TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
#SafaricomEthiopia

በSMS ጨዋታችን ስልክ መሸለማችንን ቀጥለናል! 🎊 ሌሎችም  ከ2ሺህ በላይ አሸናፊዎች በየቀኑ በሽ በሽ እያሉ ነው!

አሁንም በSMS ጨዋታ ፈታ💬🎊 እያልን በየቀኑ እንሸለም! 🎁 ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'START’ ብለን ወደ 34000 ወይም *799# በመላክ እንወዳደር! እናሸንፍ! በአንድ መልስ 1ብር ብቻ!

በሽልማት በሽ በሽ እያልን ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት ⚡️ 🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.
mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የነዋሪዎችድምጽ • “ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚተገበረው ግን መቼ ነው ? ” - የቡለን ወረዳ ነዋሪዎች • “ ‘ለምን አልመርጣችሁኝም ’ በማለት በበቀል ህዝብን መጉዳት ተገቢ አይደለም ” - ዶ/ር መብራቱ አለሙ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ‘ ለምን ፓርቲውን መረጣችሁ ’ በሚል ሰበብ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ፓርቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ…
" ከምርጫ ወዲህ ከፍተኛ ጫና እየደረሰብን ነው " - ቦሮ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ድርጅት ሰኔ 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በክልል ምርጫ ከተካሄደ ወዲህ በፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጫና እንደደሰበት እንደሚገኝ አሳውቋል።

ፓርቲው ምን አለ ?

- መተከል ዞን 3 ለክልል ምክርቤት እና አንድ የህዝብ ተወካዩች ምክርት ቤት ወንበር ማግኘት ችለናል።

- በቡሌን ወረዳ " ተቃዋሚ ፓርቲ መርጣቹሀል " ተብሎ የፓርቲው ደጋፊዎች ፣ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች ላይ ዛቻ እና ማስራርያ እየደረሰ ይገኛል። የፓርቲ አባላትም ለእስር እየተዳረጉ ይገኛሉ።

- የተቀናጀ ወከባና ዛቻ ነው የሚደርሰው። በተለይ ከምርጫው ውጤት በኃላ።

- ቡሌን ወረዳ ላይ አባላት በተለያዩ ወቅቶች ይታሰራሉ። ከልዩ ልዩ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተሳትፎ ተከልክለዋል። በንግድ፣በግብርና እንዲሁም በመንግስት ስራ ላይ የተሰማሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ላይ " ተፎካካሪ ፓርቲ ደግፋቹሀል፣ መርጣቹሀል " በሚል ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርሳል።

- የፓርቲውን አባላት መብት በመንፈግ የፖለቲካ አመለካትን መሰረት ያደረገ ጫናዎች እየደረሱ ነው።

- በፓርቲው ላይ የደረሱ የመብት ጥሰቶችን የሰብአዊ መብት ተቋማት ሊከታተሉት ይገባል።

የቡሌን ወረዳ ፖሊስ ለቀረበው ክስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

የፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ብርሀኑ ኤጄታ ፦

" በወረዳው በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ ሆነ በደል የደረሰበት ግሰለብም ሆነ ቡድን የለም።

በአካባቢው የፖለቲካ ድርጅቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ በምርጫ ተሳትፈዋል።

ፓርቲው ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የሌለው ክስ ነው። " #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProfessorBeyenePetros " ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል " - ሀድያ ዞን የጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል። የፕሮፌሰሩ አስክሬን በህክምና ሲረዱ ከቆዩበት ኬንያ ናይሮቢ ትላንት ምሽት ነው አዲስ አበባ የገባው። የቀብር ስርዓቱን ለማስፈጸም የተቋቋመ አብይ ኮሚቴ ሊኢብኮ…
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ መስከረም 9 ይፈፀማል።

ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት  ሳሪስ አደይ አበባ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ አሸኛኘት ይደረጋል።

ከአራት ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ የተለያዩ ስነስርዓቶች ይካሄዳሉ።

የቀብር ስርዓታቸው ከቀኑ 8 ሰዓት በአዲስ አበባ ብርሐናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ይፈጸማል።

መረጃው የሀድያ ቴሌቪዥን ነው።

(መስከረም 8/2017 ዓ/ም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° “ ልጆቻችን ችግር ላይ ናቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሕይወታቸው ይድረስልን ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያን ቤተሰቦች

° “ የእኛ ኤምባሲ ከዛ አገር መንግስት ጋር እየተነጋገረ ልጆች የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተሞከረ ነው ” - የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ (ባለሥልጣን)

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፦
➡️ ከአገር ሲወጡ በተዋዋሉት መሠረት ሳይሆን በተቃራኒው ህገወጥ የማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ እንደተገደዱ፣
➡️ በአግባቡ ደመወዝ እንደማይከፈላቸው፣
➡️ ይባስ ብሎ ድብደባ እየተፈጸመባቸው አካላቸው እስከመጉደል እንደደረሱ በቤተሰቦቻቸው ጭምር በቲክቫህ ኢትዮጵካ በኩል መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ስለጉዳዩ ምላሽ የጠየቅናቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ “ መረጃው ትክክል ነው፡፡ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው ተቋሙም ኃላፊነት ወስዶ ለወገኖቻችን ለመድረስ ጥረት እያደረገ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተውን ነበር፡፡

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሁንስ ቤተሰቦች ምን አሉ ?

“ ልጆቻችን ችግር ላይ ናቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሕይወታቸው ይድረስልን፡፡ ትንሽ ክፍተት አግኝተው ደውለው ሲነግሩን የከፋ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ነው የሚያስረዱን፡፡ ተጨነቅን እኮ!

በእርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ግን ልጆቻችን በዬቀኑ ድብደባና እንግልቱ እየከበደባቸው ነውና መንግስት በቻለው መጠን ተነጋግሮ ወደ አገራቸው እንዲገቡ እንድያደርግልን እንማጸናለን፡፡

መንግስትንም ለማጣደፍ የተገደድነው የወላጅ አንጀት አልችል ቢለን ነው፡፡ ልጆች በባዕድ አገር በእንዲህ አይነት የከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ማየት ሀዘኑ መራራ እንደሆነ የወለደ ሁሉ ያውቀዋል ” ብለዋል።

በችግር ላሉት ኢትዮጵያዊያን ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉና ጉዳዩን ከጅምሩ ጀምሮ የሚያውቁት ባለሥልጣን በበኩላቸው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

“ ኢትዮጵያ እንደ አገር እዛ አካባቢ ካሉ አገራት ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት የላትም፡፡ ስለዚህ ልጆቹ በግላቸው ነው የሄዱት፡፡ ማንኛውም ሰው ለሥራ የመንቀሳቀስ መብት አለው፡፡ ከዛ አኳያ ሂደዋል፡፡

ነገር ግን ዜጎች ችግር ላይ ሲወድቁ መንግስት ዝም ብሎ ስለማይመለከት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን ከሰማ ጀምሮ እየሰራ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ የሚሄዱት በታይላንድ በኩል ነው፡፡ ጉዳዩን የሚከታተሉት ህንድና ጃፓን ያሉት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም ታይላንድ ላይ ታግተው የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን ማስመለስ ተችሏል፡፡ እኛም የሥራ ስምሪት ወደ እዛ አገር ስለሌለ ዜጎች ወደዛ ባይሄዱ ይመረጣል የሚል መልዕክት ሰጥተናል፡፡

መሄዳቸው ልክ አይደለም ብቻ ሳይሆን ኃላፊነትም መውሰድ መቻል አለባቸው፡፡ ችግር ሲያጋጥም ብቻ መንግስት ላይ መጮህ ተገቢ አይደለም፡፡

ግን እዛ አካባቢ ተቸግረው የነበሩ ልጆችን መንግስት አስመልሷል፡፡ ነገር ግን ወደ ማይናማር የተሻገሩ አሉ፡፡ ወደ ማይናማር የተሻገሩት የሄዱበት ቦታ አስቸጋሪና ታጣቂዎች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ የእኛ ኤምባሲ ከዛ አገር መንግስት ጋር እየተነጋገረ ልጆች የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተሞከረ ነው። ” ብለዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ከሰጡን ማብራሪያ በተጨማሪ፣ “ በተለይ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ ወደ ደቡብ አፍሪካ መስመር ነበር የተለመዱት፡፡ አሁን ደግሞ ባልተለመደ ሁኔታ በጣም አዲስ ነገር ነው ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ ሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር በተለይ በደላሎች አማካኝነት ለአደጋ የሚያጋልጥ እንደሆነ ማንኛውም ዜጋ በተለይ ወደ ውጭ አገር ሲንቀሳቀሱ መጠየቅ፣ ማጣራት ያስፈልጋል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሆነው ሆኖ ግን ውጪ ጉዳይ ኢትዮጵያዊያኑ ካሉበት ችግር እንዲወጡ እየሰራ መሆኑን አመላክቷል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia 📣 ሰምተዋል ℹ️

ለእረፍት ቀንዎ ልዩ ነገር ይዘን መጥተናል 🥁🔥

የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 11 እና እሁድ መስከረም 12 ቀን የሚደረጉትን አስሩንም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዋች ፥ ማን ሲቲ ከ አርሰናል ጨምሮ ሌሎች አጓጊ ጨዋታዎችን በጎጆ ፓኬጆች ከ350 ብር ብቻ በቀጥታ መመልከት ይችላሉ።

ይህ ልዩ አጋጣሚ አያምልጥዎ! ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#ኢትዮ130

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲሱ አመት በነበረው የደንበኞች ጨዋታ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞቹን መሸለሙን ይህም በእጅጉ አዳዲስ ደንበኞችን ለማግኘት ያገዘው እንደሆነ ገልጿል።

ኩባንያው ከተመሰረተ 130 ዓመታትን ማስቆጠሩን አስመልክቶ በተያዘው ዓመት ለስድስት ወር የሚቆይ "ኢትዮ 130" የተሰኘ ጨዋታ በተመሳሳይ ለደንበኞቹ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።

ኩባንያው በስራቴጂው የመጨረሻ ዓመት ሊያከናውናቸው ባቀዳቸው ተግባሮች ዙሪያ በዛሬው ዕለት ተቋሙ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም፥ በ2016 በጀት ዓመት የተገኘውን 93 ቢሊየን ብር ገቢ በ74.7% በማሳደግ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት መጠንንም ወደ 282.85 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማሳደግ አቅዷል።

በተጨማሪም፦

- የደንበኞችን ብዛትንም በ6% በመጨመር 83 ሚሊዮን ለማድረስ፤

- የሞባይል ደንበኞችን በ5.5% በመጨመር 79.7 ሚሊዮን ለማድረስ፤

- የሞባይል ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በ16% በመጨመር 47.4 ሚሊዮን ለማድረስ፤

- የፊክስድ ብሮድባንድ ደንበኞችን በ25% በመጨመር 934 ሺህ በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርጸት መጠንን 73% ለማድረስ ታቅዷል፡፡ 

- 1,298 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎችን ለመገንባት፤ 500 ተጨማሪ ከተሞችን የ4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግና 15 ተጨማሪ ከተሞችን የ5ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱንም ነው የገለጸው።

ኢትዮ ቴሌኮም “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት ማስተዋወቁ ይታወሳል። አዲሱ የ2017 በጀት አመት የስትራቴጂ ዘመኑ ሶስተኛው አመቱ ይሆናል።

ተጨማሪ ያንብቡ https://telegra.ph/Ethio130-09-19

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ መስከረም 9 ይፈፀማል። ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት  ሳሪስ አደይ አበባ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ አሸኛኘት ይደረጋል። ከአራት ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ የተለያዩ ስነስርዓቶች ይካሄዳሉ። የቀብር ስርዓታቸው ከቀኑ 8 ሰዓት በአዲስ አበባ ብርሐናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ይፈጸማል። መረጃው የሀድያ ቴሌቪዥን ነው።…
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

የጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ የአስክሬን ሽኝት በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።

በሽኝት ስነ-ሥርዓቱ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ተገኝተው ነበር።

በተጨማሪ በሆሣዕና የሀዲያ ዞንና የአከባቢው ህዝብ በፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን በኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት ሲገልጽ ውሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ማባረሩና ከነበራቸው ድርጅታዊ ሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ። ድርጅቱ መስከረም 6/2017 ዓ.ም አካሄድኩት ያለውን ስብሰባ አስመልክቶ ባወጣው ባለ ሦስት ገፅ መግለጫ :-  1. አቶ ጌታቸው ረዳ  2. አቶ በየነ…
#Tigray

" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አቅዷል " - በህወሓት ጉባኤ ያልተሳተፉት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት

በህወሓት ጉባኤ ላይ ያልተሳፉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም " ህገመንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን ሌላውን የማባረር ሞራልና ስልጣን የለውም " ብለዋል።

ከሰሞኑን በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማባረሩ ይታወሳል።

የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ " ህገ-መንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ሌላውን የማባረር ህጋዊና ሞራላዊ ስልጣን የለውም " ከማለት ባለፈ " መፈንቀለ መንግስት ለማካሄድ ማቀዱን ደርሰንበታል " ብለዋል።

" የህገወጡ ቡድን መሪ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጄኖሳይድ ፍትህ እንዲያገኝና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ መታገል ሲገባው ጉዳቱ ወደ ቁጥር ጨዋታ በማውረድ የህዝብ መስዋእትና የወጣቶች ጉዳት ዋጋ እያሳጣው ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል " ኒው ሆራይዘን " ከተሰኘ የማህበራዊ ሚድያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ወቅትም " By the way ከአንድ ሚልየን በላይ አለቀ የሚለው ፤ ማስረጃ የለው፣ ጥናት የለው ፣ ለማስፈራርያ ነው የሚውለው። ተጨፍጭፈናል ለማለትም አይደለም ፣ ጄኖሳይድ ተፈፀመብን ለማለትም አይደለም። አመራሩ አስጨረሰን ይላል ፤ አመራር ለመምታት ፣ ስልጣን ለመያዝ የማይሰራ ነገር የለም። " ሲሉ ተናግረው ነበር።

በኃላም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ " በህዝባችን ላይ የተፈፀመው ጄኖሳይድ አሁንም በርካታ በወራሪዎች ስር ያሉ የትግራይ አከባቢዎች ነፃ ባለመውጣታቸው ምክንያት የተሟለ መረጃ መስጠት ባይቻልም የደረሰው እልቂት ግን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ መሆን እንደሚችል ለመግለፅ እፈልጋሎህ " የሚል ማስተባበያ ለመስጠት ሞክረዋል።

የአቶ ጌታቸው ቡድን ህገ-ወጥ ሲል የሚጠራውን የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድንን " ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ሸምጥጦ በመካድ የዓለም ማህበረሰብ የተከራከረለትና የመሰከረውና የህዝብ እልቂት ወደ ጎን በመተው ዋጋ የሌለው እንዲሆን ወሰኖ ጥላሸት በመቀባት ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።

" ህገወጥ ቡድኑ ቡድናዊ የስልጣን ፍላጎቱ በፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ፣ በማሰፈራራትና ሃሳቦች በማፈን ለመጫንና ለማሳካት ላይ ታች በማለት ይገኛል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ይባስ ብሎ የመንግስት መዋቅር አንዲፈርስና ትግራይ መንግስት አልባ ሆና የረብሻና ግርግር ማእከል እንድትሆን እየሰራ ነው " ሲል አሳውቋል።

" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ማቀዱ ግልፅ ሆኗል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ጊዚያዊ አስተዳደሩና ህዝቡ ከአደገኛ አካሄዱ ሊያስቆሙት ይገባል " በማለት አክለዋል።

50 ዓመት ያስቆጠረ ድርጅት እንደ አዲስ እንዲመዘገብ በማድረግ የትግራይ ህዝብ ትግል የካደው ቡድን ህዝቡና የዳያስፓራ አባላት እንዲታገሉት ጥሪ አቅርቦ የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ለማስመለስ ፓለቲካዊ ውይይት መጀመሩን አመልክቷል።

መላው ህዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርቧል።

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያልተሳተፉና ሂደቱን የተቋወሙት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነታቸው አባርሪያለሁ " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#Amhara

" ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ነው እቅድ የተያዘው ከነሐሴ 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ግን 1.7 ሚሊዮን ናቸው - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ልውውጥ የሚስተዋልበት አማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዘገብ እንዳቀደ፣ ከነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ግን 1.7 ሚሊዮን ተማሪዎች መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ " ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 292 ሺሕ በላይ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1.2 ሚሊዮን በላይ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 180 ሺሕ ተማሪዎች ተመዝግበዋል " ብሏል፡፡

" በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባው እየተካሄደ ነው፡፡ ትንሽ እሱ ላይ መዘግየት ይታያል፡፡ እስካሁን በጠቅላላ ወደ 1.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው የተመዘገቡት የእቅዱን ወደ 24 ፐርሰንት አካባቢ " ነው ያለው፡፡

በጸጥታው ችግር ባለፈው ዓመት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ይታወቃል፡፡  በ2017 የትምህርት ዘመንስ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች እጣ ፈንታቸው ምንድን ነው ? እውነት ተመዝግበውስ ለመማር አስቻይ ሁኔታ አላቸው ወይ ? ከዚህ አኳያ ቢሮው ምን አቅዷል ? ምንስ እየሰራ ነው? ስንል ቢሮውን ጠይቀናል፡፡

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን " በክልሉ ከ10 ሺሕ 874 በላይ ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ በአዲሱ የትምህርት ዘመን የእኛ ፍላጎት እነዚህ ሁሉም ትምህርት ቤቶች 7 ሚሊዮን ተማሪዎች እንዲያስተምሩ፣ መማር ማስተማሩ እንዲጀምር/እንዲቀጥል ነው " ብለዋል፡፡

" በተለይ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የጸጥታ ችግር ስላለ የትምህርት ሥራን ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ሁሉ የምዝገባ ሥራን ለመስራት እንቅፋቶች ቢኖሩም ምዝገባ ተጀምሯል፡፡ የምዝገባ አፈጸጻሙ በምንጠብቀው ልክ ባይሆንም ምዝገባ እየተካሄደ ነው " ሲሉ አቶ ጌታው ተናግረዋል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ እዳይደነቃቀፍ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉትን ጨምሮ ሁሉም ሰው ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ቢሮው አስምሮበታል።

" አንድንድ ቦታ ላይ ትላንት ትምህርት ሲጅሩ ልንማር ይገባል የሚል ሞቶ ሁሉ ይዘው የወጡ ተማሪዎች አሉ፡፡ ይሄ በጣም ልብ ይብራል ሰው ሆኖ ለተፈጠረ ሁሉ፡፡ ምሁራን፣ የኃይማኖት አባቶች፣ በዛኛው ወገን ያሉ ወንድሞቻችንም ጭምር ይህን ተረድተው ትምህርትን ነጻ ሆነን እንድንስራ በጎ ሚናቸውን መጫወት አለባቸው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" በ2016 ዓ/ም በተለያየ ምክንያት ትምህርት ተቋርጦባቸው የቆዩ አካባቢዎች፤ ሳይማሩ የቆዩ ተማሪዎች፤ ተዘግተው የቆዩ ትምህርት ቤቶች አሉ " ሲልም ቢሮው ገልጿል፡፡

ከውድመት ጋር በተያያዘም አቶ ጌታቸው በሰጡት ቃል፣ " በክልሉ ካለው የጸጥታ ችግር ወይም ግጭት ጋር በተያያዘ ከፍተኛም መካከለኛም ጉዳት የደረሰባቸው ወደ 1115 ትምህርት ቤቶች አሉ " ነው ያሉት፡፡

" እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ ግብዓታቸውን በማሟላት ረገድ አንደኛ በአካባቢው ማህበረሰብ የሚሸፈን በዚያው ነው የሚሸፈኑት " ብለዋል፡፡

" የእኛን የክልሉን ኢንተርቬንሽን ሚጠይቁት ደግሞ አጋር አካላትን እያሳተፍን እቅድ አቅደን እያነጋገርን ነው፡፡ ከነርሱ ሀብት እያፈላለግን ትምህርት ቤቶች እንደገና ቁስቁሳቸው እንዲሟላ፣ እንዲገነቡ የማድረጉን ሥራ ወደፊት የምንስራ ነው የሚሆነው " ሲሉ አክለዋል፡፡

በክልሉ በ2016 ዓ/ም መመዘገብ ከነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት እንዳልተመዘገቡ ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ በ2017 ትምህርት ዘመን ደግሞ ቢሮው ለመመዝገብ ካቀደው ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ተመዘገቡ የተባለው 1.7 ተማሪዎች ናቸው፡፡

#TIKvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia