Unity Park-አንድነት ፓርክ
563 subscribers
164 photos
1 video
20 links
አንድነት ፓርክ በ 2012 ተቋቋመ ፡፡ ፓርኩ የሚገኘው በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሚገኘው ታላቁ ቤተመንግስት ውስጥ ሲሆን ከመቶ ምዕተ ዓመት በላይ የመንግሥት መቀመጫ ሆኖ ቆይቷል፡፡
Download Telegram
Forwarded from Unity-መረጃ
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,707 ላቦራቶሪ ምርመራ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 287 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ17 እስከ 38 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል (ጉባ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (መተማ ለይቶ ማቆያ) እና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 7

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 7

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ ሁለት (112) ደርሷል።
Have you checked out Ask Anything Ethiopia yet? It's Ethiopia's first question and answer platform, where you can get answers to your biggest questions from thousands of people! You can join using the link below:

https://telegram.me/ask_anything_ethiopia_bot?start=i242826341
ብዙዎቹ የሙያ ዘርፎች ፍላጎትና ተሰጥኦ ይሻሉ። ለውትድርና ግን ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው። እንደ ሌላው ሙያ ውትድርና እውቀትና ጉልበት ብቻ አይፈልግም፤ ደምና አጥንትን ለመገበር ዝግጁ መሆን ጭምር እንጂ። 1/3
ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው። ታከተኝ ሳይሉ ሀገርን ከማገልገል፣ ሳይሰስቱ ፍቅርን ከመስጠት፣ በመርህ ኖሮ ለመርህ ከመሰዋት የበለጠ አኩሪ ገድል የለም። 2/3
ሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” ብላ ስትናገር እጅግ በኩራት ነው። ወታደር መሆን ደግሞ ኩራቱ የትናየት ከፍ እንደሚል አስቡት፡፡ ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን እንማር! 3/3
ለሠራዊታችን ደም እንለግስ። የዐቅመ ደካሞችን ቤት እናድስ። #አረንጓዴዐሻራችንን እናሳርፍ። የግብርና ምርታማነታችንን እናሳድግ። የየቢሮ ሥራችንን ዐቅም ጨምረን እንሥራ፤ እያንዳንዳችን ከሚጠበቅብን በላይ ስንወጣ፣ ሁሉም ነገር ይስተካከላል!
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሐፈት ቤት ሠራተኞች ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ሊሰጡ ወስነዋል።

#PMOEthiopia
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
የሰብአዊ ዕርዳታ ወቅታዊ መረጃ፦ ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ትግራይ ክልል የምግብ ዕርዳታን ይዘው የገቡ የጭነት መኪናዎች 277 ደርሰዋል።

Humanitarian Update: As of August 11, 2021, 277 trucks of food assistance have entered the Tigray Region.
‘እችላለሁ’ የሚለው የድል አድራጊዎች አመለካከት ነው! የ21 ዓመቷ ወጣት የአብሥራ ሺፈራው የዚህ ዓይነቱ የአሸናፊነት እና የጽናት ተምሳሌት ናት። ምንም ዓይነት ተግዳሮት ቢያጋጥማቸው በቆራጥነት የሚጸኑ እንዲህ ያሉ ወጣቶችን በማግኘቴ ደስ ብሎኛል።
#dr.Abiy Ahmed