Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አህመድ አል ቃጣን እና ልኡካን ቡድናቸው አንድነት ፓርክን በትናንትናው እለት ጎብኝተዋል።

@UnityPark
ከአንድነት ፓርክ ቤተሰብ የተላከ ጥያቄ: ከስልክ በተጨማሪ በካሜራ መጠቀምስ ? የመኪና ማቆሚያ? በትራንስፖርት ከሆነ የት ነው የምንወርደው መግቢያ አማራጮች ካሉ።

መልስ: ካሜራ የተከለከለ ሲሆን ፣ መኪና ከያዙ በመግቢያው አከባቢ ግራ እና ቀኝ ማቆም ይቻላል። በትራንስፖርት ከመጡ ለመውረድ የቤተመንግስት የሁዋላ መግቢያ(ከውጭ ጉዳይ ወደ ላይ ሲመጡ የሚያገኙት በር ነጭ ድንኳን የተጣለበት) እሱን መግቢያ ዪጠቀሙ ከዛ ውጭ ወደ ፓርኩ መግቢያ በር አልተዘጋጀም።

@UnityPark
ዛሬ በብድን መተው አንድነት ፓርክን የፊውቸር ታለንት አካዳሚ ሰራተኞች እና የሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር የልዩ ትኬት ጎብኝዎቻችን።

Future Talent Academy staff members and A Special Ticket Visitors from Habesha Breweries S.C.

@UnityPark
ውድ የአንድነት ቤተሰቦች እንደምን ዋላቹ? ስለ ፓርኩ ወቅታዊ መረጃ እና ለጥያቄያቹ መልስ መስጠቴን በትጋት የምቀጥል ሆኖ ከዛሬ ጀምሮ ስለ ፓርኩ ከማጋራቹ መረጃዎች ውጭ ለእናንተ ይጠቅማል የምላቸውን መረጃዎች እየመረጥኩ ላካፍላቹ አስብያለው። ስለሆነም የእናንተንም ሃሳብ ከግምት ለማስገባት እንዲረዳኝ ከታች ባለው ምርጫ ሃሳባቹን እንድታካፍሉኝ እጠይቃለው። መልካም ምሽት 😊
anonymous poll

ይቻላል 😊 – 25
👍👍👍👍👍👍👍 89%

አልስማማም – 3
👍 11%

👥 28 people voted so far.
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የአለም የሰላም ኖቤል ሎሬት ሆነው መሽለማቸውን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊ የነበሩ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የመጡ የኦሮሞ ፈረሰኞት አንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ስርዓቱን ለመታደም የመጡ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎችም ፓርኩን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ጎብኚዋች በሰጡት አስተያየትም በፓርኩ ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን በዓይናቸው ማየታቸው እንዳስደሰታቸው እና ከፍተኛ አድናቆትም እንዳደረባቸውም ገልፀዋል።

@UnityPark
ዛሬ በብድን መተው ፓርኩን ከጎበኙት ውስጥ

• ሆፕ ፎር ዮዝ ኢትዮጵያ ሰራተኞች።
• የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ሰራተኞች።
• ዚበም ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሰራተኞች።
• አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ የህብረት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ እና ቤተሰቦቻቸው ይገኙበታል።

@UnityPark
ከ8 ቀን ቡሀላ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷን ሳተላይት ታመጥቃለች ።ይህንን ኢትዮጵያ በጠፈር ምርምር አንድ ምዕራፍ የሄደችበትን የጋራ ስኬታችንን በአንድነት እናክብር።

Ethiopia will launch it’s first ever satellite on the 20th of December, 2019. Join us as we take a look at the wonders of this event that is a huge step for Ethiopia in innovation and space exploration.

#ETRSS1 @UnityPark
ከአንድነት ቤተሰብ የተላከ ጥያቄ: የ6 አመት ልጅ አለኝ ለሷ መክፈል ይጠበቅብኛል?

መልስ: መክፈል ዪኖርቦታል፣አለመክፈል ሚቻለው ከ2 አመት በታች ላሉ ህፃናት ብቻ ነው።

@UnityPark
Description about our Satellite

Name: Ethipian Remote Sensing Satellite 1 (ETRSS1)
Type / Application: Earth observation
Launch Location: China
Height from earth: 700Km
Type of orbit: Low orbit
Power: Solar arrays and batteries
Mass: 70 kg
Orbit Location: 80 degree
Coverage: Eastern and Western Africa
Launch Vehicle: as a Secondary Payload on CZ-2D(2) rocket

Source: https://space.skyrocket.de/doc_sdat/etrss-1.htm

#ETRSS1 @UnityPark
ሳተላዪቱ ከመሬት ወደ ጠፈር የሚላክበት በዚ CZ-2D(2) በተባለ Rocket ሊሆን እንደሚችል መረጃው ያመለክታል።

#ETRSS1 @UnityPark
ዐጤ ምንሊክ ፎቶ የተነሱባት ካሜራ 'በሕይወት ተገኘች'

"ይህ ጉዞ በዋናነት የዐጤ ምንሊክን የልብ ወዳጅና ምሥጢረኛ፣ ልዩ አማካሪና የቴክኒክ ሰው የነበረውን የስዊዛዊውን አልፍሬድ ኢልግ የልጅ ልጆች ዱካ ለማግኘት የተደረገ ሊባል ይችላል። እግረ መንገድም የንጉሥ ምንሊክን 106ኛ ሙት ዓመት ለመዘከር በቢቢሲ የተሰናዳ ልዩ ጥንቅር ነው።"

@UnityPark

መሉ ዜናውን ለማንበብ https://www.bbc.com/amharic/extra/j2zLpKIZY1/History_Ethiopia_Amharic
በፓርኩ ጉብኝት ካደረጉ ውስጥ በጥቂቱ

• ካራ ቃለህይወት ETC 172 Project ከቀራኒዮ ቤተልሔም ቃለህይወት ቤተክርስቲያን።
• ኦልማ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በአዳሪ ት/ቤቱ በማህበራዊ አገልግሎታቸው ምስጉን የሆኑ ከ150 በላይ ልዩ ተማሪዎች ።
• የማክስ ቪው ላይፍ ፊትነስ አባላቶች።

@UnityPark
ህጻናትን ወደ አንድነት ፓርክ ይዘው ለሚመጡ ወላጆች ፣ አሳዳጊዎች እና ት/ቤቶች በፓርካችን ውስጥ ምቹ የሆነ የህጻናት መጫወቻ ስፈራ ይገኛል።

@UnityPark
ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ


የ28 ዓመቷ ረድኤት አበበ ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ነው። ኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ረድኤት፤ በአልጎሪዝም እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) ዙርያ ትሠራለች። ረድኤት ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ስትሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪዋን የያዘችው ከሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በሒሳብ ነው።

@UnityPark
ከ Tikvah Ethiopia የተወሰደ

#ETRSS1 የመጀመሪያችን...

የመጀመሪያችን ስልክ - 1883
የመጀመሪያችን መኪና - 1900
የመጀመሪያችን የባቡር ሃዲድ - 1910
የመጀመሪያችን አውሮፕላን - 1938
የመጀመሪያችን የቴሌቪዥን ጣቢያ - 1955
የመጀመሪያችን ሳተላይት - 2012

@UnityPark #ETRSS1