ትምህርት ሚኒስቴር ™️
158K subscribers
385 photos
2 videos
38 files
431 links
📚ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው

📚 This unique channel is prepared by the community request.

Any comment & Paid Ads @Tmhrt_Ministers_bot

《Buy Ads :- https://telega.io/c/tmhrt_ministers1

#ትምህርት_ሚኒስቴር
Download Telegram
በ2015 ዓ.ም ከ91 ተቋማት የመጡ 4,413 የትምህርት ማስረጃዎችን ማጣራቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ።

የማጣራት ሥራ ከተደረገባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ውስጥ 3 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት
ሐሰተኛ ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል።

ውጤት መቀየር፣ ያልተማሩበትን የትምህርት ማስረጃ መያዝ እና ሌሎች ሐሰተኛ መረጃዎች መገኘታቸውን በአገልግሎቱ የዲጂታል ትምህርት መረጃ አስተዳደርና አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደሳለው ታፈሰ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ሐሰተኛ ሰነዶችን ማምከንና ግለሰቦቹን ከሥራ በማገድ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

ተቋማት ሠራተኞችን ሲቀጥሩና የደረጃ እድገት ሰሲጡ የትምህርት ማስረጃዎችን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ኃላፊው አሳስበዋል፡፡ #FBC

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!


Share -> @Tmhrt_Ministers
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድረሻ አከላት ጋር መክሯል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትምህርት ሥርዓቱ ን ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፌዴራል እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፈተናው የተሳካ እንዲሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው÷የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ተቋሙ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎችና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን÷በቀጣይ ሁሉንም ተማሪዎች በኦንላይን ለመፈተን ሙከራ ይደረጋል መባሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM