Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
978 subscribers
844 photos
39 videos
93 files
29 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ቻናል ነው። በግቢ ጉባኤው የሚከናወኑ ማንኛውንም ተግባራት፣መረጃዎችን፣መልዕክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል።
Download Telegram
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ፣
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፣
አሠሮ ለሰይጣን ፣
አግዐዞ ለአዳም ፣
ሰላም ፣
እምይእዜሰ ፣
ኮነ ፣
ፍሥሐ ወሰላም።

የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

•ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት መርሐ ግብር•

በነገው ዕለት ማለትም ረቡዕ ሚያዚያ 30/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ወርኃ ሚያዚያን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጸመን አምላካችንን እናመሰግን ዘንድ እንዲሁም የሚመጣውን የግንቦት ወር ይባርክልን ዘንድ በኅብረት ሆነን ጸሎት የምናደርስ ስለሚሆን ሁላችንም በሰዓቱ ተገኝተን ምስጋናችንን እንድናቀርብ ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን በትህትና ታስተላልፋለች።


ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ፥ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፥ አሠሮ ለሰይጣን ፥ አግዐዞ ለአዳም ፥ ሰላም ፥ እምይእዜሰ ፥ ኮነ ፥ ፍሥሐ ወሰላም።

•ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ

•ሚያዝያ 30 ቀን የቅዱስ ማርቆስ ዓመታዊ የእረፍቱ መታሰቢያ ቀን ሆነ ፤ ጥቅምት 30 የተወለደበት ቀን ነው።
• ቅዱስ ማርቆስ ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድእት ነው ፤ የእናቱ ስም ማርያም ይባላል ቁጥሯ ከ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው ፤ በ 50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደላቸው በዚህች ቅድስት እናት ቤት ሆነው ሲጸልዩ ነው (ሐዋ ሥራ ም 2 ቁ 1 ፤ ም 12 ቁ 12)። ይህ ሐዋርያ ወንጌሉን የጻፈው ጌታ ባረገ በ 11ኛ ዓመት በሮማይስጥ ቋንቋ ሮም ላይ ሆኖ ነው ፤ ምንም እንኳን ቅዱስ ጴጥሮስንና ቅዱስ ጳውሎስን ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች ወንጌልን ቢሰብክም በዋናነት ግብጽ በመዘዋወር ጣኦታትን አፈራርሷል ፤ ወልድ ዋህድ ብላ እንድትጸናም አድርጓል። ኢትዮጵያም ድረስ መጥቶ ወንጌልን ሰብኳል ፤ መንበረ ጵጵስናው ግብጽ እስክንድርያ ነው፤ ኢትዮጵያ በዚህ በማርቆስ መንበር የተሾሙ 111 ጳጳሳትን ከግብጽ ስታስመጣ ኖራለች ፤ እስክንድርያ እናቴ ማርቆስ አባቴ የምትለውም ለዚህ ነው ፤ ቅዱስ ማርቆስን ሚያዚያ 30 ቀን ጣኦት አምላኪዎች በበሬ አስጎትተው ገድለውታል። እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱስ ማርቆስ ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
የክርስቶስ ፍጹም ፍቅር እና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

የመዳናችን ምክንያት የሆነችልን ፤ የነፃነት እናት የሆነችልን ፤ ከመስቀል ስር የተቸረችን እጅግ ውድ እና ልዩ የሆነችው ስጦታችን ልደቷ ነገ ነው።

ለእኛ ለትዕቢተኞቹ የተሰጠችን ትሁት እናት ፣ አምላኳን የወለደች ንጽሕት ቅድስት እናት ፣ የመላእክት እህት ፣ ለሰማዕታት አክሊል የሆነች እመቤታችን ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም የዓለምን መርገም ልታስወግድ በወርኃ ግንቦት የመዳናችን ምስጢሩ ይፈጸም ዘንድ ለእኛ ተወለደችልን።

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ።


ልደቷ ልደታችን ነውና ይህችን ቅድስት ዕለት ምክንያት በማድረግ በነገው ዕለት ማለትም ሐሙስ ግንቦት 01/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ልዩ የልደታ ለማርያም መርሐ ግብር ይኖረናል እና እንዳትቀሩ በእመቤታችን ስም በታላቅ ትህትና ጠርተናችኃል።

ልደቷ ልደቱ የሆነ ፥ ነገን አይቀርም።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ።


ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።

ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን በዐቢይ ኃይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሠላም።

             ልደታ ለማርያም

{ መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን }
                🕯መዝ 86÷1🕯

እመቤታችን ልደቷ እንደእንግዳ ደራሽ እንደውኃ ፈሳሽ ሆኖ ሳይነገር ሳይታወቅ ሳይጠበቅ የመጣ አይደለም፤ እንደልጇ ሁሉ አበው ሲሿት በምሳሌ ጥላነት ሲያዩዋት፣ ነቢያቱ ሲተነበዩላት ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚኝ በማለት ሰሎሞንሞ እቴ ሙሽራዬ እያለ በትንቢት መነጽርነት ሲያናገራት የነበረች ናት እንጂ ።

አስቀድሞ ለአዳም በገባለት ቃልኪዳን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኃለው በማለት እርሱ ይወለድባት ዘንድ ያላት የመረጣት የአዳም የልጅ ልጅ እንደምትወለድና ከእርሷም እንደሚወለድ ነግሮታል።

ከዚህ በጎላ እና በተረዳ ግን ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓዐርግ ጽጌ እምኔሃ" ... ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከግንዱ ይወጣል ... በማለት በትር ብሎ በትረ አሮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእሴይ ሥር ከዳዊት እንደምትወለድና ከእርሷም ጽጌ የተባለ ክርስቶስ እንደሚወለድ ተናግሯል።

የእመቤታችን ልደት ሊቁ "መኑ ይእቲ እንተ ትሔውጽ ከመጎኅ ያላት" ... ይህች እንደማለዳ ፀሐይ ያለች ማናት ... በማለት የገለጣት ለአማናዊው ፀሐይ ጎኅ፤ ለአማናዊው ወንጌል ንዑስ ወንጌል የሆነች የእመቤታችን ልደቷ ለልደተ ክርስቶስ ጎኅ ሆኖልን፤ በእርሷ መወለድ የእርሱን ሰው ሆኖ መወለድ እውን ሆኖልን ያረጋገጥንበት ነው።

ደራሲም ድንግል በልደቷ ለአዳምና ለልጆቹ ከመርገሙ መዳኛ ስለመሆኗ እንዲህ ብሎ ይጠቅሳል :-

“ማርያም ድንግል በልደትኪ መጠነ አቅሙ፤
አዳም ይዌድስኪ ምስለ ደቂቀ ኩሎሙ፤
እስመ ለአዳም ብኪ ተስእረ መርገሙ።”
        🕯መልክአ ልደታ🕯

የእመቤታችን ልደት ከአምስቱ ልደታት አንዱ የሆነው እንደ ልደተ አቤል ያለ ይኸውም ከእናትና ከአባት የሚወለዱት ልደት ነው። ልደቷም መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን... መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው..  በማለት ቅዱስ ደዊት "አድባር ቅዱሳን" ብሎ ከገለጣቸው በምድር  ከተነሱት ሁሉ በግብራቸው በጽድቃቸው በትሩፋት በክብር  እንደ ተራራ ከፍ ብለው ከሚታዩት ከተነሱት ከታላላቅ ቅዱሳን ወገን ነው።
ታሪክ በእንተ ልደተ ማርያም

ጰጥሪቃና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ቅዱሳን ባለጸጋ ለእንሶቻቸው የወርቅ ጉትቻ እስኪያረጉ ድረስ ሁሉ የተትረፈረፋቸው ሰዎች ነበሩ። እነርሱም መካን በመሆናቸው ያዝኑ ነበር። አብዝተውም እግዚአብሔርን ለመኑት ጠየቁትም  በኋላም ሕልምን አዩ።

ሕልሙንም ሕልም ፈቺ ዘንድ ሔደው ፍቺውን ጠየቁት። እርሱም ነጭ ጥጃ መልኳ ደምግባቷ ያማረ ምግባሯ የተወደደ ሴት ልጅ ናት። እንዲህ አይነቷ እሷን የምትመስል እየወለደች ትሔዳለች፤ የመጨረሻዋ ጥጃ ጨረቃ መውለዷም ከሰማይ ዝቅ ከምድር እና ከፍጥረታት ወገን ግን ከፍ ያለች ልጅ ናት የፀሐዩ ነገር ግን አልተገለጠልኝም አላቸው። እነርሱም ይህንኑ ሰምተው ሄዱ። ሄኤማንን ወለዱ። ሄኤሜን ዴርዴንን፣ ዴርዴን ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሔርሜላን ወለደች። ሔርሜላና ማጣትም የጌታ አያቱ የምትሆን ሐናን ወለዱ።


ኢያቄም እና ሐና … ይቀጥላል።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ኢያቄም እና ሐና

ከነገሥታቱ ከይሁዳ ወገን የሚሆን ኢያቄም ቀለዮጳ የሚባል አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር። እርሱም ከካህናቱ ከነገደ ሌዊ የምትወለደውን ሐናን አገባ። እነርሱም የተቀደሱ ደጋግ ነበሩ። በደቂቀ እሥራኤል ዘንድም አብዝተው መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀንም ከደቂቀ እሥራኤል ወገን የሆነ ሮቤል የተባለ ሰው መጣና " በእኛ ፊት መሥዋዕትን ታቀርብ ዘንድ አይገባም፤ በእሥራኤል መካከል ዘር የለህምና" አለው። አይሁድ እና ካህናቱም ልጅ ስለሌላቸው ይንቋቸው ይጠሏቸው፤ መሥዋዕታቸውንም ለመቀበል እምቢ ይሉ ነበር።

ኢያቄምም ፈጽሞ አዘነና ስእለቴን እስኪሰጠኝ ወደእኔና ወደሚስቴም እስኪያይ ድረስ አልመገብም አልጠጣምም ብሎ ሱባኤ ለመያዝ ወደ ገዳም /በረሓ ወጣ። ሰባቱ ሰማያት እንደመጋረጃ ተገልጠው ነጭ ወፍ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ በራእይ አየ።

ታላቁ የፋሲካ በዓል በደረሰ ጊዜ አንዲት የመንደሩ ሴት ወደሐና መጥታ ለምን ታዝኛለሽ? ራስሽንስ ለምን ትጎጃለሽ? በዓል ስለደረሰ መምህሬ የሰጠኝን ይህንን ልብስ ልበሺ ልብሱ የነገሥታት ልብስ ነውና አንቺ ትለብሽው ዘንድ ይገባሻል አለቻት።

ሐና ግን አዝና ነበርና ብቸኛ በመሆኔ፣ ልጅም ስለሌለኝ ኀዘንተኛ ነኝና ያማረ ልብስን አለብስም፤ ደግሞም ማን እንደሰጠሽ በምን አውቃለሁ? እኔንም ከኃጢአትሽ ልትጨምሪኝ ነውን? አለቻት። ሴቲቱም በምላሹ ተናዳ እግዚአብሔር ማኅጸንሽን በመዝጋቱ ደግ አድርጓል አለቻት።

ሐናም ከቀድሞው አብልጣ አዘነች። ፈጥና ተነስታም ወደቤተ መቅደስ ሔደች። አእዋፋትንም ከልጆቻቸው ጋር ባየች ጊዜ አንስሳት አራዊት ልጆች አላቸው፤ ምድር እንኳን ፍሬ አላት ለእኔ ግን ልጅ የለኝም፤ ለሁሉ ልጅ አለውና ለእነርሱ ልጅን የሰጠህ ወደእኔ ተመልከት ልጅንም ስጠኝ ብላ እያለቀሰች ትጠይቅ ነበር።

ቅድስት ሐና ሆይ እግዚአብሔርስ አንቺን ሳይመለከት ቀርቶ አይደለም። ከተናገረው ቀን ሳያጓድል ይመጣ ይወርድ ይወለድ ዘንድ ያለበትን ጊዜ እየጠበቀ ነበር እንጂ። እነሆም ቀኑ ደረሰ እግዚአብሔርም ወደአንቺ አየ ስእለትሽን ሰማ ልመናሽንም ተቀበለ ልጅንም ሰጠሽ፤ በአንቺም ዘንድ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም "ነጸረ አብ እምሰማይ ወኢረክበ ዘከማኪ" ያላትን ከፍጡራን መካከል አምሳያ የሚተካከል የሌላትን አንድያ እናቱን አገኘ።

ቅድስት ሐናም ነጭ ርግብ መጥታ በራሷ ላይ ተቀምጣ ከራሷ ላይም ወርዳ በጆሮዋ ገብታ በማሕፀኗ ስትተኛ በራእይ ተመለከተች። እነሆም በሐምሌ 30 ቀን የጌታ መልአክ (ቅዱስ ገብርኤል) ከሰማይ ወርዶ በፊቷ ቆመ፤ ጸሎትሽ ተሰምቷል ልምናሽንም ተቀብሏል ትፀንሻለሽ አላት። እርሷም ልጅን ከሰጠኝስ እስከ ዘመኑ ፍጻሜው ድረስ እንዲያገለግል ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ አለች። መልአኩም ወደ ኢያቄምም ሔዶ ይህንን ብሥራቱን አበሠረው።ኢያቄምም ተደስቶ ሁለት በጎችንና 12 ላሞችን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።

አንድ ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ንጽሕት ብጽእት ድንግል ማርያምም ነሐሴ 7 ቀን በብሥራተ መልአከ በንጹሕ መኝታ ተጸነሰች። ስለ ጽንሰቷም የብሕንሳው ሊቀጳጳስ አባ ኅርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ .... ድንግል ሆይ ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነሽ አይደለሽም በሕግ በንጹሕ መኝታ ከኢያቄምና ከሐና ተወለድሽ እንጂ... በማለት ንጹሕ ከሆነ አልጋ ንጹሕ ከሆነ መኝታ መገኘቷን ይናገራል። ጠቢቡ ሰሎሞንም.. ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ምንም ነውር የለብሽም።.. (መኃ 4፥7) ብሎ ከማኅጸን ጀምሮ ጥንተ አብሶ እንደሌለባት ያስረዳናል።
#ተአምረ_ማርያም_እምማኅፀነ_ሐና


ሐናና ኢያቄም ይባረኩ ዘንድ ወደ ቤተመቅደስ ሔዱ። ዘካርያስም መልአኩ ለሐና እንዲነግራት ያዘዘውን ልትባረክ ስትመጣ ይነግራት ጀመረ።"ሐና የምነግርሽን ነገር ስሚ፤ በልቦናሽም ጠብቂው ከዚህ በኋላ ከባልሽ ከኢያቄም ጋር አትተኚ፤ በማኅጸንሽ ያለው ፍሬ ለእግዚአብሔር ንጹሕ መሥዋዕት ነውና። ይኸውም በዚያን ዘመን ሙሴ የተመለከተው ዕጽ ነው። በውስጡም እሳት ይነድ ነበር፤ ፍሬውንም አላቃጠለውም፤ ይኽም በበረሓው ድንኳን ውስጥ ያስቀመጡትን የወርቅ መሶብ፣ ከሰማይ የወረደ፣ ለዓለሙ ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ የተሰወረ መና ያለበት ነው። ዛሬም ለእግዚአብሔር የተቀደሰና ንጹሕ ቁርባንን እስከምትወልጂ ድረስ (ከጉድፍ) ከጉስቁልና ትጠበቂ ዘንድ አዝዝሻለው። ሥራውንም ለዓለሙ ሁሉ ለልጅ ልጅ ይናገራሉ አላት።" ሐናም ይኽን ነገር በልቧ እየጠበቀች በረከትን ተቀብላ ወደቤቷ ሔደች።

ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም በሐና መጽነስ ተደስተው ይጎበኟቸው ነበር። ከእነዚህም መካከል ሀና ቤርሳቤህ የተባለች የአጎቷ የአርሳባን ልጅ ተደንቃ ማኅጸኗን ስትዳስሳት አይኗ በርቶላታል።

ሌላም ሐና የምትወደው ሳሚናስ ወልደ ጦሊቅ በሞተ ጊዜ ተግንዞ ወደተኛበት ሄዳ የአልጋውን ሸንኮር ይዞ በምታለቅስበት ወቅት ጥላዋ ቢያርፍበት ከተኛበት ተነስቶ .. ሰማይንና ምድርን ለፈጠረው አምላክ አያቱ የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ  ይሁን .. አላት፤ አይሁድም ደንግጠው ምን አይተህ እንዲህ አልክ? አሉት።

እርሱም "ከዚህ ከሐና ማኅጸን የምትወለደው ሕጻን ሰማይ ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማኋቸው፤ እኔንም ያነሣችኝ እርሷ ናት" አለ በዚህም አይሁድ በማኅጸን ባለች ጽንሷ እንዲህ ካደረገች በእኛ ልትሰለጥን አይደለምን ብለው በምቀኝነት ተነሳሱባት። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጾ ሐናን ሊባኖስ ወደሚባል ተራራ እንዲወስዳት ነገረው።#ጊዜ_ልደት_በደብረ ሊባኖስ

ሐናና ኢያቄምም በደብረ ሊባኖስ እያሉ ግንቦት 1 ቀን ሐና እመቤታችንን ወለደች። ቅዱስ ያሬድም ይህንን በማሰብ ...ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ፤ ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ። ኢያቄምና ሀና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማይቱም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን አወጣችልን  ... አለ።

ስለ ጊዜ ልደቷም ሲናገር "በእንተ ልደታ ለማርያም አድባር ኮኑ ኅብስተ ሕይወት ወእምዕጸወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት" .. ድንግል ማርያም ስትወለድ ድንጋዮቹ ተራሮቹ ሁሉ የሕይወት እንጀራ (ምግብ) ሆኑ እጽዋትም ሁሉ የሕይወት ፍሬ አፈሩ በማለት ይገልጽልናል።

ሐናና ኢያቄምስ ወላጅነታችሁ ድንቅ ነው። በእውነት በመጽሐፍስ መካን የነበሩ ብዙ ደጋግ ቅዱሳን የተባረከ ልጅን ወልደዋል። እናንተ ግን ለፍጥረተ ዓለም በጸጋ፤ ለፈጣሪ ደግሞ በግብር እናት የምትሆንን ልጅ ወልዳቹሃልና። ለእናንተ ልጅ ናት ለኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድያ እናቱ ናት።

አብርሃምና ሣራ ብሩክ ዘር የሚሆን ይስሐቅን ወለዱ፤ ሐናና ኢያቄም ግን የምድርን አሕዛብ ይባርክ ዘንድ አምላክ የሚወለድባትን ዘር ለዓለም ሰጡ።

ሐና አልቅሳ ለእሥራኤል መስፍን ለቤተ መቅደስም አገልጋይ የሚሆን ሳሙኤልን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን ለአማናዊው ድኅነት መፈጸሚያ የሆነች ቤተመቅደስን ወለዱ።

ራሔል አልቅሳ ያዕቆብንና ዘሩን ከምድራዊ ረኃብ ከጊዜያዊ ሞት ለጊዜው የሚቤዣቸውን ዮሴፍን ወለደች፤ ሐናና ኢያቄም ግን አዳምን ከነልጆቹ ከዘለዓለማዊው ሞት አንስቶ ለዘለዓለማዊ ድኅነት በማብቃት የሚቤዣቸውን ክርስቶስን  የምታስገኘውን፤ እርሷም በፍቅሯ እየጠራች ስለኃጢአታቸውም ምሕረትን እየለመነች የምታድናቸውን መድኃኒት ወለዱ።
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
ኢያቄም እና ሐና ከነገሥታቱ ከይሁዳ ወገን የሚሆን ኢያቄም ቀለዮጳ የሚባል አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር። እርሱም ከካህናቱ ከነገደ ሌዊ የምትወለደውን ሐናን አገባ። እነርሱም የተቀደሱ ደጋግ ነበሩ። በደቂቀ እሥራኤል ዘንድም አብዝተው መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀንም ከደቂቀ እሥራኤል ወገን የሆነ ሮቤል የተባለ ሰው መጣና " በእኛ ፊት መሥዋዕትን ታቀርብ ዘንድ አይገባም፤ በእሥራኤል…
ሐናና ኢያቄምስ ከዚህ በፊት ከነበሩት ወላጆች ሁሉ ከበሩ፤ በክብር በሞገስም ከፍ ከፍ አሉ ለአምላክ አያቱ ሆነዋልና፤ ዘርን በማስቀረት ረድኤቱን በማድረግ ለአዳምና ለልጆቹ ሲሰጥ ለነበረ አምላክ እናቱን ስጦታ/መባዕ አድርጋችሁ ሰጥታቹሃልና። ይኸውም መባዕ ቅድሚያ ብቸኛ እናት ልትሆነው የምትችለውን (እስከ እርጅና ያለልጅ የቀራችሁበትን ጊዜ በእምነት ታግሳችሁ ከሌላ ሳትሄዱ) በመውለዳችሁ፤ ሁለተኛም ለእርሱ አገልጋይ ሆና ነየ አመቱ ለእግዚእነ ... እኔ ለጌታ ባሪያው ነኝ .. የምትል ለታላቂቱ አገልግሎት (ለድኅነተ አዳም) የተመረጠች ልጅን ስለሰጣችሁ ነው።

"ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፤ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና (ሃይማኖት) ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።"

              🕯መኃ 4፥8🕯

ጠቢቡ ሰሎሞን በትንቢት መነጽር ልደቷን ተመልክቶ በሊባኖስ እንደምትወለድ በሳኔር በተመሰለ ከኢያቄም በኤርሞንም በተመሰለች ከሐናም እንደምትወለድ፤ የአንበሶች የነብሮች ተራራ በማለት ከሁለቱ ኃያላን ከቤተ መንግሥት እና ከቤተ ክህነት ወገን እንደምትወለድ ተናግሯል።

የእመቤታችን ልደት የተከናወነው በደጅ፤ ከፍ ባለ ተራራ ላይ ነው። በዚህ መወለዷም የእርሷ ልደት ለዓለም ሁሉ ጥንተ መድኃኒት መሆኑና ለሁሉ የተሰጠች ስጦታ መሆኑን ለማመልከት ነው።

በስደት ላይ ያለ ሰው የላመ የተዘጋጀ ምግብ የለውምና ሐናና ኢያቄም ንፍሮ እየበሉ እመቤታችንን በደብረ ሊባኖስ መውለዳቸውን በማሰብ በዓሉን ከደጅ ወጥተን ንፍሮ በመብላት እናከብረዋለን። በበዓሉም ምዕመናን ለከርሞ ብንደርስ በማለት ብጽዓት/ ስእለት ይሳላሉ። ዕለቱን ከኪዳን ከማኅሌት ከቅዳሴው በመሳተፍ፣ ቅዱስ ቁርባኑን በመቀበል፣ ጸበል በመጠጣት በመጠመቅ፣ የእመቤታችንን የምስጋና መጻሕፍትን በተለይም መልክአ ልደቷን በማድረስ፣ በመመጽወት የታመሙትን የታሰሩትን በመጠየቅ ማክበር ይገባናል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።                                 
            
  ዋቢ መጻሕፍት📚
1.መጽሐፍ ቅዱስ የ፳፻ ዕትም
2.ድርሳነ ማርያም
3. መኃልይ መኃልይ ዘሰሎሞን ማብራሪያ በመጋቤ ሐዲስ ስቡሐ አዳምጤ
4. መዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ ትንሳኤ ዘጉባኤ እትም
5.የእመቤታችን በዓላት በመ/ር ተስፋሁን ነጋሽና መ/ር ኤርምያስ ወ/ኪሮስ
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
Voice message
ዮም ፍስሐ ኮነ ሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንስአ ክርስቶስ እሙታን 2*

ቀደሳ ወአክበራ 2* ወአልዓላ እምኲሎን መዋዕል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
         
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን አጋዕዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
በፍስሐ ወሰላም

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላቹ ጋር ይሁን የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች። እንኳን ለእናችን ወላዲተ አምላክ ልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ።

እንደ ከዚህ ቀደሙ የግቢ ጉባኤያችንን የልደቷን ቀን ልናስታውሳችሁ ዛሬ መጣን። የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ ለተከታታይ 25  ዓመታት  ብዙ የእግዚአብሔር  ቤት አገልጋዮችን ያፈራ ግቢ ጉባኤ ነው።

🌺ግንቦት 25/2016 ዓ.ም 🌺

እነዚህ የእግዚአብሔር  ልጆች ተሰብስበው ያላቸውን ትውስታ ገጠመኝ  የሚወያዩበት  ልዩ የሆነ  የቤተሰብ መርሐግብር ተዘጋጅቷል። በዕለቱ  ቀድሞ የነበሩን ግቢ ጉባኤያችን የሰጠችን እናት እና አባታችንን  አያቶቻችን ቅድመ አያቶቻችንን የምናገኝበት ልዩ መርሐግብር ይሆናል። ከወዲሁ   ተዘጋጅታቹ   በዕለቱ   ትውስታን የምናስቀርበት  መርሐግብር እንዲሆንልን በየባቻቹ የምታውቋቸውን እህት ወድሞቻችሁን ይዛችሁ ወደ እናታቹ ቤት ለመምጣት ቀጠሮን ያዙ።

እስኪ ሁላችንም በአገልግሎት በነበርንበት ጊዜ የማንረሳውን ወይም ግቢ ጉባኤያችን ይህን ስላደረገችልን አመሰግናታለሁ ብለን የምናስበውን ነገር ከስር በሀሳብ መስጫው ላይ ያስቀምጡልን።


ግንቦት 25 / 2016 ዓ.ም ቸር ያገናኘን🙏

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
እንደምን አመሻችሁ የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን?

  በነገው ዕለት ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ቀን እመቤታችን የጽዋ መርሐግብር በግቢ ጉባኤያችን የሚኖረን ይሆናል።

  በመርሐ ግብሩም ላይ እንደሁል ጊዜው ምሳችንን ለነዳያን ይዘን በመምጣት ለነፍሳችን ስንቅ የምናቆይበት መርሐ ግብር ይኖረናል።

  በመቀጠልም የሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ የሕይወት ትምህርት ተማምረን ለሕይወታችን ስንቅ ይዘን ለመሄድ በሰዓታችን ማለትም በ6:00 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሻችን እንድንገናኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም ልናሳስባችሁ ወደድን።

ግንቦት 3/2016 ዓ.ም

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን ያድለን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

እንኳን ለዳግም ትንሳኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።

ክቡራን ቤተሰቦቻችን በዕለተ ሰንበት ግንቦት 11/2016 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ህፃናትን ለመጠየቅ ቀጠሮ እንደያዝን የሚታወስ ነው። ለጥየቃ መርሐ ግብራችንም ያመቸን ዘንድ “10 ብር ለነፍሳችን” ብለን በየቀኑ ለቁርሳችን የሆነውን 10 ብር ስናስቀምጥ እንደነበር አንጠራጠርም።

አሁን ደግሞ ካጠራቀምነው ገንዘብ ሌላ ለልጆቹ የሚሆን የተረት መጽሐፍ ፣ ቀለም ያላቸው እና የተስፋ ቃልን ያዘሉ የሚለጣጠፉ ወረቀቶች ፣ የስዕል ደብተሮች እንዲሁም ለልጆች የሚሆኑ ማናቸውም አስደሳች ቁሶች ይዘን መምጣት የምንችል ይዘን እንድንመጣ በልዑል እግዚአብሔር ስም በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ከነገ ጀምሮም ያጠራቀምነውን ገንዘብ ይዘን እንምጣ ስንል በታላቅ ትህትና ነው።

ሰላም ያገናኘን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሰላም ውድ የግቢ ጉባኤ እህቶቻችን   እንደምን ሰነበታችሁልን?


እግዚአብሔር ቢወድድ እና ቢፈቅድ ኆኅተ ብርሃን ሰነበት ትምህርት ቤት ግንቦት 6/16 በሰ/ትቤቱ አዳራሽ ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የጉባኤ አንስት መርሐ ግብር ስለተሰናዳ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲገኙልን እናም
ሲመጡ ሌሎች ላልሰሙ እህቶቻችን አሰምታችሁ እንድትጋብዟቸው በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

እህቴ እንዳያመልጥሽ!

ኆኅተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት


ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

ማስታወቂያ 📢

እግዚአብሔር ቢፈቅድልን እኛ ላሰብነው የትንሳኤ መርሐ ግብር ላይ ለሚቀርብ ወረብ ልምምድ (ጥናት) እየተጠና ይገኛል እና ተማሪዎች ሰዓታችሁን እንደምንም አመቻችታችሁ ጥናቱን እንድትሳተፉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

ጥናቱም በዛሬው ዕለት ማለትም ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም ከ 6:00 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናልና ወረቡ ላይ ያለን ሁላችንም በልዑል እግዚአብሔር ስም በሰዓቱ ተገኝተን እንድናጠና ይሁን።

እግዚአብሔር አምላክ የቅዱስ ያሬድን ረድኤት ፤ በረከት ያሳድርብን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ) pinned «የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን። ማስታወቂያ 📢 እግዚአብሔር ቢፈቅድልን እኛ ላሰብነው የትንሳኤ መርሐ ግብር ላይ ለሚቀርብ ወረብ ልምምድ (ጥናት) እየተጠና ይገኛል እና ተማሪዎች ሰዓታችሁን እንደምንም አመቻችታችሁ ጥናቱን እንድትሳተፉ ለማሳሰብ እንወዳለን። ጥናቱም በዛሬው ዕለት ማለትም ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም ከ 6:00 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናልና…»