ትምህርት ሚኒስቴር
224K subscribers
604 photos
2 videos
47 files
602 links
📚 This unique channel is prepared by the community request.

Any comment & Paid Ads @Tmhrt_Ministers_bot

《Buy Ads :- https://telega.io/c/tmhrt_ministers1

#ትምህርት_ሚኒስቴር
Download Telegram
#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ታህሳስ 05 እና 06/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ 

የምዝገባ ቦታ፦
በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች

ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ከመምጣታችሁ በፊት https://portal.aau.edu.et ላይ በመግባት Freshman የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የግል መረጃቻችሁን እንድታሟሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➢ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

Note:

በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ ከታህሳስ 08 እስከ 12/2016 መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
https://portal.aau.edu.et/ ወይም http://aau.edu.et


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

የመውጫ ፈተና በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 06 እና 07/2016 ዓ.ም በሰባት የፈተና ማዕከላት ይሰጣል፡፡

የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ኮዶች፦

1.  MC: Main Campus; 6 ኪሎ ካምፓስ
2.  CoBE: College of Business and Economics; FBE ካምፓስ
3.  AAiT: Addis Ababa Institute of Technology Campus; 5 ኪሎ ካምፓስ
4.  CNCS: College of Natural and Computational; 4 ኪሎ ካምፓስ
5.  CHS: College of Health Sciences; ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ካምፓስ
6.  SoC: School of Commerce; ሰንጋ ተራ ካምፓስ
7.  EiABC: Ethiopian Institute of Architecture, Building Construction, and City Development; ልደታ ካምፓስ

በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ማዕከላት የመውጫ ፈተና ለምትወስዱ የፈተና መግቢያ ሊንክ (ረዕቡ መስራት የሚጀምር) 👇 https://exam1.ethernet.edu.et


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

አንጋፋው አዲስ አበበ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ለ74ኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ስነ-ስርዓት ያስመርቃል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU #GAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ 

በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደ ፈተና ማዕከል መርጣችሁ ለነበራችሁ ተፈታኞች ፈተናው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ፈተናው መስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም በሚከተሉት ሰባት ተቋማት ውስጥ ይሰጣል፦

1. በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣
2. በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
3. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
4. በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት፣
5. በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ፣
6. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
7. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፡፡

የተሰጣችሁን የመፈተኛ ስም (Username) ተጠቅማችሁ በሚደርሳችሁ የመፈተኛ ማዕከል እና የፈተና ሰዓት (Exam Session) መሰረት ፈተናው ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጾች (https://aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

• የመመዝገቢያ ቀናት ከማክሰኞ ጳጉሜ 05/ 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 08/ 2017 ዓ.ም ድረስ
• የዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በዩኒቨርሲቲዉ ማህበራዊ ሚዲያ እና ድረ ገጾች ላይ ይገለጻል ።

(አ.አ.ዩ ሬጅስትራር)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነጻ የትምህርት እድል (ሶኮላርሺፕ) ሊሰጥ እንደሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የመጀመርያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ስርዓት ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና ይሰጣል። በዚህም ብቃትን፣ ብዝሃነትንና ፍትሐዊነትን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን በውድድር ነፃ የትምህርት እድል ከዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎት ጋር እንደሚሰጥ አሳውቋል።

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ " ብቃትና ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች መዳረሻ ለመሆን ያለኝን ቁርጠኝነት እገልጻለሁ " ብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

ለ2017 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ ት/ት አመልካቾች የፈተና ቀናት ስለማሳወቅ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AAU

ለ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ ለመማር ቅበላ ያገኛችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ከአዲስ አበባ ውጪ የምትመጡ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የማደሪያ አገልግሎት ለተሰጣችሁ ብርድ ልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ አለባችሁ፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትኖሩ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል https://portal.aau.edu.et/NewStudent/DormitoryPlacement በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በመርካቶ፣ በላምበረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያቀርብ መሆኑን ገልጿል።

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ሆኖ ቅበላ ያገኛችሁ ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እና ዶክመንቶች ይዛችሁ ሪፖርት የምታደርጉት ሰኞ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለሁሉም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ (Orientation) ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የትምህርት ኮርሶች ምዝገባ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM