Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
ዛሬ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እና የጎዳና ተዳዳሪዋች የአንድነት ፓርክን ተዟዙረው ሲጎበኙ ውለዋል፡፡
መደበኛ የክፍያ ጉብኝት ከሚጀምርበት ከመጪው ሰኞ በፊት ፓርኩን እንዲጎበኙ ከተመረጡት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ በነገው ዕለትም ታዳጊ ህፃናት ፓርኩን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@UnityPark
በዛሬዉ እለት ብቻ 2500 የሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዋች ፓርኩን እንደጎበኙት ተነግሮዋል።
በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል?

•አንድነት ፓርክ በውስጡ ሦስት ዋነኛ የቱሪስት መስህቦች ይገኙበታል።

•የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ልጅ የተዳረችው በግብር አዳራሽ እንደሆነ ተነግሯል።

•እኚህ የታሪክ ቅርሶች ሦስት ጊዜ እድሳት እንደተደረገላቸው በገለፃው ወቅት መረዳት ተችሏል።
የመጀመሪያው በ1963 ዓ.ም በኃይለ ሥላሴ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደርግ 10ኛ ዓመቱን ሲያከብር፣ ሶስተኛው ደግሞ ቫርኔሮ በሚባል የኮንስትራክሽን ድርጅት ነው።

•በዚህ ሥፍራ መጀመሪያ የምናገኘው የፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን (አባ መላ) መኖሪያ ነው። አባ መላ የአጤ ሚኒሊክ የጦር ሚንስትር የነበሩ ሲሆን ይኖሩበት የነበረ ትንሽ የእንጨት ቤት ከአጤ ምኒሊክ መኖሪያ ቤት ጎን ላይ ይገኛል።

ጉብኝቱ ይቀጥላል...
@unitypark
•አጤ ሚኒሊክ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላም እንደ መኖሪያና ቢሮ አድርገው ሲጠቀሙበት ነበር። ቤቱ ፈርሶ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ በሙሉ ታድሷል።

•ወደ አጤ ሚኒሊክ ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያና ጽ/ቤት በሮች በእንጨት የተሠሩ ሲሆን በሚያምር መልኩ የአበባና የሐረግ ጌጥ የተፈለፈለበት ነው። ይህ ቤት ከሁለት ሌሎች ቦታዎች ጋር በድልድይ ይገናኛል። አንደኛው በሰሜናዊ አቅጣጫ የአጤ ምኒሊክ የፀሎት ቤትና የሥዕል ቤት ሲሆን እንቁላል ቤት በመባል ይጠራል። አንዳንዴም እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበት ነበር።

•በሌላ በኩል አጤ ምንሊክ ከጦር መኮንኖቻቸው ጋር የሚገናኙበት ክፍል ይገኛል። በወቅቱ የጦር ሚኒስትር የነበሩት ፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ እንደ ቢሮ ይጠቀሙበት ነበር።

•ሌላኛው የዘውድ ቤት ነው። ይህ ህንፃ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ነገሥታትንና ዲፕሎማቶችን የተለያዩ ሀገራት ተቀብለው ያስተናግዱበት ነበር።

•በዚህ ህንፃ ከተስተናገዱ የውጪ ሀገራት እንግዶች መካከል በ1965 ንግሥት ኤልሳቤጥ 2ኛ፣ በ1966 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ቻርልስ ደጎል እንዲሁም በ1956 የዩጎዝላቪያው ፕሬዝደንት ቲቶ ይገኙበታል።
ወደ ምናባዊ ጉብኝት እንመለሳለን አሁን ስለ ፓርኩ ግንባታ ጥቂት መረጃ ላካፍላቹ...

•ከተለያዩ ምንጮች በአምስት ቢሊዮን ብር ወጪ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (የኖቤል ተሸላሚ) የተገነባው አንድነት ፓርክ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ 1,600 ሠራተኞችና ባለሙያዎች በግንባታዉ ተሳትፈዉበታል።

•የፓርኩ ግንባታ ካስፈለጉት ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የመሬት አቀማመጥን ማስተካከል አንዱ ሲሆን ለፓርኩ 6000 ጊዜ የሚሆን በጭነት መኪናዎች ልዩ አፈር ወደ ፓርኩ አመላልሰዋል፡፡

•በተጨማሪም ፓርኩ በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ቀደምት መኪኖች መካከል አንዱ አሁንም ድረስ ሊነዳ የሚችል በዉስጡ ያካተተ ሲሆን፣የታክሲ ሾፌሮች ማህበር አባላት ባቀረቡት አስተያየት ይህ መኪና ወደ ስፍራው እንዲገባ ተደርጓል።

•አይ.ሲ.ጂን ኢንጂነሪንግ እና ALEC ኮንትራክተር ከዱባይ ኩባንያ የመሬት አቀማመጡን ሰርተዋል፡፡
ከዛሬ ጥቅምት 3 ጀምሮ አስቀድመው በኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ ቲኬት የቆረጡ 1500 ጎብኚዎች በፓርኩ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

አንድ ሰው ፓርኩን ለመጎብኘት ለመደበኛ ትኬት 200 ብር እና ለቪአይፒ ቲኬት 1000 ብር የሚከፍል ሲሆን የውጭ ዜጎች ለመደበኛ ጉብኝት 20 የአሜሪካ ዶላር የሚከፍሉ ሲሆን ለቪአይፒ መግቢያዎች ደግሞ 50 ዶላር ይከፍላሉ ፡፡

መልካም ቀን ይሁንልን።
ዘውድ ቤት

•ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም፣ የዚህን ህንፃ ምድር ቤት የአጼ ኃይለሥላሴን ባለስልጣናት አስሮ ለማሰቃየት ተጠቅመውበት እንደነበር ታሪክ ሰነዶች ያስረዳሉ።

•የፀሎት ቤቱና የሥዕል ቤቱ ባለ ሁለት ፎቅ ነው። ሁለተኛው ፎቅ ላይ ከፍ ብላ የተሠራች በመስታወት የተሸፈነች ቤት አለች፤ ይህች ቤት 'ቴሌስኮፕ' ያላት ሲሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ ማየት ታስችላለች።

•በዚች እንቁላል ቤት መገናኛው ድልድይ ጋ የመጀመሪያው ስልክ የገባበት ቤት ይገኛል። ቤቱ ከድንጋይና ከእንጨት የተገነባ ነው።

•አርክቴክት ዮሐንስ የኪነ ህንፃውን ጥበብ ሲገምቱ ከአርመኖችና ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ሕንዶች ሳይሳተፉበት እንደማይቀሩ ይገምታሉ።

•ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የውይይት ክበብ በመሆን አገልግሏል

•ሌላኛው ከአጤ ሚኒሊክ ቤት ጋር በድልድይ የሚገናኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤት ነው። ይህ ቤት ከቤተ መንግሥቱ በምሥራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው።

•በምድር ቤት የዙፋን ግብር ቤት ይገኛል። የነገሥታቱ መመገቢያ አዳራሽ ሲሆን ንጉሣዊ ቤተሰቦች ምግብ የሚመገቡበት ክፍል ነበር፤ ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የደርግ ምክር ቤት መሰብሰቢያ በመሆን አገልግሏል።
ታላቁ ቤተ መንግሥት ውስጥ ያለውን የአንድነት ፓርክ በፎቶ ይጎብኙ...
የምስል ምንጭ ከቢቢሲ
ጥያቄ አለኝ

ለሁሉም(9) ክልሎች በአንድነት ፓርክ ዉስጥ እልፍኝ አንደተሰጣቸዉ ይታወቃል ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኅላ ሲዳማ ክልል መሆኑ አይቀሬ ነው ምናልባትም ሌሎችም ይከተሉ ይሆናል።

እዚጋ ለፓርኩ አስተዳደር ጥያቄ ላነሳ የፈለኩት ነገር ቢኖር ለወደፊቱ ለሚፈጠሩ ክልሎች በፓርኩ reserve ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል ወይ? የሚል ይሆናል።

ምክኒያቱም ፓርኩን እንዳየነው ከሆነ ለክልሎች የተሰጠው እልፍኝ በአንድ አከባቢ ነው። ይሄ ማለት ደግሞ ለወደፊቶቹ ክልሎች እልፍኝ ይሰጣቸዉ እንኳን ቢባል ከ9ኞቹ ገለል ካለ ቦታ መሆኑ ነው። እንደዛ ከሆነ ከአዲሱ ክልል ለመጣ ጎብኚ ደስ ማይል ስሜት ሊፈጥርበት ይችላል።

ጥያቄው ተራ ነገር ሊሆን ይችላል ነገር ግን አሁን ባለንበት ሁኔታ እርስ በእር ለመጋጨት ትንሽ ምክኒያት የሚፈልግ ማህበረሰብ ተፈጥሮዋል ታድያ በዚዉ ከቀጠልን ይሄ ጉዳይ ለወደፊቱ ችግር አይፈጥርም ትላላቹ?

በዚ ጉዳይ ላይ አስተያየት ወይም ሃሳባቹን ማካፈል ለምትፈልጉ @UnityParkBot ይጠቀሙ
አንድነት ፓርክ በ15 ቀን ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አስገባ!

በብሔራዊ ቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ በአምስት ቢሊዮን ብር ወጪ የተሠራው አንድነት ፓርክ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ከሆነበት ከመስከረም 29/ 2012 ጀምሮ ከ 15 ሺሕ በላይ በሚሆኑ ጎብኚዎች ተጎብኝቶ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ።

የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ ታምራት ኃይሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከፓርኩ የሚገኘው ገቢ ፓርኩን ለማስፋፋት እና ለመጠበቅ እንዲሁም ለማሻሻል ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልጸው አረጋዊያን፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ለሀገር በጎ ውለታ የዋሉ ዜጎች ታዳጊ ህፃናት እና የጎዳና ልጆች ፓርኩን በነፃ እንዲጎበኙ መደረጉንም ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-29-8

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ