Unity Park-አንድነት ፓርክ
557 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
የሰብአዊ ዕርዳታ ወቅታዊ መረጃ፦ ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ትግራይ ክልል የምግብ ዕርዳታን ይዘው የገቡ የጭነት መኪናዎች 277 ደርሰዋል።

Humanitarian Update: As of August 11, 2021, 277 trucks of food assistance have entered the Tigray Region.
‘እችላለሁ’ የሚለው የድል አድራጊዎች አመለካከት ነው! የ21 ዓመቷ ወጣት የአብሥራ ሺፈራው የዚህ ዓይነቱ የአሸናፊነት እና የጽናት ተምሳሌት ናት። ምንም ዓይነት ተግዳሮት ቢያጋጥማቸው በቆራጥነት የሚጸኑ እንዲህ ያሉ ወጣቶችን በማግኘቴ ደስ ብሎኛል።
#dr.Abiy Ahmed
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ቃል እንደገባነው እጅን አፍ ላይ የሚያስጭን ገድል መፈፀማችንን የምናበስርበት ጊዜ ቅርብ ነው" አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ "ጠላት ወደወጥመዳችን እየገባ ነው" ያሉ ሲሆን የማሸነፍ አቅማችም ተጠናክሮ እየወጣ ነው ሲሉ አሳውቀዋል፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥም እጅን በአፍ የሚያስጭን ገድል መፈፀማችንን እናበስራለን ብለዋል።

የያዝነው የኢትዮጵያን አምላክ ነው ያሉት ጠ/ ሚኒስትሩ የምንታገለው ለኢትዮጵያ ነው ፤ የሚዋጋው የኢትዮጵያ ጦር ነው ፤ በመጨረሻም ታሪክ እንደሚነግረን አሸናፊዋ ኢትዮጵያ ናት ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጠ/ሚኒስትሩ ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ፦
- በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የሚዲያ ዘመቻ እና የዴፕሎማሲ ጫና ለመመከት እንዲረባረብ፤
- የውሸት ዜናዎችን እየተከታተለ እንዲያመክን፤
- ህወሓት በሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ሳይደናበር፤ የሴራ ትንታኔ ውስጥ የገቡ ከሴራ ትንታኔ በመውጣት ህወሓት ጦርነት የከፈተበትን የዴፕሎማሲና የጦር ግንባር እንዲቀላቀሉ፤
- ሁሉም ለሀገሩ አምባሳደር ሆኖ ለሀገሩ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

* ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል።
“የውሸት ፀሐይ ሲጠልቅ የሤረኞች ወጥመድ ይበጠሳል!”
"ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ መቼም፣ የትም፣ በምንም" በሚል መሪ ቃል፣ የብሔራዊ ቴአትር፣ የኦሮሞ የባህል ማዕከልና የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተገኝተው ዝግጅቶችን አቅርበዋል። 1/2
ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት። ዝግጅቶቹን ላቀረቡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ሌሎችም ከያንያን አርአያነታችሁን እንደሚከተሉ ተስፋ አደርጋለሁ። 2/2
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለሥራ ጉብኝት ቱርክ፣ አንካራ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በቆይታቸው ፕሬዚደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋንን አግኝተው በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ የትኩረት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ብሏል የጠ/ሚ ፅ/ቤት
Thank you to President Recep Tayyip Erdoğan for warmly receiving my delegation and I to Turkey today. The agreements we have signed are a strengthening of our relations. I appreciate Turkey’s support in #Ethiopia’s continued development and stability.
#dr.abiy.ahmed