TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አክሱም #Axum

በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የተመራ ልዑካን ቡድን #የአክሱም_ሀውልትን ጎበኘ። ለስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኘው በጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒትሯ አማንኤላ የተመራው ቡድን የአክሱም ሀውልት ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በቅርሱ ላይ እየታየ ያለውን ችግር በባለሞያዎቹም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የልዑካን ቡድን አባላቱ ቅርሱ የተደቀነበትን ችግር በአስቸኳይ ለመንግስታቸው በማሳወቅ ቅርሱ ጥገና የሚደረግበትን መንገድ እናመቻቻለን ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ዉስጥም ባለሞያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩም ተናግረዋል።

ልዑካን ቡድኑ በቅርሱ በአካል የተመለከቱትን ችግር ለመንግስታቸው አቅርበው ምላሽ እንደሚያገኙ እምነት እንዳለቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር የባህል ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ ክብርት ቡዝነሽ መሰረት ተናግረዋል።

ቅርሱ በዋናነት የከርስ ምድርና የገፀ ምድር ውሃ መጠን መጨመር ምክንያት በሀውልቱ ስር ያለውን አፈር የመሸርሸር አደጋ በማጋጠሙ ሀውልቱ ላይ የመዝመም አደጋ እንዲከሰት አድርጓል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Shire #Axum #Mekelle

በሽረ ከተማ ህዝቡ ወደመረጋጋት እና ወደቀደመው ህይወቱ እየተመለሰ መሆኑን ዶ/ር ሙሉ ነጋ (የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ) ለኢቲቪ ተናገሩ።

የወረዳ ፣ የቀበሌ ስራ አስፈፃሚዎች ተመርጠዋል ፤ ወደ ስራም ገብተዋል ብለዋል።

በተመሳሳይ በአክሱም ከተማ የወረዳና የቀበሌ አደረጃጀቶች ተዘርግተዋል ፤ እንቅስቃሴም እንደተጀመረ ገልጸዋል።

መቐለ ከተማ በሚመለከት አሁን ላይ ከተማው ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንደሆነና ሰላማዊ ሁኔታ እንዳለ ዛሬ ከመቐለ ከተማ ሆነው አሳውቀዋል።

ህዝቡ ወደስራው እንዲመለስ ፣ በስጋት ከከተማው ሸሽቶ የወጣም እንዲገባ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል በመቐለ ከተማ የህዝቡ ስጋት ዝርፊያ እንደሆነና ይህም ዝርፊያ እንዲቆም ጥያቄ እንዳቀረበ አንስተዋል ፤ ዝርፊው በቡድን በመደራጀት የሚፈፀም እንደሆነም ዶክተር ሙሉ ገልፀዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከፌዴራሉ መንግስት ጋር በመነጋገር በፍጥነት ይህ ሁኔታ መፍትሄ እንዲያገኝ እየሰራ እንደሆነ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Axum

Save the Children ዛሬ በላከልን መግለጫ በአክሱም ከ3 ወራት ወዲህ የመጀመሪያ እርዳታ ማከፋፈሉን አሳውቆናል።

በዕርዳታው በከተማው የሚገኙ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው ምግብ፣ መጠለያና የንፅህና መጠበቂያዎችን እንዳገኙ ገልጿል።

አክሱም በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ በርካታ ተፈናቃዮችን ያስጠለለች ሲሆን ከ6 ሺህ የሚልቁ ተፈናቃዮች በተጣበቡ ትምህርት ቤቶች ፣ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችና በአከባቢው ነዋሪዎች ቤት ተጠልለው ይገኛሉ።

የSave the Children ልገሳ ለተፈናቃዮች መሰረታዊ የምግብ፣ መጠለያ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ያካተተ ነው።

Save the Children በአክሱም በየካቲት መባቻ እጅግ አስፈላጊ ድጋፍ ማቅረብ ከጀመረ አንስቶ ለቀናት እህል ያልቀመሱና በሆስፒታሎች ባለው እጅግ ውስን የህክምና አቅርቦቶች የተነሳ አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶች ማግኘት ያልቻሉ ቤተሰቦችን አግኝተዋል።

ድርጅቱ በእስካሁኑ የምግብ እና ሌሎች እርዳታ ለ1,063 ቤተሰቦች ወይም 4,368 ሰዎችም መድረስ እንደቻለ ቢገልፅም አሁብም ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

* ከSave the Children የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ የያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia