TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሰሞኑን ተከታትለው የወጡት የተኩስ አቁም ጥሪዎች !

በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከጀመረ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ተኩስ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት በተከታታይ የተኩስ አቁም እና የድርድር ጥሪዎችን ሲያቀርቡ ተስተውሏል።

1ኛ. #ሩሲያ፦ በድጋሚ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጠይቃለች።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሩሲያ የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተለች እንደሆነ ገልፃለች ፤ ሰሞኑን በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የተካሄዱት ጦርነቶች የሲቪል ዜጎችን ህይወት ጎድቷል ብለዋል።

ሩሲያ #የኢትዮጵያን_ግዛት_አንድነት መከበር ለድርድር የማይቀርብ እና ግጭቱን መፈቻ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ታምናለች ብለዋል።

2ኛ. #ኬንያ ፦ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳስበዋል።

ኬንያታ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ድርድር ይጀምሩ ሲሉ ጠይቀዋል።

ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት ቅንጅት መፍጠራቸው ጦርነቱ ሌላ መልክ እንዲኖረው እና እንዲራዘም እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል እስካሁን ትርጉም ያለው ድርድር አለመጀመሩ ጦርነቱ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለዋል ኡሁሩ።

ኬንያን ጨምሮ አፍሪካ እና ዓለም ሰላማዊ ኢትዮጵያን ማየት ይፈልጋል ያሉም ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመካክሮ ለአገሩ ሰላም መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

3ኛ. #ኢጋድ ፦ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጦርነት እንዲቆምና አስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ፥ እየከረረ መጥቷል ያሉትን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ኢጋድ ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሁኔታውን በማስመልከት ጥሪ ማቅረቡን ያስተወሱት ዶ/ር ወርቅነህ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ከግጭት ተቆጥበው በመካከላቸው ያለውን መካረር እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እና እርቅ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

4ኛ. #ዩጋንዳ ፦ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሐገራት መሪዎች ጦርነቱ ሥለሚቆምበት ሁኔታ ለመነጋገር እንዲሰበሰቡ ጠይቀዋል።

5ኛ. #አሜሪካ ፦ ዛሬም (ጥቅምት 26) አሜሪካ በድጋሚ በኢትዮጵያ ተኩስ ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርባለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ማብቃት አለበት ፤ አሁኑኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድር መጀመር አለበት ብለል፤ ተኩስ እንዲቆምም ጠይቀዋል።

6ኛ. #AU ፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በቅርበትም እየተከታተሉት እንደሆነ ገልፀዋል።

ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ሰሞን ያወጡትን መግለጫ በማስታወስ የጦርነቱ ተሳታፊ ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት፣ ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲጠብቁ በድጋሚ አሳስበዋል።

በአገር ጉዳይ ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲገቡም አሳስበዋል።

ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ እንዲሁም የመንግስት መሠረተ ልማት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች ደጋፊዎቻቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ እንዲሁም ከጥላቻ ትርክቶች፣ ክፍፍልንና ግጭቶችን ከሚያበረታቱ ሁኔታዎች እንዲቆጠቡ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

በሌላ መረጃ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውንና ለድርድር የሚሆን ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ UN ፣ AU ፣ ኢጋድ ፣ አል አይን ኒውስ ፣ Daily Nation ፣ António Guterres (Twitter) ፣ BBC ፣ Antony Blinken (Twitter)

@tikvahethiopia