Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
978 subscribers
844 photos
39 videos
93 files
29 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ቻናል ነው። በግቢ ጉባኤው የሚከናወኑ ማንኛውንም ተግባራት፣መረጃዎችን፣መልዕክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል።
Download Telegram
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን ወስደን ፈተና ጨርሰን አሁን እረፍት ላይ ስለምንገኝ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ያህል መርሐ ግብር እንደማይኖረን ለመግለጽ እንወዳለን።

መርሐ ግብርም የሚጀምርበትን ቀን የምናሳውቅ ስለሚሆን እስከዚያው ድረስ ግን በጾም ፤ በጸሎት እንዲሁም በኪዳን ፤ በቅዳሴ እየበረታን እንድንቆይ በልዑል እግዚአብሔር ስም ለማሳሰብ ወደድን።

ቸር ያገናኘን

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን።

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

እግዚአብሔር ቢወድ እና ቢፈቅድ ትምህርታቸውን ዘንድሮ የሚጨርሱ ወንድም እህቶቻችን ምረቃ ሐምሌ 27 ቀን ስለሚሆን በዚያች ልዩ ቀንም ሁላችን በኅብረት እንድናጅባቸው እና እግዚአብሔርን በዝማሬ እንድናመሰግን የመዝሙር ጥናት በቅርቡ ለእናንተ በማሳወቅ የመዝሙር ጥናቱን የምንጀምር ይሆናል።

እስከዚያው ግን ከታች የተላኩትን መዝሙራት እየከለስን የጥናት ቀኑን እንድንጠባበቅ ይሁን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
በዓለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ

እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ! የአባቶቻችን የሐዋርያት የአገልግሎታቸው በረከት ከእኛ ጋር ይሁን።
ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን እንደምን ሰነበታችሁ?

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ክረምቱ እንደምናየው ፋታ የማይሰጥ ዝናም እና ብርድ የሚፈራረቅበት ሆኗል። በዚህ ወቅት ደግሞ ቤት ውስጥ ሆነን ብርድ እያቃጠለን በውጪ ያሉት ወንድም እህቶቻችን ደግሞ የሚደርቡት ልብስ ፣ ብርዱን የሚቋቋሙበት መብል ሳይኖራቸው ይህን ጊዜ ለማለፍ አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው ሁላችንም ተነቃቅተን በክርስቶስ ክርስቶሳውያን እስከሆንን ድረስ አባታችን እግዚአብሔር ይደሰትብን ዘንድ እርስ በርስ ተዋደን እና ተረዳድተን “ጎዳና ላይ ያሉ ቤተሰቦቻችንን በማልበስ” በጎ ትሩፋት ላይ እንድንሳተፍ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ከላይ የተዘረዘሩትንም ከነገ ጀምሮ እስከ ሐሙስ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም በማምጣት እንድትተባበሩን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ፥ አሜን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን ወስደን ፈተና ጨርሰን አሁን እረፍት ላይ ስለምንገኝ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ያህል መርሐ ግብር እንደማይኖረን ለመግለጽ እንወዳለን። መርሐ ግብርም የሚጀምርበትን ቀን የምናሳውቅ ስለሚሆን እስከዚያው ድረስ ግን በጾም ፤ በጸሎት እንዲሁም በኪዳን ፤ በቅዳሴ እየበረታን እንድንቆይ…
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

ከዚህ አስቀድመን እንደገለጽነው ክረምት ስለነበር ትምህርትም ስለተዘጋ ለሁለት ሳምንታት ያህል መርሐ ግብር ዝግ እንደሚሆን ነገር ግን ትምህርቱም ስለተጀመረ ከዛሬው ዕለት ማለትም ሰኞ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዘወትር መርሐ ግብራችን ቀጣይነት ኖሮት እንደሚጀምር ስንገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው።

የሰኞ ጸሎት እንደተጠበቀ ስለሆነ ሁላችንም በእናታችን ቤት ተገኝተን ጸሎቱን መካፈል እንዳንዘነጋ ለማለት እንወዳለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ