TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባቸው ውሳኔ ተላለፈ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ አንዱ ግንባታዎችን የሚመለከት ነው።

በዚህም የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ወጥተዋል።

ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ፦
ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤
ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤
ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት
በተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ሌለው ውሳኔ የተላለፈበት ጉዳይ የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ላይ ሲሆን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።

ከዚህ በተጨማሪ " የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል " ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ፦
- ለጎዳና ህይወት ፤
- ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ በሁለት ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔ ከተላለፈበት አንዱ ጉዳይ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ነው።

ምክር ቤቱ ፥ " በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል " ብሏል።

" ሆኖም እነዚህ አሰራሮች ፦
- በእውኀት፣
- በዕርቅ፣
- በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም " ሲል ገልጿል።

በመሆኑንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቀረቡን አስረድቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ #በስራ_ላይ_እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
#NewsAlert #Tigray

" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በዚህም ፤ " ፓለቲካዊ አለመግባባት ወደ ማንኛውም የፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር አንፈቅድም " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ " ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ ይታወሳል።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረዳ በዛሬ መግለጫቸው ላይ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችና ብዛታቸውን ባይገልጹም " የህግ የበላይነት ለማስከበር የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ አሳውወዋል።

የዘንድሮ የአሸንዳ በዓል አከባበርና የህወሓት ጉባኤ ከመካሄድ ጋር ተያይዞ  የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ተገቢ እና ጥብቅ የፀጥታ ስራ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል።

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እና እየከረረ መሄዱ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።

ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ደቅኗል የሚሉ አልጠፉም።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ግን ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለበት ፤ ማንኛውም ልዩነት ወደ ፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር የጸጥታ አካሉ እንደማይፈቅድ አስጠንቅቀዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

Photo Credit - TG TV

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert🚨

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል። ... ይህ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል !! " - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)


በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።

በዚህም " በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ  አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው " ብለዋል።

" ህግ እና ስርዓት ከማንኛውም ሰው ፣ ተቋም ፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ  የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ለገሰ (ዶ/ር) ፥ " የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው " ያሉ ሲሆን " ህወሓት ደጋግሞ  እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል " ብለዋል።

" ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር  ደምስሶታል፡፡ " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ድርጊቱ  የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡ " ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) " አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና  የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም  ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል " በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert🚨

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016 አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ምን አለ ?

- መመሪያው የሚመለከታቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች / የጭነት አቅማቸው ከ1 ቶን ወይም 10 ኩንታል በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ነው።

- እነዚህ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ከሰዓት 10:30 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ገደብ ተጥሎባቸዋል።

- በዋና መንገዶች ላይ ማቆም፤ ጭነት ማውረድና መጫን እንዲሁም መንቀሳቀስ በክልከላው የተካተቱ ናቸው።

- አዲሱ መመሪያ ከዚህ በፊት ከነበረው የሰዓት ገደብ ላይ በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታስቦ የወጣ እንደሆነ ተመላክቷል።

- አዲሱ መመሪያ ከመስከረም 2/2017 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናትን አይመለከትም።

የተቀመጡ የቅጣት እርከኖች ምንድናቸው ?

➡️ በተከለከለ ሰዓት በዋና ዋና መንገዶች ላይ የቆሙ የ10ሺ ብር ቅጣት፤

➡️ በተከለከለው የሰዓት ገደብ የተንቀሳቀሰ 20ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት፤

➡️ በቅጣት ሂደቱ በድጋሜ የተቀጣ አሽከርካሪ የቅጣት እርከኑን በእጥፍ የሚቀጣ ይሆናል።

➡️ በተጨማሪ የቅጣት ወረቀት በመያዝ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀስ ትዕዛዝ ባለማክበር ተጨማሪ ቅጣት የሚተላለፍባቸው ይሆናል ተብሏል።

ቅሬታ ያላቸው በጹሑፍ ቅሬታቸውን ለባለሥልጣኑ በማመልከቻ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የባለሥልጣኑ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል።

ይህ መመሪያ ቁጥር 149/2016 ከዚህ ቀደም የነበረውን መመሪያ ቁጥር 38/2013 እንዲሁም ሰርኩላሮች፣ ልማዳዊ አሰራሮች የሚሽር ነው።

ይህ መመሪያ ተግባራዊ የማይደረግባቸው የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው ?

1ኛ. የሀገር መከላከያ፤ የፖሊስ እንዲሁም በጸጥታ አካላት ስም የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች፤

2ኛ. የድንገተኛ አደጋ ተሽከርካሪዎች፤

3ኛ. ነዳጅ የሚያመላልሱ ቦቴዎችን አይመለከትም።

ከዚህ ቀደም ወጥ አተገባበር ባልተስተዋለባቸው የውሃ አመላላሽ ቦቴዎች ላይ አዲሱ መመሪያ እንዴት ይመለከተዋል ? በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳው ጥያቄ ፥ በአዲሱ መመሪያ እንደሌሎች ከባድ ተሽከርካሪዎች እንደሚስተናገዱ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia