TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሩት የሰላም ልዑክ የዛሬ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?
- ቀደም ብሎ በወጣ መርሀ ግብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልዑክ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ በምዕመናን፣ ዘማርያን፣ በክልሉ ሃይማኖት አባቶች አቀባበል ይደረግለታል ቢባልም በስፍራው ከትግራይ አባቶች ፣ ዘማርያን የተገኘ አልነበረም። የተገኙት የመንግስት አመራሮች ነበሩ።
- በመቀጠል እዛው መቐለ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ፀሎት ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ምዕመናን፣ ካህናት ፣ የትግራይ አባቶች አልተገኙም ነበር። ቅዱስነታቸው እና የመሩት ልዑክ የቤተክርስቲያኑ በር የዘግቶባቸው በር ላይ ፀሎት አድርሰው ለመውጣት ተገደዋል።
- በፕላንቴ ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ልዑኩ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዚህ ስነስርዓት ላይ የትግራይ አባቶች #አልተገኙም። ተገኝተው የነበሩት የክልሉ መንግስት አመራሮች ነበሩ።
- ልዑኩ በመቀጠል በመቐለ 70 ካሬ ተፈናቃዮችን የተመለከተ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት ተፈናቃዮች በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን ለማወቅ ተችሏል።
- ከመቐለ 70 ካሬ የተፈናቃዮች መልከታ በኃላ የሰላም ልዑኩ ከትግራይ ብፁአን አበውና የኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስተያን አመራሮች ጋር ይገናኛል ውይይትም ያደርጋል የሚል መርሀ ግብር ተይዞ የነበረ ቢሆንም ይህም አልተደረገም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ ብፁዓን አባቶች ከጥዋት አንስቶ በነበሩ መርሀግብሮች ላይ ለምን አልተሳተፉም ? የሚለውን ለመጠየቅ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም።
@tikvahethiopia

" የ2 ሰዎችን አስክሬን እየፈለግን ነው " - የዞኑ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከሰው ህይወት መጥፋት ባለፈ በአዝእርትና በብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ መፍጠሩ ተነግሯል። በጉዳዩ…
#Update
" በጎርፍ የተወሰዱ አስክሬኖች #አልተገኙም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ መምሪያ
ከሰሞኑን በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃ እንደሰጠናችሁ ይታወሳል።
በወቅቱ 5 ሰዎች መሞታቸዉንና ከነዚህ ዉስጥ የ2 ሰዎች አስከሬን አለመገኘቱ መግለጹ አይዘነጋም።
አስክሬን ፍለጋው ከምን ደረሰ ? ከአደጋው ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? ስንል የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊን አቶ ሙደስር ጉታጎ ጠይቀናቸዋል።
ኃላፊው አስከሬኖቹ አሁን ድረስ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፤ አንድ አስክሬን በዞኑ መገኘቱን በተደረገው ማጣራት አስከሬኑ ከስልጤ ዞን በጎርፍ ምክንያት የመጣ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የጎርፍ አደጋው እስካሁን መሬት ላይ የነበረዉን ሰብል ሙሉ በሙሉ እንዳወደመ ገልጸዋል።
በዞኑ ውስጥ ባለው የሀላባ ቁሊቶ ሆስፒታል ላይ ከ6 ሚሊየን 500 ሺህ ብር በላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተናግረዋል። ነገር ግን ሆስፒታሉ አሁንም በስራ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
ከዚህ ቀደም የተገለጸው ዌራ ወረዳ ሆስፒታል ግን በአደጋው ምንም ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ጎርፉ ያስከተለዉ አደጋ በህዝብና ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ እና የንብረት ውድመት ያስከተለ ሲሆን ዞኑ አሁንም አስክሬን እና የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁንም የአየር ትንበያ ዘገባዎች በደቡቡ ኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ዝናብ እንደሚኖር ስለሚጠቁሙ ማህበረሰቡ ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa