TobiaTube
111 subscribers
65 photos
5 videos
4 files
54 links
Download Telegram
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማሕበር የመንግስት ሚዲያዎች የቤተክርስቲያኒቱን ጉዳይ ሳይዘግቡ መቅረታቸውን በተመለከተ መግለጫ አወጣ።
የጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ሥነ ስርዓት በኋላ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት በሥፍራው ከነበሩ ሰዎች ደረሰኝ ባለው መረጃ መሰረት፤ "ዮናስን ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከምሽቱ 5 ዓአት ገደማ ከነባለቤቱ አስረው ወስደዋቸዋል።" ያለ ሲሆን፤ ባለቤቱ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብትፈታም ዮናስ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ገልጿል።

በትናንትናው ፕሮግራም ላይ "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ ምክንያት "ልጅቷን አምጡ" በሚል አዘጋጆቹ ተጠይቀው እንደነበር እና እስሩም ከእሱ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በሥፍራው የነበሩ ግለሰቦች እና ሌሎች ምንጮች ማረጋገጣቸው ተነግሯል።

በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዘርፍ ላይ ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ጥበበኞች በመሸለም የሚታወቀው "ጉማ አዋርድ" ዘጠነኛው የሰማያዊ ምንጣፍ ጉማ የፊልም ሽልማት ትናንት ሰኔ 02/2015 በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል።

በዚህም የሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ አንጋፋው ኪሮስ ኃ/ሥላሴ የ9ኛው ጉማ አዋርድ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሲሆን፤ የአርዓያ ሰብ ከያኒ በሚል ዘርፍ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመስራት ላይ የምትገኘው እና በትወናው ዘርፍ በርከት ያሉ ሥራዎችን ያበረከተችው አርቲስት መሠረት መብራቴ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ታጭተው የ9ኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊ የሆኑ የፊልም ባለሙያዎችም በምሽቱ ተሸላሚ ሆነዋል።

አሁን ላይ በአገራችን የተለያዩ ዓመታዊ የሽልማት ሥነስርዓቶች በየወቅቱ የሚዘጋጁ ሲሆን፤ በእነዚህም መድረኮች ላይ ተጋባዥ እንግዶች የተለያዩ አልባሳት፣ ጌጣጌጦችን እና ሜካፕ በመጠቀም፤ ባህልን፣ እሴትንና አመለካከትን ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል።

በትናንትናው ፕሮግራም ላይም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተለያዩ አልባሳት እና ጌጣጌጦች ተውበው የብዙሃን ቀልብ ስበዋል። ከእነዚህ ውስጥም የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጇ እጩ ዶ/ር ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ) ግንባሯን በጥይት እርሳስ የተቦደሰች አፏን በሽቦ የተሰፋች ሴትን ለመወከል የተጠቀመችው የብዙዎችን ትኩረት ስቦ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼር አድርጉለት🙏
ጃቢ :- አባቴ የታመመው የአእምሮ ካንሰር ነው😭
አንጋፋው የebs ፕሮግራም መሪ አስፋው መሸሻ አሁን ስላለበት ሁኔታ ልጁ ጃቢ የተናገረው አባቴ የታመመው የአእምሮ ካንሰር ነው ታሞ ወደ አሜሪካ ሲመጣም ግራ እጅ እና እግሩን ማዘዝ ተስኖት ግማሽ ፓራላይዝ ሆኖ ነበር
እንደመጣም በጆርጅ ዋሽንግተን ሆስፒታል ለ 42 ቀናት ህክምና ከተደረገለት በኋላ ከሆስፒታል እንዲወጣ ተደርጓል ሆኖም ግን የራዲዬሽን (የጨረር) ህክምናውን ለማድረግ የ24 ሰዓት ክትትል ስለሚያስፈልገውና አንዳንዴም የመርሳት ችግር ስላለበት ወደ ነርሲንግ ሆም አስገብተነዋል
በቀጣይም ከነርሲንግ ሆም አውጥቼ ወደ ቤቴ እንዳልወስደው የእኔ ቤት ደረጃ ስላለው ለሱ የሚሆን አይነት ባለመሆኑ ሌላ ቤት ተከራይቼና የህክምና ክትትሉም እንዳይቋረጥ ነርስ ቀጥሬ ላኖረው ነበር ያሰብኩት
ይሄንን ሁሉ ለማድረግ ደግሞ ብቻዬን ስላልቻልኩኝ እርዳታችሁ አስፈልጎኛል እኔ እራሱ እሱን ለማስታመም ወደ 2 ወር ገደማ ስራ በማቆሜ EBS ቴሌቭዥን ደሞዜን አስቦ እየከፈለኝ ነው እስካሁን ያለሁት
ስለዚህ በመላው ዓለም ያላችሁ የአባቴ ወዳጆች ሆይ ከቤት ኪራይ እስከ ነርስ ክፍያ እንዲሁም የጤና ኢንሹራንሴ የማይሸፍናቸው ወጪዎችን ታግዙን ዘንድ በከፈትነው GO Fund Me በኩል ያቅማችሁን እንድትረዱን በአክብሮት እጠይቃለሁ::
የGo Fund Me ሊንኩ:- https://gofund.me/77ca526b
🙏🙏🙏
almaz1.jpg
17.3 KB
የአትሌት አልማዝ አያና ወንድም ባለሃብቱ አቶ ተሰማ አያና በሾፌራቸው ተገደሉ!

ባለሃብቱ አቶ ተሰማ አያና ከወንበራ ወረዳ ገሰንጌሳ ቀበሌ እራሳቸዉ ይዘውት በመጡት ትራክተር ሾፌር በትናትና እለት ተገድለው የያዙት ንበረት ዘርፎ ከቦታው ላይ መሰወሩን ከወንበራ ወረዳ የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል።
በአዲስ አበባ ከተማ የ 6 ት/ቤቶች ዕውቅና ተሰረዘ

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን የካ ቅርንጫፍ አዋጅና መመሪያ ጥሰዋል፣ ሥርዓተ ትምህርቱን አልተከተሉም ያላቸውን በየካ ክፍለከተማ የሚገኙ 5 የቅዱስ ሚካኤል ት/ቤቶች የዕውቅና ፈቃድ ከታህሳስ 5/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዙን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ እርምጃውን ለመውሰድ ካስቀመጣቸው ምክንያቶች መካከል ት/ቤቶቹ በመመዝገቢያና በክፍያ ላይ ያደረጉት እንዲያስተካክሉ ተጠይቀው ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ አፋን ኦሮሞ ትምህርት በቢሮው በተቀመጠው ሥርዓት መሠረት አለመፈፀሙ የሚሉ ይገኝበታል።

በተመሳሳይ ሁኔታ አፖሎ ግሎባል ቅድመ አንደኛ ት/ቤት ሕግና ሥርዓት በመጣስ የዕውቅና ፈቃዱ ከታህሳስ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተሰርዟል።
መልካም ዜና ቤተሰብ ወደ አሜሪካ ለማምጣት ለምትፈልጉ፤ አዲሱ መመሪያ ከአንድ ቤተሰብ በላይ ማስመዝገብ ተፈቀደ
https://www.merejatoday.com/watch.php?vid=d09afefe2
ቶሞካ ቡና የ48 ሚሊዮን ብር ክስ በደንበል ሲቲ ሴንተር ላይ መሰረተ

ቶሞካ ቡና ኃ/የ/ የግል ማህበር በደምበል ሲቲ ሴንተር ላይ የ48 ሚሊዮን ብር የጉዳት ካሣ እንዲከፈለው የሚጠይቅ ክስ መመስረቱ ታዉቋል።

ቶሞካ ቡና ደምበል ሲቲ ሴንተር ተብሎ በሚጠራው ህንፃ ዉስጥ ከጥር 07/2011 ጀምሮ እስከ ጥር 06/2021 ድረስ ለአስር ዓመታት ይቆይ የነበረዉ የኪራይ ዉል ከህግ ዉጪ እንዲቋረጥ በመደረጉ የጉዳት ካሳ እንዲከፈለኝ ሲል ነዉ ክስ የመሰረተዉ።

"ለቡና መሸጫ አገልግሎት በማከናወን ላይ እንዳለሁ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከ ንኮማድ ኮንስትራክሽን ኃ/የ/ የግል ማህበር የንግድ ኪራይ ዉል መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሰዉ በመግለፅ የመብራት መስመር አገልግሎቱ እንዲቋረጥ እና ካፌዉ እንዲዘጋ ተደርጓል" ማለቱን ካፒታል ከክሱ መረዳት ችሏል።

ቶሞካ ቡና በደምበል ሲቲ ሴንተር ህንፃ ዉስጥ በስራ ላይ በቆየበት ዓመታት ለህንፃዉ እድሳት ያወጣዉን ወጪ እና ከህግ ዉጪ ዉሉ እንዲቋረጥ በማድረጉ የ48 ሚሊዮን 272 ሺህ ብር ጉዳት ካሣ እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ ሲል ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያስገባው አቤቱታ ያስረዳል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ካፒታል በሳምንታዊ ጋዜጣዉ ላይ ዝርዝር መረጃን ይዞ ይመለሳል።
ምንጭ:- ካፒታል
ጀግናዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ አደረገች

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በማዕከላዊ ትግራይ ክልል አበርገሌ የጭላ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የስንዴ ድጋፍ አደረገች። አትሌቷ 70 ኩንታል ስንዴ ለ280 ሰዎች ተከፋፍሏል።

በወረዳው ከ113,000 በላይ ሰዎች ለረሃብ የተጋለጡ ሲሆኑ 83 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ህይታቸው እንዳለፈ ከአበርገሌ የጭላ ወረዳ ኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ቱርክ የቴሌቪዥን ዜና አንባቢዋን ከስራ አገደች

ዜና አንባቢዋ የታገደችው ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የስታር ባክስ ቡናን ይዛ በመቅረቧ ነው

ቱርክ ስታር ባክስን ጨምሮ የእስራኤል ጦርን ይደግፋሉ በሚል ማገዷ ይታወሳል
ቱርክ የቴሌቪዥን ዜና አንባቢዋን ከስራ አገደች፡፡

የቱርኩ ቲጂአርቲ የተሰኘው መንግስታዊ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሜልተም ጉናይ የተሰኘችውን አንጋፋ ዜና አንባቢ ከስራ ማገዱ ተገልጿል፡፡

ጋዜጠኛዋ በዜና ሰዓት የአሜሪካው ስታርባክስ ቡናን ይዛ መቅረቧ ብዙዎችን ያስቆጣ ሲሆን የሚዲያው አመራሮችም ጋዜጠኛዋ ህግ በመጣስ ላደረገችው ድርጊት ከስራ ማገዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

የቴሌቪዥን ጣቢያው በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ ጋዜጠኛ ሜልተም የድርጅቱን ህጎች በመጣስ በቀጥታ ስርጭት ወቅት ብዙ ስህተቶችን እንደፈጸመች ገልጿል፡፡
ስታርባክስ ኩባንያ ከእስራኤል-ጋዛ ጦርነት በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት ወቅት የትኛውንም ምርት ማስተዋወቅ እንደማይቻል የሚደነግገው የድርጅቱ ህግ መጣሱንም አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ከጋዜጠኛ ሜልተም በተጨማሪ የቴሌቪዥኑ ዳይሬክተርም ከስራ የታገደ ሲሆን የቴሌቪዥኑ ድርጊት የብዙ ብዙሃን መገናኛዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
ምንጭ:- አል አይን
አሶሳ የተባለችው መርከብ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምፅዋ መላኳ ተሰማ

ኢትዮጵያ አሶሳ የተሰኘችዉን የንግድ መርከብ ከአምስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤርትራ የወደብ ከተማ ወደሆነችዉ ምፅዋ መላኳ ተዘግቧል።

መርከቧ ታህሳስ 17 ከጅቡቲ ተነስቶ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ምፅዋ መድረሷ ነዉ የተነገረው።

ይህ እድገት የመጣዉ መቐለ የተባለችው የኢትዮጵያ መርከብ 11,000 ቶን ኤርትራ ዚንክ በመያዝ ከምፅዋ ወደ ቻይና በ2018 በማቅረቧ ሳቢያ የሁለቱ ሀገራት መቀራረብ ማሳያ ሳይሆን እንዳልቀረ የኤርትራ ፕረስ ዘገባ ያሳያል ።

በዚሁ አመት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች አሰብን ሌላውን የኤርትራ ወደብ ለማዘመን እና ሁለቱን ሀገራት ከ4 መስመሮች ጋር የሚያገናኘውን መንገዱን ለማስፋት ማቀዱንም አስታውቀዋል።
(ካፒታል)
ኢትዮጵያ ለሱማሊላንድ ዕውቅና ለመስጠት መስማማቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታው አመለከቱ

ራስ ገዟ ሱማሊላንድ እንደ ሀገር የሚያስቆጥራትን “ዓለማ አቀፋዊ ዕውቅና” ከኢትዮጵያ ለማግኘት ከስምምነት ላይ መድረሷን በመግለጽ ያወጣችውን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አስታወቁ።

አምባሳደር ምስጋኑ ያስተላለፉት ይህ መልዕክት ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ለሱማሊላንድ ዕውቅና ልትሰጥ መሆኑን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ የመጀመሪያው አስተያየት ነው።

ኢትዮጵያ ለወታደራዊ እና ለባሕር ንግድ አገልግሎት የሚውል የባህር በር ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት ከሱማሊላንድ ጋር መድረሷን ያስታወቀችው ትላንት ሰኞ ታህሳስ 23፤ 2016 ዓ.ም. ነበር።

በዕለቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ይህንን የተመለከተ የመግባቢያ ስምምነት እንደተፈራረሙ በሁለቱ መንግሥታት ይፋ ተደርጓል።

ከፊርማ ስነ ስርዓቱ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚንስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በመግባቢያ ሠነዱ መሠረት ኢትዮጵያ ለ50 ዓመት የሚቆይ የባሕር ጠረፍ ሊዝ ስምምነት እንደምታገኝ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአንጻሩ የኢትዮ ቴሌኮምን ወይም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ድርሻ ለሱማሊላንድ እንደምትሰጥ ሬድዋን አስታውቀዋል።

በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ሱማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ግን ሀገራቸው በሊዝ ለምትሰጠው 20 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው የባሕር ጠረፍ ተጨማሪ ጥቅም ከኢትዮጵያ እንደምታገኝ አመልክተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ ኢትዮጵያ “ለሪፐብሊክ ኦፍ ሶማሊላንድ በይፋ ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ አገር ትሆናለች” ብለዋል።

ከ23 ዓመታት ገደማ በፊት ራሷን ከሶማሊያ ገንጥላ ነጻነቷን ያወጀችው ሱማሊላንድ እስካሁን ደረስ ከየትኛው ሀገር እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋም እንደ ሀገር የሚያስቆጥራትን እውቅና አላገኘችም።

ከትላንቱ ስምምነት በኋላ የሱማሊላንድ የውጭ ጉዳዮች እና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ላይም የእውቅና ጉዳይ በተመሳሳይ ተስተጋብቷል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ለመስጠት የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመችው በምላሹ “ዓለም አቀፋዊ እውቅና” ለማግኘት መሆኑን አስታውቋል።

“ይሄ ታሪካዊ ስምምነት ለሶማሊላንድ ሪፐብሊክ መደበኛ እውቅና በመስጠት ለባሕር ኃይሏ የባሕር በር እንደምታገኝ ያረጋግጣል” ሲል በመግለጫው የስምምነቱን ጭብጥ ያስረዳል።

የሱማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴም በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ “በመግባቢያ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለሱማሊላንድ ሪፐብሊክ እውቅና ስትሰጥ፤ ሱማሊላንድ ደግሞ ለ50 ዓመት በሚቆይ ሊዝ ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል እና ለንግድ አገልግሎት የሚውል ባህር ትሰጣለች” ሲሉ ይህንን ሀሳብ አጠናክረዋል።

ኢትዮጵያ ለሱማሊላንድ እውቅና ለመስጠት መስማማቷ ከሀርጌሳ በኩል በተደጋጋሚ ቢነሳም ከአዲስ አበባ በኩል በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ማብራሪያም ሆነ ማረጋገጫ አልነበረም።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ ዛሬ በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ግን ከሱማሊላንድ በኩል የተነሳውን ይህንን ጉዳይ ኢትዮጵያም እንደምትጋራው አስታውቀዋል።

የሱማሊላንድ የውጭ ጉዳዮች እና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር የሰጠውን መገለጫ በቲውተር ገጻቸው ያጋሩት ሚኒስትር ዲኤታው፤ ከመግለጫው ጋር ባያያዙት መልዕክት “በሱማሌላንድ መንግሥት የተሰጠውን መግለጫ እንቀበላለን” ሲሉ የኢትዮጵያ መንግሥት በመግለጫው ላይ የተነሱትን ጉዳዮች እንደሚስማማባቸው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ እና በሱማሊላንድ መካከል ተደርጓል የተባለው ይህ ስምምነት ግን ሱማሊላንድን የግዛቷ አንድ አካል አድርጋ በምትቆጥረው ሶማሊያ በኩል ቁጣን ቀስቅሷል።

የሶማሊያ መንግሥት ካቢኔ ዛሬ ማክሰኞ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ እና የሱማሊላንድ ስምምነት ሕጋዊ መሠረት የሌለው እና ተፈጻሚ ሊሆን የማይችል ነው ብሏል።

የሶማሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሩን አቡድላሂ ዋርፋንም ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።
(ቢቢሲ)
ስምምነቱ ሶማሊላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት ያስችላል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈረመው የትብብር መግባቢያ ስምምነት ሰነድ በዛሬው እለት ማብራሪያ ሰጥቷል።

በሰጠው ማብራሪያም፤
ስምምነቱ ለኢትዮጵያ በኤደን ባህረሰላጤ ላይ ዘላቂና አስተማማኝ የባሕር ኃይል ቤዝ እና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት በሊዝ የምታገኝበትን ዕድል የሚያስገኝ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መንግሥት አስቀድሞ ይፋ ባደረገው አቋሙ መሠረት ሶማሌ ላንድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሊዙ የሚታሰብ ድርሻ እንዲኖራት ያስችላል ብሏል መግለጫው።

ከዚህ ባሻገር በሂደት ሶማሌ ላንድ ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት በጥልቀት አጢኖ አቋም የሚወስድበትን አግባብ ያካትታል ብሏል።

በስምምነቱም ሁሉም ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም የቀጣናው ሰላም የሚገዳቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ሁሉ ሊደሰቱ ይገባል ሲል አክሏል።

በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም፤ የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም ሲል መግለጫው አብራርቷል።

በተያያዘ ዜና
የአውሮፓ ኅብረት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ማክበር ያስፈልጋል ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡
ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ለኢትዮጵያ የባሕር ጠረፍ ያስገኛል የተባለ የመግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረት የሶማሊያን ሉዓላዊነት ማክብር አስፈላጊ ነው ብሏል።

የአውሮፓ ኅብረት የስምምነቱን መፈረም አስመልክቶ ባወጣው አጭር መግለጫ የፌደራል ሪፐብሊክ ኦፍ ሶማሊያ ሕገ-መንግሥት እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተሮች መሠረት የአገሪቱን አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር ጠቃሚ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን ብሏል።

በአውሮፓ ኅብረት ቃል አቀባይ በኩል ትናንት የወጣው መግለጫ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋገትን ለማስፈን የሶማሊያ ሉዓላዊነትን ማክበር ቁልፍ መሆኑንም ህብረቱ አመልክቷል።

(Ethio FM)