Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
977 subscribers
846 photos
39 videos
93 files
29 links
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ቻናል ነው። በግቢ ጉባኤው የሚከናወኑ ማንኛውንም ተግባራት፣መረጃዎችን፣መልዕክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል።
Download Telegram
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
Voice message
ዮም ፍስሐ ኮነ ሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንስአ ክርስቶስ እሙታን 2*

ቀደሳ ወአክበራ 2* ወአልዓላ እምኲሎን መዋዕል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
         
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን አጋዕዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
በፍስሐ ወሰላም

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላቹ ጋር ይሁን የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች። እንኳን ለእናችን ወላዲተ አምላክ ልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ።

እንደ ከዚህ ቀደሙ የግቢ ጉባኤያችንን የልደቷን ቀን ልናስታውሳችሁ ዛሬ መጣን። የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ ለተከታታይ 25  ዓመታት  ብዙ የእግዚአብሔር  ቤት አገልጋዮችን ያፈራ ግቢ ጉባኤ ነው።

🌺ግንቦት 25/2016 ዓ.ም 🌺

እነዚህ የእግዚአብሔር  ልጆች ተሰብስበው ያላቸውን ትውስታ ገጠመኝ  የሚወያዩበት  ልዩ የሆነ  የቤተሰብ መርሐግብር ተዘጋጅቷል። በዕለቱ  ቀድሞ የነበሩን ግቢ ጉባኤያችን የሰጠችን እናት እና አባታችንን  አያቶቻችን ቅድመ አያቶቻችንን የምናገኝበት ልዩ መርሐግብር ይሆናል። ከወዲሁ   ተዘጋጅታቹ   በዕለቱ   ትውስታን የምናስቀርበት  መርሐግብር እንዲሆንልን በየባቻቹ የምታውቋቸውን እህት ወድሞቻችሁን ይዛችሁ ወደ እናታቹ ቤት ለመምጣት ቀጠሮን ያዙ።

እስኪ ሁላችንም በአገልግሎት በነበርንበት ጊዜ የማንረሳውን ወይም ግቢ ጉባኤያችን ይህን ስላደረገችልን አመሰግናታለሁ ብለን የምናስበውን ነገር ከስር በሀሳብ መስጫው ላይ ያስቀምጡልን።


ግንቦት 25 / 2016 ዓ.ም ቸር ያገናኘን🙏

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
እንደምን አመሻችሁ የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን?

  በነገው ዕለት ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ቀን እመቤታችን የጽዋ መርሐግብር በግቢ ጉባኤያችን የሚኖረን ይሆናል።

  በመርሐ ግብሩም ላይ እንደሁል ጊዜው ምሳችንን ለነዳያን ይዘን በመምጣት ለነፍሳችን ስንቅ የምናቆይበት መርሐ ግብር ይኖረናል።

  በመቀጠልም የሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ የሕይወት ትምህርት ተማምረን ለሕይወታችን ስንቅ ይዘን ለመሄድ በሰዓታችን ማለትም በ6:00 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሻችን እንድንገናኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም ልናሳስባችሁ ወደድን።

ግንቦት 3/2016 ዓ.ም

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን ያድለን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

እንኳን ለዳግም ትንሳኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።

ክቡራን ቤተሰቦቻችን በዕለተ ሰንበት ግንቦት 11/2016 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ህፃናትን ለመጠየቅ ቀጠሮ እንደያዝን የሚታወስ ነው። ለጥየቃ መርሐ ግብራችንም ያመቸን ዘንድ “10 ብር ለነፍሳችን” ብለን በየቀኑ ለቁርሳችን የሆነውን 10 ብር ስናስቀምጥ እንደነበር አንጠራጠርም።

አሁን ደግሞ ካጠራቀምነው ገንዘብ ሌላ ለልጆቹ የሚሆን የተረት መጽሐፍ ፣ ቀለም ያላቸው እና የተስፋ ቃልን ያዘሉ የሚለጣጠፉ ወረቀቶች ፣ የስዕል ደብተሮች እንዲሁም ለልጆች የሚሆኑ ማናቸውም አስደሳች ቁሶች ይዘን መምጣት የምንችል ይዘን እንድንመጣ በልዑል እግዚአብሔር ስም በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ከነገ ጀምሮም ያጠራቀምነውን ገንዘብ ይዘን እንምጣ ስንል በታላቅ ትህትና ነው።

ሰላም ያገናኘን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሰላም ውድ የግቢ ጉባኤ እህቶቻችን   እንደምን ሰነበታችሁልን?


እግዚአብሔር ቢወድድ እና ቢፈቅድ ኆኅተ ብርሃን ሰነበት ትምህርት ቤት ግንቦት 6/16 በሰ/ትቤቱ አዳራሽ ከ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የጉባኤ አንስት መርሐ ግብር ስለተሰናዳ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲገኙልን እናም
ሲመጡ ሌሎች ላልሰሙ እህቶቻችን አሰምታችሁ እንድትጋብዟቸው በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

እህቴ እንዳያመልጥሽ!

ኆኅተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት


ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን።

ማስታወቂያ 📢

እግዚአብሔር ቢፈቅድልን እኛ ላሰብነው የትንሳኤ መርሐ ግብር ላይ ለሚቀርብ ወረብ ልምምድ (ጥናት) እየተጠና ይገኛል እና ተማሪዎች ሰዓታችሁን እንደምንም አመቻችታችሁ ጥናቱን እንድትሳተፉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

ጥናቱም በዛሬው ዕለት ማለትም ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም ከ 6:00 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናልና ወረቡ ላይ ያለን ሁላችንም በልዑል እግዚአብሔር ስም በሰዓቱ ተገኝተን እንድናጠና ይሁን።

እግዚአብሔር አምላክ የቅዱስ ያሬድን ረድኤት ፤ በረከት ያሳድርብን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ) pinned «የክርስቶስ ፍጹም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን። ማስታወቂያ 📢 እግዚአብሔር ቢፈቅድልን እኛ ላሰብነው የትንሳኤ መርሐ ግብር ላይ ለሚቀርብ ወረብ ልምምድ (ጥናት) እየተጠና ይገኛል እና ተማሪዎች ሰዓታችሁን እንደምንም አመቻችታችሁ ጥናቱን እንድትሳተፉ ለማሳሰብ እንወዳለን። ጥናቱም በዛሬው ዕለት ማለትም ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም ከ 6:00 ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናልና…»
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ)
Voice message
እንደምን አመሻችሁ እናንት ውድ ቤተሰቦቻችን…

ማስታወቂያ 📢

በነገው ዕለት የትንሳኤ ወረብ ጥናት 7:30 ላይ ስለሚኖር ሁላችንመወ በሰዓት እንድንገኝ እናሳስባለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
Unity Gebi-Gubae( ዩኒቲ ግቢ-ጉባኤ) pinned «እንደምን አመሻችሁ እናንት ውድ ቤተሰቦቻችን… ማስታወቂያ 📢 በነገው ዕለት የትንሳኤ ወረብ ጥናት 7:30 ላይ ስለሚኖር ሁላችንመወ በሰዓት እንድንገኝ እናሳስባለን። ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ»
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ፥ በዓቢይ ኃይል ወስልጣን ፥ አሰሮ ለሰይጣን ፥ አጋዕዞ ለአዳም
ሰላም ፥ እምይእዜሰ ፥ ኮነ ፥ በፍስሐ ወሰላም።

ከስድስቱ ቃላተ ወንጌል መካከል አንዱ የሆነው “ታምሜ ጠይቃችሁኛልና” የሚለውን የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል እና ትዕዛዝ ለመፈጸም ያስችለን ዘንድ እሑድ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም በእግዚአበ‍እሔር አጋዥነት የተሰናዳው የጥየቃ መርሐ ግብር 3 ቀናት ብቻ ቀሩት።

በዋነኝነት ያጠራቀምነውንም ገንዘብ ከዛሬ ጀምሮ እየያዝን እንድንመጣ እና በቢሮ ስም እና ስልክ እያስመዘገብን እንድናስቀምጥ አደራ በማለት በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ፥ በዓቢይ ኃይል ወስልጣን ፥ አሰሮ ለሰይጣን ፥ አጋዕዞ ለአዳም
ሰላም ፥ እምይእዜሰ ፥ ኮነ ፥ ፍስሐ ወሰላም።

ማስታወቂያ 📌

ቅዳሜ ቀን ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ በገርጂ ኆኅተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የክርስቶስን ትንሣኤ በኅብረት ሆነን እናከብር ዘንድ ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን በትህትና ታስተላልፋለች።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ማስታወሻ

በነገው ዕለት ሁላችንም ያጠራቀምነውን ገንዘብ ይዘን እንድንመጣ እና ለእሑዱ የህሙማን ጥየቃ መርሐ ግብራችን እንድናሟላ በልዑል እግዚአብሔር ስም በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ዛሬ አይቀርም!!!

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ሰላም ውድ ወንድም እና እህቶቻችን በነገው ዕለት ለሚኖረን የጥየቃ መርሐ ግብር ከዚህ በፊት እንደገለጽነው ለልጆቹ የሚሆን ፦
• የተረት መጽሐፍ ፣
• የስዕል ደብተር ፣
• የሚያስደስቱ ቀለም ያላቸው ቁሶች ፣
• ተስፋን ያዘሉ መልዕክቶች ይዘን መምጣታችን እንዳለ ሆኖ የቻልን ደግሞ
• ስኳር ፣
• የንጽሕና መጠበቂያዎች ፣
• ሳሙና ፣
• ሶፍት ፣
• ኦሞ ፣
• ዳይፐር እና
• ለልጆች የሚሆኑ ልብሶችን ይዘን ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ በግቢ ጉባኤያችን እንገናኝ።

በአካል መገኘት ላልቻላችሁ ደግሞ የቻላችሁትን ከስር ባለው የባንክ ሂሳብ እንድታስገቡልን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

🏦 CBE 1000261402401 • Hewan Hailu

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም!

"ባንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደሆነው፥መሰብሰባችንን አንተው ርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ"።
•••ዕብ.10÷25•••

የተከበራችሁ የቀድሞ አባላትና ተማሪዎች አንኳን ለዩነቲ ግቢ ጉባኤ 25ተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን እያልን የግቢ ጉባኤያችን 25ተኛ የምሥረታ ዓመት ግንቦት 25/2016 ዓ.ም ከ5:00 ሰዓት ጀምሮ ይከበራል። ስለሆነም በዚህ በዓል ላይ አብራችሁን እንድትገኙ ስንል በግቢ ጉባኤው ስም በአክብሮት ጠርተናችኋል።

ለዚሁ በዓል ዝግጅት ይረዳን ዘንድ በዕለቱ የሚወጣ ዕጣ አዘጋጅተናል።

ትኬቱን ለማግኘት በቴሌግራም አድራሻ @Arsema212121 ወይም በ @Sofi2124 ያነጋግሩን።

ግንቦት 25 ቸር ያገናኘን!

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለግቢ ጉባኤያችን ምስረታ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም  በገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ አይቀርም

የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ