TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.6K photos
1.39K videos
200 files
3.74K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል።

ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236  ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር።

ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#Mekelle

በመቐለ ከተማ መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ በእጣ መሬት ተሰጣቸው።

ለመኖሪያ በእጣ በተሰጠው መሬት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ የመቐለ መምህራን ተጠቃሚ እንደሆኑ ተነግሯል።  

ዛሬ የተካሄደው የመምህራን የመኖሪያ መሬት በእጣ የማስተላለፍ ስነ-ሰርዓት ሂደት ከጦርነት በፊት የተጀመረውን ያሰቀጠለ ነው።

ከጦርነቱ በፊት የትግራይ ክልል መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ የሚሆን በዕጣ የተሰጣቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይ በመቐለ የዕድሉ ተጠቃሚ ሳይሆኑ የቆዩት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ መምህራን ዛሬ ተጠቃሚ ሆነዋል።

መምህራን ደመወዝ ጨምሮ ሌሎች የሚጠይቁዋቸው ጥያቄዎች በየደረጃው መመለስ እንዳለበት ይህም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የትግራይ መምህራን ፦

° በጦርነቱ ምክንያት ያልተሰጣቸው ውዙፍ 17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው ፣

° የመኪና የሰርቪስ አገልግሎትም ጨምሮ ሌሎችም ጥያቄዎች ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ደጋግመው ጠይቀው አጥጋቢ መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ የሚመለከቱ ተከታታይ ዘገባዎች ስናቀርብ መቆያታችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
                                  
@tikvahethiopia            
#AddisAbaba

“ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው ” - ኮማንደር ማርቆስ

ኢዩኤል ታዬወርቅ የተባለ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጣበት ከህንፃ ላይ በወደቀ ብረት በድንገት ሕይወቱ ማለፉ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞን ለአደጋው ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቀ ሲሆን፣ “ እኛ አገልግሎት አልሰጠንም ” ብለዋል።

ሆኖም፣ ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኮማንደር በሰጡት ምላሽ፣ “ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው። 4 ሰዓት ላይ ነው የሞተው በሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ” ብለዋል።

“ ሟቹ ኢዩኤል የሚባል ልጅ ነው። እድሜው 23 ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ እንደሆነ ነው የተነገረኝ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ አደጋው የደረሰው “የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ሟቹ የኪነህንፃ  (Architecture) #ተመራቂ ተማሪ እነደነበር ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ አስታውቆ፣ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

“ ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር የሄደ ሲሆን፣ በማግስቱ ከታናሽ ወንድሙ ጋር እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝ ከፍተኛ ፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ  ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል ” ብሏል ዩኒቨርሲቲው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በእጣ ያስተላልፋል። ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት ተመዝግበውና ቆጥበው መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የሠራዊት አባላትና ስቪል ሠራተኞች 1236  ቤቶችን በእጣ አስተለልፎ ነበር። ዛሬ ደግሞ 1336 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በእጣ ያስተላልፋል ተብሏል። #FDREDefenseForce @tikvahethiopia
የመከላከያ_ሠራዊት_ፋውንዴሽን_የቤት_ባለዕድለኞች_ዝርዝር.pdf
11.1 MB
መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያሥገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ ለባለ ዕድለኞች በዕጣ አስተላልፏል።

በዕጣ የተላለፉት አጠቃላይ 1,336  የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦
- ባለ 4 መኝታ
- ባለ 3 መኝታ
- ባለ 2 መኝታ
- ባለ 1 መኝታ ናቸው።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ለሠራዊት አባላት እና ቋሚ ለሆኑ ስቪል ሰራተኞች ነው የተላለፉት።

(የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ከላይ በPDF ተያይዟል)

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#Tigray #Exam

የትግራይ ክልል በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተፈታኞ በ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ የሚፈተኑበት መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

🔥 አርሰናሎች የ20 ዓመት የዋንጫ ጥማታቸውን ሊቆርጡ መድፋቸውን እያገላበጡ ወደ የፕሪሚየር ሊግ አፋፉ ተቃርበዋል።

አፋፉ ላይ ደግሞ ቀያዮቹ ቆመዋል!

⚽️ እሁድ ከምሽቱ 12፡30 ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ብቻ!

ይህ ታሪካዊ ፉክክር እንዳያመልጥዎ…

👉 ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#AddisAbaba

ከላይ ባለው ፎቶ የምትመለከቱት ትላንት ለሊት 6:50 በአዲስ አበባ የረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል አጠገብ የተከሰተ የእሳት አደጋ ያደረሰው ከፍተኛ ውድመት ነው።

እሳቱ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን የህዝብ ርብርብ ተደርጎ ፣ በ12 የእሳት አደጋ መኪኖች አገልግሎት እና በጸጥታ አካላት ተባባሪነት ከሌሊቱ 9:00  ላይ መቆጣጠር ተችሏል።

ርብርቡ እሳቱ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይዛመት አድርጓል።

በሌሊቱ አደጋ በቤተክርስቲያን ዙሪያ የነበሩ 13 የንግድ ሱቆችና ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በጋራዡ ውስጥ የነበሩ 5 ተሽከርካሪዎች በተመሳሳይ ሙሉ ሙሉ ሲወድሙ በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

በጋራዡ የነበሩ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ማዳን ተችሏል።

በአደጋዉ ሰው ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።

Photo Credit ፦ Media of Addis Ababa Diocese

@tikvahethiopia
" ... ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " - የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር አደረኩት ባለው ማጣራት በክልሉ ውስጥ ባሉት የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህራን ሁሉም በሚባል መልኩ  ትምህርታቸውን በፋይናንስ እጥረት በአግባቡ እየተማሩ አይደለም።

ዕጩ መምህራን በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆች ሲገቡ ከመንግስት የሚሰጣቸዉ 450 ብር በቂ እንዳልሆነ እየታወቀ ቢጀመርም እስካሁን ሊስተካከልላቸው አልቻለም።

ይህን ችግር በተመለከተ ኮሌጆቹ በቦርድ ደረጃ ያመኑበት ከመሆኑ ባለፈ ማስተካከያ እንዲደረግ ለክልሉ መንግስት ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ይሁንና የክልሉ መንግስት ለጥያቄው ተገቢ ምላሽ ባለመስጠቱ በክልሉ በተለያዬ ደረጃ የመምህራንነት ስልጠና ለመዉሰድ ወደኮሌጆች ገብተዉ በትምህርት ላይ የሚገኙ በርካታ ዕጩ መምህራን በችግር እየተጠበሱና ትምህርታቸዉን ትተዉ ወደመጡበት እየተመለሱ መሆናቸዉን የክልሉ መምህራን ማህበር አውቂያለሁ ብሏል።

የመምህራን ማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ አማኑኤል ጳዉሎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ፤ " ከነዚህ ተማሪዎች መካከል አብዛኛዉ ወንዶች በትምህርት ሰአት ሁሉ የቀን ስራ በመስራት ርሀባቸውን ለማስታገስ በጥረት ላይ ሲሆኑ  ሴቶችም ላልተገባ ችግር ተጋልጠዉ መማር አልቻሉም " ብለዋል።

" በመሆኑም ተማሪዎች በ450 ብር በልተዉና ጠጥተዉ እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን ሸፍነዉ  መማር አይችሉምና የክልሉ መንግስት በተለይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ባስቸኳይ ችግራቸዉን ይፈታላቸዉ ዘንድ ማህበሩ በደብዳቤ ሁሉ ጠይቋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ስለምን ተማሪዎቹ በዚህ ልክ እስኪሰቃዩ ድረስ መፍትሄ አልተፈለገም ? በማለት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።

ምላሽ ሲሰጥ ምላሹን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#SOS

"ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ" የተሰኘው ድርጅት ከሰሞኑን የ50ኛ ዓመት በዓሉን አክብሮ ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ ድርጅቱ በአጠቃላይ፦
- በአማራጭ የቤተሰብ ክብካቤ -በቤተሰብና ማህበረሰብ አቅም ግንባታ
- በአስቸኳይ ጊዜ ሰብዓዊ ድጋፍ በትምህርት
- ጤና እና በወጣቶች ማብቂያ ፕሮግራሞች ከ8.1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን እንደደረሰ ገልጿል።

እንዲሁም በእነዚሁ ፕሮግራሞች መሠረት በዚህ ዓመት 700 ሺሕ አካላትን ለመድረስ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በጦርነት፣ በድርቅ እና መሰል ክስተቶች ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችን ራሳቸውን እንዲችሉ እርዳታ ማድረግ ዋነኛ ዓላመው መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ በኢትዮጵያ በ9 ክልሎች እየሰራ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

° በተለያዩ ክልሎች በተካሄዱት ጦርነቶችና እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ድርጅቱ ምን ያህል ወላጅ አልባ ህፃናትን አገኘ ?

° በአዲስ አበባ ከተማ ጎዳና ላይ ለሚተዳደሩ ወላጅ አልባ በርካታ ልጆን ለመርዳት ምን እየሰራ ? ነው ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ምክትል ብሔራዊ ዳይሬክተር ኤቢሳ ጃለታ ቁጥቸውን ለመግለጽ ቢታቀቡም በጦርነት ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በጎረቤት፣ በቅርብ ቤተሰቦቻቸው አስጠግቶ እየረዳ መሆኑን ተገናግረዋል።

አ/አ የሚገኙትን በተመለከተም ፕሮጀክት በመቅረጽ እየሰራ መሆኑንን አስረድተዋል።

ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ከ1949 ዓ/ም ጀምሮ የቤተሰብ እንክብካቤ ላጡ ህፃናት በፍቅር የተሞላ ቤተሰብ ሲሰጥ የቆየው የዓለም አቀፉ የኤስ ኦ ኤስ ፌደሬሽን አካል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@TikvahEthiopia
#ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር
Yonathan BT furniture

ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸውን እቃዎች ከብዙ አማራጮች ጋር ከዮናታን ቢቲ ያገኛሉ!

የውበት ፣የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !

አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ):
+251 957 86 8686
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት:
+251 995 27 2727
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ ሀያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ):
+251 993 82 8282