Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የአለም የሰላም ኖቤል ሎሬት ሆነው መሽለማቸውን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊ የነበሩ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የመጡ የኦሮሞ ፈረሰኞት አንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ስርዓቱን ለመታደም የመጡ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎችም ፓርኩን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ጎብኚዋች በሰጡት አስተያየትም በፓርኩ ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን በዓይናቸው ማየታቸው እንዳስደሰታቸው እና ከፍተኛ አድናቆትም እንዳደረባቸውም ገልፀዋል።

@UnityPark
ዛሬ በብድን መተው ፓርኩን ከጎበኙት ውስጥ

• ሆፕ ፎር ዮዝ ኢትዮጵያ ሰራተኞች።
• የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ሰራተኞች።
• ዚበም ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሰራተኞች።
• አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ የህብረት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ እና ቤተሰቦቻቸው ይገኙበታል።

@UnityPark
ከ8 ቀን ቡሀላ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷን ሳተላይት ታመጥቃለች ።ይህንን ኢትዮጵያ በጠፈር ምርምር አንድ ምዕራፍ የሄደችበትን የጋራ ስኬታችንን በአንድነት እናክብር።

Ethiopia will launch it’s first ever satellite on the 20th of December, 2019. Join us as we take a look at the wonders of this event that is a huge step for Ethiopia in innovation and space exploration.

#ETRSS1 @UnityPark
ከአንድነት ቤተሰብ የተላከ ጥያቄ: የ6 አመት ልጅ አለኝ ለሷ መክፈል ይጠበቅብኛል?

መልስ: መክፈል ዪኖርቦታል፣አለመክፈል ሚቻለው ከ2 አመት በታች ላሉ ህፃናት ብቻ ነው።

@UnityPark
Description about our Satellite

Name: Ethipian Remote Sensing Satellite 1 (ETRSS1)
Type / Application: Earth observation
Launch Location: China
Height from earth: 700Km
Type of orbit: Low orbit
Power: Solar arrays and batteries
Mass: 70 kg
Orbit Location: 80 degree
Coverage: Eastern and Western Africa
Launch Vehicle: as a Secondary Payload on CZ-2D(2) rocket

Source: https://space.skyrocket.de/doc_sdat/etrss-1.htm

#ETRSS1 @UnityPark
ሳተላዪቱ ከመሬት ወደ ጠፈር የሚላክበት በዚ CZ-2D(2) በተባለ Rocket ሊሆን እንደሚችል መረጃው ያመለክታል።

#ETRSS1 @UnityPark
ዐጤ ምንሊክ ፎቶ የተነሱባት ካሜራ 'በሕይወት ተገኘች'

"ይህ ጉዞ በዋናነት የዐጤ ምንሊክን የልብ ወዳጅና ምሥጢረኛ፣ ልዩ አማካሪና የቴክኒክ ሰው የነበረውን የስዊዛዊውን አልፍሬድ ኢልግ የልጅ ልጆች ዱካ ለማግኘት የተደረገ ሊባል ይችላል። እግረ መንገድም የንጉሥ ምንሊክን 106ኛ ሙት ዓመት ለመዘከር በቢቢሲ የተሰናዳ ልዩ ጥንቅር ነው።"

@UnityPark

መሉ ዜናውን ለማንበብ https://www.bbc.com/amharic/extra/j2zLpKIZY1/History_Ethiopia_Amharic
በፓርኩ ጉብኝት ካደረጉ ውስጥ በጥቂቱ

• ካራ ቃለህይወት ETC 172 Project ከቀራኒዮ ቤተልሔም ቃለህይወት ቤተክርስቲያን።
• ኦልማ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በአዳሪ ት/ቤቱ በማህበራዊ አገልግሎታቸው ምስጉን የሆኑ ከ150 በላይ ልዩ ተማሪዎች ።
• የማክስ ቪው ላይፍ ፊትነስ አባላቶች።

@UnityPark
ህጻናትን ወደ አንድነት ፓርክ ይዘው ለሚመጡ ወላጆች ፣ አሳዳጊዎች እና ት/ቤቶች በፓርካችን ውስጥ ምቹ የሆነ የህጻናት መጫወቻ ስፈራ ይገኛል።

@UnityPark
ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ


የ28 ዓመቷ ረድኤት አበበ ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ነው። ኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ረድኤት፤ በአልጎሪዝም እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) ዙርያ ትሠራለች። ረድኤት ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ስትሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪዋን የያዘችው ከሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በሒሳብ ነው።

@UnityPark
ከ Tikvah Ethiopia የተወሰደ

#ETRSS1 የመጀመሪያችን...

የመጀመሪያችን ስልክ - 1883
የመጀመሪያችን መኪና - 1900
የመጀመሪያችን የባቡር ሃዲድ - 1910
የመጀመሪያችን አውሮፕላን - 1938
የመጀመሪያችን የቴሌቪዥን ጣቢያ - 1955
የመጀመሪያችን ሳተላይት - 2012

@UnityPark #ETRSS1
ኢትዮ ቴሌኮም የአንድነት ፓርክ የመግቢያ ቲኬትን ኦንላይን መግዛት የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ አደረገ
*********************
ኢትዮ ቴሌኮም በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የውጭ አገር ዜጎች ካሉበት ሆነው አንድነት ፓርክን ለመጎብኘት የሚያስችላቸውን የመግቢያ ቲኬት ኦንላይን መግዛት የሚችሉበት አገልግሎት ተግባራዊ አድርጓል፡፡
አገልግሎቱ ከውጭ በመምጣት ፓርኩን መጎብኘት የሚፈልጉ ሰዎች ካሉበት ቦታ ሆነው ቲኬቱን መግዛት እና አገር ቤት ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በስጦታ ማበርከት ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡
በዚሁ መሰረት ቲኬቱን የአጋር ድርጅት ድረገጽ በሆነው
www.remit.et ላይ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት መግዛት እንደሚቻል ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ለኢቢሲ የላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ያብራራል፡፡
በሌላ በኩል የአገር ውስጥ ጎብኚዎች በአጭር የፅሁፍ መልእክት አማካኝነት ወደ 6030 "አ"ን ወይም "ሀ"ን በመላክ ወይም በፓርኩ ድረ ገፅ https://www.unitypark.et በኩል ቲኬቱን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

Source: EBC

@UnityPark
የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት አሁን ላይ ከ 113 ሚሊዮን አልፏል። በከተማ የሚኖረው ግን 23 ሚሊዮን ገደማ ነው። ይህም ከአገሪቱ ጠቅላላ ህዝብ ላይ 20.9 በመቶውን ይሸፍናል። በገጠሩቱ ኢትዮጵያ የሚኖረው ደግሞ 89.9 ሚሊዮን ሲሆን የአገሪቱን 79.1 በመቶ ይይዛል።
https://www.worldometers.info/world-population/ethiopia-population/

@UnityPark
መብራትን በሪሞት [ውይ ቻይና]

ዜናው #ኬንያ#ኢንዶኔዥያ እና #ታይላንድ ከቻይና አቅርቦት እንደሚያገኙ ያስረዳል።

እኛም አስገብተናል ይሆን ?

የቴክኖሎጅ መዘዙ ይሄ ነው እንግዲህ። በራስ ባለሙያ የማይሰራ ከሆነ፤ ሁሌም ከውጭ ማስገባት አደጋ ላይ ይጥላል። ሚስጥር መጠበቅ እና በራስ መተማመን የሚባል ነገር ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። አሁን አሁን በአገራችን DIGITALIZATION በሚል ብዙ ነገር እየተሰራ እንደሆነ እንሰማለን። እና በዚህ አጋጣሚ ጥንቃቄ ቢደረግ መልካም ነው።

@UnityPark
Tikvah Ethiopia በትንሽ ጊዜ ውስጥ ብዙ ቤተሰቦችን ማፍራት የቻለ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን አኔም አንዱ የቻናሉ ተከታይ ነኝ።

ይህን ላነሳ የፈለኩት የቻናሉ ስም Tikvah Ethiopia ከሚለው Tikvah ምን ማለት እንደሆነ አብዛኞቻችን ምን ማለት እንደሆነ ትኩረት ሰተነው ላናጣራ እንችል ይሆናል በሚለው የስሙን ትርጉም ላካፍላቹ ወደድኩ።

Google Dictionary እንዲ ብሎ ተርጉሞታል

"The name Tikvah is a Biblical Name given for new born childs. In Biblical Names the meaning of the name Tikvah is: Hope"

Tikvah Ethiopia : Hope Ethiopia

@UnityPark @TikvahEthiopia
2 Days, 10 Hours and 23 Minutes left for lift off

#ETRSS1 @UnityPark
በአለም ላይ ካሉ ሀገራት ቴሌግራምን በስፋት የሚጠቀሙት ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና ኡዝቤኪስታን ብቻ እንደሆኑ ያውቃሉ?

በአለም ላይ በስፋት ሰዎች የሚጠቀሙት የሶሻል ሚድያ ፕላትፎርም ሗትስአፕ ሲሆን 1.6 ቢልዮን ገደማ ሰዎች ይገለገሉታል፣ የሗትስአፕ ባለቤት የሆነው ሁለተኛው ፌስቡክ ደግሞ 1.3 ቢልዮን ገደማ ተጠቃሚዎች አሉት። የቻይናው ዊቻት ደግሞ በ1.1 ቢልዮን ተጠቃሚዎች ሶስተኛ ነው። የቴሌግራም ተጠቃሚዎች 200 ሚልዮን ገደማ ናቸው፣ በኢትዮጵያም አንደኛው ሆኖ ይገኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል ሰዎች ቴሌግራም እንደሚጠቀሙ ግን አልተጠቀሰም። እንዲያም ሆኖ ከ 6-7 ሚልዮም ኢትዮጵያውያን ፌስቡክ ይጠቀማሉ ተብሎ ይገመታል።

Source: Elias Meseret

@UnityPark