመለስ ነው ያለበት።ተጨማሪ የሰው ሐቅ ካለበት ሀቁን መመለስ ወይም ይቅር ማስባል አለበት።የዚህ ሁሉ ግንባር ቀደሙ መስፈር ደግሞ እስልምና ነው።ያለ እስልምና የትኛውንም አይነት ተውበት ሊገኝ አይችልም።

ኩፍር፣ሽርክ፣ቢዳዓ፣ከባባድ ወንጀሎች በተስፋፋበት ሀገር ውስጥ እንዲህ አይነት የአላዋቂ ቀልድ እየቀለዱ ወደ ዲን ማላከክ አግባብ አይደለም።ራስህንም ሙፍቲ አድርጎ መሳል ተገቢ አይደለም።የዚህ ሁሉ እህቶቻችን እንባ ባልታበሰበት ምኑን ነው ለትውልድ መጥፎ ነገር አናስቀምጥ በሚል መርህ ሰሩ የሚባለው?አሏህን በበደል አይነቶች ሁሉ እየታመፀ (በርቸ ንስድድነ)በሚል መርህ ሌላ ሽርክ በሚሰራበት ተጨማሪ "ምንም ከሸሪዓ ጋር የሚጋጭ የለውም" ብለህ ምስክርነት ትሰጣለህን?ይህ ካላደረግን ትውልድ ላይ ለወደፊቱ የሚቀመጥና የሚፈጠር ችግር ይኖራል እያሉህ እኮ ነው አልገባህም?

      እንደ ሰሃቦች አባት በደል የሰራ አለ እንዴ?የዒክሪማህ رضي الله عنه አባት እኮ አቡ ጀህል ነው።የኻሊድ رضي الله عنه አባት እኮ ወሊድ ኢን ሙጊራህ ነው።የሰፍዋን رضي الله عنه አባት እኮ ኡመየተ ኢብኑ ኸለፍ ነው።,,,,,,,,,,እነዚህ ሰዎች ማለት ነብያችንን صلى الله عليه وسلم በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ያደረጉ። ሲሰገዱ የእንግዴ ልጅ የደፉ፣መልእክታቸውን እንዳያደርሱ የከለኩ፣ከሀገር ያባረሩዋቸው፣ተከትለውም በመሄድ የተዋጉዋቸው፣የፈነከትዋቸው፣ያ ሁሉ ሰሃባን የገደሉ አረመኔዎች ናቸው።

ይህ ሁሉ ወደር የሌለው የአባቶች ክፋት እንቁ በሆኑ ሰሃቦች ላይ የፈጠረው ችግር አለን?።ወይስ መጥፎን ነገር ለልጆቻችን እንዳይተርፍ ብለው ያደረጉት ባህለዊ ሸንጎ ነበራቸው?በርቸ እያልክ ከባህላዊ እና ከሽርክ አመለካከት ያልተላቀቁ ሰዎች የሚያዜሙት የሽርክ ዜማ አብረኽ ባትዘምር የተሻለ ነው።

"የእርቅ ሂደቱ ራሱ ከሸሪዓ ጋር አይጋጭም" የምትለው።ኒቃብ እንዳይለበስ መወሰኑን ነው፣ወይስ የቂጫና የጉርዳ (ቂጫ=የጉራጌ ሽማግሌዎች መተዳደሪያ ሲሆን ጉርዳ ማለት ደግሞ ባህላዊ የቃልና የመሀላ ሂደት ነው።) ሂደቱ ነው?
ይህ የተሳሳተ ብይንህን ወደ ጎን ተወውና ዳኝነት ከሸሪዓ አይጋጭም ለመባል በሸሪዓ መዳኘት ይፈልጋል።ከሸሪዓ ውጪ ያሉ ፍርዶች ወደን ተቀብለን ፣ከሸሪዓ አስበልጠንና አማራጭ እያለን ወደ ሌሎች የምንዳኝ ከሆን ብይኑ ምን እንደሆነ ጠፍቶህ አይመስለኝም።ጥቂት ግለሰቦች ዘንድ ለመወደድ መሰረታዊ የዲን ነጥቦችን መናድ እጅጉን የሚያሳዝን ውርድት ነው።


ይህን በተመለከተ ለህዝበ ሙስሊሙ ማስተላለፍ ምፈልገው መልእክት:-በርቸ የሚባል ነገር የለም።ስህተት የሰራ መስፈርቱን አሟልቶ ተውበት ካደረገ አላህ ወንጀሉን ይምረዋል።ድንገት በህይወት ዘመናችን የሚከሰቱ አደጋዎች ካሉ አንድም በአላህ ውሳኔ ነው ሌላም እጃችን በሰራው መጥፎ ስራና ወንጀል  እንጂ ሌላ አይደለም።
Forwarded from ŘŁŘ¨Ůˆ ماهر
ኡስታዝ ባህሩ ተካና  የጉንችሬ እርቅ 05
_
=>
በህሩ ተካ    " የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የዛሬው ቀን ላይ ደርሶ ይህን ታሪካዊ ሰላም ሲያስመዘግብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀንና ለሊት በእግር ሩቅ ቦታ በመጓዝ  ከገጠር እስከ ከተማ ከሚመለከተው አካል ጋር በመገናኘትና ነገሩን ከስር መሰረቱ በመረዳት ቂምና በቀል እንዳይኖር በሁሉም ልብ ውስጥ የተከሰተው ነገር  አስተማሪ ሆኖ ያለፈ ክስተት ሆኖ እንዲቀር በማድረግ ነው ። "አለ

መልስ=>ጉዳዩ ከላይ እንዳየነው ሆኖ እያለ እነዚህን ሰዎች በዚህ ልክ እያደነቅክ ወረዳው ላይ ተውሂድን ለማንገስና ሸርክን ለማጥፋት ብቸኛው የህይወት ግባቸው አድርገው የሚተጉ ዱዓቶችን በአንዳንድ ቅርንጫፋዊ ነጥቦች ካንተ ጋር ስላልተስማሙ ብቻ  በዚህ ልክ ለመጎንተልና የዳዕዋ ጠላቶች በሚል ለመወረፍ ብእርህን ስታሾል ማየት እጅጉን ይገርማል።


  á‰ áˆ…ሊ ተካ=>"  ይህ የሀገር ሽማግሌ የሰላም ውጤት ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በአላህ እርዳታ የአንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው ወንድማችን ልፋት ውጤት ነው ። ይህ ወንድማችን ሁኔታው ተከስቶ በሁለቱም ጎራ ሁሉም ስሜታዊ ሆኖ ነገሩ ወደ ሀይማኖት ግጭት ሊቀየር እየሄደ ባለበት ወቅት በዋነኝነት ሙስሌሞቹን በማረጋጋት በአስተዋይነታቸውና ሚዛናዊነታቸው የሚያውቃቸውን ክርስቲያን የከተማ ነዋሪ የእነሞር ተወላጆችን  በየግል የሁኔታው አደገኝነትና የሚያስከትለው ውጤት ምን ሊሆን እነደሚችል እንዲያዩትና እነርሱ ባሉበት ዘመን እንዲህ አይነት ክስተት ተክስቶ ለትውልድ የተበላሸ ታሪክ መተው እንደሌለበት በመንገር ነበር ። እነዚህ አስተዋይና ሚዛናዊ የሆኑ ክርስቲያን የእነሞር ተወላጆች ከእነርሱ በፖዚሽንም ሆነ በትምህርት ደረጃ የሚያንሰው ወንድማቸው ያቀረበላቸውን ሀሳብ በቅል ልቦና በመቀበል ወደ ተግባራዊነቱ መገባት እንዳለበት ወሰኑ ። "አለ።

መልስ=>እንዲህ አይነት ፁሁፍ በመፃፍ አንዱ ወንድማችን ብቻው ባታሳቅቀው ጥሩ ነው።ሌሎችም የሚታዘቡት እውነታ የብዙዎች ልፋት ወደ አንድ ግለሰብ ስትጠቀልለው እሱም ወዶ የተቀበለውና ብቸኛ የድል ባለቤትነትን ለመጎናፀፍ ያደረገው ጥረት አታስመስልበት።ሞኝ ባያፍር የሞኝ ባለቤት ያፍር እንደተባለው።

ሌላው ሰላም ወዳዱ የመላው ሙስሊም ሰፊ ጥረትና ውጣ ውረድ ለአንድ ግለሰብ ብቻ በስጦታ መልክ ማቅረብ  ምን ያህል ለውለታ ስግብግብ መሆንህን ያሳያል።

ደግሞም አስተዋይና ሚዛናዊ እያልክ በፍትሃዊነት ጥግ እየገለፅካቸው ያሉ ግለሰቦች እውነትህ ነው? በልበ ሙሉእነት ትገልፀዋለህን?(ሙመይዓነት)አይሆንብህምን?
06
     በህሩ ተካ =>"የጀመሩት ተገናኝቶ በጋራ በመነጋገር ሲሆን ቀጥሎ ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም ተጨማሪ የከተማ ነዋሪ ጋር የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ውይይት በማድረግ ሲሆን ውይይት ካደረጉ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሀገር ሽማግሌ ማድረስ እንዳለባቸውና ይህንኑ ሀሳብ ለደቡብ ክልል ፕሬዝዳት አቶ እርስቱ ይርዳው አቅርበው እሱም ባለበት በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ላይ ከህብረተሰቡና ሀገር ሽማግሌ ጋር ውይይት እንዲደረግ ወሰኑ ። በዚሁ መንገድ ቀጥለው ጉዳዩ ወደ ፕሬዝዳቱ አቀረቡት ። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ እርስቱ ይርዳው በጣም በሚገርም ሁኔታ ሀሳቡን ተቀብሎ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ አመቻቸ !!!!! ። "አለ።

መልስ=>ወላሂ ሳቄን ነው የመጣው أستغفرالله  "በጣም በሚገር ሁኔታ አላለም"?ደግነቱ እርስቱ ማን አንደሆነ ድፍን የደ/ብ/ብ/ህ/ጠንቅቀው ስለሚያውቁት እነሱ ቢመሰክሩ የተሻለ ነው።ለማንኛውንም በትውልድ ቀዬው ያ ሁሉ ትርምስ ሲፈጠር የችግሩ ተዋናይ ሆኖ ለዚህ ሁሉ ውድመትና በደል ማእከል በሆነችበት ወረዳ እርስቱን ለማድነቅ ምንም አይነት ሞራል አይኖረኝም።እውነታው ደግሞ የገፈቱ ቀማሽ የሆነው ህዝብ ይፍረድ።



 á‰ áˆ…ሊ ተካ=>"   ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ጉንችሬ ከተማ ላይ በጣም አሳዛኝ ነገር ተከሰተ ። ብዙ ንብረት ወደመ ብዙ ሰውም ተጎዳ ። ምናልባትም በተያዘው የሰላም ሂደት የሚከስሩ አካላት ምክንያት ሆነው ሊሆን ይችላል ። ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰው ታሰረ ። ወረዳው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሾር ሆነ ። "አለ

መልስ=>ጥሩ ጥንቅር ነው።ሪፖርተራችን ከፉሪ

    በህሩ ተካ=>"ይሁን እንጂ እነዚያ ሰላም ወዳድ የሆኑ ብርቅዩ የእነሞር ተወላጆችም ሆነ የክልሉ ፕሬዝዳንት ነገሩን ያሰቡበት ከማድረስ አላገዳቸውም ። እዚያ ወንድሞች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተነጋግረው ጉንችሬ ላይ ቀጠሮ ተያዘ ። በተባለው መልኩ የክልሉ ፕሬዝዳንት ወደ ጉንችሬ በማቅናት ለህዝብና ለሀገር ያለውን አክብሮት በተግባር አሳየ ። የህዝቡን ሀሳብ ከሀገር ሽማግሌው ጋር አዳምጦ የሀገር ሽማግሌው የጉዳዩን ሀላፊነት ወስዶ እንዲያስተካክል ሀላፊነት በመስጠት ለተግባራዊነቱ ከጎን እንደሚቆም ገለፀ ።  "አለ።

መልስ=>ፁሁፉ ስለረዘመ እየሰለቸኝ መጣሁ።ግን ወገኔ "ብርቅዬ "ማለት ገብቶሀል?ስሙን ማይጠቀሰው ወንድሙና ሌሎች ክርስቲያን ሰላም ወዳዶቹ ብቻ ነው"።

የኛ ብርቂዬዎች ግን ትምርታችን ከሂጃባችን አይበልጥብንም ያሉ እንቁ እህቶቻችን፣እስልምናዬ ተነክቶ ተኝቼ አላድርም፣ሱቄንም ከፍቼ አነግድም።ያሉ ጀግኖቻችን ናቸው።እድሜያቸውና አባወራነታቸውን ከልጆቼ ጎን ከመቆም አያግደኝም ብለው የተንገላቱና የታሰሩ ጀግና አባቶቻችን።መኖር ተከልክለው የተሰደዱ አንበሶቻችን ለዲናቸው የተንገበገቡ በሀገሪትዋና ከሀገር ውጪ ያሉ የእኖር ልጆችና ኢትዮጵያውን ለኛ ብርቅዬ ናቸው።


    =>በህሩ ተካ "እነዚያ ወንድሞች በዚህ መልኩ ለሀገር ሽማግሌ ጉዳዩን አስረክበው ከጎን በመሆን እስከ ፍፃሜው አብረው ሄዱ ። በዚህም የሀገር ሽማግሌው ከቅድመ አያቶቻቸው በወረሱት " መጥፎ ነገር ለትውልድ እንዳይተላለፍ እናጥፋው " በሚለው መርህ መሰረት ብዙ ዋጋ ከፍለው ችግሩ ከስር መሰረቱ እንዲቀረፍ በማድረግ ሰላም አሰፈኑ ። "አለ

መልስ=>የበርቸ ጉዳይ ደገመው።"ከስር መሰረቱ እንዲቀረፍ በማድረግ ሰላም አሰፈኑ።"እውነት ከስር መሰረቱ ነው።ይህ አንባቢና ተጨባጩ የእርቅ ሂደት የሚያውቁ ሰዎች ይፍረዱት።እኛ ግን ሙስሊሞች ሂጃባቸውን ለብሰው እስካልተማሩ ሁሌም ልባችን እንደቆሰለ ነው።የደም እንባ ያፈሳል።አንተ ተደስተህ ሊሆን ይችላል።


     በህሩ ተካ=>"በዚህም መሰረት ንብረታቸው ለተጎዳ ተወላጆች ሁሉም ማህበረሰብ የሚችለውን በማድረግ እንዲዶጉም , ተጎጂዎችም ምርቃት ተደርጎላቸው የተሰጣቸውን ተቀብለው አውፍ እንዲሉ , ከሁለቱም በኩል በዳዮች በባህሉ መሰረት በድለናል አውፍ በሉን ብለው እንዲቀርቡ  በማድረግና ለበደላቸው የሚመጥን ባይሆንም ሽማግሌም ሆነ ተበዳይ ሙሉ በሙሉ አውፍ እንዲላቸው የተወሰነ የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ጨርሰው የታሰሩት እንዲፈቱና ሁሉም ተስማምተው እንዲማሩ በማድረግ እርቀ ሰላም እንዲወርድ አደረጉ ። ይህን ስምምነት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ይዘው በመሄድ የሰሩትን ሾል በማስረዳት የታሰሩት እንዲፈቱላቸውና ለደረሱበት የሰላም ስምምነት እውቅና እንዲሰጥላቸው ጠየቁ ።
    ፍትህ ሚኒስቴርም የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የሰራውን ሾል ትልቅ ቦታ በመስጠት ባጭር ጊዜ በአካል እነሞር ድረስ ባለሞያ በመላክ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በሟሟላት እስረኞቹ እንዲፈቱና የጉራጌ የሀገር ሽማግሌ የሰራውን ሾል እውቅና ሰጥቶ ተፈፃሚ እንዲሆን አደረገ ። !!!!!"አለ


መልስ=>እሺ በቃ ጥሩ ጥንቅር ነው።ሪፖርተራችን ከፉሪ
አላሁ አክበር አላሁ አክበር አልሀምዱሊላህ ከጉንችሬ ከ12ኛ ክፍል ካፊር ተማሪዎች እሰከ አሁን ባለን መረጃ ከተፈተኑቱ ምንም ተማሪ ያለፈ የለም‼

እስከ አሁን ከፍተኛ ውጤት 264 ነው።
የጉንችሬ ሰቃዮች‼
=============
✍ እነዚህ የሞኣ አንበሳ ዩኒፎርም እያሠሩ በመልበስና ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ይሄዱ ይመስል ነጠላ ለብሰው ት/ቤት በመመላለስ ኒቃብስቶች እንዳይማሩ ሴራ በመጠንሰስ እህቶቻችንን ከትምህርት ገበታቸው አፈናቀሉ እንጂ ቀድሞውኑ እየተማሩ አልነበረም።

ለመሆኑ ፈተናው ከ25 ነበር እንደ?
ሰው እንደት ህይዎት እያለው ማትስን ከ100 ዜሮና አንድ ያመጣል?
ምርጫ የሌለው workout ፈተና ነበር እንደ?

እነዚህ ልጆች በዚህ የማትስ ዕውቀታቸው የበፊቱን የሽንኩርት ዋጋ ከአሁኑ ላይ ቀንሱና ውጤቱን ንገሩኝ ብንላቸው ካልኩለስ የሚሆንባቸው ይመስለኛል¡ አሰዳቢ!

እኔን ዓይኔን ጨፍኜ ምንም ሳልሠራ ከ A-D ካሉት ምርጫዎች መካከል ለሁሉም ጥያቄ አንዱን ፊደል ብቻ መርጨ ብሞላ በትንሹ ከ10 በላይ አመጣለሁ¡

ምድረ ደነዝ! ምቀኝነትና ድግምት ብቻ እንጂ ዕውቀት'ማ ባዶ ናቸው።

ኢንሻ አላህ! የጉንችሬዋ እንቁ ግን ተምራ አንድ ቀን ታኮራናለች።

||
t.me/MuradTadesse
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙአለይኩም የእኖር_ሙስሊም ሚዲያ አባላት አብዛኞቻን በእኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ መስተዳደር ውስጥ እየተገነባ ያለው የአል-አቅሳ መስጂድ ግንባታን በተመለከተ ብዙዎቻችን ችላ ብለነዋል። ከሰሞኑ ከወገናችን መላኩ ቢረዳ/አርቲስት ከአካባቢ ተወላጅነት በመነጨ ሞራል ስለዚህ መስጂድ መልእክቱን አስተላልፏል። ከመልእክቱም እንደሰማችሁት ለሙስሊሙ አንገት በሚሰብር ሁኔታ ግንባታው ከተጀመረ 3 አመታትን አስቆጥሮዋል!! እኛስ ወዴት ነው ያለነው!? ለመሆኑ ለዚህ መስጂድ ግንባታ የበኩላችንን አስተዋፆ አርገን ይሆን?! ካላደረግንም አሁኑኑ ለአኺራ ሚተርፍን ሰደቀተል ጃሪያ ተካፋዮች እንሁን እያሉ መልዕክቱን ያስተላልፋሉ የመስጂዱ ኮሚቴዎች።

የመስጂዱ ባንክ አካውንቶች
ዳሽንባንክ =2960044778611
ንግድ ባንክ👉  1000363997825
አቢሲኒያ ባንክ   👉 46766008
የጉንችሬ አል-አቅቅሳ መስጂድና መድረሳ

የመስጂዱን ኮሚቴዎች ለማግኘት
ሳኒ በድር +251912241897
አቡበከር ብዛ +251923575655
ኡሥማን ኡመር +251911046347
@voice_of_enor_Muslims
ሰላሙአለይኩም እቺ በፎቶ እምትመለከቷት እናታችን የ6ልጆች እናት ስትሆን በጅማ ዞን አሰንዳቦ በሚባል አካባቢ የምትገኝ ሲሆን አካባቢው ላይ ያሉ ወንድሞች ምን ገጥሞሽ ነው ኬትስ ነው የመጣሽው የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡላት ከእኖር ወረዳ ጠረደ ከሚባል አካባቢ የሄደች መሆኑዋን ተናግራቸዋለች። እናታችን የአዕምሮ ህመም እንዳለባትም ጥርጣሬያቸውን ነግረውናል ከባለ ቤታቸውም ተጣልተው እንደወጡ የገለፁ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑልንም ብለዋል። በመሆኑም የእኖር ሙስሊም ሚዲያ አባላት እኚህ እናት ከቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እንረባረብ ጠረደ አካባቢ ያላችሁ ልጆች ምስሉን በማረጋገጥ ደውሉልን🙏
+251923600505
እኛ የዚያ ከረሃብ የተነሳ ሆዳቸው ላይ ድንጋይ
ያሰሩት😥 ነብይ ህዝቦች ነን...


የዛ የመልካም ስነምግባር ቁንጮ መልክተኛ  ህዝቦች !
የዚያ ህዝቦቹ ናፍቀውት  ያነባው  ረሱል ህዝቦች
ያ በመለየቱ የቴምር ዛፍ የተንሰቀሰቀለት ታላቅ ሰው ፣ አይደለም የሰው ደም ዉሃ እንኳን ያለ አግባብ ሲፈስ የሚቆጡት ነቢይ ህዝቦች ነን...ተወዳጅ በሆኑት ነብያች ሰ.ዐ.ወ ላይ በሚቀጥፉት ላይ አላህ ቁጣውን ያውርድ🤲

የልብ እርጋታን ምታገኙበት ጁሙዓ ይሁንላቹ ፣ በዱዓ እንተዋወስ ።❤️🖤
وَقَالَ الْمَلِكُ ائْتُونِي بِهِ أَسْتَخْلِصْهُ لِنَفْسِي ۖ فَلَمَّا كَلَّمَهُ قَالَ إِنَّكَ الْيَوْمَ لَدَيْنَا مَكِينٌ أَمِينٌ
ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ ግለኛ አደርገዋለሁና» አለ፡፡ ባናገረውም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟል ታማኝ ነህ» አለው፡፡

قَالَ اجْعَلْنِي عَلَىٰ خَزَائِنِ الْأَرْضِ ۖ إِنِّي حَفِيظٌ عَلِيمٌ
«በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ (ሹም) አድርገኝ፡፡ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና» አለ፡፡

وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي الْأَرْضِ يَتَبَوَّأُ مِنْهَا حَيْثُ يَشَاءُ ۚ نُصِيبُ بِرَحْمَتِنَا مَن نَّشَاءُ ۖ وَلَا نُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ
እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው፡፡ በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን፡፡ የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም፡፡
ሱረቱ ዩሱፍ 54-56

ወህኒ ቤት ውስጥ ከዩሱፍ ጋር  ሁለት ወጣቶች እንደነበሩ ታስታውሳለህ አይደል? ስለዩሱፍ የልብ ንፅህናና ፈሪሃ አላህነት ጥያቄ የለብንም። ብርሃናማ ሰው ነበር። ግን ደግሞ እርሱ በእስሩ ለተወሰኑ ዓመታት እንዲቆይ ተደርጎ ሁለቱ ወጣቶች ነፃ ተባሉ። የመጀመሪያው  አገልጋይ ለመሆን ወጣ ሌላኛው ደግሞ ለሞት ፍርድ ከእስር ተለቀቀ። ዩሱፍ ደግሞ ከረጅም ጊዜ በኋላ የግብፅ ንጉስ ለመሆን ከግድግዳው መሀል ተጠራ።

ምን ልልህ ነው? "ስጦታውን ሊያበዛልህ ሲፈልግ አንዳንዴ መንገዱ ሊርቅህ፣ እግርህም ሊጎተት ይችላል። ጌታህ ልክ እንደዩሱፍ ዓለምህን እየሰራው ነው…  አንተ ግን ጥበቡ አልደረሰህም።" እያልኩህ ነው።


اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
በማያልቀው የጌታዬ የሁን ቃሉ መሻታችን የሚሞላበት ፣ የተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን የታመመ መዳንን የሞቱት ሸሂድነትን á‹¨áˆšá‹ˆáˆá‰á‰ á‰ľ á‰ áˆ°áˆˆá‹‹á‰ľ በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ የታጀበ ምርጥየ ጁምዓ ይሁንልን🖤🖤🖤
« በነብዩ ዘመን ላይ ተገኝቶ እሳቸውን መከተል ያልቻለ አለ። ታላቁን የፍጥረታት እንቁን ተመልክቶ በመንገዳቸው ያልተራመደ አለ። እኛስ? አላየናቸውም ግን እንናፍቃቸዋለን። በዘመናቸው አልተገኘንም ግን እንከተላቸዋለን። አንድም ቀን ጋሻ ሆነ መከታ አልሆንናቸውም ግና ብንችል ነፍሳችንን ብንሰዋ ደስተኞች ነን።
ይህ ሁሉ በእኔ፣ ባንተ ወይም ባንቺ የተቻለ ይመስላችኋል? በፍፁም! አላህ ቢወደን ነው። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ በልባችን ነብዩን  እንድንወድ፣ እንድንናፍቅ ስላስቻለን ብቻ ሌላ ነገር ከመጠየቅ ሀፍረት ሊይዘን በተገባ ነበር። ግና ሰዎች ነን።
ይህንን የአላህ ጸጋ አታቅልሉት በቃላት የማይገለፅ ረቂቅ እና ፍፁም ፍቅር የሆነ በረከት ነውና። መቼም አላህ ሲወድ ማስወደድን ያውቃል። እናሳ ለዚህ ጸጋው አልሀምዱሊላህ አለማለት ንፉግነት አይደለም ወይ? አልሀምዱሊላህ!
አላህ የሚወደውን የሚወድ ማክበርና ማላቅ ከእሱ በቀር አንድም የሚችል የለም። ለዚህ ምስክሩ በሰለዋት የማይዘናጉ ባሮቹ ምስክር ናቸው።
አላህ እሳቸውን መውደድና መናፈቅን አድሎናል። በትክክለኛው በሳቸው መንገድ ላይ የምንፀና ያድርገን!
ለወደደው ባርያው ሙሃባዎን ዘርቶ
እንዳሻው ያደምቃል
መቼም አላህ ሲወድ ማስወደድን ያውቃል። »
[አብዱልሀኪም ሰፋ]

للهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ለአለማት እዝነት ሆነው በተላኩት የቃሲም አባት💚 ላይ አብዝተን ሰለዋት ምናወርድበት በሱናቸው ምንበረታበት
በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች የታጀበ ጁምዐን ተመኘሁ💚
እሁድ → እግሮች ሁሉ ወደ ጉንችሬ ያመራሉ‼
===============================
✍ በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ የካቲት 3, 2016 E.C. ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የጉራጌ ዞኗ ጉንችሬ ከተማ ደምቃ ትውላለች። ላለፉት አመታት በኩፋሩም በጙላቱም ተፅዕኖ ስር ወድቃ የነበረችው ውቢቷ ጉንችሬ፤ ትክክለኛው የዳዕዋ ጮራ ዳግም ይፈነጥቅባታል። በዕለቱ ከአዲስ አበባ በሚሄዱ ታላላቅ ዳዒዎች ከሚዳሰሱ የሙሐደራ ርዕሶች መካከል፦

①) የቢድዓህ አደጋዎች፣
②) የሲሕር መዘዞቹ እና መፍትሄው፣
③) ተውሒድ የነብያት ጥሪ፣
④) በሱንና ላይ መፅናት… እና ሌሎችም ወሳኝ ወሳኝ ርዕሶች ይዳሰሳሉ።



√ የእለቱ ተጋባዥ ዱዐቶች፦

ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ
ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ
ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
ዶክተር ዐብዱ ኸይሬ
ኡስታዝ ዐብዱል ካፊ ሙሐመድ
ኡስታዝ ዐብዱ-ር'ረሕማን ዐባስ


√ የፕሮግራሙ ቦታ፦ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ ከሃይስኩል ጀርባ መነኻሪያ አካባቢ ሰላም መስጅድ ውስጥ


ይህ አጓጊ የሆነ ፕሮግራም ላይ ቤተሰብዎንና ወዳጅ ዘመድዎን በመያዝ በጊዜ ይገኙ።

√ ለሴት እህቶቻችን በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።

እናንተም በዚህ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በክብር የተጋበዛችሁ ስለሆነ፤ ከወዲሁ ቀጠሯችሁን በማስተካከል በሰዓቱ ተገኙ።


✔ ለጉዞው ቅልጥፍና ይመች ዘንድ ለመሄድ ያሰባችሁ ሰዎች ወደ እነዚህ የዳዕዋው አስተባባሪዎች ጋር በመደወል እስከ ነገ ጁሙዓህ ድረስ እንድታሳውቁ አሳስበዋል።

🔹ቤተል፣ ዓለም ባንክ እና ዙሪያው አስተባባሪዎች

ዐብዱልጀሊል ፋሪስ  0937775792
ዐብዱልሀዲ ሙሐመድ  0947540222
አሕመድኑር አይታ  0911106306

🔹ኮካ, አብነት መርካቶ
ሬድዋን  0909113696
መኑር ዲኖ  0911082208
ዐብዱሰላም ኸይሩ 0913842798
ኢብራሂም   0921776328

🔹ፉሪ ኬንተሪ
ሙባረክ ኑሩ  0911921980
ዐብዱልጀባር  0911895313
ሙሐመድ ዑመር 0919411289
ኢብራሂም ኸሊል 0912420191
አብራሂም ዐረብ 0911830951

🔹ወለቴ
መኑር ዐባስ 0920969361
ሬድዋን ዑመር 0919225578

🔹ቦሌ ገርጂ
ሰኢድ ሙሐመድ  0913786613
ሱፊያን ለማ  0922976870
ዐብዱልጘፋር  0910122537

🔹አጠና ተራ
ዐብዱልፈታሕ በህሩ 0961065933
ከማል አወል  0919225568



♠
የላ! ጉዞ ወደ ጉንችሬ!
||
t.me/MuradTadesse
#በ_8ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት ኢማሙ ማሊክ ረህመቱላህ ዐለይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ኪታባቸውን "ሙወጠእ"الموطأ አበርክተው ነበር። ይህ ኪታብ በኢስላሚክ ኢምፓየሩ ተሰራጭቶ  ደረሶች እየቀሩት ሙፍቲዎች እየጠቀሱት ዳኞች እየተመረኮዙበት በጣም ታዋቂነቱ ናኘ። ይህንን ያዩ የዛ ዘመን ሸይኾች ከእውቅናው ለመቋደስ አስበው ኪታብ እየጻፉ ርእሱን "ሙወጠእ" ይሉት ጀመር (plagiarism)። እናም በርካታ  ሙወጠኦች ታትመው ወጡ። ይህንን የታዘበው ልጃቸው አባቱ ጋር ሄዶ "የእርሶን ኪታብ እያስመሰሉ ብዙ ሰዎች እያሳተሙ ነው ምን ይሻላል? አላቸው። እሳቸውም አብሽር አታስብ ለአላህ ተብሎ የተሰራው ብቻ ምድር ላይ ይቀራል فقال ما كان لله يبقى  አሉት።
ታድያ ዛሬ ላይ በዚህ ስም የሚታወቅ ኪታብ የእርሳቸው ብቻ ሆኖ ቀሪው ሁሉ ጠፍቷል።
ስራንም ሆነ ንግግር፣ ፍቅርንም  ይሁን ወቀሳ ለአላህ ብለን ካደረግነው ግቡን ይመታል። ከዛ ውጭ ለእውቅና ለገጽታ ግንባታ ቀብድ ከሆነ በዱንያም በአኼራም ያዋርደናል።


اللهم صل وسلم وزد وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وعلى آله وصحبه أجمعين
ስራችን ከይሉኝታ እና ከይስሙላ የፀዳ ኢኽላስ ላይ የፀና የሚሆንበትና ከንትርኮችና ከመጠላለፍ ወጥተን በጋራ ዲናችንን የምንረዳበት: ለአለማት እዝነት ሆነው በተላኩት የቃሲም አባት ላይ አብዝተን ሰለዋት ምናወርድበት በሱናቸው ምንበረታበት በሱራህ አልካህፍ በዱዓእ በተሳኩ ምኞቶች የታጀበ ምርጥየ ጁምዐን ተመኘሁ💚

™𝑎𝑏𝑑..
Forwarded from áˆ˜áˆ­áŠ¨á‹ ኢብኑ ቃሲም የቁርአንና የተለያዩ ኪታቦች መቅሪያ እና ኢስላማዊ ተርቢያ ማእከል
አሰላሙ አለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካትሁ
የተከበራችሁ የዚህ ቻናል አባላት ሁላችሁም ባላችሁበት ሰላማችሁ አላህ ያብዛው
ይህ ቻናል የተከፈተበት አላማ ከዚህ በፊት online ላይ በኢሞ ግሩፓችን የጀመርነው የቁርአን ቲላዋ ሒፍዝ እና አዲስ ለቁርአን ጀማሪዎች ቃኢዳ አኑራኒያ እንደዚሁም ለጀማሪዎች የሚሆኑ የአጫጭር ኪታቦች ደርስ ፕሮግራም ማሕደሩ በማስፋት ለሑሉም ተደራሽ ለማድረግ ነዉ ስለዚሕ ቁርአን ያልጀመረ በቁርአን ፕሮግራማችን ላይ ተገኝቶ መጀመርና እንደዚሁ ኪታብ መጀመር የሚፈልግ በኪታብ ፕሮግራማችን ላይ ተገኝቶ መሣተፍ ይችላል