Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
978 subscribers
844 photos
39 videos
93 files
29 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ቻናል ነው። በግቢ ጉባኤው የሚከናወኑ ማንኛውንም ተግባራት፣መረጃዎችን፣መልዕክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል።
Download Telegram
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም! •ዕርገተ ክርስቶስ• ሐሙስ ሰኔ 6/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቲ ግቢ ጉባኤ ስለ ክርስቶስ ዕርገት የምንማማር ይሆናልና በዕለቱ ሁላችንም በቸር እንድንገናኝ የልዑል እግዚአብሔር ፍቃዱ ይሁንልን። ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለ ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ እያልን በዛሬው ዕለት ስለ ክርስቶስ ዕርገት በመርሐ ግብር ሰዓታችን ማለትም ከ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እግዚአብሔር በመምህራችን ላይ አድሮ ሊያስተምረን ይፈልጋልና ስለዚህም ምክንያት ሁላችንም እንዳንቀርባት ግቢ ጉባኤያችን መልዕክቷን በትህትና ታስተላልፋለች።

ቸር ያገናኘን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•የአገልግሎት ስልጠና•

የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን በዛሬው ዕለት ማለትም ቅዳሜ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ6:00 ሰዓት “የአገልግሎት ስልጠና” የሚኖር ይሆናል። በስልጠናውም ላይ አገልግሎት እንዴት እናገልግል ፣ ለምንስ እናገለግላለን የሚሉትን እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች በሰፊው የሚመለሱበት ስለሆነ ሁላችንም የክርስቶስ አገልጋይ ባሪያ እንደመሆናችን መጠን የአገልግሎትን ጥበብ እንማር ዘንድ በሰዓቱ ተገኝተን ልንማር ያስፈልጋል እና አደራ እንዳንቀር በማለት ግቢ ጉባኤ ጥሪዋን በትህትና ታስተላልፋለች።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•አንድ ወር ስለ አንድ ሐዋርያ•

በሃይማኖት ጸሎታችን ላይ “ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” እያልን ዘወትር እንመሰክራለን ስለዚያም ምክንያት ዛሬ ክርስቶስ ለእኛ የሰራልንን ቅድስት ቤታችንን በዓለሙ ሁሉ ዞረው ፣ በየሀገሩ ቋንቋ ሰብከው ይህችን የምድር ገነት የሆነችውን ሰላማዊ ስፍራ እና የነፍስ ሐኪም ቤት ፥ ቤተ ክርስቲያንን ያስተላለፉልን ሐዋርያት በመሆናቸው ከወርኃ መስከረም እስከ ግንቦት ሐዋርያትን በሚገባቸው ቅደም ተከተል ስናስብ እና የእነርሱን ጽናት አብነት አድርገን በትንሹም ቢሆን ስንማማር ዛሬ ላይ ደርሰናል።

በወርኃ ሰኔ ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ የሚታሰብ መሆኑን ለመግለጽ እየወደድን በጽዋ መርሐ ግብራችን ላይም ፦

፩. ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ማነው ፣

፪. በየትኛው አኅጉረ ስብከት ተመድቦ ቅዱስ ቃሉን ዘራ ፣

፫. ከክርስቶስ እንዲሁም ከእናቱ ከእናታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የነበረው ቅርበት እንዴት ያለ ነበር? የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በጽዋችን ላይ መልስ የምናገኝበት እና ስለ ቅዱስ ታዴዎስ የምንመሰክረው አንዳች ነገር ይዘን የምንመለስበት ይሆናልና በዕለቱ አንዳንቀር አስቀድመን የአክብሮት ጥሪያችንን ለማስተላለፍ ወደድን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሠላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!! ፈጣሪ በአማላጅነቱ ይቅር ይበለን። አፎምያን ከጠላት ማታለል ያዳነ፤ የባህራንን የሞት ደብዳቤ የለወጠ ቅዱስ ሚካኤል ለኛም ይድረስልን። መልካም በዓል🙏
በዓለ ጰራቅሊጦስ
መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ነው። ጰራቅሊጦስ ማለት ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬)
ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይከበራል፡፡ የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡

ከታች ይቀጥላል …
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
በዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ነው። ጰራቅሊጦስ ማለት ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት…
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ 71 ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ፣ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.፪፥፳፰)
በትምህርቱም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን ሐዋርያት እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?››ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ንስሓ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፡፡(ሐዋ.፪፥፩-፵፩)
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡

ምንጭ:-
- በኢ.ኦ.ተ.ቤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ (eotcmk.org)
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ፣ ፍቅር እና ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

በዛሬው ዕለት የመውጫ ፈተናችሁን የምትወስዱ ውድ ቤተሰቦቻችን ጥበብ እና ዕውቀትን ለቅዱሳን የገለጸ አምላከ ቅዱሳን ለእናንተም ገልጾላችሁ መልካም ውጤት እንድታገኙ እግዚአብሔር አምላክ ይፍቀድላችሁ/ይፍቀድልን።

በማርቆስ እናት ቤት በጽርሐ ጽዮን በእሳት ላንቃ ወርዶ ሐዋርያትን አዲስ ቋንቋ እንዲናገሩ እና እንዲበረቱ ያጽናናቸው መንፈስ ቅዱስ እናንተንም ያረጋጋችሁ ፣ ያበረታቸሁ እና ዕውቀቱን ይገልጽላችሁ ዘንድ ለእናንተ የተሰጠ ‍እና የተላከ ይሁንልን።

ሁሌም በጨነቀን ከጎናችን አትጠፋምና የቃናዋ እመቤት እናታችሁ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያጠናችሁትን እያስታወሰች ፣ የጎደለውን እየሞላች ከጎናችሁ ሳትለይ በውጤታችሁ አስደስታችሁ እኛንም ታስደስቱን ዘንድ እርሷ እመቤታችን ትፍቀድልን።

እግዚአብሔር አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን።

ማክሰኞ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
🎙️ 🔴 LIVE 🔴🎙️

በነገው ዕለት ማለትም በሰኔ ረቡዕ 19/2016 ዓ.ም በሚኖረን የLIVE ትምህርተ ወንጌል መርሐ ግብር ላይ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ለመገኘት ከወዲሁ ቀጠሮ እንድንይዝ እና በሰዓቱ እንድንገኝ በትህትና ለማሳሰብ ወደድን።

ለማስታወስ ያህል

ቀን - ሰኔ ረቡዕ 19/2016 ዓ.ም
ሰዓት - ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ዛሬ ምሽት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ
Live stream scheduled for
Live stream finished (52 minutes)
ትምህርተ ወንጌል በዲያቆን ዘአማኑኤል
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
“ከኃጢአታችን ያወጣን ዘንድ ፥ በጽድቁም ያድነን ዘንድ ፥ እርሱ ስለ ኃጢአታችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሰቀለ።”

•፩ኛ ጴጥሮስ ም ፪ ቁ ፳፬•

በዕለተ ረቡዕ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም በነበረን የOnline ትምህርት ላይ የነበራችሁ እንዳተረፋችሁበት በማመን ለመገኘት አቅዳችሁ ያልቻላችሁ ደግሞ በሌላ ተመሳሳይ መርሐ ግብር ላይ እንድትገኙ እና እንዲሁም በግቢ ጉባኤያችሁ በአካል እየተገኛችሁ እንዲህ እንደ ወተት የጠራ እንደ ማር የጣፈጠ እና ተስፋ በልባችን እንዲኖር የሚያደርገውን የልዑል እግዚአብሔርን ቃል መጥታችሁ እንድትማሩ የዘወትር ማሳሰቢያችን ነው።

ዓለም በምታመጣብን ወጀብ እንዲህ ተከበን ሳለን ቃሉንም ሳንሰማ አንዲት ቀን ማሳለፍ አይቻለንምና ፤ የሕይወት ቃል የሆነውን እርሱን በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት በግቢ ጉባኤ ተገኝተን መማር ላልቻልን የተዘረጋ መርሐ ግብር ስለሆነ በዚህ የማህበራዊ ደረ-ገጽ ስብስብ ውስጥ ያላችሁ የተከበራችሁ ውድ ወንድም እህቶቻችን በዚህም ብቻ ሳይሆን ግቢ ጉባኤያችን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ6:20-7:20 ሰዓት ድረስ በምታሰናዳው የዕለት ዕለት መርሐ ግብራት ላይ እየተገኘን ትህትና እና ፍቅርን ፣ ምግባር እና እምነትን እንዲሁም ተስፋን ለወደፊት እንድንሰንቅ በታላቅ ትህትና በድጋሚ ለማሳሰብ ወደድን።

በትምህርቱ ሰዓትም መገኘት ላልቻላችሁ ቤተቦቻችን እነሆ የድምጽ ቅጂውን አጋራናችሁ። በማስተዋል ሆነን እንድናደምጠው እርሱ ቸሩ መድኃኔዓለም ይፍቀድልን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Forwarded from ገሊላ
የክርስቶስ ፍጹም ፍቅር እና ሰላም ከሁላችን ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር አድሮ ለዘለዓለም ይኑ ውድ ቤተሰቦቻችን።

•የጽዋ እና ልዩ የርክክብ መርሐ ግብር•

በዛሬው ዕለት ማለትም ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም በሚኖረን የጽዋ መርሐ ግብር ላይ ምሳችንን ለነዳያን እየያዝን እንድንመጣ እና ስለ እመቤታችን እንዲሁም ስለ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ለመማማር ሁላችንም በመርሐ ፍብር ሰዓታችን ማለትም 6:20 ሰዓት ጀምሮ በግቢ ጉባኤው አዳራሽ እንድንገናኝ ለማስታወስ ወደድን።

•••

በመቀጠልም ልዩ የርክክብ መርሐ ግብር የሚኖረን ስለሚሆን የቻልን ሁላችንም በዛሬው ዕለት ባለው በተሰናዳው መርሐ ግብር ላይ እንድንገኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም በትህትና ለማሳሰብ እንወዳለን።

ማስታወሻ

አደራ ምሳችንን ለነዳያን ሳንዘነጋ ይዘን እንምጣ።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ለ 2017 ዓ.ም…
ከጸዋ መርሐ ግብር ጋር በልዩ ሁኔታ ስለምናከብረው አደራ እንዳነቀር ሁላችንም እንድንገኝ ይሁን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ