TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
EU_Cotonou and Samoa Agreement_merged.pdf
1.8 MB
#CotonouAgreement (እ.ኤ.አ 2000 የተፈረመ)

#SamoaAgreement (እ.ኤ.አ 2023 የተፈረመና የኮቶኑ ስምምነት ተከታይ)

PDF ፋይሉን በመክፈት ሁለቱንም ስምምነት ማንበብ ይችላሉ። የሚፈልጉትን ቃላትም 🔍 Search የሚለውን በመጫን በመፃፍ መፈለግ ይችላሉ።

ከእስከ 179 ገፅ ያለው የ #CotonouAgreement ሲሆን ከዛ በታች ያለው አዲሱ ስምምነት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
EU_Cotonou and Samoa Agreement_merged.pdf
#SamoaAgreement

ከወር በፊት ሀገራችን #ኢትዮጵያን ጨምሮ አጠቃላይ 79 የአፍሪካ እና የካረቢያንና ፓስፊክ ሀገራት / 48 ከአፍሪካ፣ 16 ከካረቢያን፣ 15 ከፓስፊክ / ሳሞአ ላይ አንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የተፈረመው ስምምነት " #የአፍሪካ#የካረቢያን እና #የፓስፊክ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር የሚያደርጉት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር " የሚል ነው።

ስምምነቱ 22 ዓመታትን የዘለቀው " የኮቶኑ ስምምነት " ቀጣይ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህ ስምምነት ግን ብዙ ጥያቄ ተነስቶበታል። 

በቅድሚያ ስምምነቱ ላይ ጥያቄ እና ከፍተኛ ጥርጣሬ የተነሳው #ካረቢያን አካባቢ ነው። 

ስምምነቱ ፤ በካሪቢያን አካባቢ ከባህል እና ከእሴቶች ጋር የማይጣጣሙ ህጎችን በካሪቢያን ህዝብ ላይ ይጭናል በሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው በቅድሚያ የገለፁት ፦
- በትሪንዳድ እና ቶቤጎ የሚገኘው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን 
- የጃማይካ ጥምረት ለጤናማ ማህበረሰብ (JCHS) ናቸው።

በትሪኒዳድ የሚኖሩ አንድ #የሃይማኖት_አባት በሀገር ውስጥ በሚገኝ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቃለ ምልልስ ካደረጉ በኃላ ነው ስምምነቱ ላይ #ህዝባዊ_ትችት የመጣው።

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባት የስምምነት ሰነዱ ' የአውሮፓ ህብረት ' " የእኛ ያልሆነን ርዕዮተ ዓለም " በአስገዳጅነት እንዲጭን የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የጃማይካ ጥምረት ለጤናማ ማህበረሰብ (JCHS) ደግሞ " ተቀባይነት የሌለውን / ውድቅ የተደረገውን አጠቃላይ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ትምህርተ ሥርዓተ ወደ ጃማይካ የመማሪያ ክፍሎች እንደሚመልስ እና የጃማይካውያንን መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ይጎዳል ፤ ከሀገሪቱ ባህልም ያፈነገጠ ነው " በሚል ጠንካራ ተቃውሞ አስምቷል።

እንዚህ አካላት፤ " በማዕቀብ ሰበብ እና ውል በማሰር " ህዝብ የማይቀበለውን #ከባህል_ያፈነገጠ ተግባር ያለማምዳል ፤ ይጭናል በሚለው ነው የተቃወሙት።

በ ' ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲንስ ' ከዚህ ከባለ 400 ገፆች የሳሞአ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ስጋት ተሰቅስቅሶ ነበር። እሱም ስምምነቱ ፦
- ሀገሪቱ በፅንስ ማቋረጥ ፣
- በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ 
- በLGBTQ መብቶች ላይ ሀገሪቱ ህጎቿን ለማሻሻል #ትገደዳለች የሚል ነው።

ይህ ጉዳይ እና ስጋት በካረቢያን አካባቢ ከተነሳ በኃላ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ መናጋገሪያ ሆኖ ወደ አንዳንድ #የአፍሪካ_ሀገራት ተሰራጭቷል።

በተለይ ደግሞ በናይጄሪያ፣ በናሚቢያ፣  በታንዛኒያ ... የመሳሰሉ ሀገራት ውስጥ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስምምነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልጹ ነበር።

ምንም እንኳን በርካታ ሀገራት ስምምነቱን #በሰዓቱ ቢፈርሙም አንዳንድ ሀገራት ግን ሰነዱ ላይ ዘግይተው ነው የፈረሙት።

ለአብነት ሰነዱን ዘግይተው ከፈረሙት ውስጥ በሰነዱ ላይ በቅድሚያ ከዜጎቿ ጥያቄ የተነሳባት #ጃማይካ አንዷ እና ዋነኛዋ ስትሆን እነ ፦
* ቦትስዋና፣
* ናሚቢያ፣
* ሰኔጋል፣
* ታንዛኒያ፣
* ሶማሊያ፣
* ሩዋንዳ ዘግይተው ከፈረሙት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

➡️ ጥያቄ እና ስጋት በተነሳባቸው ሀገራት ምን ምላሽ ተሰጠ ?

➡️ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ጉዳዩ ምን ተባለ ?

➡️ ስምምነቱን በተመለከተ ፤ " ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግብረሰዶም እንታደግ ማህበር " ምን አለ ?

➡️ በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያን መስፋፋት ምን ያህል አስከፊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ አጠቃላይ ያለውን ሁኔታ ዳሷል ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-10

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ‘ልጆቼን ልያቸው’ ብሎ ማታ ሲመጣ ከሁለት አቅጣጫ ተተኮሰበት ሞተ። " - የመተሃራ ነዋሪ ከታህሳስ 19/2016 ዓ/ም ወዲህ ባሉት ቀናት ብቻ በተለያዩ ቦታዎች ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ከአሥር በላይ ተጓዦች መታገታቸውን፣ እንዲሁም ስምንት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን የዓይን እማኞችና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አንድ…
#Update

" እግዚአብሔር አምላክ አትሙቺ ያላት ነብስ ሆናነው እንጂ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበርን " - ከእገታ የተለቀቁ ግለሰብ

ታህሳስ 19 ለቁልቢ ንግስ በዓል ወደ ቁልቢ ደርሰው ሲመለሱ በታጣቂዎች የታገቱ 11 ሰዎች መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም አንድ የተለቀቀ ታጋችን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

አንድ ከእገታው ነፃ የሆነ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ግለሰብ ፤ ወደ ቁልቢ ሲሄዱና ሲመለሱ ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጿል።

ታህሳስ 17 ወደ ቁልቢ ሲሄዱ ከወለንጪቲ ወጣ ባለ ቦታ ዘረፋ የተፈፀመባቸው ሲሆን ሲመለሱ ታህሳስ 19 በታጣቂዎች ጥቃት ተከፍቶባቸዋል።

አስተያየት ሰጪው ፤ " ዋናውን የአዋሽ ፓርክ በር አልፈን ያልታወቁ ታጣቂዎች ተኩስ ከፈቱና የነበርነው 19 ሰዎች ነበር ከ19ኙ 5 ሰዎች ህይወቱ አልፎ እዛው አስክሬናቸው ከመኪናው ጋራ ተቃጠለ። እኛ በህይወት ያለነውን 11 ሰዎች ውረዱ ... ውረዱ ብለው አስወርደውን በማናቃቸው ኃይሎች ታግተን በጣም እሩቅ የሚባል 10 ሰዓት የሚፈጅ እግረ መንገድ ወደማናቅበት ተራራማ አካባቢ ከተቱን " ብለዋል።

አጋቾቹ እገታውን ከፈፀሙ በኃላ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የጠየቁ ቢሆንም ታጋቾች ግን አቅም እንደሌላቸው ነግረዋቸዋል። በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙ ተመላክቷል።

ታጣቂዎቹ ሲጠይቁ የነበረው ገንዘብ ከ100 ሺህ ብር አንስቶ እስከ 250 ሺህ ብር የሚደርስ መሆኑን የገለፁት ከእገታ ነፃ የሆኑት ግለሰብ " እኛ ይህን ገንዘብ ማግኘት አንችልም አቅማችን አይፈቅድም አልናቸው በጨረሻ ተስፋ ሲቆርጡ ገርፈው ለቀቁን " ብለዋል።

" ምሽት 4 ሰዓት ነው የተነሳነው ነግቶ ነው ከወልጪቲ ወጣ ብለን ቤተሰብ ጋር ደውለን በኮንትራት መኪና ወደቤት የሄድነው " ሲሉ አክለዋል።

ታጣቂዎቹ ሲለቋቸው ስለነበረው ሁኔታ ለማንም እንዳይናገሩ እንዳስጠነቀቋቸው የገለፁት እኚሁ ስሜ አይገለፅ ያሉ ግለሰብ  በወቅቱ በጥይት እጇን የተመታች ባለቤቱን ጨምሮ 3 ሴቶች ሳይታገቱ መቅረታቸውን አመልክተዋል።

" እግዚአብሔር አምላክ አትሙቺ ያላት ነብስ ሆናነው እንጂ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበርን። የሚለበስ ነገር የለ፣ የነበርነው በቲሸርት ነው ብርዱ ውርጩ ዝናቡ ከነድብደባው ከፍተኛ ስቃይ ነበር። ከእኛ መሃል አንድ ልጅ ግንድ ላይ አስረው የደበደቡት እጅግ በጣም ተጎድቷል፤ ከአንገቱ እስከ እግሩ ቁስል ብቻ ነው። እሱን ሆስፒታል እንዲሄድ አድርገናል። " ሁኔታውን ገልጸዋል።

አጋቾቹ እነማን ናቸው ? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ " ከ20 በላይ ፤ 25 ወይም 30 ይጠጋሉ። የተወሰኑት ፀጉር አላቸው ፤ የወታደር ልብስ የበከተ አይነት ሬጀር ያደረጉ ነበሩ፤ ግማሾቹ ጭንብል አላቸው። ያስፈራል በጣም። ስለማንነታቸው አይነግሩንም ነበር። ወስደው ሁለት ተራራ መሃከል ባለ ዋሻ ውስጥ አስገቡን ለሽንት ብቻ ነበር የሚወጣው ፤ ግማሹ ኦሮሚኛ፣ ግማሹ አፋርኛ በቃ ድብልቅልቅ ያለ ቋንቋ ነው የሚሰማው ይሄ ነው የሚባል አይደለም። ድብልቅልቅ ያለ ነው። የሚጠራሩትም በኮድ ስም ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ታግተው ከተለቀቁት መካከል የአንዱ ቤተሰብ የሆኑ አባት ሁሉም ታግተው የተለቀቁ የአካል እና ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ ከተማ የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አለ ?

ትላንት እንዲሁም ዛሬ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብዙ ተከታይ ያላቸው ገፆች እና ግለሰቦች ፤ " በአዲስ አበባ የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳለ፣ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተደረገ እንደሆነ፣ 4 ኪሎ አካባቢ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የሚገልፁ መረጃዎች " እያዘዋወሩ ይገኛሉ።

መሰል መረጃዎችን እያሰራጩ የሚገኙት ገፆች እና ግለሰቦች ሶማሊያን እንደግፋለን በሚል የሚንቀሳቀሱ የሶማሊያ አክቲቪስቶች ሲሆኑ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ዜጎችም ሲያጋሯቸው መመልከት ተችሏል።

አንዳንድ የግብፅ ገፆችም እና ግለሰቦችም ተመሳሳይ መልዕክቶችን ሲያሰራጩ የነበረ ሲሆን የእነሱንም መልዕክቶች አንዳንድ የኢትዮጵውያን ዜጎች ሲያጋሯቸው ነበር።

እነዚህ አካላት እያሰራጩ ስላሉት ጉዳይ ምልከታ ያደረግን ሲሆን የተባለው አይነት ነገር አዲስ አበባ ውስጥ ፈፅሞ እንደሌለ ለማረጋገጥ ችለናል።

ዛሬ 4 ኪሎን ጨምሮ መላው አዲስ አበባ ላይ በመዟዟር ምልከታ አድርገናል። ምንም አይነት ያልተለመደ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም ፣ ተኩስ የሚባልም ነገር የለም።

አዲስ አበባ በተመለከተ እየወጡ ያሉት መረጃዎች በጠቅላላ ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጠናል።

መሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ያሉት ሆን ተብለው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ለመጣል እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

በተለይ ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኃላ ሶማሊያን በመደገፍ የተለያዩ ብዙ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች እና ገፆች ኢትዮጵያን በተመለከተ የተፈበረኩ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሆነ ለማታዘብ ተችሏል።

ከዚህ ባለፈ በሶማሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲደርስ የሚቀሰቅሱ ፅሁፎችን ሲያጋሩ ታይተዋል።

እነዚህ የውጭ ሀገር ሰዎችና በርካታ ተከታይ ያላቸው ገፆች የሚያሰራጯቸውን መልዕክቶች የሚያጋሩ የሀገራችን ሰዎችም ስለመኖራቸው መረዳት ተችሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቅኝት

" ኢትዮጵያውያን ከሶሚሊያ ይውጡልን " እስከ " ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት ይነጠቅ " ዘመቻ !

ከሰሞኑን #የሶማሊያ እና #የግብፅ አክቲቪስቶች እንዲሁም " ሶማሊያን ነው የምንደግፈው " የሚሉ የኢትዮጵያ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ዘመቻ ከፍተዋል።

ጉዳዩ ኢትዮጵያ የባህር በር ለመጠቀም እድል ይሰጣታል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ካደረገችው የመግባቢያ ስምምነት በኃላ የመጣ ነው።

ከስምምነቱ ማግስት ጀምሮ የሶማሊያ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ መግለጫ የማውጣት፣ አጉል ዛቻ የማድረግ ፣ ኢትዮጵያውያን እንደ * ወራሪ * እንዲታዩ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።

የሀገሪቱ ብሄራዊ የመንግሥት የዜና አውታሮች እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣  አክቲቪስቶች እንዲሁም የግብፅ ሰዎች #የተናበበ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን ጫና ውስጥ ይከትልናል ያሉትን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።

ቀላል የማይባል የተከታይ ቁጥር ያላቸው ገፆች #ነጭ_ውሸት ከማሰራጨት ባለፈ ኢትዮጵያውን እንዲጠቁ የማድረግ ዘመቻ እያደረጉ ነው።

ለአብነት ፤ " አዲስ አበባ ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት እየተደረገ ነው ፣ መዲናዋ በተኩስ እየተናጠች ነው ፣ የሀገሪቱ መንግሥት  ለሁለት ተከፋፍሏል ፣ እርስ በእርሱ እየተዋጋ ነው፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መልኩ ተዳክማለች " የሚሉ ነጭ ውሸቶችና እና ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ።

እንዲሁም " ኢትዮጵያውያን ሶማሊያ ውስጥ ምን ይሰራሉ ? ፣ ጠራርገን እናስወጣቸው፣ ወደ ሀገራቸው እንሸኛቸው ፣ ወራሪ ናቸው " የሚሉ ለጥቃት የማመቻቸትና የጥላቻ ቅስቀሳዎችን ከዚህ አለፍ ሲልም የግድያ ዛቻዎችን እስከማስተላለፍ ደርሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንድትፈጥር ላደረጉት ስራ የተሰጣቸው ዓለም አቀፉ " የኖቤል የሰላም ሽልማት " እንዲነጠቁ የሶማሊያ ሰዎች ዘመቻ ማድረግ ጀምረዋል።

ዘመቻው በብሄራዊ የሶማሊያ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና ብሄራዊ ዜና አገልግሎት ጭምር ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት ሰዎች እንዲፈርሙት እየተደረገ ይገኛል።

ይህንን ዘመቻም የግብፅ አክቲቪስቶችም አብረው እያሟሟቁት ይገኛሉ።

NB. የኖቤል የሰላም ሽልማት አንዴ ከተሰጠ እንደማይሻር / እንደማይነጠቅ ይታወቃል፤ በስቶክሆልምና በኦስሎ ያሉት የሽልማት ሰጪ ኮሚቴዎች አንድም ጊዜ ሽልማትን ለመሻር/ ለመንጠቅ አስበው አያውቁም።

በአጠቃላይ የሶማሊያ ሰዎች " የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቤል ሽልማት ይነጠቅ " ከማለት አንስቶ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት እንዲከፈት ፣ በአዲስ አበባ እና ክልል ያለው ህዝብ እንዲሸበር በማህበራዊ ሚዲያ እየሰሩ ያሉትን ዘመቻ የግብፅ ሰዎችም ሲደግፏቸው ታይቷል።

በዚህ የሶማሊያ እና የግብፅ ሰዎች የጋራ የሚመስል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #የሀገራችን_ዜጎችም ሲሳተፉ መመልከት ተችሏል።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ፤ ኢትዮጵያ ማንንም ባልወረረችበት ፣ የሰው ሀገር ባላጠቃችበትና ፍትሃዊ ጥያቄ በመጠየቋ ብቻ የሀገራችን ዜጎች ሆነው ከሶማሊያ እና ግብፅ ጋር በማበር የሚያደርጉት ድርጊት እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

" የኖቤል ሽልማት ማሻር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣን ማስወረድ ፣ የሀገሪቱን መንግሥት መቀየር ይህ ሁሉ #ኢትዮጵያውያንን ብቻ የሚመለክት ነው " ያሉ ሲሆን " በሀገር ውስጥ የቱንም ያህል ተቃውሞ፣ ቅሬታ ቢኖረን እንዴት ከሌላ ሀገር ሰዎች ጋር ለዛውም ለኢትዮጵያ መልካም ከማያስቡ ሰዎች ጋር እናብራለን ? ይህ ተገቢ አይደለም መታረም አለበት ፤ ማንኛውም የውስጥ ጉዳዮች በውሥጥ ማለቅ አለባቸው " ብለዋል።

#ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዞናችን ሰላም ነው ! ...ሰብዓዊ መብት የሚባለው መቼ መጥቶ አጣራ ? " - የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የኢሰመኮን መግለጫ በተመለከ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አባይነህ አበራ " ኢሰመኮ ያወጣው ሪፖርት መሰረት የሌለውና በመረጃ ያልተደገፈ " ሲሉ አጣጥለዋል። " እንደዛ አይነት ነገር (ኢሰመኮ በመግለጫው ያነሳቸው ጉዳዮች) ጋሞ ዞን ውስጥ…
#Update

" በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዳግም ግጭት ተቀስቅሶ የሰዉ ህይዎት ጠፋ የሚለዉ ዜና " የጸረሰላም ኃሎች በሬ ወለደ ዜና ነዉ አለ የአካባቢዉ ፖሊስ ጽ/ቤት።

በወረዳዉ ለአመታት የቆዬ ግጭት መኖሩ ቢታወቅም አስፈላጊዉ መፍትሔ አለመሰጠቱን ተከትሎ አሁንም የጸጥታ መደፍረስ የሚታይበት የአርባምንጭዙሪያ  ወረዳ ዛሬም መረጋጋት አለመቻሉ እየተገለጸ ነዉ።

ከሰሞኑ በአካባቢው ማህበረሰብና የመንግስት አካላት መካከል ዉይይት እየተደረገ ባለበት ወቅት ዳግም ብዙዎችን ለችግር የዳረገ ግጭት መቀስቀሱን የሚገልጽ መረጃ ቲኪቫህ ኢትዮጵያ  ደርሶት ነበር።

በጉዳዩ ላይ አስተያዬታቸዉን የጠየቅናቸዉ የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል በሰጡት ምላሽ አካባቢዉ በጸጥታ አካላት ላይ ታህሳስ አስራ ዘጠኝ ከደረሰዉ ጥቃት በኋላ አካባቢዉ ላይ ችግር አለመከሰቱን ገልጸዉ በወቅቱም ወደአካባቢዉ ሲያቀና በነበረዉ የጸጥታ ሀይል ላይ የተሰነዘረው ጥቃት መክሸፉን ገለጸዋል።

አሁን ላይ የአካባቢውን ሰላም ለመመለስ ከመንግሥት አመራሮች በተጨማሪ የኢዜማን አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችን ያቀፈ ዉይይት ተደርጎ ጫካ የወጣው ሀይል የሚመለስበት መንገድ እየተመቻቸ ቢሆንም ሰላሙን የማይፈለጉ አካላት በበሬ ወለደ ዜና ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኮማንደሩ አክለዉም በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ የሀሰት ወሬ የሚያሰራጩ አካላት ከዚህ ድርጊታቸዉ   እንዲቆጠቡና  አሁን ላይ በአካባቢዉ ያለዉን ሰላም ለመመልከት ቢመጡ እዉነታዉን ለማሳየት ዝግጁ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

ዘገባውን የላከዉ የሀዋሳ ቲኪቫህ ኢትዮጵያ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች በመቐለ ከተማ እንዲዘጉ እየተደረገ ነው። በመቐለ የቤቲንግ ቤቶች ከቅዳሜ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግተዋል። ጨዋታው የፀጥታ አካላት በከተማዋ ሁሉም አከባቢዎች እየዞሩ ነው እንዲዘጋ ያዘዙት። የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በቤቲንግ መጫወቻ ቤቶች ስለተወሰደው የመዝጋት እርምጃ ምክንያት የተጣራ መረጃ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው…
#ትግራይ

" በመቐለ የተወሰደው የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች የመዝጋት እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል "  -ፓሊስ 

" እርምጃው ከመቐለ ውጪ ባሉ ከተሞች ተግባራዊ አልሆነም " - የህዝብና የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምልከታ

የመቐለ ፓሊስ ፅህፈት ቤት እንደገለፀው ፤ በከተማው ከታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ የተወሰደው የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች የመዝጋት እርምጃ በማጠናከር 420 የቤቲንግ ፣ የጌም ዞንና የቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች ዘግቷል። 

እርምጃው በሰባቱ የከተማ ክፍለ ከተሞች መፈፀሙ የገለፀው ፓሊስ ፤ " የወንጀል መነሻና መፈልፈያ ናቸው "  ባላቸው የጫትና የሺሻ ቤቶች በመዝጋት ቀጣይ የሆነ ህግ የማስከበር ስራ እንደሚሰራ አስታውቋል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በአካልና በስልክ ደውሎ እንዳረጋጠው በማይጨው ፣ በውቕሮ ፣ በዓዲግራትና ሌሎች የክልሉ ከተሞች አሁንም የቤቲንግ ፣ የጌም ዞንና የቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች ክፍት ናቸው።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                    
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
ሶማሊያ እና ኤርትራ ምን መከሩ ? የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል። ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በማብራሪያቸውም ፤ " ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት " ብለዋል። ወደ ኤርትራ የሄዱት ፦ - ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ…
ፎቶ፦ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚይ ሽኩሪ ዛሬ ኤርትራ አስመራ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ተቀብለዋቸዋል።

በኃላም ሚኒስትሮቹ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሀን የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ምክክር አድርገዋል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የሱዳን ጉዳይ ፣ የቀይ ባህር ደህንነት እና በጋዛ ሰርጥ ስላለው ጦርነት ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ከቀናት በፊት የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ በማቅናት ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
🤩የአፍሪካን ምርጦችን በላቀ ጥራት ለማየት ዝግጁ ናችሁ?🏆

🔥ከጥር 4 - የካቲት 3 2016 ድረስ  የሚካሄደው  34ተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሁሉንም 52 ጨዋታዎች በላቀ ጥራት በቀጥታ በዲኤስቲቪ  ሱፐርስፖርት ቻናሎች በቀጥታ በሁሉም ፓኬጆች ይመልከቱ!

👉አንድም ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ፈጥነው የዲኤስቲቪ ዲኮደር ይግዙ!

👉የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

#AFCONonDStv #AFCON2023#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#CBE

እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!

• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***********

የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://t.me/combankethofficial