Tsegaye R Ararssa
16.2K subscribers
1.69K photos
252 videos
164 files
2.51K links
TA
Download Telegram
Itiyophiyaan uummata Tigrayif hin tolle Oromoo dhaaf tolti jettee hin dhama’in. Injifannoon Adwa uummata Tigray hammachuu dadhabe Oromoo hammachuu hin danda’u.

Itiyoophiyaan Haacaaluu ajjeefattee Jawartu na hafe jettee shubbisaa maraattu eenyufuu hin taatu.

Itiyophiyaan Baqqalaa Garbaa umriisaa guutuu mana hidhaatti deddeebistee dararaa baatee, har’as du’asaa dheebottu, Oromoo dhaf hin taatu.

Oromoonni Itiyophiyaa dhaaf akka gaariitti ergamaa turan tokkoon isaaniituu abbaa biyyaa hin taane. (OPDOn barcuma nafxanyaa marsitee eegdu duris jirti. Har’as guutteet yaati. Seenaan barcuma jaraa marsanii eeguu kun seenaa qabsoo Oromoo, seenaa gootummaa Oromoo ibsu dha, jechuun of gowomsuu dha.

#Liqimsi!

ለትግራይ ልጆች ያልተመቸች ኢትዮጵያ፣ ለኦሮሞ ትመቻለች ብለህ አትድከም::

የትግራይን ህዝብ ማቀፍ ያልቻለ የአድዋ ድል ፍሬ፣ ኦሮሞን (እና ሌሎቹን' የኢትዮጵያ ሌሎች ህዝቦች) ሊያቅፍ አይችልም፤ ሊያቅፍ ይችላል ብለህ አትድከም። ብዙዎች ሞክረው ሞክረው ሞክረው አቅቶአቸዋል።

ሃጫሉን ገድላ፣ ጀዋር ይቀረኛል ብላ በጭፈራ ያበደች ኢትዮጵያ፣ ለአንተም ለማንም አትሆንም።

በቀለ ገርባን እድሜውን ሙሉ በእስር ቤት እያመላለሰች አሰቃይታ ስታበቃ፣ በዚሁ ዘመን በአደባባይ (በሚዲያ) ሞቱን የምትናፍቅ/ሞቱን የምትጣራ ኢትዮጵያ፣ ለኦሮሞ አትሆንም።

ለኢትዮጲያ በወግ የተላላኩ (ኢትዮያ አገራችን ነው ብለው በታላቅ ብቃት ያገለገሉ) ኦሮሞዎች ብዙ ነበሩ:: አንዳቸውም የዜግነት እኩልነት እና የአገር ባለቤትነት ክብር አልተጎናፀፉም፣ ልጆቻቸውም በአገር አፍራሽነት ከመከሰስ ወይም ከመጠርጠር አልተረፉም። (ከዚህ በተረፈ፣ ዙፋኑን ከበው 'ሚጠብቁ ኦሮሞዎች ድሮም ነበሩ፣ ዛሬም አሉ። (የኦህ-dead አይነት ዙፋን ተንከባካቢ መች ጠፍቶ!?!) ይህ የመላላክ እና ዙፋን የማገድ ታሪክ ግን የኦሮሞ ህዝብ የትግል ገድል ወይም የኦሮሞን ጀግንነት የሚያሳይ ታሪክ ነው ብሎ መመፃደቅ ግን እራስን መደለል (እንደውም በሚያሳፍረው መኩራት) ነው።

ባንዶችን ለማጀገንና ጀግኖችን ከታሪክ ለመሠረዝ በሚደረግ የታሪክ መቀራመት ሂደት ውስጥ "እኛም ጥሩ አሽከር ነበርን" እያሉ መፎከር፣ ወይ ታሪክን አለማወቅን ነው፣ ወይ እራስን መስደብ ነው።

#ትኩረት!!!!
#የራስህን_ታሪክ_ፃፍ!