Victoria St. Gabriel Church የቪክቶሪያ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
8 subscribers
1 photo
3 links
"መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ" ዕብ ፲፥ ፳፭ ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቪክቶሪያ መንበረ ብርሃን ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ገጽ ነው።
Download Telegram
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ኢንኅድግ ማኅበረነ - መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።" ዕብ ፲፥ ፳፭
“Not forsaking the assembling of ourselves together, as the manner of some is; but exhorting one another: and so much the more, as ye see the day approaching” Heb 10: 25

✥✥✥ይህ የዳግማዊ ቁልቢ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለማኅበረ ምዕመናኑ መልዕከቷን (የእግዚአብሔርን ቃል) የምታስተላልፍበት ገጽ ነው።✥✥✥

“ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሓነጻ ወልድ ለዛቲ ቤት ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ፤ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ"
“ይህችን ቤት አብ አስቀድሞ መሠረታት፣ ወልድ ገንባት፣ መንፈስ ቅዱስ ፈጸማት። ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ገስግሱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ አለና” ቅዱስ ያሬድ

“The Father Initially Established this Church, The Son Built It, The Holy Spirit Completed It. Come to her (the church), for the power of God is upon her” St. Yared

✣✣“አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፤ በፍጹም ኃይልህ ውደደው። የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። የምትመስላት ሁለተኛይቱ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል ናት” ማቴ ፳፪፥፴፯-፴፰
“Love the Lord your God with all your heart and with all your soul and with all your mind. This is the first commandment. The second is like it: Love your neighbor as yourself.” Mat. 22:37- 38
Channel name was changed to «የቪክቶሪያ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን»
Channel name was changed to «የቪክቶሪያ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን Victoria St. Gabriel Church»
Channel name was changed to «Victoria St. Gabriel Church የቪክቶሪያ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን»
ከኮሮና ቫይረስ እንዴት እንጠበቅ? በእጅ መታጠብ ብቻ? ያንብቡት እምነታችን ቦታው የት እንደሆነ ይረዳሉ እንዴት ለዚህ ወረርሽኝም እንደሚረዳ ይገነዘባሉ።

#ኮሮና_ቫይረስ #ኮሮናቫይረስ #ኮቪድ19 #COVID2019 #eotc #theorthodoxway #coronavirus https://stgabrieleotcvictoria.org/health/2020/03/18/ከኮሮና-ቫይረስ-እንዴት-እንጠበቅ/
ይኽ ያዝነው ሳምንት የ፴፰ ዓመት ሕመምተኛ፣ በቀቢፀ ተስፋ የሚኖር በሽተኛ፣ ደዌ የጸናበት የአልጋ ቁራኛ… ወደ ሆነው መፃጉዕ ጌታችን ቀርቦ "ልትድን ትወዳለህን?" እንዳለው ዛሬ እኛ ግን ስለደረሰብን ጭንቅ ወደጌታችን ቀርበን "ልታድነኝ ትወዳለህን?" ብቻ ሳይሆ እንደ ልበ አምላክ ቅዱስ ነቢይና ንጉሥ ዳዊት "አቤቱ እኔን ታድነኝ ዘንድ ውደድ" እያልን ልንማፀን የሚገባበት ወቅት ነው!

ሙሉውን ያንብቡት #ኮሮናቫይረስ #COVID-19 👇

https://bit.ly/2IUUnA4