TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.6K photos
1.39K videos
200 files
3.74K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የሀገሪቱን ፓርላማ በኃይል ጥሰው የገቡት መንግሥት ያረቀቀውን የፋይናንስ ሕግ የሚቃወሙ የኬንያ ወጣቶች በፓርላማው ካፍቴሪያ ምግብ ሲበሉ ታይተዋል። ወጣቶቹ ዛሬ ጨምሮ ላለፉት ተከታታይ ቀናት " ታክስ ለመጨምር ያሰበው ረቂቅ ሕግ ኖሮ ያከብድብናል ፤ ተውት ይቅር ! አንደግፈውም " በማለት እየተቃወሙ ይገኛሉ። በዛሬው ተቃውሞ የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን ወጣቶቹ ግን…
#Kenya

የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ሰላምና የህግ ስርዓትን እንዲያስከብር ትዕዛዝ ተሰጠው።

የሀገሪቱ መንግሥት ለቀናት ከዘለቀው የፋይናንስ ህግ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የኬንያ መከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ደህንነት፣ ሰላምና የህግ ስርዓት እንዲያስከብር አሰማርቷል።

በሌላ በኩል ፤ የኬንያው ፕሬዜዳንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው የዛሬውን ታቃውሞ ፤" እንደ ሀገር ክህደት / ከሃዲነት " የሚቆጠር እንደሆነ ገልጸው ፤ የጸጥታ ኃይሎች የኬንያውያንን ደህንነት እንዲያስጠብቁ መመሪያ እንደሰጡ ተናግረዋል።

ተቃዋሚዎች የኬንያ ፓርላማን ሰብረው ስለገቡበት ክስተት ጉዳይም ምርመራ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

የወንጀል ድርጊትና ወንጀለኞችን ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ሰልፍ ከሚያደርጉት መለየት ይገባል ብለዋል።

ፕ/ት ሩቶ " አደገኛ ወንጀለኞች " ሲሉ የጠሯቸው አካላት ሊፈጸሙት የሚችልን ማንኛውም ሙከራ ከንቱ ሆኖ እንዲቀር የደህንነት አካላት እርምጃ እንዲወስዱ እንዳዘዙ ገልጸዋል።

ህዝቡንም " ዛሬ ማታ ተኙ ! የናተ፣ የቤተሰቦቻችሁ እና የንብረቶቻችሁ ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥተን እንጠብቃለን " ብለዋል።

" የተቃውሞው የፋይናስ ምንጮች ላይም ምርመራ ይደረጋል " ሲሉ አክለዋል።

በኬንያ ዛሬ ማክሰኞ በነበረው ተቃውሞ እስካሁን በታወቀው ብቻ 10 ሰዎች ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።

#Kenya
#FinanceBill2024

@tikvahethiopia
#eQUB_APP

በ20ሺህ ብር ብቻ ዕቁብ ገብታችሁ የቤት ዕቃዎችን የምታሟሉበት መተግበሪያ - eQUB APP! የሄ እድል እንዳያመልጥዎ!

Download the App Here👇
📱 Android - Google Play  | 📱 iPhone - App Store

Telegram Channel: @equbapp

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0116671717 ወይም 0116670404 ይደውሉ።
#ዳሽን_ከፍታ: በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "ዳሽን ከፍታ" የሥራ ፈጠራ ውድድር ሶስተኛ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡

በዳሸን ከፍታ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድሮች ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሸልማትና የፋይናስ ድጋፍ አግኝተው በተለያዩ የስራ ዘርፎች ስኬታማ እየሆኑ ነው፡፡ ለሌሎችም የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

ዳሽን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምዕራፍ ሶስት የቅድመ ውድድር ጅማሬ ስልጠና ለመስጠት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይንቀሳቀሳል!

የስልጠና ቦታዎች ፡ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ አዳማ ፣ መቀሌ ፣ ድሬዳዋ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ፣ ጅማ እና ደሴ

ምዝገባ እስከ #ሰኔ_22/2016 ዓ.ም. ድረስ በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 6333 ይደውሉ ወይም የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይጎብኙ፡፡

ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!
" በየሶሻል ሚዲያ የሚፈጸም ስም ማጥፋት በህግ እንጅ በሶሻል ሚዲያ መልስ መስጠት አያስፈልግም " - የሰላምና ጸጥታ ቢሮ

የሀዋሳ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ፥ ያለ ማስረጃ በየተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የከተማዋን ስም እያጠፉ ያሉ አካላትን ጉዳይ በህግ እየተከታተልኩ ነው አለ።

ይህን ያለው ከሰሞኑን ' ቲክቶክ ' እና ' ዩትዩብ ' ላይ የከተማዋን ሁኔታ የሚገልጽ የወጣቶች ንግግር ከተሰራጨ በኃላ ነው።

ወጣቶቹ ከተማይቱ ለደህንነት የምታሰጋ ፣ እግታም የሚፈጸምባት እንደሆነ በመግለጽ ዜጎች ወደ ሀዋሳ እንዳይሄዱ ጥሪ ሲያቀርቡ ይደመጣል።

ይህንን ተከትሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፤ " ጉዳዩን በህግ አግባብ  እየተከታተልነዉ ነዉ " ብሏል።

" በየሶሻል ሚዲያ የሚፈጸም ስም ማጥፋት በህግ እንጅ በሶሻል ሚዲያ መልስ መስጠት አያስፈልግም " ሲል አመልክቷል።

" በእኛ በኩል እንዲህ ያለን የስም ማጥፋት አይተን ባናልፈውም ነዋሪው እና ሀዋሳን የጎበኙ እንግዶች ራሳቸዉ ምን አይነት አስተማማኝ ደህንነት እንዳለ ምላሽ ቢሰጡበት የተሻለ ነዉ " ሲል አክሏል።

ቢሮው ፥ " አሁን ላይ በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች ሀያ አራት ሰአት ሰዉ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚችልባት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ላረጋግጥላችሁ እዉዳለሁ " ብሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታችንን መስጠት እንፈልጋለን ያሉ ወጣቶች ደግሞ ተጎዳው የሚል ማንኛውም ዜጋ በማስረጃ ለፍትህ አካል ማመልከት ይቻላል ብለዋል።

" እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከተማይቱ የምታስፈራ ከተማ አይደለችንም ፤ ሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ከተሞች ደህንነት ያለባት ናት ፤ በዚህ ደረጃ ስም ማጥፋት እና መግለጽ ፍጹም ያልተገባ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ…
#Update

“ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ”- የታጋች ባለቤት

መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ደብዛቸው እንደጠፋ መሆኑን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ወደባቱ ለስራ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በታጣቂዎቸ ታገቱ የተባሉት ሠራተኞቹ ያልተለቀቁት አጋቾቹ ገንዘብ ጠይቀው ከ2.8 ሚሊዮን ብር ከተላከ በኋላ እንደሆነ የታጋች ቤተሰቦች ከዚህ ቀደምም ገልጸው ነበር።

አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ? 

- አቶ ልዑል አስፋወሰን
- አቶ ሰይፉ እንዳለ
- አቶ አብዩ ደገፋው የተባሉ ሠራተኞች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አይታወቅም።

ትላንት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ 2 የታጋች ቤተሰቦች ስለ 3ቱም ታጋቾች ምንም የሰሙት ፍንጭ እንኳ እንደሌለ ገልጸዋል።

አንዷ የታጋች ባለቤት “ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ” ሲሉ ሀዘን ያጀበው ጥያቄ አንስተዋል።

የሰው ልጅ ለ9 ወራት ያህል ያለበት እንኳን አለማወቅ ከባድ ሀዘን መሆኑን ፤ ኤሌክትሪክ ኃይልን በቅርቡ ቢጠይቁም ካቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረበለት የኤሌክትሪክ ኃይል ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹ ይታወቃል።

#TikvahEthiopaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Reminder 🔔

የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ ሊጠናቀቅ 11 ቀናት ቀርቶታል።

አከራይ እና ተከራዮች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።

ከሰኔ 30 በኃላ የሚደረግ ማንኛውም ምዝገባ ቅጣት እንደሚኖረው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ' ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል ' የሚል ግለሰብ ማስረጃ በማቅረብ ስልኩን መውሰድ ይችላል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ ከግለሰቦች ሞባይል በመንጠቅ ሱቅ ውስጥ ሲያከመቹ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

አቶ ሱራፌል ቢያብል የተባሉ የግል ተበዳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14  ዋና ስራ አስፈፀሚ ሲሆኑ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም  በክፍለ ከተማው ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነበር።

በወቅት 2 ተጠርጣሪዎች በጥቁር ሞተር ሳይክል ኮድ 2 A19216 ደ.ሕ (ደቡብ ህዝብ) በሆነ 1ኛ ተጠርጣሪ እያሽከረከረ ፣ 2ኛ ተጠርጣሪ ሞተር ሳይክል ላይ ከኋላ በመሆን ከግለሰቡ  ሞባይል ስልክ ነጥቀው በፍጥነት እያሽከረከሩ ከአካባቢው ይሰወራሉ።

የግል ተበዳይ ወንጀሉ እንደተፈፀመባቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለገርጂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ያመለክታሉ።

ፖሊስም የግል ተበዳዩን አቤቱታ በመቀበል  ባደረገው ክትትል ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ከሌቦቹ የሚረከቡ 2 ተጠርጣሪዎች  በድምሩ  4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ህግን ተከትሎ ባደረገው ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ተከራይተው የሞባይል ጥገና የሚሰሩበት ሱቅ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ግለሰቦች ተቀምተው የተከማቹ 32 ስማርት ሞባይል ስልኮችን በኤግዚቢት ተይዘዋል።

" ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል " የሚል ማንኛውም ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያያ በአካል  በመቅረብና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መውሰድ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Kenya

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል።

ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።

ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤ ይህንንም ተቀብዬ በሕጉ ላይ አልፈርምም፣ ስለዚህም ቀሪ ይሆናል። ሕዝቡ ፍላጎቱን አሳውቋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሕዝቡ ረቂቅ ሕጉን እንደማይፈልገው ገልጿል ያሉት ሩቶ " እኔም በዚህ ተስማምቻለሁ " በማለት ነው በሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ በይፋ ያሳወቁት።

ከሰሞኑን በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ ነበር። ትላንትም ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባት ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። #BBC

@tikvahethiopia
#ያንብቡ

የገንዘብ ሚኒስቴር በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ማስተካከያ የተደረገበት መመሪያ አውጥቷል።

መመሪያው " በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1007/2016 " ይሰኛል።

አዲሱ የተስተካከለ መመሪያ ከከዚህ ቀደሙ ጭምሪ የተደረገበት ነው።

የአልኮል መጠጦች እና የፕላስቲክ ከረጢት(ፌስታል) ኤክሳይዝ ታክስ መጣኔ፦

➡️ ከብቅል የተዘጋጀ ቢራ - የተስተካከለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ተመርቶ በበቀለ ገብስ የተመረተ ቢራ - የተስተካከለው 35% ወይም 23 ብር በሊት ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ ውሃን ሳይጨምር ቢያንስ ከክብደቱ 75% የሚያህለው በአገር ውስጥ ግብዓት የተመረተ ቢራ - የተስተካከለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ 30% ወይም 21 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ የሚፈሉ መጠጦች (ሲዳር፣ ፔሪ፣ ኦፓክ ቢራ፤ የሩዝ አልኮል መጠጥ)፣ የሚፈሉ መጠጦችና የአልኮል አልባ መጠጦች ድብልቅ፣ ስታውት፤ ሌሎች ከቢራ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መጠጦች፣ ዱቄት ቢራ፣ የአልኮል ይዘታቸው ከ7% ያልበለጠ - የተስተካከለው 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ በድብልቅ የተዘጋጁ፣ የአልኮል ይዞታቸው ከ7% ያልበለጠ ጥንካሬ ያላቸው መጠጦች - የተስተካከለው 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ የፕላስቲክ ከረጢት(ፌስታል) - የተስተካከለው 103 ብር በኪሎግራም

ትምባሆና የትምባሆ ውጤቶች የኤክሳይዝ ታክስ መጣኔ

🔵 ትምባሆ የያዙ ሲጋሮች፤ ቼሩትስና ሲጋሪሎስ - የተስተካከለው 30% + 644 ብር በኪሎግራም

🔵 ትምባሆ የያዙ ሲጋራዎች - የተስተካከለው 30% + 20 ብር በፓኬት (20 ፍሬ)

🔵 እንደ ትምባሆ ከሚያገለግሉ የተዘጋጁ ሲጋሮች፣ ቼሩትስና ሲጋሪሎስ እና ሲጋራዎች - የተስተካከለ 30%+20ብር በፓኬት ( 20 ፍሬ)

🔵 የሚጨስ ትምባሆ፣ በማናቸውም ምጣኔ እንደ ትምባሆ የሚያገለግሉ ነገሮችን የያዘ ቢሆንም (የፍራፍሬ ጣዕም እንዲኖራቸው የተደረጉም ያልተደረጉም የትምባሆና ግላይሰሮል ቅልቅል የያዘ ትምባሆ ለማጨስ የሚያገለግል በውሃ ማስተላለፊያ ቱቦ የሚጨስ መዓዛ ሰጭ ዘይት እና ምዝሞዙች ፣ ሞላሰስ ወይም ስኳር ከተጨመረባቸውም ካልተጨመረባቸው በስተቀር) - የተስተካከለው 30% + 644ብር ኪሎግራም

🔵 " የተዋሐደ " ወይም " እንደገና የተዘጋጀ " ትምባሆ - የተስተካከለ 30%+644 ብር በኪሎግራም

🔵 ሱረት፤ የትምባሆ ምዝምዞችና ኤስንሶች - የተስተካከለ 30%+644ብር በኪሎግራም

መረጃው የተላከው ከገንዘብ ሚኒስቴር ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል። ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤…
" በእስራት የምታቆዩበት ምንም ምክንያት የላችሁም ፤ ልቀቋቸው " - የናይሮቢ ፍርድ ቤት

ትላንት በኬንያ ናይሮቢ ከነበረው የፋይናንስ ረቂቅ ህጉ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ነበር።

የታሰሩ ሰዎች 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ናይሮቢ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱም " ከእስር ልቀቋቸው " ብሏል።

ዛሬ ረቡዕ ፍ/ቤት የቀረቡት 56 ሰዎች ሲሆኑ ፖሊስ " ልመርምራቸው 14 ቀን ይፈቀድልኝ " ሲል ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ግን የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

" ሰዎቹን የሚያሳስርና ዋስ የሚያስከለክል አንድም ጠንካራ ምክንያት ስለሌለ ከእስር ልቀቋቸው " ሲል አዟል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል።

57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ቅሬታ ካቀረቡት መካከል፦
- የማኔጅመንት
-የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
- የቬተርነሪ ሳይንስ
-የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ይጠቀሳሉ።

ከዚህም ባለፈ ፥ " የተሰጠን ሰዓት በቂ አልነበረም ፣ፈተና ዘግይቶ የመጀመር፣ ለፈተናው በቂ ሰዓት አለመመደብ ችግር ነበር " የሚል ቅሬታ ያቀረቡም አሉ።

የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ፈተናም በድጋሜ እንዲሰጥ ተደርጓል።

አጠቃላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተላኩለትን ቅሬታዎች ይዞ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን አነጋግሯል።

ከፍተኛ አመራሩ ፤ " የዘንድሮው 2016 የመውጫ ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ሲሉ ገልፀዋል፡፡

" ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም " ያሉት ኃላፊው፤ " አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ብለዋል፡፡

ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ " በቅርብ ቀን ውስጥ ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

Via @tikvahuniversity
" ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ነው ተጠንቀቁ " - የጠ/ሚ ጽ/ቤት

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘው ተደረጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

የጠ/ሚ ጽ/ቤት ያወጣው መግለጫ አስመስሎ አንድ የተቀነባበረ የጠ/ሚ ጽ/ቤት አርማ ያለበት መግለጫ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይኸው መግለጫ ፦

- ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ከተለየችው ' ክልል ' ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘችው ፤
- ኢትዮጵያ ከዩኬ፣ ከG7 እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወያይታ የሶማሌላንድን ሉዓላዊ ሀገርነት የምትደግፍበት ማስረጃ እንዳላገኘች
- የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሁን በኃላ ህጋዊ ያልሆነ ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር እንደማያደርግ
- ኢትዮጵያ ፤ የሶማሌላንድ ጉዳይ የሶማሊያ ስለሆነ ፖለቲካዊ ችግራቸውን በአንድ ሀገር ጥላ ስር እንዲፈቱ እንደምትተው ... የሚገልጽ ነው።

ይህ ግን ፍጹም ሀሰተኛና መግለጫው የተቀነባበረ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምን አለ ?

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፤ ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈጸመው የመግባቢያ ስምምነት በኦንላይን እየተዘዋወረ እና እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ስለሆነ ህዝቡ እንዲጠነቀቅ መክሯል።

በሀገር ውስጥ ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች መግለጫም ሆነ መረጃ የሚሰጠው በይፋዊ የጽ/ቤቱ ገጾች / ቻናሎች ላይ ብቻ እንደሆነ አመልክቷል።

ሁሉም ሰው የጽ/ቤቱን ይፋዊ አርማ በመጠቀም ከሚሰራጩ  እንደዚህ አይነት የውሸት መረጀዎች / ይዘቶች እራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia