TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

የአውሮፓ ህብረት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ2021 የመጀመሪያቸው የሆነውን ስብሰባ ትላንት አካሂደዋል።

በስብሰባው የሩስያ ፖለቲካ ጉዳይ፣ ኮቪድ19 ስጋት፣በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ሁኔታ ተነስቶ ውይይት ተካሂዶበታል።

የአፍሪካ ሁኔታን በሚመለከት፦

የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል፥ "የአፍርካ ቀንድን ሁኔታ በጥልቀት አይተናል። በአካባቢው ሌላ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳይፈጠር ጥረት ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑንም ተገንዝበናል። በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታና በኢትዮጳያና ሱዳን የደንበር ውዝግብ ላይ ለሚኒስትሮቹ ማብራሪያ ሰጥቻለሁ" ብለዋል።

ሁኔታውን በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አክላት ጋር ለመወይየትም  የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፔካ ሀቪስት የአውሮፓ ህብረትን ከፍተኛ ልኡክ በመምራት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አካባቢው የሚሄዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ህብረት፣በትግራይ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችና የሰብዊ መብት ጥሰቶች የሚያሳስቡት መሆኑን በመግለጽ  ተደጋጋሚ መገለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል።

የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ገብተው የርዳታ ስራቸውን በነጻ እንዲያከናዉኑ  እንዲፈቀድላቸው፣ጋዜጠኞችና የሰባዊ መብት ድርጅቶቸ ወደ ክልሉ ገበተው ያለውን ሁኔታ እንዲያዩና እንዲዘግቡ በአጠቃላይ በክልሌ የህግ የበላይነት እንዲከበርና የዜጎች መብት እንዲጠበቅ በመጠየቅ፣ ይህ መሆኑ እስከሚረጋገጥ ድረስ ለዚህ ወቅት የሚሰጠውን 90 ሚሊዮን ኢሮ የበጀት ድጎማ የሚያዘገይ መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።

መንግስት ግን የሚቀርብበትን ክስና ውንጀላ ሲያስተባብል መቆየቱን፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት የዕርዳታ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ገብተው የተራዶ ስራቸውን በነጻ እያከናወኑ  እንደሆነ እየገለጸ እንደሞገኝ #ዶቼቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መቼ ነው የሚጠሩት ?

የ2012 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ካወቁ ሁለት ወር ገደማ ሆኖታል።

እስካሁን ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ አያውቁም። 

መቼ ትምህርት እንደሚጀምሩም አያውቁም።

ቃላቸውን ለ "ጀርመን ድምፅ ሬድዮ የወጣቶች አለም" የሰጡ ተማሪዎች ቀድሞውንም ሳይማሩ ጊዜያቸው እንደባከነ ገልፀው ያለፉትን የትምህርት ዘመኖቹን መለስ ብሎ ሲቃኝ ብዙ ቁጭት ያለበት መሆኑን ያስረዳሉ።

በፊትም ትልቅ በደል ነበረብን የሚሉት ተማሪዎቹ በሀገሪቱ የሰላም እጦት ምክንያት 12ኛ ክፍሎች ሳንማር ብዙ ጊዜ አልፏል። 11ኛ ክፍልም እንዲሁ ረብሻ ነበር። በመጨረሻም የኮሮና ወረርሽኝ ታክሎበት ብዙ ትምህርት እንዳመለጣቸው ተናግረዋል።

 ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ የ2012 ዓ/ም ፈተና ቢወስዱና ውጤታቸውን ካወቁ ወራት ቢቆጠሩም አሁንም ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚሄዱበትን ቀን አያውቁም፤ ይህም ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና ዳርጓቸዋል።

የሳይንስ እና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር ከሳምንት በፊት ሁሉም ዩንቨርስቲዎች አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እስከ ግንቦት 30/2013 ይቀበላሉ ሲል አሳውቆ ነበር። ሰኔ 1 ፤ 2013 የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ትምህርት ይጀመራልም ብሏል።

በእርግጥ ሰኔ 1 ሁሉም አዲስ የዩንቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ትምህርት ይጀምራሉ ? ይህስ ዮንቨርስቲው በግሉ የሚወስነው ነው ወይስ ወጥ የሆነ አሰራር አለ ?  ተብለው የተጠየቁት የ ሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር ወ/ሮ አለምወርቅ ሕዝቅኤል «ምርጫውን ታሳቢ በማድረግ ከምርጫ በኋላ በአብዛኛው አዲስ ተማሪዎች ይገባሉ ብለን እናስባለን» ሲሉ መልሰዋል። ትክክለኛ ጊዜውም ሊለያይ እንደሚችል እና ሁሉም ዩንቨርስቲዎች በአንድ ጊዜ ላይጠሩ እንደሚችሉ አስረድተዋል።

#ዶቼቨለ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አህመድ ቀጣን እና በሳኡዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቆንስላ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተሚም አል ዶሰሪ ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው የነበረው ፥ በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያ ግንኙነት፣ የጋራ ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በሳኡዲ አረቢያ…
በሳዑዲ ዓረቢያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ መንግሥት የፀጥታ ኃይላት ከፍተኛ ወከባ፣ እስር እና ዝርፊያ እየደረሰባቸው ነው።

የሳዑዲ ዓረቢያ የጸጥታ ኃይላት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ቤቶች እየዘረፉ ለእስር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን የችግሩ ሰለባ ኢትዮጵያውያን ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ቃላቸውን ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል ለ8 ዓመት በጅዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ካልድ ሲራጅ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳላቸው እየተናገሩ ከባለቤታቸው እና ሁለት ልጆቻቸው ጋር ለ3 ቀን ታስረው መፈታታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ካሊድ፥"ቀጥታ መጡ፤ ልክ ከዝሁር በኋላ ከምሳ ሰአት በኋላ መጡ፤ ሰበሩ። ኢቃማ [ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ] አለን እያልናቸው እንኳን ሊሰሙን አልቻሉም፤...ተንጋግተው መጥተው ነው ቤቱን ሰብረው የገቡት" ብለዋል።

ከትናንትና ወዲያ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ የጸጥታ ኃይላቱ "ሀበሻ" የሚሏቸውን ኢትዮጵያውያን ማሰርና ቤቶቻቸውን መስበር መቀጠላቸውን ነዋሪዎች አመልክተዋል።

አቶ አሕመድ ሁሴን የተባሉ ነዋሪ ደግሞ ወከባ፣እስርና ዝርፊያው መቀጠሉን ተናግረዋል።

«ተደበደበ፤ኅብረተሰቡ ንብረቱን ተወረሰ። ምነው ሂዱ ከተባልን ንብረታችንን እንኳን ይዘን ብንሄድ ? እንኳን የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የመኖሪያ ፈቃድ ያለንም ብንሆን ወደ ሀገራችሁ ግቡ ብንባል በሰላም ብንገባ ምንአለበት እና ኅብረተሰቡ ተዘረፈ እያልን አሁንም ኤምባሲ እየደወልን እየተናገርን ነው" ብለዋል።

አክለውም፥ "ሰሞኑን በሐበሻ ላይ የሚሠራው ሥራ ያለአግባብ ነው፤ ይመጣሉ ፤ ቤት ይሰብራሉ፤ሰብረው ሰዉን ይወስዳሉ ፤ ከዚያ ተከትሎ ወጣቱ ተከትሎ እየገባ ኅብረተሰቡ ተዘርፏል" ሲሉ ገልፀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Saudi-Arabia-06-15

#ዶቼቨለ
@tikvahethiopia