#Election2012
ሲዳማ በክልልነት ለምን አልተካተተም ?
በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የምርጫ ክልልን ይፋ ማድረጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ለምን 'ሲዳማ በክልልነት' እንዳልተካተተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረሱ አቶ በቀለ ገርባ ጠይቀው ነበር።
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦
"የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ ስራውን ጨርሷል። የስልጣን ርክክቡ ተፈጽሞ ፤ ሲዳማ ክልል መሆኑ formalize ካልተደረገ ፤ ለፓርላማ መቀመጫ ቆጥረን ማቅረብ አይጠበቅብንም። ብናደርግም ስህተት ነው"
#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በኮቪድ19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግስት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አቀረበ።
“ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
ኢትዮጵያ በህገ መንግስቱ መሰረት እስከ ነሃሴ ወር ማለቂያ ድረስ አጠቃላይ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ቢኖርባትም የኮቪድ19 ወረርሽኝ ምርጫን ማከናወን የማያስችል ደረጃ ላይ በማድረሱ ምክንያት ህግና እውነታውን አጣጥሞ መሄድ አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምክትል አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንዳሉት ችግሩን ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በማያፋልስ መልኩ ለመቅረፍ አራት የመፍትሄ አማራጮች ተቀምጠዋል።
1. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን
2. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ
3. ህገ መንግስት ማሻሻል
4. የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ ናቸው ብለዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ