ትምህርት ሚኒስቴር
231K subscribers
670 photos
2 videos
47 files
658 links
📚 This unique channel is prepared by the community request.

Any comment & Paid Ads @Tmhrt_Ministers_bot

《Buy Ads :- https://telega.io/c/tmhrt_ministers1

#ትምህርት_ሚኒስቴር
Download Telegram
#ExitExam

📌ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች
📌ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የመውጫ ፈተናን ድጋሚ የሚወስዱ ተፈታኞችን ይመለከታል፤

በ2015 የትምህርት ዘመን በሁሉም የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል፡፡በተሰጡት ፈተናዎች የማለፊያ ነጥብ #ያላገኙ ተፈታኞች በጥር ወር መጨረሻ ላይ ለዳግም ፈተና እንዲቀመጡ ታቅዷል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ተፈታኞች በተቋማት እየኖሩ ስላልሆነ ተገቢውን ዝግጅት ለማድረግ እየተቸገሩ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይገልፃሉ፡፡

በመሆኑም ተቋሞቻችሁ በሚችሉት መንገድ ተፈታኞቹ #ቤተመጽሐፍት መጠቀም እንዲችሉ አስፈላጊው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉላቸው እንጠይቃለን፡፡  [ትምህርት ሚኒስቴር]

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam

የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትፈተኑ አመልካቾች በሙሉ‼️

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስለሆነም በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትናችሁ ያላለፋችሁ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የምታካሂዱትና የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የምትመርጡት ከታች በተገለጸው ማስፈንጠሪያ (Link)
( https://exam.ethernet.edu.et )
ስለሆነ፣ ከጥር 08 እስከ ጥር 15/ 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በቴሌ ብር ብቻ በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል registration@ethernet.edu.et በኩል ድጋፍ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ‼️
➡️ ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የምታካሂዱት  እና የአገልግሎት ክፍያ የምትፈፅሙት በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam #Result

በመቐለ ዩንቨርሲቲ የመውጫ ፈተና የወሰዳቹህ ተማሪዎች ውጤታችሁን ከዛሬ ጀምሮ በኮሌጆቻቹህ በኩል ማየት እንደምትችሉ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ፈተናውን 250 ሺህ ለሚደርሱ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ገልጿል፡፡

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና እንዳሉት፥ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲወጡ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመለካት የሚሰጥ ነው፡፡

የሚወጡ ጥያቄዎችም የየትምህርት ክፍሎች ምሩቃን እንዲኖራቸው የሚጠበቀውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ናቸው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቅሰው፤ፈተናው ተዘጋጅቶ እንዲገመገም ተደርጓል ነው ያሉት።ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ዝርዝር በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተረጋግጦ ነው ወደ ሚኒስቴሩ የሚላከው ብለዋል፡፡

በፈተናው ሞባይል ይዞ የሚመጣና መታወቂያ ሳይዝ የሚመጣ ተማሪ ፈተናውን መውሰድ እንደማይችል ጠቅሰው፥ ተማሪዎች ይህን አውቀው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam
#Re_Exam
#UnityUniversity

ድጋሚ የመውጫ ፈተና ሰኔ ላይ ለምትወስዱ
(June 2016 Re-Exit Exam)

1. 2015 ዓ.ም ለመፈተን ተመዝግባችሁ "Username"  ወስዳችሁ፣ ፈተናውን ያልወሰዳችሁ እና በቀጣዩ ሰኔ ላይ መውሰድ የምትፈልጉ ተማሪዎች፣ በአካል እስከ አርብ ድረስ ቢሮ ቁጥር 02 ማመልከት ይኖርባችኋል።

2. በ2016 የካቲት ላይ "username" ወስዳችሁ ያልተፈተናችሁ ቀጥታ መመዝገብ ስለምትችሉ ቢሮ መምጣት አይጠበቅባችሁም።

3. ፈተናውን በድጋሚ የምትወስዱ ተማሪዎች፣ ምዝገባና ክፍያ በራሳችሁ ሲሆን፣ ቀኑን እንዳሳወቁን እናሳውቃለን።

4. ክፍያ የሚከፈለው በቀጥታ በቴሌብር ለትምህርት ሚኒስቴር ነው።


🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam #ReExam

የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።
2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል። ( የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር)

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam

ለ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ከዛሬ 10፡45 ጀምሮ ለፈተና የምትጠቀሙበትን የይለፍ ቃል
👇
https://exam7.ethernet.edu.et/login/index.php ብቻ በመግባት እንድትቀይሩ እናሳስባለን፡፡

ሊንኩ አልከፍት ካላቹህ በግቢያቹህ ኔትዎርክ(ዋይፋይ) ሞክሩት።

©Wolkite University

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተናዎች እየተሰጡ ነው፡፡

የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እና በድጋሜ ተፈታኞች ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

የአካውንቲንግ እና ሕግ ፈተናዎችን ጨምሮ የሰባት ትምህርት አይነት ፈተናዎች ዛሬ ሙሉ ቀን እየተሰጡ ነው፡፡ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው እስከ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ምስል፦ ቦረና፣ አዲግራት እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam #Result

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል።

በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#PrivateCollege #ExitExam

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ከትምህርት ሚኒስቴር ለተቋማቱ በመላክ ላይ መሆኑን ሰምተናል።

የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሲደረግ እናሳውቃቹሃለን።።

የመውጫ ፈተና ውጤት ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ቀድሞ የተላከ ሲሆን ተማሪዎችም ውጤታቸውን በተቋማቸው በኩል በማየት ላይ ይገኛሉ።


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam

የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ?

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

ይህን ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን አድርሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት ዴስክን ጠይቀናል።

" ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን " የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር)  ተናግረዋል።

" ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ በበኩላቸው ፥ " ከግል ተፈታኞች አጠቃላይ መረጃ እና ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚለቀቅ "  ተናግረዋል።

ማኅበሩ 178 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአባልነት ይዟል፡፡

የግል ተቋማት ተማሪዎች የፈተና ውጤት ለተቋማቱ አለመላኩን ከተቋማት በኩል ባገኘነው መረጃ የተረዳን ሲሆን ከሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ተልኳል፣ እየተላከ ነው ፣ ውጤት ሊለቀቅ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሀሰተኛ እንደሆነ ተገንዝበናል። 


ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

🔻የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ 🫥

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM