TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#WKU " አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል። ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው። ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል። በየጊዜው እንዲህ…
#Update

ተማሪውን በመድፈር የተከሰሰው የዩኒቨርሲቲ መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

ከሳምንታት በፊት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ስለተደፈረች ተማሪ እና ሂደቱም በሕግ እንደተያዘ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።

ይኸው መምህር በ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

ተከሳሽ አየለ ሀይሉ ሞላ  ይባላል።

የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከረፋዱ 9፡00 ሰዓት ላይ የሚያስተምራትን የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ " የተበላሸብሽን ዉጤት አስተካክልሻለሁ ፤ አሳይመንት ይዘሽ ኢስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነይ " ሲል ይቀጥራታል።

የግል ተበዳይ ተማሪ ነይ ወደ ተባለችበት ቦታ ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለች ተከሳሽ በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክ/ከተማ ከሚገኘዉ  የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ ላይ ሆኖ  የግል ተበዳይን ጠርቶ ወደ መኖሪያ ክፍሉ እንድትገባ  ያደርጋታል።

ተከሳሽ የግል ተበዳይን ውጤት ለማስተካከል ሴትነቷን ለመጠቀም ያቀረበላትን ጥያቄ " አልቀበልም " ስትል በእምቢታ ትፀናለች።

ተከሳሽ ካንተ ጋር አልተኛም ስትል አሻፈረኝ ያለችውን የግል ተበዳይ በጥፊ እያላጋ  ከለፈቃዷ በኃይል አስስገድዶ እንደደፈራት  የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሽ የተከሰሰበት ክስ የወልቂጤ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎት ቀርቦ የተነበበለት ክስ የወንጀል ድርጊቱ " አልፈፀምኩም " ሲል ክዶ ተከራክሯል።

ዐቃቤ ህግም የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አስቀርቦ አሰምቷል። በዚህም ግለሰቡ የወንጀል ተግባሩን መፈፀሙ አረጋግጧል።

ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር አስቀርቦ ቢያሰማም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል።

ፍ/ቤቱ መምህሩን በ9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ፥ " የዚህ መምህር የቅጣት ዉሳኔ በመሰል ችግር ዉስጥ ለተዘፈቁ መምህራን የማስጠንቀቂያ ደወል ይሁን " ሲል አስጠንቅቋል።

https://t.me/tikvahethiopia/88052

#CentralEthiopiaPolice

@tikvahethiopia