TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ተቃውሞ እና ደስታ በጎረቤት ኬንያ ! ዛሬ በኬንያ የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ውጤቱን እንደማይቀበሉ የገለፁ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸው ፤ በአንዳንድ ቦታዎችም አመፅ መቀስቀሳቸው ተሰምቷል። ከዚህ በተቃራኒው በጠባብ ውጤት እንዳሸነፉ የተነገረላቸው የዊሊያም ሩቶ ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን እየጨፈሩ በመግለፅ ላይ ናቸው። የራይላ ደጋፊዎች በተለይም በኪሱሙ…
" ውጤቱን አልቀበልም " - ኦዲንጋ

ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት አልቀበለም ብለዋል።

ትላንትና ሰኞ የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዊልያን ሩቶ ማሸነፋቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።

በቦማስ በተደረገው ስነስርዓት ወቅት ጭራሽ በማዕከሉ ያልተገኙት የሩቶ ተፎካካሪ ኦዲንጋ እስከ ዛሬ ከሰዓት ድረስ ስለ ምርጫው ምንም ሳይሉ ቆይተዋል።

ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ የምርጫውን ውጤት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንደሌለውና እሳቸውም እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ሰው እንዲረጋጋ እና ህግ እንዲያከብር አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ በኬንያ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ አለመግባባት እና ውዝግብ ተፈጥሯል። የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ውጤት ያሳውቃሉ ተብለው በሚጠበቁት የኮሚሽኑ ባለሥልጣንት መካከል ክፍፍል መፈጠሩ ነው የተነገረው። በዚህም 4 የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በይፋ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ከሚነገርበት ማዕከል ውጪ መሃል ናይሮቢ በሚገኘው ሴሬና…
ራይላ ኦዲንጋ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና በወቅቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚደገፉት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱ ሕጋዊ ያልሆነ እና ተፈጻሚ የማይሆን ነው ብለዋል።

ኦዲንጋ በመግለጫቸው  ፦

•  ውጤቱን አልቀበልም ብለዋል።

• ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል።

• የኮሚሽኑን ዋና ሰብሰቢ ዋፉላ ቼቡካቲን " አምባገነን " ሲሉ በመጥራት ተችተዋቸዋል። ይፋ ያደረጉትንም ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ አንቀበለውም ሲሉ ገልፀዋል።

• የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ የምርጫ ውጤቱን ይፋ ሲያደርጉ የአገሪቱን ሕገ-መንግሥት በመተላለፍ ትልቅ የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል ብለዋል። በኮሚሽነሮች መካከል ልዩነት እያለ ዋፉላ ቼቡካቲ የምርጫ ውጤቱን ይፋ ማድረጋቸው ስህተት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

NB. የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ያስፈጸመው ገለልተኛ የድንበር እና ምርጫ ኮሚሽን 7 ኮሚሽነሮች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ መካከል 4ቱ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ አለመስማማታቸውን ትላንት መግለፃቸው ይታወሳል።

ከፍተኛ ደጋፊ ያላቸው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ማለታቸው በአገሪቱ ምርጫውን ተከትሎ ግጭት እንዲቀሰቀስ ሊያደርግ ይችላል የሚሉ ስጋቶች ከአሁኑ አይለዋል።

መረጃው ቢቢሲ የራይላን ኦዲንጋን መግለጫ ዋቢ አድርጎ ካዘጋጀው የተወሰደ ሲሆን ፎቶው ከNTV የቀጥታ ስርጭት የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
የአስተዳደር ወሰን !

በአዲስ አበባ ከተማ እና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ማካለል ስራ መጠናቀቁ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተደረሰውን ስምምነት እና ውሳኔ " ታሪካዊ  እና ዘመን ተሻጋሪ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ኦሮምያም በሚያስተዳድርበት ፤ አዲስ አበባም ስታስተዳድርበት በነበረው ቦታ እንድትቀጥል ከስምምነት መደረሱን ከንቲባ አዳነች አሳውቀዋል።

በኦሮምያ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ውስጥ በመግባት በርቀት በአዲስ አበባ የተገነቡ ኮንዶሚኒየሞች ለአብነት ኮየፈጨ፤ ቱሉዲምቱ በከፊልና ጀሞ ቁጥር ሁለት የሚገኙበትን ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን ተካለዋል ብለዋል።

ኦሮምያ የገነባው የቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ወይም ለቡ አካባቢ ከፉሪ ሃናና የኦሮምያ ኮንዶሚኒየሞች ጨምሮ እስከ ቀርሳ ወንዝ ያለውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲካለሉ በማድረግ ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል።

ከዚያ ውጪ ሁሉም ባለበት ቦታ እንዲያስተዳድር ስምምነት ላይ መደረሱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

የአስተዳደር ወሰን በሚነካባቸው አካባቢዎች፦
- የትኛውም አይነት መንግስታዊ አገልግሎት እንደማይቋረጥ፤
- የአገልግሎትና የፀጥታ ስራዎች በሁለቱም ወገን በጋራ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሰራ ፤
- በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እንደማይቆሙ፤
- የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት እንደሚቀጥል፤
- የሚሰጡ መንግስታዊ  አገልግሎቶች ላይ ቋንቋ ምንም አይነት ተፅእኖ እንዳያሳርፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

(ከንቲባዋ ከአስተዳደር ወሰን ውሳኔ ጋር በተያያዘ ያሰራጩት መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#MohamedSalah

ከሰሞኑን በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 5 ሺህ ምዕመናን በተሰበሰቡበት በተነሳ የእሳት አደጋ የቤተክርስቲያኑን አገልጋይ ካህን እንዲሁም እድሜያቸው ከ3 እስከ 16 ዓመት የሚሆኑ 18 ሕጻናትን ጨምሮ 41 ምዕመናን ሕይወታቸውን አጥተው ነበር።

ይህን እጅግ አሳዛኝ ክስተት የሰማው የ #ሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ ኮከቡ ግብፃዊው ሞሀመድ ሳላህ ጉዳት የደረሰባት ቤተክርስቲያን ዳግም እንድትገነባ ለማገዝ ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል።

ሞሀመድ ሳላህ ድጋፍ ያደረገው ሶስት ሚሊዮን የግብፅ ፓውንድ መሆኑ ተገልጿል።

የሳላህ ድጋፍ በዝነኛው የግብፅ ስፖርት ጋዜጠኛ ኢብራሂም አብድል ጋዋድ የተረጋገጠ ሲሆን የተጫዋቹን በጎ ተግባር የሰሙ ሁሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረቡለት ይገኛሉ ሲል ዘ ናሽናል በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

ምንጭ፦ www.thenationalnews.com (Cairo)

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን #በአየር_ንብረትና #በጤና ዙርያ የቀረቡ ረቂቅ ሕጎች ላይ ፊርማቸውን እንዳኖሩ ቢቢሲ ዘግቧል።

ባይደን በፊርማቸው ያጸኑት ሕግ በሃብታሞች ላይ ጠንከር ያለ ግብር የሚጥል ነው።

ይህ ረቂቅ ሕግ ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ኩባንያዎች ላይ ግብር በመጣል በአየር ንብረት ለውጥና በጤና ዙርያ ለሚሠሩ ሥራዎች የሚውል ገንዘብ የሚያስገኝ እንዲሆን የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

ጆ ባይደን ትናንት በረቂቅ ሕጉ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ እንዲሆን አጽንተውታል።

ይህ ሕግ ከዚህ ወዲያ በጤና ዙርያ በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች ዋጋ እንዲስተካከል የሚያደርግ ነው።

የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ለዓመታት በሚታዘዙ መድኃኒቶች ዋጋ ላይ #ቅናሽ እንዲደረግ ሲወተውቱ የቆዩትን ጥያቄ ይመልሳል ተብሏል።

ተጨማሪ : https://telegra.ph/BBC-08-17

@tikvahethiopia
በጎመን ተጠቅልሎ የተያዘው የጥይት ካዝና !

በሀገራችን በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ከተሞች እና ቦታዎች ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ይሰማል።

ህገወጥ የጦር መሳሪያ ለጥፋት ዓላማ የሚውል ሲሆን በተለይ በዚህ ድርጊት ውስጥ ያሉ አካላት መሳሪያውን ለማዘዋወር የተለያዩ መንገዶችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።

ከዚህ በፊት በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተሰሙት መካከል #በምግብ_እህል_ውስጥ ጥይት በመቅላቀል ለማዘዋወር ሲሞከር፣ በመኪና በሮች ላይ ሻግ በማድረግ ለማሳለፍ ሲሞከር፣ በኩርሲ ወንበር ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞከር ... ብዙ ብዙ ነው ተይዘው ታይተዋል።

ትላንትና ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ በሰማነው መረጃ በከተማው ማናኸሪያ 60 የጥይት ካዝና በጎመን ተጠቅልሎ ለጥፋት ዓለማ በህገወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሲሞከር በህበረተሰብ ጥቆማ ተይዟል።

ከጠዋቱ 5 ሰዓት አከባቢ ከሲዳማ ክልል ፤ ጩኮ አከባቢ የተነሳ አንድ ግለሰብ #በ3_እስር_ጎመን ውስጥ በመደበቅ ለጥፋት አካላት ሊደርሰው የነበረ 60 የጥይት ካርታ በቁጥጥር ስር መዋል መቻሉን ፤ መዳረሻውም ያቤሎ እንደነበር ያገኘነውም መረጃ ያሳያል።

የህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር በተለያየ መንገድ እየተፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ የደህንነት አካላት የተጠናከረ ፍተሻ እንዲሁም ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን በመጠቆም ተባባሪ መሆን ሲችል የህገወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን ድርጊት በእጅጉ መቀነስ ፤ የሁሉንም ዜጋ ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላል።

ፎቶ ፦ አስቹ (ከቡሌሆራ Tikvah Family) እና የቡሌ ሆራ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia