TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " - ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

የትምህርት ሚኒስቴር እና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው መገምገሙን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምር እና የ14 የአፕላይድ አጠቃላይ 22 ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር መገምገሙ ተነግሯል።

በግምገማው ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ፤ የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

አስፈጻሚ መ/ቤቶች እና የስራ ሀላፊዎች በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ፤ " በሚቀጠለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም " ብለዋል።

ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ገንዘብ ?

በየዩኒቨርሲቲዎች " ለሥራ ኃላፊዎች የሚከፈል ክፍያ " በሚል የሚመዘበረው ገንዘብ  ከፍ ያለ ነው።

ሰዎቹ ከመንግሥት በጀት / አካል ውጭ ተጻጽፈን በሚመጣልን ድጋፍ ፕሮጀክት እየሰራን ብር ይከፈለናል ነው የሚሉት።

ክፍያው ግን እጅግ የተጋነነ ከመሆኑ የተነሳ ግልጽነት የጎደለው፣ ብዙ ጥርጣሬንም የሚያጭር ነው።

መንግሥት ደመወዛቸውን እየከፈላቸው እያለ " ላስተባበሩበት " በሚል እዛው ግቢያቸው ውስጥ ለሚሰራ ስራ የሚከፈላቸው ብር ብዛት የሚገርም ነው።

ለአብነት፦

ሰሞኑን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ስለሚፈጸም አይን ያፈጠጠ የለየለት የህዝብ ሀብት ምዝበራን በተመለከተ በተሰራጨው የፋና ምርመራ ዘገባ ላይ ዶ/ር ተመስገን ቶማስ በሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ብቻ የተከፈላቸው ገንዘብ በርከት ያለ ነው።

ዶክተሩ ምንም እንኳን " ቁጥሩም እኮ ሳይገለጽ መነጋገር እንችላለን " ቢሉም አይገለጽ ያሉት ቁጥር ግን ይህንን ይመስላል።

19,500 ብር (ሰንድ 1)
11,700 ብር (ሰንድ 2)
23,212 ብር (ሰንድ 3)
19,500 ብር (ሰንድ 4)
7,800 ብር (ሰንድ 5)
23,400 ብር (ሰንድ 6)
19,500 ብር (ሰንድ 7)
19,500 ብር (ሰንድ 8)
15,600 ብር (ሰንድ 9)
14,644 ብር (ሰንድ 10)
14,644 ብር (ሰንድ 11)
22,000 ብር (ሰንድ 12)
17,500 ብር (ሰንድ 13)
23,400 ብር (ሰንድ 14)
39,000 ብር (ሰንድ 15)
19,500 ብር (ሰንድ 16)
14,644 ብር (ሰንድ 17)
19,500 ብር (ሰንድ 18)
14,644 ብር (ሰንድ 19)
21,450 ብር (ሰንድ 20)

እኚህ ሁሉ በሰኔ ወር 2013 የተከፈሉ ናቸው።

ዶክተሩ ግን እስቲ ልየው 😳 በሰኔ ወር ነው የተከፈለው ? ብለው ይጠይቃሉ ዶክመቱም ይሰጣቸዋል፤ በኃላም ዶክመንቱን ያገላብጡና " እስቲ 2013 የሚለው የታለ ? " ሲሉ ድጋሜ ይጠይቃሉ " ይኸው ! " ይባላሉ ፤ በዝምታ ከተዋጡ በኃላ " እ ! " ብለው ዶክመንቱን መልሰዋል።

ዶ/ር ተመስገን በተለያየ ጊዜ የተባከ ክፍያ የፋይናንስ ባጀት ስለሌለ በአመቱ መጨረሻ ባጀት ሲያገኝ ገብቶ ነው እንጂ በአንዴ የተላከ አይደለም ብለው ተከራርክረዋል።

ሌላው የዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር ማርቆስ ዮሐንስ ብዙ ገንዘብ የተከፈላቸው ሲሆን " እኔ ብዙ ፕሮጀክት ስለምሰራ ነው። ቀንም ማታም ቅዳሜና እሁድም በፕሮጀክት  ላይ ሰራው ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ ለዛ ነው የተከፈለኝ ባይ ናቸው።

ዳይሬክተሩ በቀን 18 ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም 13,650  ብር እንዲገባላቸው የታዘዘበት ዶክመት የተገኘ ሲሆን በቀን 23 / 2013 ዓ/ም 15,600 ብር እንዲገባላቸው ታዟል በተመሳሳይ ቀን 19,600 ብር እንዲገባላቸው ተደርጓል።

ሌሎችም በርካቶች ናቸው ነው ያሉት።

ዶ/ር ተመስገን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ዶክተር ሀብታሙ አበበ ጋር የፋይናንስ ዳይሬክተሩ ስም በክፍያ ዶክመት ላይ " ፕሮጀክት " ተብሎ ተገኝቷል።

በአጠቃላይ በዋቸሞም ሆነ በመሰል ተቋማት በፕሮጀክት ስም የሚወጣው ብር እጅግ ብዙ ፣ ከደመወዛቸው እጥፍ፣ ግልጽነት የጎደለው ነው።

ሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎችስ ?

@tikvahethiopia
Forwarded from telebirr
ባልተገደበ የፕሪሚየም ጥቅላችን ከወዳጅ ዘመድ ጋር ግንኙነትዎ ሳይቋረጥ የስራ እንቅስቃሴዎ ሳይገደብ ዘና ብለው ይጠቀሙ !

በሳምንታዊና በወርሃዊ ያልተገደበ ፕሪሚየም አማራጮች የቀረቡትን ጥቅሎች በቴሌብር  ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ያገኟቸዋል!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Ethiopia

የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል።

አዲሱ አዋጅ የግል ፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰው ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።

ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው።

አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች አሻሽሏል የተባለ ሲሆን የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል ተብሏል።

አዋጁ ምን ይዟል ?

- ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ ይችላል።

NB. በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት " መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው "። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው " ለመንግስት እና ለህዝብ " ነው።

- የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልበታል።

- የወል ወይም የመንግስት ይዞታ ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር ይቀጣል።

- ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።

- ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።

- ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል።

ምንጭ፦ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

ከተመሩት ረቂቅ አዋጆች መካከል አንዱ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ነው።

የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አዋጁ በስራ ላይ ከዋለ 6 አመት ያስቆጠረ መሆኑንና አሁን ካሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር ማጣጣም ማስፈለጉን ገልጸዋል።

የመንግስት ሰራተኞች የሰው ሀይል ምልመላና መረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉንም ባካተተና ብዝሀነትን በጠበቀ መልኩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርአት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ፦

የደሞዝ ጭማሪ፣

የደሞዝ እርከን፣

ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ማትጊያና ማበረታቻ ስርአት፣

የሰራተኞች ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስልጠና አሰጣጥ ስራ ስምሪት እና ነጻ ገለልተኛ ስርአት መገንባት፣

የመንግስት ሰራተኛነት ውል ማቋረጥና ማራዘም የሚሉና ሌሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 13/2016 ሆኖ በሙሉ ደምጽ ለሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

ሌሎች ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመሩ ረቂቅ አዋጆች ምንድናቸው ? በዚህ ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Ethiopia-05-14-8

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ባለፈው ሳምንት ብቻ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ” - ነዋሪዎች በኮሬ ዞን ፤ #በታጣቂዎች አማካኝነት ንጹሃን ላይ የሚደርስ ጥቃት በእርቀ ሰላም ተፈቶ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ከ4 ወራት ወዲህ በማገርሸቱ የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል። ባለስልጣናቱና ነዋሪዎቹ ለድርጊቱ  የ " ኦነግ…
#ኮሬ

° " የንጹሀን ሞት ይቁም፤ገዳዮች ለፍትህ ይቅረቡልን !! " - የዳኖ ቀበሌ ነዋሪዎች

° " በግጭቱ ሁለት ሰዎች ሲጎዱ የአንደኛው ህይዎቱ አልፏል " - የኮሬ ዞን የሰላምና ጸጥታ ሀላፊዉ ተፈራ ቦንዶሮ

በኮሬ ዞን ፤ ዳኖ ቀበሌ ከትናንት ጀምሮ የደረሰ በቆሎ ታጥቀው በመጡ አካላት በመጨፍጨፉ ምክንያት በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት አልፏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ይህ ድርጊት ታጥቀው ከምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላናና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ ቀበሌያት ወደ ኮሬ ዞን ዘልቀው በገቡ አካላት ነው የተፈጸመው ብለዋል።

እነዚሁ ታጣቂዎች " ከዚህ ቀደምም ከብቶች ሲነዱብን አርሶአደሮች ሲገደሉብን ቆይተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህ አመት ብቻ #ከ20_በላይ ሰዎች መሞታቸውን አስረድተዋል።

በመሆኑም " እነዚህን አካላት መንግስት አስታግሶ ለህግ / ለፍትህ ያቅርብልን ፤ የንጹሀን ሞት ይቁም ፤ ሰሚ በማጣታችን እሄዉ ዛሬም ግጭቱ ቀጥሏል " ብለዋል።

በአካባቢው ያለዉ ተኩስም የታጠቁ አካላትን ወሰን አልፈዉና ወደመንደሩ ተጠግተዉ የጀመሩት ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የኮሬ ዞን የሰላምና ጸጥታ ሀላፊዉ ተፈራ ቦንዶሮ ፥ (ቃላቸውን በሰጡበት ሰዓት / ከሰዓት ) አካባቢው ላይ ከባድ ተኩስ እንደነበር ገልጸዋል።

ግጭቱን ለማርገብ ርብርብ ላይ በመሆናቸዉ ምላሽ ለመስጠት አይመችም ቢሉም ቆይተዉ የተብራራ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከምዕራብ ጉጂ ዞን የመጡ ታጣቂ ሀይሎች አካባቢው በመመንጠርና የበቆሎ ማሳዎችን በመጨፍጨፋቸው ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

በግጭቱ አንድ ሰው #ሲሞት ፤ አንድ ሰው ቆስሏል ብለወል።

ግጭቱን በቀሰቀሱት በኩል የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው አሁን ላይ አካባቢዉ መረጋጋቱን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለዘላቂ ሰላም ምን ታስቧል ? ሲል ጠይቋል።

እሳቸውም ፤ ከአካባቢው በተወሰነ ርቀት ላይ የሀገር መከላከያ ሀይሎች እንደሚኖሩና ከሚቆጣጠሩት ቦታ በተጨማሪ የታጠቁ ሀይሎች የሚመጡበትን መንገድ እንዲቆጣጠሩ ለመነጋገር ማሰባቸዉን ገልጸዉ ይህ ግን በመከላከያው ፈቃድና የስምሪት ሁኔታ የሚወሰን ነው ብለዋል።

ግጭቱ ያለበት የኮሬና ጉጂ ማህበረሰብ መሀከል በአካባቢዉ ባህል መሰረት የእርቅ ስርዓት በተደጋጋሚ ቢካሄድም ዕርቁ ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን ለማወቅ ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በምዕራብ ጉጂ ዞን በኩል ምላሽ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካም ፤ ከዚህ ቀደምም ሙከራ ቢደረግም ምላሽ ሰጪ አልተገኘም። አሁንም ምላሽ አለኝ የሚል ምላሹን መስጠት ይችላል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
" በዝርፊያው ለጊዜው #ተለይተው_ያልታወቁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ተወስደዋል " - የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ እንደተፈጸመበት ተነግሯል።

በፖሊስ ጣቢያው ላይ ዝረፊያ የተፈፀመው ሰኞ ለሊት 7፡40 ገደማ ነው።

" በዝርፊያው ለጊዜው ተለይተው ያልታወቁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ከፖሊስ ጣቢያው ተወስደዋል " ሲል የከተማው ሰላምና ፀጥታ ፅ / ቤት አሳውቋል።

በተጨማሪም ከጣቢያው ተዘርፎ የነበረ ፓትሮል መኪና መንገድ ላይ መገኘቱን አመልክቷል።

ፖሊስ ጣቢያው ታሽጎ የማጣራት ሂደት እየተከናወነ እንደሆን ገልጿል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

ከማረት ከተስረቁት 2 መኪኖች አንደኛዋ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ።

ማሕበር ረድኤት ማሕበር (ማረት) በመጋቢት እና በያዝነው ግንቦት ወር አንድ ላንድክሩዘር V8 እና ላንድክሩዘር ማርክ 2 መኪናዎችን ተዘርፏል።

የድርጅቱ ንብረት የሆነች በሰሌዳ ቁጥር 35 - 2723 የተመዘገበችው V8 መኪና መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተሰርቃ ሳትገኝ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታ ነበር።

ይህች መኪና ሳትገኘ ከቀናት በፊት ላንድ ክሮዘር ማርክ 2 መኪና ተዘርፋለች። 

ፓሊስ የድርጅቱ መኪኖች ያየና ያገኘ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ በያዝነው ሳምንት የተሰረቀችው ላንድክሩዘር ማርክ2 መኪና ከመቐለ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አክሱም ከተማ በፓሊስ ተይዛለች።

የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ መኪናዋ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 በፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋልዋን አሳውቋል።

ፖሊስ መኪናዋን ያገኘው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል ነው።

በሰዓቱ መኪናዋን የያዛት ሹፌር ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ማክሸፉን አሳውቋል።

ከነሹፌሩ በተጨማሪ " የኔ ንብረት ናት " የሚል አመልካችም በፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

የአክሱም ከተማ ፖሊስ " መሰል ስርቆት ከጦርነቱ በኋላ መታየት የጀመረና በትግራይ ያልተለመደ ነው " ያለ ሲሆን " ማንኛውም ወንጀለኛ ከህዝብ አይንና ጀሮ መደበቅ አይችልም ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ስለ መኪኖቹ ስርቆት ከማሕበር ረድኤት ትግራይ (ማረትረት) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
                                           
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል።

አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው።

ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው። 

ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው።

የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። "

Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና፦

" ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር።

አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። "

Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው።

ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል። 

ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው።

የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል።

አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። "

Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው።

መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ።

አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም።

Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል።

መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል።

መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። "

Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው።

ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም።

ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ?

@tikvahethiopia
#ProsperityParty #TPLF

ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል።

ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል።

ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል።

" ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ፦

- " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

- ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

- የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል።

- የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

#ProsperityParty #TPLF

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ሞተዋል !! " - ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት

በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይፈለጉ የነበሩ የመጨረሻው ሁለት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተከሳሾች መሞታቸውን ማረጋገጡን በጉዳዩ ላይ የተቋቋመው ችሎት አስታውቋል።

ርያንዱካዮ በሚል ስም ብቻ የሚጠራው እና ቻርለስ ሲኩብዋቦ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ጉዳይ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ችሎት ሲፈለጉ የነበሩ የመጨረሻዎቹ ተከሳሾች ናቸው።

በብሔራዊ ደረጃ ግን አሁንም ድረስ ከ1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በመፈለግ ላይ ናቸው።

2ቱ ግለሰቦች ከ30 ዓመት በፊት 800 ሺ ቱትሲዎችን እና ለዘብተኛ ሁትዎችን በጨረሰው የዘር ፍጅት ላይ ተሳትፎ አላቸው በሚል ለሩዋንዳ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በእ.አ.አ 1995 ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

ሲኩብዋቦ በእ.አ.አ 1998 በቻድ መሞቱን እና በዛው መቀበሩን እንዲሁም ርያንዱካዮ ደግሞ ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከሸሸ በኋላ ከዛም ወደ ዛየር ተሻግሮ ኪንሻሳ ላይ በ1998 ሕይወቱ ማለፉን ፍ/ቤቱ አስታውቋል።

በሩዋንዳው የዘር ፍጅት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ሲፈለጉ የነበሩ ተከሳሾች ሁሉ መለየታቸውንም ችሎቱ አስታውቋል። #ቪኦኤ

#RwandaGenocide

@tikvahethiopia
#SouthEthiopiaRegion

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል።

በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም።

ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ለመመገብም ሆነ ልጆቻቸዉን ለማስተማር መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል።

የገዢዉ ፓርቲና የክልሉ ባለሥልጣናት ሠራተኞቹን " በትዕግሥት ጠብቁን " የሚል ምላሽ ቢሰጡም ሠራተኞቹ ግን " ረሐብ እንዴት ቀን ይሰጣል ? " በማለት ጠይቀዋል።

ሠራተኞቹ በወረዳው በተለያዩ ጽ/ቤቶች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሠራተኞቹ ተወካዮች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia