TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ

የመኪና አደጋ የአባትና ልጅ ህይወት ቀጠፈ።

ሦስት ተጓዦች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

ዛሬ ጠዋት ጥር  25/2016 ዓ.ም ከዓድዋ ወደ መቐለ 5 ሰዎች ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ባለቤትነቱ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ የሆነ ትዮታ ዳብል ጋቢና መኪና ተምቤን ልዩ ቦታ " መነወ " በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተጓዦች ላይ የሞትና የጉዳት አደጋ አድርሷል።

በመኪናው የነበሩ የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ማርኬቲንግ መምሪያ ሃላፊ ከነልጃቸው ህይወታቸው ሲያልፍ ፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ተጓዦች ደግም በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

የራስ አሉላ አባነጋ የትውልድ ቦታ የሆነው " መነወ " ጠመዝማዛ ቦታና ተደጋጋሚ የመኪና አደጋ የሚከሰትበት በመሆኑ መንገዱ ትኩረት እንደሚያሻው አደጋው አስመልክተው የሚሰጡ የህዝብ አስተያየቶች ያመለክታሉ። 

የመኪና አደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ፓሊስ ትራፊክ ገልጿል።

መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።
                                    
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው እለት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ቃለመጠይቅ ለክልሉ ሚድያዎች ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሳትፎውበት ከፌደራል መንግስት ጋር በአዲስ አበባ ስለተካሄደው ውይይትና ውጤት አስመልክቶ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

አቶ ጌታቸው ፤ " ለፌደራል መንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበናል። በአከባቢያችን ያለው ፓለቲካዊ ሁኔታ እጅግ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ እንደ አገር የውስጥ ሰላማችን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ ከፌደራል መንግስት ጋር መግባባት  ተደርሷል " ብለዋል።

ከፌደራል መንግስት በተካሄደው ውይይት በሃይል ስለተያዙ የትግራይ ግዛቶች መነሳቱ ያብራሩት ፕረዚደንቱ " በተለይ በምዕራባዊ ዞን  በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰፋሪዎች በሰፈሩበት፤ የፌደራል ተቋማት ዴሞግራፊ ለመቀየር በሚንቀሳቀሱበትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ፤ መፍረስ የሚገባቸው ሳይፈርሱ ፤ ህዝባችን ነፃ ባልወጣበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማድረግ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ወር መጋቢት የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በተገኙት የፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል ያሉት አቶ  ጌታቸው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለውይይቱ ስኬት የበኩሉ አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓት መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄም ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም፤ ከህወሓት የፓለቲካ ፓርቲነት ምዝገባ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው በመግለፅ ያለው የህግ ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም ጉዳዩ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተመርቷል ብለዋል።

መረጃውን የትግራይ ሚድያዎችን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀድ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                 
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" ደማቁ የዓድዋ የድል መታሰብያ በዓልን በእርስ በርስ ግጭት ማቆሸሽ አይገባም " - ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መልእክት አስተለልፈዋል። ከ3 ዓመት ተኩል በኃላ በትግራይ ታሪካዊትዋ የዓድዋ ከተማ በመገኘት በዓሉን ለማክበር በመቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል። ፕረዚደንትዋ #እንባ_እየተናነቃቸው ያለፈውን አስከፊ ጦርነት በማስታወስ ፣ ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ…
#ትግራይ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 😢

" ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታ ሳይለያይ የመሪውን ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክን ጥሪ በመቀበል ተሰባስቦ በመዝመት በነዚህ ተራሮች እና ኮረብታዎች ታሪክ እንዳልሰራ ሁሉ ለራሱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ ለአፍሪካ አህጉራችን እንዲሁም ለመላው የተጨቆነ ህዝብ ተስፋ የሰጠ ሳለ በዚህች መሬት፦
- ወንድም በወንድሙ ላይ ቃታ የሳበበት የተጋደለበት
- ንፁሃን የተገደሉበት
- ብዙዎች የተሰደዱበት
- በርካቶች በገዛ ሀገራቸው የተንከራተቱበት፣ የተፈናቀሉበት
- ንብረት የወደመበት
- #ሴቶች_የተደፈሩበት ሁኔታ ታሪክ ጅብዱ በተሰራበት ምድር እንዲያይ ያደረግነው። እነዚህ ተራራዎች ለዚህም እማኝ እንዲሆኑ ያደረግነው።

እነዚህ ተራሮች መናገር ቢችሉ እንዲነግሩን የምንፈልገው ግን የህዝባችንን ጀግንነት፣ ታሪክ ሰሪነት፣ አንድነት ነው፤ ምስክሮቻችን ናቸው።

በትግራይ ጦርነቱ እንደጀመረ ሰሞን መጥቼ ነበር። ከጦርነቱ ሁለት ወር በፊት እዚህ ነበርኩ። የጦርነት ደህና ገፅታ የለውም እጅግ አስከፊውን ግን አላየሁም ብዬ ነው የማስበው። "

#TikvahFamilyAdawa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 😢 ፦ " ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታ ሳይለያይ የመሪውን ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክን ጥሪ በመቀበል ተሰባስቦ በመዝመት በነዚህ ተራሮች እና ኮረብታዎች ታሪክ እንዳልሰራ ሁሉ ለራሱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ ለአፍሪካ አህጉራችን እንዲሁም ለመላው የተጨቆነ ህዝብ ተስፋ የሰጠ ሳለ በዚህች መሬት፦ - ወንድም በወንድሙ ላይ ቃታ የሳበበት የተጋደለበት…
#ትግራይ

" ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን 2 ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ ! " - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ በነበረው የዓድዋ ድል በዓል  ላይ እምባ እየተናነቃቸው 😭 ንግግር አድርገው ነበር።

እሳቸው በእንባ ንግግር ሲያደርጉ የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ ከፍተኛ የሀዘን ስሜቱ ከፊቱ ይነበብ እንደነበር በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምን አሉ ?

" ዛሬ ወደ ትግራይ ስመለስ በህሊናዬ የሚመጡብኝ ብዙ ትዝታዎች አሉብኝ።

ይቅርታ አድርጉልኝና አጋጣሚውን ተጠቅሜ ማንሳት እፈልጋለሁ።

በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው ከነበሩ ወገኖች መካከል አንዷ ፈንጠር ብላ የተቀመጠች አንዲት ሴት ለማነጋገር ሞክሬ ነበር።

በተፈናቃዮች ካምፕ ጉብኝት ልብን የሚሰብር  ነው። ከቤት ንብረታቸው ወጥተው ፣ ክብራቸውን አጥተው ቁጭ ብለው ጉብኝት .. እኛ ደግሞ እንመጣለን ልናያቸው።

ታዲያ ያችን ሴት ጠጋ ብዬ ሳነጋግራት፤ በጥሩ አልመለሰችልኝም። ጥቂት ያመጣሁትን እቃ እንድታከፋፍልልኝ ነበር ልጠይቃት የነበረው ' ያንቺን እቃ አልፈልግም ' አለችኝ።

በሆስፒታል እና በመጠለያ ጣቢያቸው ሄጄ ያየዋቸዋን ሴቶች በእጅጉ አስባቸዋለሁ። እቺን ሴትዮ ለምንድነው የምትመልሽልኝ ስላት ' ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን ሁለት ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? ' ነው ያለችኝ መልስ የለኝም ፤ አይመልስም ብቻ ነው ያልኳት።

ጦርነቱ ተዛምቶ በአፋር ክልል ሰመራ ሆስፒታል ህክምና ላይ የነበሩ የተማረኩ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን አግኝቻቸዋለሁ ሳናግራቸው ያሉኝ ከልቤ አይጠፋም ፤ ቦታቸው እዛ አልነበራም ትምህርት ቤት ነው።

ያሉኝ ' እኛ መመለስ የምንፈልገው ወደ ትምህርት ቤት ነው ' ይሄንን ወግቼ ያንን አሸንፌ የሚል ዓላማ አልነበራቸውም። በክፍላቸው ግርግዳ ላይ የፃፉት የለጠፉት የአፋር ህዝብ እንዴት ደግ እንደሆነ ነው። ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያዊ እንዴት እንደሚረዳዳ ነው።

ሌሎችም አሉ ብዙ እርጉዝ ሆነው ሶስት ልጅ ወልደው ሲንከራተቱ የነበሩ ... ለማንኛውም ብዙ መንከራተት ነበር።

ዛሬ እዚህ ቆሜ የትግራይ እናቶች ያሳለፉትን #ሰቆቃ በእውነቱ እረዳለሁ ለማለት ነው ይሄን ሁሉ የምናገረው። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥዎ !!

ዞሮ ዞሮ የማንኛውም ግጭት መጨረሻው ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የሰላም ስምምነት መፈረሙ አይቀርምና ይህ ሳይሆን ተጨራርሰን ተጨካክነን ፣ ዘርና ሃይማኖት መለያያ አድርገን ሃይማኖቶችን ከፋፍለን ሳይሆን በቅድሚያ መከላከል እንዳለብን መገንዘብ አለብን።

የዓድዋ ባለቤቶች እንዳልሆንን ገፅታችንን አጉድፈን አበላሽተናል። "

#TikvahFamilyAdawa

@tikvahethiopia
#ትግራይ

"...መግለጫው የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ ያመላከተ ነው " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም

የትግራይ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ የኤርትራ ጦር  የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን መሬቱን ለቆ እንዳልወጣ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደርን ጨምሮ ሀገራትና ተቋም በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

በቅርቡ እንግሊዝ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ አውጥቶት በነበረ አንድ መግለጫ የኤርትራ ጦር በትግራይ ግዛት ውስጥ እንደሌለ፣ ባድመም ጨምሮ ሌሎችም አከባቢዎች ህወሓት በህገወጥ መንገድ ለሁለት አስርት ዓመታት ይዟቸው የቆዩ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛቶች ናቸው ብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኤርትራ ጦር በምስራቃዊና ሰሜን ምዕራብ የትግራይ አካባቢዎች ጨምሮ በተለያየ አካባቢ እንዳለ በተደጋጋሚ በመግለፅ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ያሉ የውጭ ኃይሎችን የማስወጣትና ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ኃላፊነት የፌዴራል መንግሥት መሆኑን ገልጿል።

የትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ረዳዒ ኃለፎም በኤርትራ መግለጫ ዙሪያ ምን አሉ ?

- የኤርትራው ኤምባሲ መግለጫ የኤርትራ ጦር የተለያዩ አካባቢዎችን በኃይል ይዞ እንደሚገኝ አመላካች ነው።

- ከአልጀርስ ስምምነት አፈፃፀምናና ሌሎች የድሮ በ90ዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎች ጉዳዮች ካሉ በህጋዊ መንገድ በዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈፀም ማድረግ እንጂ ጉልበት አለኝ ብሎ በጉልበት የያዛቸውን አካባቢዎች " የኔ ናቸው " የሚል መግለጫ መስጠቱ ተቀባይነት የለውም።

- ከአልጀርስ ስምምነት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በኃይል የተወረረው መሬት ከተመለሰ በኃላ በህጋዊ መንገድ ሊፈፀም የሚችል ነው።

- መግለጫው አንድ ውለታ የዋለው በኃይል የያዧቸው አካባቢዎች እንዳሉ ገልጸ " በኃይል የያዝኩት የኔ ነው " የሚል መስፋፋት ነው። " የለሁም " አላለም መኖሩን አምኗል ይሄ የያዘው ቦታ ነው በጉልበት ስለያዝኩት " የኔ ነው " እያለ ያለው ይሄ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።

- የፌዴራል መንግሥት ማስወጣት አለበት እነዚህን ኃይሎች ሁሌም እያልን ነው። ማለት ያለበትን ማለትም አለበት። ኃላፊነቱን መወጣት አለበት።

- በትግራይ ከኤርትራ ጦር በተጨማሪ የአማራ ክልል ታጣቂዎችም አሉ። ይህ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረር በትግራይ ያለውን አሳሳቢ የተፈናቃዮች ችግር እንዳይፈታ ያደረገ ነው።

- እንዚህ ኃይሎች እያሉ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ማድረግና ማቋቋም አይቻልም። ከሞት አምልጠው የመጡ ገዳዮች ወዳሉበት እንዴት ነው የሚመለሱት ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት እንደደረሰበት የገለጸልን የዓዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሃገረ ስብከት ተራድኦ ድርጅት ለ364 ሺህ 311 የጦርነት ተፈናቃዮች የድርቅና ረሃብ ተጠቂዎች እርዳት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገለፀ።

ከፓለቲካ ነፃ መሆኑ የሚጠቅሰው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተራድኦ ድርጅት በትግራይ ጦርነት ጊዜ ለሰብአዊ አገልግሎት ስራ ሲጠቅምባቸው  የነበሩ 14 መኪኖች መዘረፉ አስታውሶ ዘራፊዎቹ ለሰብአዊ አገልግሎት መኪኖቹ እንዲመልሱ " በፈጣሪ ስም እማፀናለሁ " ብሏል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወልደ ሃይለስላሴ ወደ ዓዲግራት ለተጓዘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት ቃለመጠይቅ እንደገለፁት ፤ ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ባለፈው 2023 የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ433 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ364 ሺህ 311 ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ አቅርበዋል።

ከተረጂዎቹ 50 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው ያብራሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እገዛው በመላ ትግራይና ዓፋር ዞን 2 እንደተከናወነ አብራርተዋል።

ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-09

#TikvahFamilyAdigrat

@tikvahethiopia