ትምህርት ሚኒስቴር
104K subscribers
293 photos
2 videos
81 files
50 links
ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support Us🙏

ማስታወቂያ ለማስነገር በዚህ ያናግሩን
@Adis_probot
Download Telegram
የመጀመሪያው ዙር አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከረዕቡ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በዛሬው የሦስተኛ ቀን ፈተና፣ በጠዋቱ መርሐግብር የታሪክ ትምህርት ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡

ሁለተኛው ዙር ፈተና ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://aa.ministry.et/account#/student-result

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219  በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል !

የ8ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ተለቋል። ወንድም ሴትም 50ና ከዚያ በላይ ያመጡ ናቸው ወደ ሚቀጥለው ክፍል የሚያልፉት። የአካል ጉዳተኞች ማለፊያ ነጥብ 45 እና ከዚያ በላይ ነው።

78 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞቻችን አልፈዋል።

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል። ”__

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መመልከቻ : https://aa.ministry.et/account#/student-result
(መለያ ቁጥርና ስም ያስገቡ)
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
በወረቀትና በኦንላይ የሚሰጠውን የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል።

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ ከ 9-11/ 2016 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በበይነ መረብ (Online) እና በወረቀት ፈተናው ይሰጣቸዋል።

ፈተናውን የምትወስዱ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በሙሉ መልካም እድልን እንመኝላችኋለን።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በመላ አገሪቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በጠዋቱ መርሐግብር የእንግሊዝኛ ፈተና እየተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የሒሳብ ትምህርት ፈተና ይሰጣል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል፡፡

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 09/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን በመላ አገሪቱ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በዛሬው የሦስተኛ ቀን ፈተና፤ በጠዋቱ መርሐግብር የኬሚስትሪ ትምህርት ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ በከሰዓቱ መርሐግብር የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በትግራይ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ሲሆን፤ ነገ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል፡፡
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንደሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በከተማዋ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው፥ በ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,046 ተማሪዎች መካከል 80,198 ተማሪዎች ወይም 94.3 በመቶዎቹ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡ ወይም ከስር የተቀመጠውን የቴሌግራም ቦት ይጠቀሙ፡፡

ውጤት ለማየት፦ https://aa6.ministry.et/#/result

በቴሌግራም ቦት፦ **@emacs_ministry_result_qmt_bot

@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
#እንዳያመልጥዎ!

ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን
#ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች።

ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል።

ምን መማር ይቻላል ?

- Android Kotlin Development Fundamentals
- Data Science Fundamentals
- Programming Fundamentals

ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?

ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው።

ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ።

ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል።

የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ (
https://ethiocoders.et/ ) ላይ መመልከት ይችላሉ።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፋም ተባለ

የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ እንደሆነ ተነግሯል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ አሳልፈዋል ተብሏል።

202 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘንድሮ የመውጫ ፈተና ተማሪዎቻቸውን ቢያስፈትኑም 22ቶቹ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ኘ/ር) ተናግረዋል::
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ የሚካሔደው ከሐምሌ 24/2016 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመሆኑም በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶችን በሟሟላት በተጠቀሰው ጊዜ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

ለመመዝገብ 👇
https://NGAT.ethernet.edu.et

@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡

በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ነጥብ 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡ በክልሉ የገጠር አካባቢዎች ለተፈተኑ የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 48፣ ለሴቶች 45 ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 45 እና ለሴቶች 42 እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የ6ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት 👇
https://oromia6.ministry.et/#result

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

የ8ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት 👇
https://oromia.ministry.et/#result

የ8ኛ ክፍል ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
የጤና ባለሙያዎች የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት

በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም የተሰጠው የጤና ባለሙያዎች የመውጫ እና ብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተመዛኞች ከዛሬ ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል regulatory.moh@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁ እና የጤና ሚኒስቴርን የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች ከነሐሴ 03/2016 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ይላካል ተብሏል።

በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ይህን ተከትሎ በሚወጣ ማስታወቂያ የተግባር ምዘና (OSCE) ፈተና የምዝገባ መርሐግብር ስለሚወጣ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ዝቅተኛ ነጥብ 50 በመቶ ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኞች 45 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም በክልሉ 110,772 መደበኛ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 48,728 ወይም 44 በመቶ ተማሪዎች 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች https://ce.ministry.et/ ላይ የአድሚሽን ቁጥራቸውንና ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
@Timihirt_Minister
@Timihirt_Minister