TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Big 5 Construct Ethiopia's opening ceremony today was honored by the presence of H.E. Temesgen Tiruneh, Deputy Prime Minister of Ethiopia and H.E. Chaltu Sani, Minister, Ministry of Urban and Infrastructure who shared their insights on the construction industry and officially declared the show open.

Register now for free entry and join the exhibition happening at the Millennium Hall until 1 June 2024.

Click here: https://bit.ly/3UsrL5I
ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ #በ77_ከተሞች የ4G LTE አገልግሎት ጀመረ.።

ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም ይታይባቸዋል ባላቸው 77 ከተሞች አዲስ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አስጀምሯል።

በኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ የ4ጂ LTE አገልግሎት ተጠቃሚ ከተሞች ብዛት 417 መድረሱንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

(የከተሞቹን ዝርዝር ከላይ በምስሉ ላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ማንኛውንም ሰው #ከሀገር_እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለህ/ ተ/ ም/ ቤት  ቀርቧል።

የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ?

ማሻሻያው ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ይሰጣል።

ነባሩ ህግ ምን ይላል ?

" ማንኛውም ሰው #ከኢትዮጵያ_እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት #በፍርድቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው " ይላል።

ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ ላይ የተቀመጠውን የፍርድ ቤትን " #ብቸኛ_ስልጣን " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት #ያጋራ ነው።

ማሻሻያው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ፦

⚫️ ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት ፤

⚫️ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል ሲል ደንግጓል። 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍ/ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት "ም ይላል የአዋጅ ማሻሻያው። 

ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።

አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " ሲል የረቂቅ አዋጁ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ማሻሻያ አዋጁ " #አስተዳደራዊ_ቅጣት " አንቀጽ ይዟል።

" ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል።

በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል።

#የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል።

" ይህን አዋጅ አሊያ በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው።

Credit:
#EthiopiaInisider 
#JournalistTesfalemWoldeyes

@tikvahethiopia
#ሬዚደንት #JU

“ የ3 ወራት ያህል ደመወዝ አልተከፈለንም ” - የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬዚደንት ሀኪሞች

“ ይህ ጉዳይ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው ” - ዩኒቨርሲቲው

በ2016 ዓ/ም በጤና ሚኒስቴር #በጅማ_ዩኒቨርሲቲ  ተመድበው በሆስፒታሉ ሥራና ስፔሳላይዜሽን ስልጠና የሚወስዱ 70 የአንደኛ ዓመት ሬዚደንት ሀኪሞች የ3 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታ አቅርበዋል። 

“ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ከፍተኛ ችግርና ስቃይ ውስጥ ወድቀናል ” ያሉት ቅሬታ አቅርቤዎቹ፣ ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግሩም ‘ መፍትሄ እየፈለግን ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው በጀት የለውም ’ እንደተባሉ ገልጸዋል።

መጀመሪያ 100 ሬዚደንት ሀኪሞች እንደነበሩ ፤ በኋላ ግን ለቀው ለመሄድ በመገደዳቸው አሁን ላይ የቀሩት 70 ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ቤተሰብ ጭምር ይዘው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሄዱ ሬዚደንት ሀኪሞችም እንዳሉ ፤ የሚተዳደሩት ከደመወዝ በሚያገኙት ገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው። ደመወዙ በዚህ ሳምንት ሊገባልን ይገባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፣ “ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው። እኛን አይመለከትም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመጠየቅ ወደ #ጤና_ሚኒስቴር የተደረገው ሙከራ ኃላፊዎቹ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ቃላቸውን ማካተት አልተቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

የነጻ (Free) ወይም የህዝብ (Public)ዋይፋይ ስጋቶች እና መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች።

የተለያዪ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።

https://t.me/BoAEth
የአየር ሰዓት ለመሙላት ፈልገው የማይችሉበት ሁኔታ ቢፈጠር፤ *810# ላይ በመደወል የአየር ሰዓት እና የጥቅል ብድር አገልግሎታችንን ተጠቅመው ግንኙነትዎን መቀጠል ይችላሉ፡፡

ቀጣይ ከሚሞሉት የአየር ሰዓት ላይ 10% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Ethiopia

በዛሬው ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አካሂዶ ውሳኔዎች አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ አንዱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ አዋጅን የሚመለከት ነው።

ም/ቤቱ " ከህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም " ብሏል።

" በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ መልሶ መመዝገብ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ረቂቅ የአዋጅ ማሸሻያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል " ሲል ገልጿል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

ሌላው ደግሞ ምክር ቤቱ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አድርጎ ስለማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀረበው አዋጅ ላይ መወያየቱን አሳውቋል።

" በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል የደህንነት ስጋት ከመሆኑ በተጨማሪ የፋይናንስ ስርዓቱ የተረጋጋ፣ ግልጸኝነት ያለው፣ ጤናማና ቀልጣፋ እንዳይሆን የሚያደርግ ነው " ብሎታል።

ይህን ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን የገለጸው ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን አመልክቷል።

(ተጨማሪ የምክር ቤቱን የስብሰባ ውሳኔዎች ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TPLF

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የህወሓት (TPLF) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የተሳተፉበት ውይይት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል ባለስልጣናት ጋር መደረጉ ይታወሳል።

በወቅቱም ከ ' ህወሓት ' ህጋዊ እውቅና  ማግኘት ጋር በተገናኘ ውይይት ተደርጎ ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከውይይቱ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫቸው ፤ ' ህወሓት / TPLF ' መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው ገልጸው ነበር።

በዚህም ያለው #የህግ_ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም መመራቱን ሲናገሩ ተደምጠው ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም ሲል የ ' ህወሓት ' ን ህጋዊ ሰውነት #መሰረዙ ይታወቃል።

ፓርቲውም " ስረዛው ይነሣልኝ " ሲል ጥያቄ ቢያቀርም ቦርዱ ያን ሊያደርግ የሚችልበት ምንም ህጋዊ መንገድ እንደሌለ አሳውቆ ነበር።

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ " ምናልባትም ህወሓት ዳግም እውቅና ሊያስገኝለት የሚያስችለው እንደሆነ እየተነገረ ነው።

@tikvahethiopia
" ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ ይደረግ " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ የእሳት አደጋዎች ደርሰው ከባድ የንብረት ወድመት ደርሷል።

ትላንት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ ከቀኑ 6:30 ሰዓት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉ የደረሰዉ ንብረትነቱ " ባህርን ኃ/የተ/የግል ማህበር " ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች የሚያስቀምጥበት መጋዘን ነው።

በእሳት አደጋዉ በመጋዘኑ የነበሩ ንብረቶች ወድመዋል።

እሳቱ ወደቤተክርስቲያኗ እንዲሁም በአካባቢዉ ባሉ የንግድ ድርጅቶችና የመኖሪያ ቤቶች ላይ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉ ታውቋል።

ከትላንት በስቲያ ደግሞ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ምናለሽ ተራ በተነሳ የእሳት አደጋ 18 የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሁን ያለው ሞቃታማና ነፋሻማ አየር ለእሳት አደጋ መከሰት እና መባባስ አስተዋጽኦ ስላለው ከወትሮ የተለየ ጥንቃቄ ይደረግ ብሏል።

#Ethiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#19_ዓመት ?

የ14 ዓመቷን ልጅ የደፈረው እና ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ19 ዓመት መቀጣቱ ተሰምቷል።

ተከሳሹ አላዩ ሞገስ ደሳለኝ ይባላል።

ጥር 29 ቀን 2015 ዓ / ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት ይገባል።

ከዛም በጥፊ በመምታት ፣ እንዳትጮህ በአፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት ይፈጽምባታል።

በአፏ ውስጥ #ጨርቅ_በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ጉዳዩም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ሲታይ ቆይቷል።

የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሹ ክሱን እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ግን ሊከላከል አልቻለም።

ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት " በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ " ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፍትህ ሚኒስቴር ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

እናት ፓርቲ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ።

ፓርቲው ለኮሚሽኑ በጻፈው ደብዳቤ ፤ " ኢትዮጵያ ሕልውናዋን በመፈታተን ደረጃ ላይ ከደረሰው ቀውስ ብቸኛው መውጫ መንገድ ሁሉን አቀፍ #አገራዊ_ምክክር ማድረግ ፤ እንደ አገር በዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሆነ በጽኑ እናምናለን " ብሏል።

" የምክክር ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የአጀንዳ ልየታ ውይይቶችን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንና ለዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ቀናት በሚደረጉ ስብሰባዎች የአጀንዳ ልየታ የሚያደርግ ጉባዔ መጥራቱ ይፋ ተድርጓል ፤ ጥሪው ለእኛም ደርሷል " ብሏል።

" የሚደረገው ምክክር ስልጣንን የጨበጠ አካል #በቀጥታም ሆነ #በስውር የሚመራው ውይይት መሆን እንደሌለበት እናምናለን " ሲል አስገንዝቧል።

ፓርቲው ፤ " በእኛ እሳቤ ይህ ምክክር በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት በመሠረታዊ መልኩ እስከ ማሻሻል አስፈላጊ ከሆነ እስከ መለወጥ ድረስ የሚያዘልቅ እንደሆነ ብናምንም በሥራ ላይ ያለው የአሸናፊዎች ሕገ መንግሥት ዓይነት ተግባር እንዳይፈጸም እና እንደ አገር ዳግም ስህተት እንዳንሠራ ከፍተኛ ሥጋት አለን " ሲል አሳውቋል።

" አገር ልትመክርበት ይገባል ብለን የምናስባቸው የምክክር አጀንዳዎች ፦
➡️ ወቅት የማይለውጣቸውና ወጥነት ያላቸው፣
➡️ መንግሥት ብንሆን ልንተገብራቸው ይገባል ብለን ያስቀመጥናቸው ነጥቦች ስለሆኑ ከአጀንዳ ልየታው ጋር ምንም ችግር የሌለንና ይህንኑ ያቀረብን መሆናችንን ኮሚሽኑ እንዲያውቀው የአገራችን ሕዝብም እንዲረዳልን እንወዳለን " ብሏል።

እናት ፓርቲ ፥ " አጀንዳዎቻችንን የማቅረቡ ሂደት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የምክክር መድረክ ፦

1ኛ. አገር በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ሁኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ፣ ከአገራት ተሞክሮ እንዲህ ባለ ሁኔታ የሚደረግ ምክክር ውጤታማ እንደማይሆን ታውቆ በተቃራኒ ወገን የተሰለፉ ወንድማማቾችን እያጨራረሰ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሄ ሳይበጅለት ፤

2ኛ. በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በየእሥር ቤቱ ታጉረው ባሉበትና ፍትሕ ተነፍጓቸው የሰቆቃ ሕይወት በሚገፉበት፤

3. የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ለምክክሩ ጭምር ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችሉ ወገኖቻችን ያለ ፍርድ በየእሥር ቤቱ በሚማቅቁበት፤

4ኛ. አገር በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባለችበት፤

5ኛ. በምክክሩ ከመሳተፍ ራሳቸውን ከመጀመሪያ ጀምሮ ከሂደቱ ያገለሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክር ማምጣት ባልተቻለበትና በመሳሰሉ ምክንያቶች ምክክሩ አገራችን በእጅጉ የምትሻውን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ያስገኝላታል ብለን አናምንም። " ሲል አሳውቋል።

" እነዚህ ሁኔታዎች አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እስከሚደረግበት ባለው ጊዜ በቀዳሚነት መፍትሄ አግኝተው ሊፈቱ ካልቻሉና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ በምክክሩ ለመሳተፍ እንቸገረለን " ሲል ገልጿል።

(ፓርቲው ለኮሚሽኑ የላከው ሙሉ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፎቶ ⬆️ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ደረጃ እያካሄደው የሚገኘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 3ኛ ቀን መርሀ ግብር ዛሬ አከናውኗል።

ዛሬ በከተማ ደረጃ " #ታዋቂ#ተጽዕኖ_ፈጣሪ " ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ተገኝተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ስለ ሂደቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ በተለየ ቦታ ላይ ከ112 ወረዳዎች ከ11 የህብረተሰብ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በየማኅበረሰብ ክፍላቸውን አጀንዳዎችን የለዩ  ሲሆን የሚወክሏቸውን 121 ተሳታፊዎች መርጠዋል።

ነገ ጠቅላይ የሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶችና ዛሬ የተመረጡ 121 ተሳታፊዎች ፤ መግለጫ የተሰጣቸው ተባባሪ አካላት በድምሩ ከ3 ሺ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ሀገራዊ የመክፈቻ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

@tikvahethiopia