TIKVAH-ETHIOPIA
1.42M subscribers
55.2K photos
1.38K videos
199 files
3.7K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) #NBE @tikavhethiopia
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦

" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility) ይስጣል፡፡

እነዚህ የአንድ ቀን የብድር ወይም የተቀማጭ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ምክንያት ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ፍሰት አቋማቸውን ለማስተካከል እንዲረዳቸው ነው፡፡

እነዚህ ቋሚ አገልግሎቶች የሚሰጡት ከብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን 3 በመቶ በማስበለጥ ወይም በማሳነስ ይሆናል፡፡ "

#NBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
#Africa

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ " ደመወዘኔን 40 በመቶ እቀንሳለሁ " ሲሉ አስታወቁ።

ጽ/ቤታቸው፤ " ፕሬዜዳንቱ ይህ እርምጃ የሚወስዱት ተጠያቂ አስተዳደር በመፍጠር አርዓያ ለመሆን እና ከዜጎች ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ነው " ብሏል።

ፕሬዚዳንት ቦአካይ ፥ ከጥቂት ወራት በፊት ዓመታዊ ደመወዛቸው 13 ሺህ 400 ዶላር (769 ሺህ ብር በላይ) እንደሆነ ገልጸው አሁን ባቀረቡት 40 በመቶ ቅነሳ ወደ 8 ሺህ ዶላር (459 ሺህ ብር በላይ) ያደርሰዋል።

የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የዚህ ዓመት በጀት ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር ይጠጋል።

አንዳንዶች የፕሬዚዳንቱን የደመወዝ ቅነሳ እርምጃ ቢያደንቁም ሌሎች ግን እንደ ዕለታዊ አበል እና የህክምና ሽፋን ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ጠቅሰው " ይህ በእውነት መስዋዕትነት ነው ወይ ?  ሲሉ ጠይቀዋል።

ከሳቸው በፊት የነበሩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ደመወዛቸውን 25 በመቶ ቀንሰው ነበር።

በሀገሪቱ ባለው ከፍተኛ ኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ ያሉት ላይቤሪያውያን አንደኛው ቅሬታ የሚያነሱት ጉዳይ የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ነው።

በላይቤሪያ ውስጥ በአማካኝ ከአምስቱ አንዱ ሰው ከ2 ዶላር (114 ብር) ባነሰ ዕለታዊ ገቢ ኑሯቸውን ለመግፋት ተገደዋል። #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦ " የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የአንድ ቀን የብድር አገልግሎት (overnight lending facility) እና የአንድ ቀን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት (overnight deposit facility) ይስጣል፡፡ እነዚህ የአንድ ቀን የብድር ወይም የተቀማጭ አገልግሎቶች የሚሰጡበት…
#Ethiopia

" ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ካደረገው አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ፦

" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርስ የሚበዳደሩበትን የተነቃቃ የገንዘብ ገበያ ለመመሥረት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት በቅርቡ ለመዘርጋት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

የገንዘብ ገበያው በኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ላይ ተመሥርቶ በሚገባ ሥራ ላይ ሲውል ትርፍ ገንዘብ ያላቸው ባንኮች የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው ባንኮች ማበደር ይችላሉ፡፡

በመሆኑም፣ ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ወይም ትርፍ ገንዘብ ሲኖራቸው እርስ በርስ የመገበያየት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህ አሠራር ሥራ ላይ ሲውል የባንክ ለባንክ የወለድ ተመን ከማዕከላዊ ባንኩ የፖሊሲ-ነከ የወለድ መጣኔ ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ ይህ ካልሆነ ግን ብሔራዊ ባንኩ ሁኔታውን ለማስተካከል ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታን ይጠቀማል፡፡ "


@tikvahethiopia
#NationalExam

አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው።

የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጀመራቸው ይታወሳል።

Via @tikvahuniversity
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተገነቡት መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የጣሉ ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሄዱ እንዲሁም በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን ' በግዴለሽነት ' በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት መቀጣታቸውን አሳውቋል።

3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር ተቀጥተዋል።

5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር መቀጣታቸውን አሳውቋል።

11 ሰዎች ደግሞ ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር እንደተቀጡ ገልጿል።

ነዋሪዎች የተገነቡትን መሰረተ ልማቶች እንዲጠብቁ እና እንዲንከባከቡ ራሳቸውንም ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርቧል።

(የቅጣት ደረሰኞቹ ከላይ ተያይዘዋል)

#AddisAbaba #MayorOffice

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን በዛሬው እለት አቅርቧል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ሪፖርቱን በማቅረብ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህም ተቋሙ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢውን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በ21.7% ወይም በ16.7 ቢሊዮን ብር በማሳደግ 93.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።

21.79 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ነው።

የእቅዱን 103.6% ማሳካቱንም አሳውቋል።

ተቋሙ የቴሌኮም ደንበኞቹንቁጥር ከአምና ተመሳሳይ ወቅት በ8.9% በማሳደግ 78.3 ሚሊዮን አድርሶ የእቅዱን 100.4% ማሳካቱን ገልጿል።

ቴሌኮሙ በበጀት አመቱ የቴሌኮም እና የዲጂታል መሰረተልማት አቅምን ለማሳደግ ምን ሰራ ?

- የ4G ኔትወርክ አገልግሎትን ወደ 124 ተጨማሪ ከተሞች እና ወረዳዎች በማስፋፋት በአጠቃላይ 4G ተደራሽ የሆነባቸውን ከተሞች ቁጥር ከ300 ወደ 424 ማሳደጉን ገልጿል።

- በተጨማሪም በ79 የሞባይል ጣቢያዎች ላይ የ5G የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራ በማከናወን የ5ጂ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 189 ማድረስ እንደቻለ ጠቁሟል።

- አዲስ አበባን ጨምሮ 5 የከልል ዋና ከተሞችን የ5G ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ተጨማሪ 4 ከተሞችን የ5G ተጠቃሚ ለማድረግ የትግበራ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል።

የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር እና የተቋሙ የሞባይል ገንዘብ ቴሌብር አፈፃፀም ምን ይመስላል ?

- ቴሌኮሙ የቴሌብር ደንበኞቹን ብዛት 47.55 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዱን 107.8% ማሳካቱን አሳውቋል።

- የገንዘብ ዝውውርን በቴሌብር ዲጂታላይዝ በማድረግ በበጀት አመቱ 1.81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር በቴሌብር
ተከናውኗል።

- አገልግሎቱ ከተጀመረ (May 11, 2021) ጀምሮ አጠቃላይ በኢኮኖሚው ላይ 2.55 ትሪሊየን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ልጆቻችን ... በማይናማር !

በርካታ የሀገራችን ልጆች ፦
- የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ ህይወታቸውን ለመቀየር፣
- ደክመው ያሳደጓቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም፣
- እድሜያቸው ሳይገፋ ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሲሉ ወደ ተለያዩ ሀገራት ይሰደዳሉ።

አንዳንዶቹ እጅግ አደገኛ ነው የተባለውን የህገወጥ ስደት በእግር ፣ በበረሃ ፣ በባህር አድርገው ይጓዛሉ።

አንዳንዶች ደግሞ እዚሁ ሀገር ውስጥ በየከተማው በተቀመጡ ደላሎች ማካኝነት ተታለው ምንም እንኳ በኤርፖርት በኩል ከሀገር ቢወጡም የሚሄዱት ግን መጀመሪያ ወደ ተባለው ቦታ ሳይሆን ሌላ እጅግ አደገኛ ቦታ ነው።

ለአብነት ማይናማር ይጠቀሳል።

የሀገራችንን ልጆች ' ታይላንድ ነው ለስራ የምትሄዱት ' ተብለው በደላሎች ተታለው ከሀገር የሚወጡ ሲሆን የሚወሰዱት ግን ወደ ማይናማር (ማያዋዲ) ነው።

ማይናማር ከደረሱ በኋላ የሚወሰዱት የቻናይና ማፊያ ቡድኖች ወደያዟቸው ቦታዎች እጅግ ደህንነት ወደ ሌለባቸው ስፍራዎች ነው።

በዛም የተለያዩ ህገወጥ ስራዎችን እንዲሰሩ በኃይል ያስገድዷቸዋል።

ከኢትዮጵያ ሲወሰዱ 1200 ዶላር እንደሚከፈላቸው ቢነገራቸውም እዛ ከደረሱ በኋላ ግን ለወራት ጉልበታቸውን ይበዘብዙታል። ስቃይና መከራ ይደርስባቸዋል።

ልጆቹ ድብደባ ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ፣ በሰንሰለት መገፈ ጭምር ነው የሚደርስባቸው።

ያለ ምግብ መጠጥ እስርም ይፈጽምባቸዋል።

ህይወታችንን እንቀይራለን ብለው የሄዱት ወጣቶች በስቃይ እና መከራ ውስጥ ያልፋሉ። ለወራት ያህል ስራ እያሉ እያሰሯቸው በኪሳቸው አንድም ብር የላቸውም።

በነገራችን ላይ በስፍራው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሌሎች በርካታ ሀገር ዜጎችም አሉ።

አንዳንድ ሀገራትም ልጆቻቸውን ያስወጣሉ።

በታይላንድ ጎረቤት፣ ማይናማር (በርማ፣ ማይዋዲ) የሚገኙ ' ድረሱልን ፍትህ እንሻለል ' ሲሉ ቃላቸውን የሰጡ የሀገራችን ልጆች፦

- ለስራ ተብለው ወደ ታይላንድ የሄዱ ከ1500 በላይ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ፤

- በአሁን ሰዓት ላይ የሚገኙት ማይናማር (በርማ) ፤ ማያዋዲ (Myanmar-Myawaddy) በሚባል ቦታ እንደሆነ፤

- በህገወጥ የቻይና ጋንጎች ተይዘው በአሰሪዎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸመ እንዳለ፤

- በግዴታ ህገወጥ ስራ (ሰዎችን በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል / Online Scamming) ስራ የሚያሰሯቸው እንደሆነ፤

- ከፍተኛ ድብደባ፣ የኤሌክትሪክ ቶርቸር፣ ሴቶችን መድፈር ፣ ምግብ መከልከል እንዲሁም እስከ መግደል የሚደርስ ግፍ እየተፈጸመ እንደሆነ፤

- እስከ አሁን በርካታ ሰዎች በድብደባና ቶርቸር ብዛት ህይወታቸው እንዳለፈ፤

- ካሉበት የስቃይ ቦታ ነጻ ወጥተው ወደ ሀገራቸው መመለስ እንዲችሉ የህዝብንና የመንግስትን እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው፤

- በኤጀንሲዎች በኩል ወደ ታይላንድ ለስራ ለመሄድ ፕሮሰስ ላይ ያሉ ወገኖችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ

... ድምጻቸው አሰምተዋል።

በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መልዕክቶች በተከታታይ እናጋራለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🎉 የምስራች!  🎁 ተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች ተመልሰው መጥተዋል! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳
  
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether