TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ?

ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር።

በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል።

" በእርግጥም ፤ የBRICS አባል መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ፊዳን " ስለዚህ በዚህ አመት እንዴት እንደሚሄድ እናያለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ነገር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ቱርክ የBRICS  አባላት ሀገራትን ትብብር እየተመለከተች ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊትም ወደ ሩስያ አቅንተው ከBRICS አባሏ ሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።

ፑቲን ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቱርክ ስብስቡን ለመቀላቀል (አብሮ ለመስራት) ያሳየችውን ፍላጎት በደስታ ተቀብለው ፤ ወደ ስብስቡ እንድትቀላቀል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የቱርክ መንግሥት BRICS'ን ለመቀላቀል ርምጃ ይወስድ እንደሆነ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በይፋ ስብሰቡን ለመቀላቀል ያለውን ፍላጎት በይፋ አሳውቆ አያውቅም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#BRICS
#Turkey
#China
#Russia

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በአቢሲንያ አሚን አገልግሎት ውስጥ “መሸ” የሚል ቃል አይታወቅም - ፀሐይም አትጠልቅም! በቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን 24 ሰዓት እርስዎን በሐቅ ለማገልገል ዝግጁ ነን!

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia  #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#AddisAbaba

° “ መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን ” - ማኀበራት

° “ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” - የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር


በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት በማኀበር ተደራጅተው ከቱሉዲምቱ እስከ ዓለም ባንክ ድረስ ቤት እየገነቡ የየበሩ ማኀበራት፣ “መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በሰጡት ቃል፣ “እንደ ማኀበር በጋራ ሆነን ጥያቄ አቅርበን እየተከታተልን ነው ከ3 ዓመታት በላይ የቆየነው። ‘ያኔ ለጊዜው ይቁም፣ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣል’ ተብሎ ቆሞ ነበር አሁን ስንሄድ ነው የሚያናግረን ሰው ያጣነው” ብለዋል።

ቦታዎቹ #ከቱሉዲምቱ እስከ #ዓለምባንክ እንደሚገኙ አመልክተው፣ “ አጠቃላይ 960 ማኀበራት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 217ቱን ‘ መስተንግዶ ያግኙ ’ ብለው ለቀውላቸዋል። የቀረነው ግን ‘ ይለቀቃል ’ ተብሎ ለረጅም ጊዜ እየታሸን ነው ” ሲሉ አማረዋል።

➡️ ቤት ለመገንባት ከባንክ ገንዘብ የተበደሩ እንዳሉ፣ 
➡️ የባንክ እዳቸውን ከፍለው ባለመጨረሳቸው መሬታቸው ለጨረታ የቀረበ እንዳሉ፣ 
➡️ ቤታቸውን ለመሸጥ የፈለጉ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

ይህ የሆነው ፣ “ ሕገ ወጥ #የመሬት_ወረራ በመኖሩ ኦዲት ይደረግ ” በሚል ሰበብ እንደሆነ፣ እነርሱ ግን መሬታቸው ሕገ ወጥ እንዳልሆነ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ከተማ አስተዳደሩ ኦዲቱን በፍጥነት አጣርቶና አጠናቆ እግዱን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የቅሬታ አቅራቢዎቹ ሰነድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቱ ውል ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ የተገባ መሆኑን ፣ ከባንክ #በ100_ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደተበደሩ ያስረዳል።

ማኀበራቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ኃላፊዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በከተማ አስተዳደሩ የቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይነህ አመርቆ ቅሬታውን በተመለከተ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጡት ቃል ግን፣ “ግለሰቦች በሌላ ማኀበር የከተማዋን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ እንደነበር ይታወቃል” ብለዋል።

“ ይህንምን መነሻ አድርጎም የተወሰኑ የታገዱ አሉ ፣ Specific የሚታወቁ ማለት ነው ” ብለው ፣ የእኚሁ አካላት ጉዳይ “ትክክለኛ ነው? ትክክል አይደለም ? የሚለው ነገር ተጣርቶ ውሳኔ የሚሰጣቸው ” እንደሆኑ አስረድተዋል።

“ ከዛ ውጪ ግን ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Info

ዋትስአፕ በድምጽ እና በምስል ጥሪ ላይ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል።

የቪዲዮ ጥሪ ተሞክሮን ለማሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ ዋትስአፕ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል።

እነዚህ ማሻሻያዎች ዓላማቸው የዋትስአፕ ቪዲዮ ጥሪን የበለጠ ሁለገብ እና ምቹ ለማድረግ ነው ፣ በተለይ ለትላልቅ ቡድኖች።

ዋትስአፕ አዲስ ይዞ የመጣው አዲስ ነገር ምንድነው ?

▪️የቪድዮ ጥሪ ላይ የሚሳተፍ ሰው ብዛት ጨምሯል።

ዋትስአፕ በሁሉም መሳሪያዎች ማለትም ሞባይል፣ ዊንዶውስ እና ማክ-ኦኤስ ላይ በቪዲዮ ጥሪ ላይ መሳተፍ የሚችሉትን ሰዎች ብዛት ወደ 32 አሳድጎታል። ይህም ትላልቅ የቡድን ስብሰባዎችን ዋትስአፕ ላይ ማድረግን ያስችላል።

▪️ስክሪንን ከድምጽ ጋር ማጋራት እንዲቻል አድርጓል።

ይህ ማሻሻያ በቪዲዮ ጥሪ ጊዜ ስክሪን ላይ የሚታየውን ነገር ከማንኛውም ኦዲዮ ጋር ማጋራትን ያስችላል። ይህ በቀጥታ በዋትስአፕ ውስጥ አብሮ ቪዲዮ ማየትን፣ ወይም አብሮ መስራትን ያስችላል።

▪️ቨዲዮ ጥሪ ላይ ተናጋሪው ሰው ላይ ምልክት ማድረግ እንዲቻል አድርጓል።

በቡድን የቪዲዮ ጥሪ ውስጥ የሚናገረውን ሰው ላይ የተለየ ምልክት መስጠት ጀምሯል። ይህም በቡድን ውስጥ ያሉ ንግግሮችን ለመከታተል ቀላል ያደርገዋል።

የደውል ጥሪን የበለጠ ለማሻሻል በተለይም ደካማ ኔትወርክ ወይም ቆየት ያሉ ስልኮች ላላቸው ተጠቃሚዎች የዋትስአፕ እናት ኩባንያ ሜታ (Meta) የሜታ ሎው ቢትሬት (MLow) አስተዋውቋል።

ይህ ስርአት የተነደፈው ከተገቢው ባነሰ ኔትወርክ ሁኔታ ውስጥ እንኳን የተሻለ ጥራት ለማቅረብ ነው።

#TikvahTechTeam

@tikvahethmagazine
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia            
በፍቅር እና መተሳሰብ በሚከበረው የኢድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል ልዩ ድምቀት የሆኑትን የሞባይል ጥቅሎች እስከ 25% በሚደርስ ቅናሽ ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው!

በቴሌብር ሱፐርአፕ ከ10% ስጦታ ጋር፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም *999# ለራስዎም ይግዙ፤ በበዓል ስጦታ ወዳጅ ዘመድ ይዘይሩ።

ቴሌብር ሱፐርአፕ ለማውረድ http://onelink.to/fpgu4m ይጠቀሙ!

ኢድ ሙባረክ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን /የትምህርት ካላንደር/ ይፋ አደረገ።

የትምህርት ካላንደሩ በከተማው አስተዳደር ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ባለው መልኩ ይተገበራል ተብሏል።

ይፋ በተደረገው በዚህ የትምህርት ሰሌዳ መሰረት ፥ ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ እንደሚከቅናወን ፤ ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚከናወን ተመላክቷል።

በከተማው መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ/ም   መደበኛ ትምህርት እንደሚጀምር የትምህርት ሰሌዳው ያሳያል።

ከጥር 19 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የ2ኛ ወሰነ ትምህርት እንደሚጀምር ተመላክቷል።

የ2017 ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የትምህርት ካላንደሩ (ሰሌዳው) ከሰኔ 9 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይገልጻል።

(ሙሉውን ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Afar #Somali🚨

" የግጭቱ ማገርሸት ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ ገልጿል።

ኮሚሽሙ ግጭቱ እንዳሳሰበውም አመልክቷል።

ኢሰመኮ በቅርቡ በሚያዚያ ወር የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሶማሊ ክልል ሽንሌ ዞን እና አፋር ክልል አዋሳኝ ያገረሸው ግጭት አሳሳቢ ነው ብሏል።

ግጭቱ ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት እንዳሆነ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰኢድ ደመቀ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል ፤ " የአሁኑ ግጭት የተጀመረው ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም 2024 ወዲህ ነው " ብለዋል።

" በግጭቱ የተወሰኑ ሰዎች ሞት፤ መፈናቀል እና የአካል ጉዳት፤ የንብረት መውደም እንደደረሰ ነው ያለው መረጃ በእኛ በኩል ግጭቱ እንዳገረሸ። በትክልል ስንት ሰው ሞተ፤ ቆሰለ የሚለውን ገና በምርመራ የምናጣራው ነው " ብለዋል።

" በአሁኑ ወቅት ግን ጠቅለል ባለ መልኩ የሰው መፈናቀል፤ ሞት እና ጉዳት እንዳለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ከሁለቱ ክልሎች የመንግስት አስተዳዳሪዎች ተረዳሁት ባለው መሠረት ፥ በሁለቱም ክልሎች በኩል የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀሎች ተፈጽሟል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተገኘው አዎንታዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ሁለቱ ክልሎች ያሰጡትን አዎንታዊ ምላሽ ያደነቀው ኢሰመኮ፤ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል የፌዴራልም ሆነ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት የቀጠለውን ግጭት እንዲያስቆሙት ጥሪውን አቅርቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የግጭት ማስቆም ጥረት እንዲያስደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሁለቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በቀጣይ ሕዝበ ሙስሊሙ ከሚያከብረው የኢድ አል-አደሃ በዓል አስቀድሞ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

#DWAmharic #EHRC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BahirDarUniversity ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ ሊያደርግ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በፀጥታ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በ2016 ዓ/ም አዲስ ለተመደቡለት የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ጥሪ ሳያደርግ ቆይቷል። ረቡዕ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት ያደረገው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑን ቲክቫህ…
#BahirDarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሬሜዲየል ተማሪዎች ጥሪ አደረገ።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ለመከታተል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23 ቀን 2016 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በ " ፖሊ ካምፓስ " ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ በ " ግሽ ዓባይ ካምፓስ " ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

Via @tikvahuniversity
Embargoed_Copy_CARD_Voice_of_Guji_Eng_Oro_Amh_HR_Situation_Report.pdf
6.3 MB
#የጉጂ_ሰቆቃ : በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል (ካርድ) ያዘጋጀው ሪፖርት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Embargoed_Copy_CARD_Voice_of_Guji_Eng_Oro_Amh_HR_Situation_Report.pdf
ካርድ "የጉጂ ሰቆቃ / Voice For Guji" በሚል ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ አደረገ።

የመብቶች እና ዲሞክራሲ እድገት ማዕከል / ካርድ በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አስመልክቶ " የጉጂ ሰቆቃ / Voice For Guji " በሚል ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

➡️ በእነዚህ አከባቢዎች እየደረሰ ያለው የህዝብ ሰቆቃ በመገናኛ ብዙኃን ችላ ተብሏል።

➡️ ጉዳት የደረሰበት ሕዝብ ድምጹ እንዳይሰማ ሆኗል።

➡️ በተለይ በ2015 መጀመሪያ ላይ የምስራቅ ቦረና ዞን መመስረትን ተከትሎ የተፈጠሩ የፖለቲካ ችግሮች ውጥረቱን አባብሰወል።

ሪፖርቱ 36 ማሳያ ታሪኮችን አካቷል።

ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም ወገኖች (የመንግሥት እና የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች) ተሳታፊ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

ሪፖርቱ በማሳያ ታሪኮቹ ፦

° ከሕግ ውጪ ንፁኃን ላይ የተፈፀሙ ግድያዎች፣
° የዘፈቀደና የጅምላ እስሮች፣
° ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣
° የንብረት ውድመት፣
° አስገድዶ የመሰወር እና የገንዘብ ማግኛ እገታ ድርጊቶች፣
° የማሰቃየት እና ኢሰብዓዊ አያያዝ የመፈፀም፣
° የማፈናቀል ድርጊት የተፈፀመባቸው ንፁኃን ዜጎችን ታሪኮች ይዟል።

በሪፖርቱ ከተካተቱ ማሳያ ታሪኮች መካከል ...

አንድ ባለታሪክ " መንግሥት የአሮሞ ነጻነት ግንባርን ወደ ኢትዮጵያ ሲጠራ  የኛ ልጆች ብለን ተቀብለናቸዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት 'ሸኔ' እያለ መጥራት ከጀመረ በኋላ ሁኔታው ተባባሰ። በሌሊት የሸኔ ተዋጊዎች ያስተዳድሩናል፣ ቀን ላይ ደግሞ የመንግሥት ኃይሎች ያስተዳድራሉ " ብለዋል።

ሌላዋ ባለታሪክ ፥ " በጉጂ የሚገኙ ማዕድናትም የግጭቱ መንስኤ ናቸው። ከጉጂ ጎሮ ዶላ ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመንግሥት ታጣቂዎች ሽኔ የሚል ስያሜ ስለተሰጣቸው ዕርዳታ ለማግኘት ተቸግረዋል " ስትል ገልጻለች።

ሌላኛው ባላታሪክ " ሁለቱም ወገኖች በጠላትነት የሚፈረጁትን ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይይዛሉ፣ ይህም የአመፅና የመፈናቀል አዙሪቱን እንዲቀጥል አድርጓል" ቃሉን ሰጥቷል።

በሪፖርቱ በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት በስፋት የተዳሰሰ ሲሆን ከ #8_ዓመት ሕጻን አንስቶ ባለትዳር እና የልጆች እናት የሆኑ ሴቶች ከአንድ በላይ በሆኑ ታጣቂዎች ተገደው መደፈራቸውን ማሳያ ታሪኮቹ ያሳያሉ።

ሪፖርቱ ወንድ ወታደሮች በጾታ ላይ የተመሰረተ ወንጀሎች ላይ የሚሳተፉት አከባቢን የመቅጣት ፤ የማዋረድ እና የመቆጣጠር ፍላጎቶች ምክንያትነት መሆናቸውን በምክንያትነት ያስቀመጠ ሲሆን በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም አካላት በኩል የሚፈጸም መሆኑን አንስቷል።

በተጨማሪም፥ በሁለቱም አካላት ሰዎችን በመያዝ ለመልቀቅ ገንዘብ የመጠየቅ ተግባራት ፤ ኢሰብአዊ ድብደባና ዝርፊያ መስተዋላቸውን ተገልጿል።

በግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በአግባቡ አለመታወቁ እና ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በመኖራቸው ነዋሪው መቸገሩ በሪፖርቱ ተነስቷል።

የቀረበው ምክረ-ሐሳብ ምንድነው ?

ገለልተኛ፣ ነጻ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግ፤ ሁለቱም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የጀመሩትን ድርድር እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

ሙሉ ሪፖርት ፦ t.me/tikvahethiopia/88262

@tikvahethiopia