TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " አስቸኳይ " ያለውን ሰብሰባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። ዛሬ መሰከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት አዳራሽ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን ህወሓት በይፋ የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ካድሬዎች ተገኝተዋል።  አቶ ጌታቸው በሰብሰባው መክፈቻ…
#Update

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሚመራው የህወሓት ቡድን ጋር ያላቸው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደሚሰራ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን ተናግሯል።

በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከፍተኛ ካድሬዎች መስከረም 20/2017 ዓ.ም በመቐለ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።

ውይይቱ ለሁለት የተከፈለው ድርጅት ለማዳንና የትግራይ ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ያለመ  ነው ተብሏል።

በዚህም ወቅት በአቶ ጌታቸው የሚመራው ቡድን የተፈጠረው ልዩነት እንዲሰፋ እየሰራ ያለው " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይሳካ የተሰለፈ የሰላም ፀር የሆነ ሃይል ነው " ብሏል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የህወሓት ህጋዊነት እንዳይመለስ እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይፈፅምና የተገኘው ተነፃፃሪ ሰላም እንዳይቀጥል እንቅፋት የሆነው " የሰላም ፀር " ሲሉ የጠሩትን በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራውን ህወሓት ከሰዋል። 

" በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ሃይል ጉባኤ አካሂጃለሁ በሚል ሽፋን ራሱን እንደ ህጋዊ በመቁጠር የወረዳና የከተማ ምክር ቤቶች እየሰበሰበ ይገኛል " በማለት አክለዋል።

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ሃይል በስም ማጥፋት ተግባራት መሰማራቱ የገለፀው በምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው የሚመራ ህወሓት ከዚህ ተግባሩ እንዲቆጠብና ሰርዓት እንዲይዝ ጠይቋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ዛሬ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ላይ መሰረት ያደረገ ውይይት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ የተያዘ ፕሮግራም የለም ፤ ምናልባት ወደፊት ሊኖር ይችላል " - የሕ/ተ/ም/ቤትና የአፈ ጉባዔው አማካሪ ኮሚቴ አባል (ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ)

የ6 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶችን የ2017 የሥራ ዘመን ነገ ያስጀምራሉ። 

የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በተገኙበት ነገ ሰኞ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ የሕ/ተ/ም/ቤት መረጃ ያሳያል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የመጀመርያ የሥልጣን ዘመናቸውን ያገባደዱ ቢሆንም፣ ሰኞ የሚጠበቀው የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ከተካሄደ በኋላ ቀጣዩ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ምርጫ የሚካሄድ ስለመሆኑ ግን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መረጃ ያለው ነገር የለም። 

የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሥልጣን ዘመን 6 ዓመት እንደሆነ፣ ነገር ግን ርዕሰ ብሔሩ ለሁለተኛ ጊዜ ሊመረጥ እንደሚችል ሕገ መንግሥቱ ይደነግጋል። 

የሥልጣን ዘመናቸውን ባጠናቀቁት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ምትክ ሌላ ርዕሰ ብሔር ይመረጥ ይሆን ? ወይም እሳቸው ለሁለተኛ ጊዜ በርዕሰ ብሔርነት የመመረጥ ዕድል ያገኙ ይሆን ? የሚለውን ለማወቅ ሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ የም/ቤቱ አባላትን ያነጋገረ ቢሆንም ሁሉም ስለዚህ ጉዳይ የሰሙት ነገር እንደሌለና ከምክር ቤቱም ይህንን ጉዳይ የተመለከተ መረጃ እንዳልደረሳቸው ገልጸዋል።

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የአፈ ጉባዔው አማካሪ ኮሚቴ አባል ፤ ሰኞ በሚጀመረው የሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ አዲስ ርዕሰ ብሔር ምርጫ የሚካሄድ ቢሆን ኖሮ እሳቸው ሊያውቁት እንደሚችሉ በመጠቆም፣ የርዕሰ ብሔር ምርጫ ይካሄዳል የሚል ዕምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። 

" የፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ የተያዘ ፕሮግራም የለም፣ ምናልባት ወደፊት ሊኖር ይችላል " ብለዋል።

አንድ የሕግ ባለሙያ ስለ ጉዳዩ በሰጡት ቃል ደግሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በርዕሰ ብሔርነት የተሰየሙት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም መሆኑን አስታውሰው 6ኛ ዓመታቸውን የሚያገባድዱት በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. በመሆኑ አዲስ ርዕሰ ብሔር የመምረጥ ሒደት እስከዚያ ድረስ ሊገፋ እንደሚችል አስረድተዋል።

ከ20 የአገሪቱ የካቢኔ አባላት ግማሹ ሴት ሆነው በተመረጡ በሳምንቱ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ በወቅቱ አድርገውት በነበረው ንግግር በዋናነት ሰላምና ሴቶች ላይ ያጠነጠኑ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣" በኃላፊነት ቆይታዬ ዋነኛ ትኩረቴ ሰላም በማስፈን ላይ እንድንረባረብ ማድረግ ይሆናል… ኢትዮጵያዊነትን ከሰላም ጋር አንድና ህያው ለማድረግ በጋራ እንሥራ "  ብለው ነበር።

አክለውም፣ " የሴቶችን ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት የማይቀበል ትውልድ መገንባት አለብን… ሴቶች የቤተሰብም የአገርም ምሰሶ ናቸው፡፡ ሴት አገር ነች፣ አገርን ደግሞ ሴቱም ወንዱም ሊንከባከበው ይገባል " ብለው ነበር።

" ስለሴቶች አብዝቼ የተናገርኩ ከመሰላችሁ ገና ምኑ ተነክቶ ? " ሲሉ የምክር ቤቱን አባላት በፈገግታ ሞልተውት ነበር። 

በተጨማሪ " ታላቅ አገር የመገንባት ህልማችንን ዕውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ አቋራጭም አማራጭም የለንም፡፡ ስለዚህም ሁላችንም ሰላማችንን አጥብቀን እንድንጠብቅ ከሁሉም በላይ ሰላም ሲታወክ በምትሰቃየዋ የእናት ስም አጥብቄ እጠይቃችኋለሁ " በማለት ጥሪ አቅርበው ነበር።

የሥልጣን ዘመን ጉዟቸው እጅግ ውስብስብና በርካታ ፈተናዎች ያሉበት እንደሚሆን እንደሚጠብቁ ያስታወቁት ፕሬዚዳንቷ " የተጀመረው ለውጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባትን አገር ዕውን እንደሚያደርግ እተማመናለሁ " በማለት ተስፋቸውን ገልጸው ነበር።

ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን፣ " ዋነኛ ትኩረቴ ሰላም በማስፈን ላይ እንድንረባረብ ማድረግ ይሆናል " እንዳሉት ሳይሆን እንደ ሥጋታቸው ማለትም፣ " እጅግ ውስብስብና በርካታ ፈተናዎች ያሉበት ኃላፊነት ይሆናል " ብለው እንደ ሠጉት ሆኖ አልፏል። 

በርካታ ሰብዓዊ ጉዳትና የኢኮኖሚ ውድመት ካስከተለው የሰሜኑ ጦርነት አንስቶ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እስካሁን ደም እያፋሰሰ የዘለቀው ግጭትና መከራ በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሥልጣን ዘመን ተከስቷል።

በዚህም ዋነኛ ገፈት ቀማሾቹ ሴቶችና ሕፃናት ዋነኛ ገፈት ቀማሾች መሆናቸው፣ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት ጭምር የተረጋገጠ መሆኑ ይታወሳል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአዲስ አበባ ከተማ ተወልደው ያደጉ ሲሆን፣ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ተከታትለው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ፈረንሣይ ከሚገኘው ሞንትፔለ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ አግኝተዋል።

የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛና የአማርኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያን በመወከል ፦
- በሴኔጋል፣
- በኬፕቨርዴ፣
- በጊኒ ቢሳኦ፣
- በጋምቢያ
- በጊኒ በአምባሳደርነት አገልግለዋል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና የኢጋድ ቋሚ መልዕክተኛ በመሆንም አገልግለዋል፡፡

በተጨማሪ በፈረንሣይ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ፣ በቱኒዚያና በሞሮኮም የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተቀናጀ የሰላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በርዕሰ ብሔርነት ከመሾማቸው በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ልዩ ረዳትና በአፍሪካ ኅብረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ በመሆንም አገልግለዋል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። ይህ የሆነው አሁን ከመሸ ከ2:00 በኃላ ነው። በአንዳንድ ቦታዎችም ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል። የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በስጋት ወደ መሬት ወርደው ተሰብስበዋል። ተጨማሪ መረጃዎች ከባለሙያዎች ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው። @tikvahethiopia
#Update : በአዲስ አበባ ከተማ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽት 2 ሰዓት በኃላ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር።

ህፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት።

ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች አንዳንድ ከተማዎች / ቦታዎች መሰል ሁኔታ እንደነበር ከቤተሰቦቻችን በሚላኩ መልዕክቶች ተረድተናል።

በጉዳዩ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሰጡትን አስተያየት እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update : በአዲስ አበባ ከተማ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል። ከምሽት 2 ሰዓት በኃላ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር። ህፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት። ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች አንዳንድ ከተማዎች / ቦታዎች…
#Update

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሾሙ በእጩነት ቀረቡ። @tikvahethiopia
#Update

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።

አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

@tikvahethiopia
#Update

በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ ለ4ኛ ጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱ ተሰማ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በእነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ በተሰሙ የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለ4ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ፦
- ቄስ በላይ መኮንን፣
- በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
- በኮሚሽን ስራ ላይ በተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር
- አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
- የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ በተባሉት ላይ ከባድ ማታለል ሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

በዚህም ተከሳሾቹ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትእዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር ለተከሰሱ ተከሳሾች በተለያዩ የዶላር መጠን ክፍያ ይፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ በአንደኛ ተከሳሽ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ ማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል።

በዚህ መልኩ የቀረበውን ክስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ብቻ ችሎት የቀረቡና የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ እንደሚጣራ ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።

ከዚህም በኋላ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው ተከሳሾቹ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ህግ የአፍሪካ ህብረት ቅርጫፍ የባንክ ባለሙያዎችን አጠቃላይ ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር፡፡

በዚህም ዐቃቤ ህግ ቀረበ ስለተባለው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የምስክር ጭብጥ በማስመዝገብ በዋና ጥያቄ ምስክሮቹን ቃል ያሰማ ሲሆን በዕለቱ የተከሳሽ ጠበቆች ለምስክሮች በመስቀለኛ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በፍርድ ቤቱ የማጣሪያ ጥያቄ ተነስቶ ከምስክሮች መልስ ተሰጥቶበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግ ምስክር ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ከሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት ጊዜ ቀጥሮ ነበር፤ ይሁንና ዛሬም በነበረ ቀጠሮ በተለያዩ ስራዎችና ምክንያት መዝገቡ ተመርምሮ ተሰርቶ አለመጠናቀቁ መዝገቡን በሚመለከቱት ዳኛ በኩል ተገልጾ በድጋሚ ለ4ኛ ጊዜ ለጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጥሯል።

የመረጃው ምንጭ ኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #ሲዳማክልል

“ ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው  ” - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ

በሲዳማ ክልል ሰሜን ሲዳማ ዞን ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ ባለይዞታዎች፣ “ ፓሊሶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል ” ሲሉ ለቲክቫህ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ምላሽ ሰጥቷል።

ለዛውም በፍርድ ሂደት ላይ ባለ ጉዳይ “ ጠመንጃ በመደቀን ድብደባ መፈጸም ” ተገቢ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳዬሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አሀመድ፣ “ ህዝቡ ተደብድቧል የሚል ቅሬታ አልመጣም። ተደብድቦ ከሆነ የምናጣራ ይሆናል ” ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ቅር ያሰኛቸው መንገድ መከፈቱ ሳይይሆን ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሂደት እያለ ደርጊቱ መፈጸሙ፣ በፓሊስ ደብደባ ስለተፈጸመባቸው፣ በንብረት ላይ ውድመት ስለደረሰባቸው፣ ካሳ ስላልተከፈላቸው በመሆኑ ነውና ለዚህስ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ሀሚድ አሀመድ

“ አዎ በእርግጥ ፍርድ ቤት ያለ ኬዝ ነው። ከላይ ያለ አካል አቅጣጫ ሲያስቀምጥ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማይጠበቅበት ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ከመጣ እንደዚህ አይነት ጉዳዮች አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች የሚጠቅባቸው አይነት ነገሮች ሳይመጡ ሲቀሩ ላይጠበቅ ይችላል።

የሚገመት አይነት ንብረት አይደለም። ፎቶውን ሳይ የተወሰነ አትክልት ነገር አለ ፤ ድንች ፣ ቀይ ሽንኩርት ነበረ። ካሰ የሚከፈል ከሆነ እንደ ካሳ ነው የሚነጋገሩት። ካልሆነ ደግሞ በሌላ ካሳ እንዲከፈላቸው ነበር ማድረግ የነበረባቸው።

‘ በጭራሽ መንገድ አይወጣም ’ ነው እነርሱ ሲሉ የነበሩት። ካሳ ተከፈለ አልተከፈለ የግድ ይላል ህዝቡ ያነሳው ጥያቄ መንገድ የለንም’ የሚል ነውና።

ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው። 

የፍርድ ቤት ኬዛቸውንም ይከታተሉ። ይሄ ደግሞ እንዳይከታተሉ የሚያደርጋቸው ነገር አይደለም። ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ ፍርድ ቤቱ ካሳ ሊያስከፍልላቸው ይችላል።


እኔ ጉዳዩን አጣርቻለሁ። ባለፈው ፕሬዝደንቱ እዛ ሂደው ነበር። አጋጣሚ የፓሊስ ግንባታ ፕሮጀክት ሊያስመርቁ በሄዱበት ‘ እዛ መንገድ እንዲወጣ ነበር ’ ያሉት። 

መንገድ በፊት ተከልክሎ ነበር እዚያ ቦታ እንዳይወጣና ፕሬዚደንቱ ካዩ በኋላ መንገዱ እንዲወጣ ነበር ያዘዙት። ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት ነው መንገዱ እንዲወጣ የተደረገው።

የመንገድ ከፈታ የትም ያለ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀዋሳ መጥተው በነበረበት ወቅት ማግስት ‘ምንድን ነው ችግራችሁ?’ ብለው ሲጠይቁ፣ ‘ሀዋሳ መውጫና መግቢያ መንገድ አጥተናል። ምንም መንገድ አልተከፈተልንም’ የሚል ቅሬታ ሲያነሱ ‘በሲዳማ ክልል ከተሞች የውስጥ መንገድ ሁሉም ቦታ እንዲከፈት ነበር አቅጣጫ አስቀምጠው የወጡት።

በክስ ያሉ ቦታዎች ነበሩ። መንገድ ከፈታ ላይ አንዳንድ ማህበረሰብ እንዲወጣላቸው ይፈልጋሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ እንዲወጣ አይፈልጉም። 

አንዳንድ ንብረት ይነካል። ይሄ ደግሞ የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። የምንጓዘው፣ መድኃኒት የሚደርሰው፣ ችግር የሚፈታው በመንገድ ነው። ግን ‘መንገድ አይከፈት’ በማለት ሁከት እንዲነሳ የሚፈልጉ አካላት አሉ።

ወደ 6፣ 7፣ 8 ሰዎች ሆነው ነው እዛ ሲጨቃጨቁ የነበረው። ነገር ግን አብዛኛው መንገድ እንዲከፈትላቸው የሚፈልጉ አሉ። በዚህም ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው እንዲከፈት የተደረገው። ”


#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዘረት እንደሰሙ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል። " በተለይም ፎቅ ላይ በደንብ ይታወቅ ነበር " ብለዋል። ጎተራ፣ አያት ፣ ባልደራስ ፣ ሰሚት ፣ መካኒሳ ፣ ጀሞ ፣ ኮዬ ፣ ጣፎ ፣ ቱሉ ዲምቱ ፣ ጦር ኃይሎች ፣ ቀጨኔ፣ ጎፋ ... እንዲሁም ከሌሎች በርካታ አካባቢዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ ንዝረቱ መሰማቱን የሚመለከቱ…
#Update

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' ዛሬ ምሽት ልክ 5:11 ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን በኩል 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እና በተለያዩ የክልል ከተሞች ተሰምቷል።

አዋሽ አካባቢ ባለፉት ሳምንታት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ሲሆን አዲስ አበባ ድረስ የዘለቀ ንዝረት ሲሰማ ይህ በቀናት ልዩነት ለ3ኛ ጊዜ ነው።

ከቀናት በፊት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከዛ በፊት ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ መሰማቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update በመርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው እሳት እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም።

እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ከእሳቱ መፋፋምና ከቦታው አለመመቸት የተነሳ ሁኔታውን እንዳከበደው በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል።

እሳቱ ያልደረሰባቸው ሱቆች እቃቸውን ከስፍራው እያሸሹ ናቸው።

እስካሁን የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቀም በርከት ያሉ ሱቆች ግን እየተቃጠሉ ናቸው።

ተጨማሪ መረጀዎችን እንልክላችኋለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በመርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው እሳት እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም። እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ከእሳቱ መፋፋምና ከቦታው አለመመቸት የተነሳ ሁኔታውን እንዳከበደው በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል። እሳቱ ያልደረሰባቸው ሱቆች እቃቸውን ከስፍራው እያሸሹ ናቸው። እስካሁን የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቀም በርከት ያሉ ሱቆች ግን እየተቃጠሉ ናቸው።…
#Update

“ አደጋውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ”  - አቶ ንጋቱ ማሞ

መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከኮሚሽኑ ቃላቸውን የሰጡትን አቶ ንጋቱ ማሞ፣  አደጋውን ለመቆጣጠር እርብርብ እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

“ ከመሸ ነው ጥሪ የመጣው። ጥሪው እንደመጣ በአቅራቢያው ካሉ የአዲስ ከተማ፣ አራዳ ክፍለ ከተሞች ልከን ነበር ” ብለዋል።

“ ነገር ግን በእነርሱ የሚሸፈን ስላልሆነ ከሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያ የአደጋ መቆጣጠር ማሽነሪዎች፣ አደጋ ጊዜ ሠራተኞች፣ አምቡባንሶች፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ አመራሮች ጭምር ቦታው ላይ ሆነው አመራር እየሰጡ ነው እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ” ሲሉ አክለዋል።

“ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች እሳቱ ወደተነሳበህ ቦታ ላይ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቦታው ትንሽ አስቸጋሪ አድርጎታል ” ያሉት አቶ ንጋቱ፣ “ ዞሮ ዞሮ ርብርብ እየተደገ ነው ” ብለዋል።

“ በዚህ ሂደት የጸጥታ ኃይሎች የአካባቢው ማህበረሰብ አሉ። አደጋውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ያሉትን ሂደቶች እንደሚያደርሱን የገለጹ ሲሆን፣ መረጃው እንደደረሰን የምናጋራ ይሆናል።

ቪድዮ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

መርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ እስካሁን አልቆመም።

እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ " በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መርካቶ🚨 በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳው እሳት እስካሁን ሊቆም አልቻለም። @tikvahethiopia
#Update

ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳውን እሳት እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም።

ርብርቡ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ እሣትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ምን አሉ ?

- የእሳት አደጋው የተከሰተው 1 ሰዓት ገደማ ነው።

- እሳት መነሳቱን በሰማን ጊዜ አብዛኛዎቹ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች ርብርብ እንዲያደርጉ አሰማርተናል።

- መኪናዎች በወቅቱ ነበር የደረሱት፤ ከደረሱ በኃላ የእሳቱ ባህሪና ሁኔታ ሲታይ ለሌሎች አጋዥ አካላት ፦
° አየር መንገድ
° ፌዴራል ፖሊስ
° ሌሎች ከተማ ውስጥ ያሉ ውሃ አቅራቢ ተቋማት በሙሉ እንዲረባረቡ ተደርጎ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረግን ነው።

- ቦታው በጣም አስቸጋሪ ነው።

- በሁሉም አቅጣጫ በኩል መኪና ገብቶ እሳቱን ለማጥፋት በጣም ፈትኖናል። በተለይ በዙሪያ የሚቀመጡ እቃዎች ቶሎ ተገብቶ የእሳቱን መሰረት እንዳይመታ አድርጓል።

- አካባቢው በቆርቆሮ የተያያዘ ነው። መንገዱ በጣም ጠባብ ነው። ገብተን ለማጥፋት ተቸግረናል።

- በአጋጣሚ ባለሱቆች፣ ነጋዴዎች ዘግተው ወጥተው ነበር። የቆሙ መኪኖችንም ለማስነሳት ችግር ሆኖብን ነበር።

- አሁን ላይ ከቅድሙ እየተሻሻለ ነው። የመቀነስ እና የመጥፋት አዝማሚያ አለው። በተለይ ከዚህ እንዳይሰፋ ወደታች ከወረደ በጣም ሰፊ ቦታ ነው ያለው ቆርቆሮ በቆርቆሮ እሱ ጋር እንዳይደርስ ከበን ለመያዝ ሞክረናል።

- አጋዦች ከመጡ በኃላ እሳቱ ባህሪው እንዳይሰፋ ተሞክሯል። አሁንም ህብረተሰቡ አግዞን ለማጥፋት እየሞከርን ነው። እናጠፋዋለን ብለን እናምናለን።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ከኤ ኤም ኤን ነው የወሰደው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳውን እሳት እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም። ርብርቡ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ተሰምቷል። የአዲስ አበባ እሣትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ምን አሉ ? - የእሳት አደጋው የተከሰተው 1 ሰዓት ገደማ ነው። - እሳት መነሳቱን በሰማን ጊዜ አብዛኛዎቹ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች ርብርብ እንዲያደርጉ አሰማርተናል።…
#Update

" እዚህ ላይ ባይገታ እሳቱ ሰፊ አካባቢዎች ላይ  ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ሃብትም ይወድም ነበር " - አቶ ፍቅሬ ግዛው

በመርካቶ ሸማ ተራ የደረሰው ውድመት አሳዛኝ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው አሁናዊ ሁኔታውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኮሚሽነር ፍቅሬ ፤ " አሁን ላይ እሳቱን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ፤ የማጥፋትና የመልቀም ስራ ነው የሚቀረን " ብለዋል።

" እጅግ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ እዚህ ላይ ባይገታ በጣም ብዙ ቦታ ፣ ሰፊ አካባቢዎች ላይ እሳቱ ደርሶ ህይወት ያጠፋ ነበር ፤ ከዚህ የበለጠ ሃብትም ይወድም ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

" የአካባቢው አስቸጋሪትነት እሳቱን ለመቆጣጠር ረጅም ሰዓታት ወስዷል " ያሉት ኮሚሽነሩ " ከዚህ በኃላ ብዙ ጉዳት ያደርሳል ብለን አናስብም፤ ተቆጣጥረነዋል ማለት ይቻላል " ብለዋል።

" እሳቱ ዳግም እንዳይቀጥል ቦታውን አዳሩን በሙሉ ተቆጣጥሮ ቅሪት ነገሮች ካሉ እነሱን እያጠፋን እንቀጥላለን ፤ ህብረተሰቡ እሳት ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ ነገሮችን ያስወግድ " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራው ካሉ ነዋሪዎች በደረሰው መልዕክት በእሳቱ በርካታ ንብረት መውደሙን ፣ ከቆርቆሮ ቤቶቹ ወጥቶ አጠገብ ያለ ህንጻ ተያይዞ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን፣ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም ከቅድሙ አንጻር ሲታይ እሳቱ የከፋ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጤናባለሙያዎች " ቀን ፣ ምሽት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ ነው " - ጤና ባለሙያዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዲዩቲ ክፍያ አልተከፈለንም ያሉ ከ 80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል። በከምባታ ዞን ፤ አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የ6…
#Update

" የጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም " - የሆስፒታሉ ሰራተኞች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የጤና ባለሞያዎቹ እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሲሆን ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸውልናል።

ስራ አቁመው በቆዩባቸው ቀናት ከወሊድ ጋር በተገናኘ ወደ ሆስፒታሉ መጥተው የነበሩ እናቶች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው ባለሞያዎች እና ከሆስፒታሉ አመራር ተረድቷል።

ጉዳያቹ ከምን ደረሰ ? ስንል በድጋሚ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የጤና ባለሞያዎች " የስራ ማቆም አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 በሚሆኑ ባለሞያዎች ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶ እየተፈለጉ መሆኑን እና ይህንንም ፍራቻ ከአካባቢው ርቀው መደበቃቸውን ተናግረዋል።

" እኛ ስራ ካቆምን በኋላ የምንጠብቀው የሚመለከታቸው አመራሮች ችግራቹ ምንድነው ? እንዴት ዘጋቹ ? ምንድነው ችግሩ ? ብለው መጠየቅ እና መሰብሰብ ሲገባቸው ጭራሽ ወደ ማሳደድ ገብተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሸሽተን ነው ያለነው በፖሊስ ማዘዣ ወጥቶ በተገኙበት ይያዙ ተብሏል እየተፈለግን ነው። ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽተናል " ሲሉ አክለዋል።

" ተቋሙ በቂ መድኃኒት እና የህክምና ግብአቶች የሉትም ለበርካታ ጊዜያት የመድኃኒት ግዢ አልተፈጸመም ሆስፒታሉን የምናገለግለው ባለው ነገር ነው " ያሉ ሲሆን ነገር ግን ስብሰባ ላይ ያለውን ችግር የሚናገሩ ሰዎች '" አድመኛ እና ሌላ አላማ ያላቸው ተብለው እየተፈረጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ " ይህንን ችግር ችለን እየሰራንም የሰራንበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ደሞዛችን ለምንም የሚበቃ አይደለም ነው " ያሉት።

" ስራ በማቆማችን የኛን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ በማህበረሰቡ ዘንድ እንድንጠላ ሥራ እየሰሩ ነው " ያሉ ሲሆን " እየተሰቃየ ቀን እና ማታ የሚሰራ ሰው የ2016 ዕዳውን ሳይከፍል ፣ የቤት ኪራይ ክፈል ወይም ልቀቅ እየተባለ በስቃይ ነው ያለው ባለሞያው ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥቶ ነው ስራውን የሚሰራው እረፍት ወጥቶ ሄዶ እናቱን እና አባቱን እንዳይጠይቅ የህክምና ስራ እረፍት የለውም " ብለዋል።

" ችግርህ ምንድነው ተብሎ አይጠየቅም ? ሲሪንጅ (Syringes) የለም ብለን ማውራት የለብንም እንዴ ? ማቴሪያል ለዚህ ተቋም ያስፈልጋል ህዝቡ መንገላታት የለበትም ብለን መጠየቅ የለብንም ? ይህንን ባወራን በፖሊስ መጥሪያ መውጣት የለበትም አግባብ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም ይሄንን ሌላ ቦታ አላወራንም ስብሰባ ላይ ነው ያወራነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለሙያዎቹ ፥ " እኛ ስራውን ከማቆማችን በፊት ሁሉም ባለሞያ ቀደም ብሎ ተኝቶ ታካሚዎችን ወደ ሌላ ቦታ ሪፈር አድርገን ነው የወጣነው " ያሉ ሲሆን እነሱ ግን ታካሚዎችን ትተን እንደወጣን በማስመሰል በማህበረሰቡ ዘንድ የማጥላላት ሥራዎችን እየሰሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፥ " ለመንግስት የስራ ሰዓት ብለን ለምንሰራው ሥራ የሚከፈለን ደሞዝ ለእኛ በቂ አይደለም ኢኮኖሚውን መቋቋም አልቻልንም። " ብለዋል።

" የቆየ ችግር ነው ከ2015 ጀምሮ እየተቆራረጠ ነው የሚመጣው እያቃተን ነው ። የሚገባልን ደሞዝ እዳችንን ራሱ መክፈል አልቻለም። አሁንም ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ' ለሌላ ሆስፒታል ሰራተኞች ማስተማሪያ የሚሆን እርምጃ ይወሰድባቸው ' ተብሎ እየተፈለግን ነው ሲሉ ነግረውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሆስፒታሉን አመራር አግኝቶ ስለ ችግሩ ጠይቋል። የአመራሩ ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም " - የሆስፒታሉ ሰራተኞች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የጤና ባለሞያዎቹ እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው…
#Update

" ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው " -የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ

ከክፍያ ጋር በተያያዘ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ዘግተው ስለወጡና ስራ ስላቆሙ ጤና ባለሞያዎች በተመለከተ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።

" እኔ እንደ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ይከፈላቸው ብዬ እየጠየኩ ነው በዕለቱም ይህንን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ለመነጋገር ስሄድ ነው ዘግተው የወጡት " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስመጣ ሁሉም ክፍል ዝግ ሆኖ ነው የጠበቀኝ ታካሚው ውጪ ሲጉላላ ነው የደረስኩት " ብለዋል።

ወረዳውም የተጠየቀውን ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ነው ያሉት አቶ ተሰማ " ነገር ግን ' የገንዘብ እጥረት አለብኝ 'ታገሱ ' ብሏል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ጤና ጣቢያ ለአንድ ደቂቃም መዘጋት የለበትም " የሚሉት ሃላፊው " እነሱ ግን ዘግተው ወጡ እንደዚህ ሲሆን ማስታወቂያ አወጣን ' ወደ ስራቹ ተመለሱ ' የሚል አልመጡም በመሃል ወሊድ ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ የመጡት እናቶች ሪፈር በሚደረጉ ወቅት ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል " ብለዋል።

" ላብራቶሪ ፣ ማዋለጃ ፣ መድሃኒት ክፍል ሁሉንም ዘግተው ነው የሄዱት ቁልፍ አስረክበው ቢሄዱ አንድ ነገር ነው ትልቅ ወንጀል ነው ሰርተው የሄዱት " ሲሉ ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጁ አምናም በተመሳሳይ ከዲዩቲ ክፍያ ጋር በተያያዘ ሆስፒታሉ ተዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል።

" ያኔ ምንም እርምጃ አልተወሰደም በዚሁ ከቀጠለ ጤና ተቋማት እየተዘጉ ህዝብ ያልቃል እርምጃ ካልተወሰደ ነገም ቢሆን እየዘጉ ይወጣሉ በዚህ መሃል ሰው ይሞታል የሞተ ሰውን ደግሞ መመለስ አይቻልም " ብለዋል።

በተቋሙ ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው የዘጓቸውን ክፍሎች ግን በህጋዊ መንገድ ሰብረን ገብተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ለጊዜው ከሌሎች አካባቢዎች ባለሞያዎችን አምጥተው ሥራ ለመጀመር እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከ80 በላይ ባለሞያዎች በአንድ ጊዜ ነው ስራ ያቆሙት ምን ያህል ባለሞያዎችን አግኝታቹሃል ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ " ባሉት ዋና ዋና ጊዜ የማይሰጡ የወሊድ እና የድንገተኛ ህክምና ቦታዎች ላይ 7 ባለሞያዎች አምጥተናል ኦፕሬሽን ላይ ግን ሰው ማግኘት አልተቻለም " ብለዋል።

እነዚህ ባለሞያዎች ክፈተቱን ለመሸፈን የመጡ እንጂ ቋሚ ተቀጣሪዎች አይደሉም ሲሉ አስረድተዋል።

ስራ ያቆሙት ባለሞያዎች ተመልሰው ቢሙጡ ትቀበላላቹ ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ  " እስካሁን የመጣ ባለሞያ የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ' በሌሎች ተገፋፍተን አስፈራርተውን ነው ' የወጣነው የሚሉ ባለሞያዎች አሉ የሚመለሱ ከሆነ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ነገር ግን አስቀድመን ከማህበረሰቡ ጋር ውይይቶችን አድርገን ነው የሚሆነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ሃላፊው ፥ " ስራ በማቆማቸው ቀዳሚ ተጎጂ ማህበረሰቡ መሆኑን ጠቁመው ከሰኞ በኋላ ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግረን ይመለሱ አይመለሱ የሚለውን የምንወስን ይሆናል " ሲሉ አክለዋል።

ወደ አመራርነት ከመጡ 2 ወራቸው እንደሆነ የገለጹት አቶ ተሰማ " በሆስፒታሉ ውስጥ የአከፋፈል ስርዓት ችግር አለ ከታካሚው አንጻር ትርፍ ባለሞያ ነው ያለው አንዳንድ የማሻሻያ ስራዎች እየሰራን ነው ተቋሙ ላይ መድኃኒት መኖር አለበት መድሃኒት በህገወጥ መንገድ የሚወጣበት ተቋም ነው። ይህ እንዳይሆን አንዳንድ ስራዎችን መስራት ጀምረናል ይህ ያስቆጣቸው ሰዎች አሉ " ብለዋል።

ቲክቫክ ኢትዮጵያ ሰራተኞቹ የጠየቁት የተጠራቀመ እና የሰሩበትን ክፍያ ነው በምን ያህል ጊዜ ችግራቸውን ትፈታላቹ ? የሚል ጥይቄ አንስቷል።

ስራ አስኪያጁ ፤ " እኔ ያሰራኋቸውን የሁለት ወር የዲዩቲ ክፍያ ለመክፈል 1.4 ሚልዮን ብር ያስፈልጋል ይህንንም ለመክፈል ቀኑን መወሰን አይቻልም ወረዳው ' ያለውን ነገር ተነጋግረን እንፈታለን ' ብለዋል ይከፈላቸዋል " ሲሉ መልሰዋል።

" ያልተከፈላቸውን ክፍያ ሁሉ ለመክፈል ወረዳው ዝግጁ ነው " ያሉ ሲሆን ነገር ግን የበጀት እጥረት በመኖሩ ቀኑን መወሰን እንደማይቻል ገልጸዋል።

በ2016 የጥር ወር ላይ የ4 ወር የዲዩቲ ክፍያ ባለመከፈሉ በተመሳሳይ ሰራተኞች ስራ አቁመው እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ነው።

በወቅቱ ሆስፒታሉ ከወረዳው ከሚገኙ የጤና ጣቢያዎች 17 ያህል ባለሞያዎችን ቀጥሮ ስራ አስጀምሮ ነበር።

ከዚያ በኋላም የአንድ ወር እንዲከፈላቸው ተደርጎ ወደ ስራ ተመልሰው የነበረ ሲሆን በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩት 17 ባለሞያዎች አብረው እንዲቀጥሉ ተደርገዋል።

አቶ ተሰማ እኚህ 17 ባለሞያዎች አሁን የስራ ማቆም አድማ ካደረጉት ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ባለሞያዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ በወረዳው አስተዳደር መወሰኑን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሆስፒታሉን ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ እና የአንጋጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#መምህራን በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል። እስሩ የተፈፀመ ያለድ መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል። ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው " አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል " በሚል መሆኑን…
#Update

🔵 “ መምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን ” - የወላይታ ዞን መምህራን

🔴 “ ከ10,500 በላይ መምህራን ደመወዝ አልተፈጸመላቸውም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን ያልተከፈላቸውን ደመወዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታ ለማስገባት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ “ በፓሊስ መታሰራቸው ” ተሰምቶ ነበር።

የደመወዝ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ የመብት ጥያቄ ለማንሳት ባደረጉት ፒቲሽን የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ነበር ፓሊስ “ አመጽ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል። የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል ” በሚል ያሰራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የታሰሩት መምህራን ተፈቱ ? የደመወዝ ቅሬታችሁስ መፍትሄ አገኘ ? ሲል ዛሬ ቅሬታ ያላቸው መምህራንን ጠይቋል።

ምን መለሱ ?

ምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። ሦስቱም መምህራን ተፈትተዋል። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን። 

‘ መንግስትን ከሕዝብ አጣልታችኋል ’ የሚለው ክስ በፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም መረጃ የላቸውም። ከዚያ ጋር ተያይዞ ነው ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው።

የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።

አሁንም ደመወዝ እንዲከፈለን እንፈልጋለን።

መምህራን ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ሥራ ስለሚሰሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በትክክል እንዲተገብሩ ደመወዝ መከፈል አለበት።

የሐምሌ ደመወዝ እስካሁን አልተከፈለም። ለመምህራንና ለጤና ባለሙያ 40 በመቶ፣ ለፓሊስ 20 በመቶ እንጂ ከዚህ ውጪ ደመወዝ አልተከፈለም።

አሁን እንደገና አጠቃላይ የትምህርት ባለሙያም ወደታች ወርዶ ‘የሐምሌን ደመወዝ እንከፍላለን’ በማለት አመራርም በአጠቃላይ ተረባርቦ መምህራን ወደ ስራ አስገብተዋል።

ፍርድ ቤትም ገና የራሱን ቀጠሮ እየሰጠ ነው የሐምሌ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት
” ብለዋል።

ደመወዛቸው በወቅቱ አለመፈጸሙ ትልቅ ጥፋት ሆኖ እያለ ይህንኑ ቅሬታ መምህራን ታስረው መቆዬታቸው ግፍ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም በዚሁ ቅሬታ ላይ ምን እየሰሩ እንደሆነ የክልሉና የዞኑን መምህራን ማኀበር ጠይቋል።

የክልሉ መምህራን ማኀበር የመምህራንን መታሰር በተመለከተ እስካሁን ሪፓርት እንዳልተደረገለት/ቅሬታ ያደረሰው አካል እንደሌለ ገልጾ፣ በይበልጥ የዞኑ መምህራን ማኀበር እንዲጠየቅ አሳስቧል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የወላይታ ዞን መምህራን ማኀበር ሊቀ መንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ፣ “ በቅርቡ ታስረዋል ስለተባሉት መምህራን ለኛ ኦፊሻሊ የቀረበልን ምንም መረጃ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ያመለከተልን አካል የለም። ከውጪ ወሬ ነው እየሰማን ያለነው። ወደ አክሽን እንዳንገባ የመጣልን መረጃ የለም ” ያሉት ሊቀመንበሯ፣ “ እንነጋገርበት ወደኛ መምጣት ይችላሉ ” ብለዋል።

የደመወዝ ክፍያን ቅሬታ በተመለከተም በሰጡን ምላሽም፣ ከ10 ሺህ 500 በላይ መምህራን ደመመወዝ እንዳልተፈጸመላቸው ገልጸው፣ ማኀበሩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

የክፍያ አለመፈጸምን በተለመከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከዚህ ቀደም የጠየቅናቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎደና፣ “ አራት ወረዳዎች ላይ መሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው ” ብለው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ማብራሪያ ሰጥቷል።

ቢሮው እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከአውድ ውጪ በተተረጎመ መንገድ እንደሆነ ጠቁሟል።

" የ1997 የጋራ መኖርያ ቤት ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው የተሳሳተ መረጃ ትክክል ባልሆነ መልኩ  ከአውድ ውጪ ተተርጉሞ የቀረበ ነው " ብሏል።

ቢሮው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?

" ከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ለማስተላለፍ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2011 መሰረት ክፍል 3 አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 2 መሰረት ብቁ እና ንቁ ማለትም ' የቤት ፈላጊዎች በገቡት ግዴታ መሰረት የቁጠባ መጠን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትክክል ተቀማጭ ማድረጋቸውን ከእጣ በፊት ያረጋግጣል ' ይላል።

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢዎች በወቅቱ በመረጃ ቋት ውስጥ ንቁ እና ብቁ  የነበሩ ተመዝጋቢዎችን ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አስተናግዶ ያጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በወቅቱ ብቁ ያልነበሩትን የ1997 ተመዝጋቢዎች እና ሌሎች የ2005 እጣ ያልደረሳቸው የቤት ፈላጊዎች እየተተገበሩ ባሉ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በወቅቱ ብቁ እና ንቁ  ያልነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች ከየትኛውም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጪ እንደተደረጉ ተደርጎ የተሰራጨው የሀሰት መረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ እና ይህንን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን ከተማ አስተዳደሩ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

ከተማ አስተዳደሩ ተመዝግበው የሚጠባበቁትን ሆነ ሌሎች የከተማችዋን የቤት ፈላጊዎች ቤት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ አዳዲስ የቤት ልማት አማራጮችን በመቀየስ እየተገበረ ይገኛል " ብሏል።


NB. ቢሮው ስለ 1997 ተመዝጋቢዎች የትኛው ሚዲያ ከአውድ ውጭ የተተረጎመ ሀሰተኛ መረጃ እንዳሰራጨ በግልጽ ያለው ነገር የለም ነገር ግን መረጃውን የሚያሰራጩትን በህግ እጠይቃለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministrationBureau

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ከለሊቱ 6:04 ላይ አፋር ክልል፣ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ ተሰምቷል። በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። አርብ ምሽት 3:55 ላይ እንዲሁም ለሊት በዚህ ሰዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር። በአዋሽ የሚገኝ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " አላህ ክፉን ሁሉ…
#Update #Earthquake

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " - ቤተሰቦች በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ የታገቱት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ የሕክምና አገልግሎት በመዘጋቱ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ነቀምት ሄደው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።…
#Update

በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች  ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " ነበር ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ታጋቾቹ እንደተለቀቁ ከቤተረቦቻቸውና ከታጋቾች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል።

ከታጋቾቹ መካከል አንዱ እንደሆኑ የገለጹና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ፤ " ሰው ተደብድቦብን ለሞት ደረሰና ወደ ነቀምት ሆስፒታል ሪፈር አፅፈን ወደ ነቀምት ተጓዝን። እዛ እስከምንደርስ ምንም ችግር አልደረሰብንም ነበር " ብለዋል።

ሕክምናውን ጨርሰው እየተመለሱ  በነበረበት ወቅት ኣጋቾች ከጫካ ወጥተው መታወቂያ ከጠየቁ በኃላ ማገታቸውን ጠቁመዋል።

" የአማራ ተወላጅ ወደዛ መሄድ ስለማይችል ከእኛ ጋር አንድ የኦሮሞ ተወላጅ አብረን ይዘን ሄደን ነበር። እርሱን 'ና ውረድ ለምን ለአማራ ተወላጅ ብለህ አብረህ የሄድህ? ' ብለው ወደጫካ ወስደው በጣም ደበደቡት፤ አሰቃዩት " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

" እኛ ላይ ዛቻ አደረሱብን እንጂ አልደበደቡንም። ከዚያ ገንዘቡ ሲላክ ለቀቁን " ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

ያገታችሁ ማነው በሚን ለቀረበ ጥያቄ  በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ መሆኑን ገልጸዋል።

" ሌሊቱን በጫካ ውስጥ ሲያዞሩን ነው ያደሩት የእግር ጉዞ አለው። እኔ ደግሞ ኦፕራሲዮን ነኝ። ያገተን ታጣቂ ‘ መናኸሪያ ላይ መታወቂያ የጠየቃችሁ ፓሊስ የለም ወይ ? ’ አለኝ። አዎ ጠይቆናል አልኩት። ‘ እርሱ ነው እንደመጣችሁ የነገረኝ አለኝ ’። ሌላ የማውቀው ነገር የለም " ሲሉ መልሰዋል።

እኚሁ ታግተው የነበሩ ግለሰብ፣ " እኛ ተሰቃዬንም፤ ገንዘብ ከፈልንም ተለቀናል። ለወደፊት ግን ማንኛውም ሰው መብቱ ተጠብቆ በማንነቱ የሚደርስበት ጉዳት ይቁምልን " ሲሉ ተማጽነዋል።

ታጋቾች ከእገታ እንዲለቀቁ ከወዳጅ ዘመድ እርዳታ ጠይቀው ለአጋቾቹ ገንዘብ እንደላኩ የገለጹልን አንድ ስማቸው እንዲነሳ ያልፈለጉ የታጋች ቤተሰብ ፥ " ወንድሞቻችን ከነቀምት ከህክምና እየተመለሱ ኪረሙ ወረዳ ለመድረስ 5 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ታግተው ነበር " ብለዋል።

" ምንድን ነው ችግሩ ? ብለን ስንጠይቅ የተፈለገው 300 ሺሕ ብር ላኩ ተባልን፡፡ ብሩን ላክን " ነው ያሉት።

ለአጋቾቹ በምን መልኩ ነው ገንዘቡን የላካችሁት ? ተብሎ ለቀረበላቸው የቲክቫህ ጥያቄ ፥“በአካውንት እንላክላችሁ አልናቸው 'አይቻልም በእጃችን ነው፣ በአንዲት መኪና ሰዎች ይመጣሉ ለእነርሱ ስጡ ያኔ ሰዎቹን እንለቃለን' አሉ፡፡ ከወረዳው የተላከችው መኪና መጣች 300 ሺሕ ብር ላክን፡፡ ሰዎቹ ተለቀቁ። መኪናይቱ ከወረዳ የመጣች ናት " ብለዋል።

አጋቾቹ  ፥ ከታጋቾቹ ጋር አብሮ የሄደውን ግለሰብ ' ለምን አብረህ ሄድክ? በሚል'እንገለዋለን' በሚል ዛቻ አንለቅም ብለው  ሲያስፈራሩ እንዳይገድሉት ተማፅኖ ሲቀርብ '100 ሺሕ ብር ጨምሩ' በማለታቸው ብሩ ተጨምሮ እርሱም ከእገታ መለቀቁን ጠቁመዋል።

በአሙሩ፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋና በሌሎችም " ቦታዎች ሰዎች ታግተው ብር ተጠይቆባቸው ብሩ ከተላከ በኋም በአጋቾች ተገድለዋል። እኛ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ብሩን ከፍለን ተለቀውልናል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ እገታው ከተፈጸመበት ቦታ በቅርብ ርቀት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እንደነበሩ የታጋች ቤተሰብ አስረድተዋል።

ሌላኛው የታጋች ቤተሰብ ደግሞ ፥ " ከዘመድ ወዳጅ አሰባስበን 400 ሺሕ ብር ከፍለን ታጋቾቹ ተለቀዋል፡፡ ሴቶች፣ የሶስት ቀን ሕፃናት ሁሉ ተገድለዋሌ፡፡ ግን እስከ መቼ ድረስ ነው ፍትህ የማይሰጠን? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአካባቢውንና የክልሉን የጸጥታ አካላት ምላሽ ለማካተት ጥረት ቢያደርግም ባለስልጣናቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው " -የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ከክፍያ ጋር በተያያዘ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ዘግተው ስለወጡና ስራ ስላቆሙ ጤና ባለሞያዎች በተመለከተ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል። " እኔ እንደ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ይከፈላቸው ብዬ እየጠየኩ ነው በዕለቱም ይህንን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር…
#Update

" ጥያቄያችን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " - ቅሬታ አቅራቢ የጤና ባለሙያዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መግለጻችን ይታወሳል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ማለትም 12/02/17 እስከ 18/02/17 ድረስ ስራ ሳይገቡ ቆይተው ማክሰኞ በ19/02/2017 ዓ.ም ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር የወረዳው ባለሥልጣናት በተገኙበት በተደረገ ውይይት ሽማግሌዎች ከወረዳው ሃላፊዎች ጋር ለማደራደር በመስማማታቸው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ይሁን እንጂ ከስብሰባው ማብቃት በኋላ " አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 የሚሆኑ ባለሞያዎች ለእስር ተዳርገዋል።

በተለያየ ቀናት ለእስር የተዳረጉት እነዚህ ባለሞያዎች ከ 2 እስከ 6 ቀናት ለሚሆን ጊዜ ታስረው በዋስ ከእስር ተፈተው ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእስር ከተዳረጉት ባለሞያዎች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሯል።

ባለሙያዎቹ  " ጥያቄያችን ፓለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጓል " ብለውናል።

" የጠየቅነው የሰራንበትን ክፍያ ሆኖ ሳለ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ' ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳ አድርጋቹሃል፣ ሰዎችን ወደ ሥራ እንዳይጋቡ አስፈራርታቹሃል ' የሚል ክስ ተነቦልናል " ነው ያሉት።

በተጨማሪም ባለሞያዎች ወደ ሆስፒታል ሲመለሱ ከአሁን በኋላ ተመሳሳይ የሆነ የስራ ማቆም አድማ ውስጥ ቢገቡ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ ተደርጓል ብከዋክ።

ሰራተኞቹ ከተመለሱ በኋላ BPR የተሰኘ በየስምንት ሰዓቱ በሺፍት የሚቀያየሩበት አሰራር እንዲዘረጋ መደረጉን ተናግረዋል።

በአዲሱ አሰራር መሰረት ጠዋት 12 ሰዓት ወደ ስራ የገባ ሰራተኛ 8 ሰዓት ከስራ የሚወጣ ሲሆን 8 ሰዓት የገባው ምሽት 4 ሰዓት ከስራ ይወጣል።

ይሁን እንጂ ይህ አሰራር " ሆስፒታሉ ለሰራተኞች ሰርቪስ የሌለው በመሆኑ እና በምሽት ሺፍት ከስራ ስንወጣ እና ስንገባ ለጅብ እየተጋለጥን ነው " በሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

" ይህ አይነቱ አሰራር የተዘረጋው የወረዳው አስተዳደር ለመቀጣጫ እንዲሆን በሚል ነው " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ " የትርፍ ሰዓት ሥራ ለማስቀረት የተደረገ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከታቸውን የአንጋጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የሆስፒታሉ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን ቅሬታውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ለማናገር ተደጋጋሚ የሆነ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ አቶ ተሰማ አበራ አዲሱ  አሰራር ለአደጋ አጋልጦናል የሚለውን የሆስፒታሉን ባለሞያዎች ቅሬታ አይቀበሉም።

" የትርፍ ሰዓት ስራ ሲሰሩ ያልነበረ ጅብ ዛሬ ከየት መጣ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ አይነቱ አሰራር ያልነበረና አዲስ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ብለዋል።

አክለውም " ይህን ጭቅጭቅ የሚያመጣው ወረዳው የመክፈል አቅም የሌለው በመሆኑ ነው በቀጣይም መጋጨት የለብንም " በማለት አሰራሩ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሞያዎቹ የሰሩበት ገንዘባቸው ሳይከፈላቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል መቼ ክፍያቸው ይፈጸማል ስንል በድጋሚ ላነሳንላቸው ጥያቄም "አሁንም እየተነጋገርን ነው ከወረዳ መንግሥት ጋር የገንዘብ ክፍተት ስላጋጠመ እንጂ መከፈል እንዳለበት ተግባብተናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia