Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
978 subscribers
844 photos
39 videos
93 files
29 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ቻናል ነው። በግቢ ጉባኤው የሚከናወኑ ማንኛውንም ተግባራት፣መረጃዎችን፣መልዕክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል።
Download Telegram
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•የምሥረታ መዝሙር ጥናት•

ውድ ቤተሰቦቻችን እግዚአብሔር አስችሎን ለምሥረታ በዓላችን ይደርስልን ዘንድ ባሳለፍነው ማክሰኞ ዕለት የመዝሙር ጥናት እንደጀመርን የሚታወስ ነው። ጥናቱም በዛሬው ዕለት ማለትም ዓርብ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም ከ 9:30 ሰዓት እስከ 10:30 ሰዓት የሚቀጥል ስለሆነ ሁላችንም በሰዓቱ እንድንኝ አደራ ለማለት ወደድን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ውድ የግቢ ጉባኤ ቤተሰቦቻችን።

•የደም ልገሳ ቀን•

“ደም በማጣት የምታልፍን ሕይወት ካለን ላይ ሳይጎድል በማካፈል እንታደግ።”

ነገ ቅዳሜ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም ከመርሐ ግብር ሰዓት በኃላ ወይንም ከ 6:00 ሰዓት ማንም ሊለግስ ቢወድ እንዳይቀር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ደረሰ ደረሰ ደረሰ
🌸"የግቢ ጉባኤያችን የ 25 ዓመት ጉዞ"🌸

በብዙ የጓጓንለት  የልደቷ ቀን 7 ቀናት ብቻ ቀሩት
ከ አንድ ዓመቷ ጀምሮ እስከ 24 ዓመቷ ድረስ ሻማ ስታበሩ የነበራችሁ ሁላችሁ  የዛሬ ሳምንት ግንቦት 25/2016 ዓ.ም መገኛችሁን ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን  አድርገን የ25ተኛ ዓመት የምሥረታ በዓሏን  ሻማ 🕯️ በጋራ  አብረን እናብራ ።
መሰብሰቢያችን፣ ህይወትን ያገኘንብሽ፣ መልካም እህት እና ወንድም የሰጠሽን፣ በዓለም ውስጥ ከመጥፋት ያዳንሽን  ግቢ ጉባኤያችን  እንኳን ለልደት በዓልሽ አደረሰሽ🙏
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

እንኳን ደስ አላችሁ ፥ ለምሥረታ በዓላችን እነሆ 6 ቀናት ብቻ ቀሩን…

ውድ ቤተሰቦቻችን ሁላችንም እንደምናውቀው እሑድ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም የግቢ ጉባኤያችንን 25ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እናከብራለን ፤ ለዚያችም ልዩ ዕለት ዝግጅታችንን ከወዲሁ እየጨረስን እንደሆነ በማመን በዕለቱ የዝማሬ መርሐ ግብር ስለሚኖረን ሁሉም አንደበት በኅብረት እግዚአብሔርን ያመሰግነው ዘንድ ከታች የምናጋራችሁን መዝሙሮች እያጠናችሁ ዕለቱን እንድትጠባበቁ ስናሳስብ በታላቅ ትህትና ነው።

ግንቦት 25 ቸር ያገናኘን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ይረድአነ አምላክነ አምላክነ ወመድኃኒነ
አምላክነሰ አምላከ አድኅኖ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ
ትርጉም:
ይረዳናል አምላካችን (፪) መድኃኒታችን
አምላካችን የምሕረት አምላክ ነው ምስጋና ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ
እመቤታችን ማርያም ማህበራችንን
ጠብቂልን በምልጃሽ

ከጠላት ሰይጣን ከከሃድያን
ከጠላት ሰይጣን ሰውረሽን
እንድትጠብቂን በምልጃሽ
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ) pinned «ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም! እንኳን ደስ አላችሁ ፥ ለምሥረታ በዓላችን እነሆ 6 ቀናት ብቻ ቀሩን… ውድ ቤተሰቦቻችን ሁላችንም እንደምናውቀው እሑድ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም የግቢ ጉባኤያችንን 25ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እናከብራለን ፤ ለዚያችም ልዩ ዕለት ዝግጅታችንን ከወዲሁ እየጨረስን እንደሆነ…»
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•ኦርቶዶክሳዊት ሴት እና ዓለማዊ ሕይወት•

የምንወዳችሁ እና የምናከብራችሁ እህቶቻችን እግዚአብሔር አስችሎን በዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከ6:20 ሰዓት ጀምሮ ለእህቶች የተዘጋጀ ልዩ ጉባኤ የሚኖረን ይሆናል።

በዚያም ጉባኤ ላይ “እማሆይ ዜና ማርያም” ልዩ ተጋባዥ እንግዳችን ናቸውና “ኦርቶዶክሳዊት ሴት እና ዓለማዊ ሕይወት” በሚለው ሀሳብ ላይ ተንተርሰው ዕውቀት እና ጥበባቸውን ሊያካፍሉን በመከካላችን የሚገኙ ይሆናል ፤ እኛም ደግሞ ሕይወትን እናገኝበት ዘንድ መጥተን በሰዓቱ ጉባኤውን እንድንካፈል እህቶችን ከታላቅ ትህትና ጋር ልናሳስብ ወደድን።

ቀን • ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም
ሰዓት • ከ 6:20 ሰዓት - 7:20 ሰዓት ድረስ
አድራሻ • ገርጂ ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ

እህቶች መቅረት ዋጋ ያስከፍላልና በጎውን እንማር ዘንድ አደራ እንዳንቀር።

ማሳሰቢያ

ላልሰሙ እህቶችም እንድናሰማ እና ከያለንበት ተጠራርተን እንድንመጣ በልዑል እግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•የወረብ ጥናት•

ክቡራን የምትሆኑ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦቹ በሰኔ 1/2016 ዓ.ም ለሚኖረን የዝክረ ቅዱስ ያሬድ መርሐ ግብር ላይ የወረብ አገልግሎት ስለሚኖር ጥናት ከወደሁ ጀምረናልና በነገው ዕለትም ከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ የወረብ ጥናቱ ስለሚኖር በሰዓቱ ተገኝተን እንድናጠና አደራ ለማለት ወደድን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ሐምሰ ዕለታተ ፤ ትዕምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ ፤ ሚመጠነ ማርያም ታስተፌሥሒ ትፍስሕተ ፤ ኅድረሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሑ መዓልተ ፤ ብፁዕ ዘርዕየኪ በሕልሙ ሌሊተ ፡፡

ትርጉም

“የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሳ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል !

በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ሁሉ ምስጉን ነው"

አባ ጽጌ ድንግል

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ

ግንቦት 21 / 2016 ዓ.ም

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
4 ቀናት ብቻ ቀሩት
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•ኦርቶዶክሳዊት ሴት እና ዓለማዊ ሕይወት•

የምንወዳችሁ እና የምናከብራችሁ እህቶቻችን እግዚአብሔር አስችሎን በዕለተ ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከ6:20 ሰዓት ጀምሮ ለእህቶች የተዘጋጀ ልዩ ጉባኤ የሚኖረን ይሆናል።

በዚያም ጉባኤ ላይ “እማሆይ ዜና ማርያም” ልዩ ተጋባዥ እንግዳችን ናቸውና “ኦርቶዶክሳዊት ሴት እና ዓለማዊ ሕይወት” በሚለው ሀሳብ ላይ ተንተርሰው ዕውቀት እና ጥበባቸውን ሊያካፍሉን በመከካላችን የሚገኙ ይሆናል ፤ እኛም ደግሞ ሕይወትን እናገኝበት ዘንድ መጥተን በሰዓቱ ጉባኤውን እንድንካፈል እህቶችን ከታላቅ ትህትና ጋር ልናሳስብ ወደድን።

ቀን • ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም
ሰዓት • ከ 6:20 ሰዓት - 7:20 ሰዓት ድረስ
አድራሻ • ገርጂ ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ

እህቶች መቅረት ዋጋ ያስከፍላልና በጎውን እንማር ዘንድ አደራ እንዳንቀር።

ማሳሰቢያ

ላልሰሙ እህቶችም እንድናሰማ እና ከያለንበት ተጠራርተን እንድንመጣ በልዑል እግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

•የምሥረታ መዝሙር ጥናት•

የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችነ በዛሬው ዕለት ጉባኤያችንን እንደጨረስን ማለትም ከ7:30 ሰዓት ጀምሮ የምሥረታ መዝሙር ጥናት ስለሚኖረን ሁላችንም በሰዓቱ እንድንገኝ አደራ እንላለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ