TIKVAH-ETHIOPIA
1.44M subscribers
55.9K photos
1.4K videos
202 files
3.77K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ ታይቷል።

ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን ገልጿል።

" በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል " ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቋል።

@tikvahethiopia
የትንሳኤ ልዩ የሞባይል ጥቅል የቆይታ ጊዜ ነገ ያበቃል!

ልዩ የበዓል ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ በማበርከት እስከ 25% ቅናሽ ያግኙ!


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba

ሀሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ፈተናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን ነው የሚሰጡት ተብሏል።
 
ፈተናው በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺህ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በፈተና ወቅት ተመዛኞች ስልክ ሆነ ማንኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዞ ፈተና ክፍል መግባት እንደማቻል ተገልጿል።

ተመዛኞች ፦

➡️ የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣

➡️ ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና ፈተና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን ፈተናው በፍቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,491 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ቢገለጽም የምዘና ፈተና ለመውሰድ #ስላልተመዘገቡ ወይም ፍቃደኛ ስላልሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ምንም የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #ጅቦቹ ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ ጀምረዋል " - ነዋሪዎች

" በኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጸናት በጅቦች ተበልተዋል። 2ቱ ሲሞቱ አንዷ ተርፋለች " - አቶ ማርቆስ ቡታ

ከሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተራቡ ጅቦች እያደረሱ ስላለው ጥቃት የሚመለከቱ መረጃዎችን ማጋራታችን ይታወሳል።

በተለይ በስልጤ ዞን እና በሀላባ ዙሪያ በተፈጸሙ የጅብ ጥቃቶች ምክኒያት የሰው ህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መድረሱን መግለጻችን አይዘነጋም።

በወቅቱ " የጅብ መንጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ተከስቷል " የሚለውን ዜና የሰሙ የሲዳማ ክልል፣ የሀዋሳ ከተማ ዙሪያ ነዋሪዎች " ችግሩ እኛም ጋር አለ እንዲያዉም ከህጻናት ባለፈ አዋቂዎችንም አሳስቦናል " በማለት መልዕክቶቻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድረሰዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ አባል በሀዋሳ ዙሪያ ቡሽሎ ፣ ፊንጭ ውሀና ገመጦ... ወዘተ ቀበሌዎች ያሉ ማህበረሰቦችና የጸጥታ አካላትን አነጋግሯል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በጊዜ ወደ ቤታቸው መግባት መጀመራቸውን በመጥቀስ ህጻናት ልጆቸውም ፍርሀት እንዳደረባቸዉ ገልጸዋል።

በተለያየ ጊዜ በ5 ሰዎች ላይ የጅብ ጥቃት ደርሶ እንደነበር እና 2 ህጻናት እንደሞቱ 1 ህጻን እንዲሁም 4 አዋቂዎች ደግሞ እንደተጎዱ አስረድተዋል። የሚመለከተው አካል አንዳች መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

በአካባቢው ለረዥም ጊዜያት ጅቦች እንደነበሩ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰው መተናኮስ ፤ በቀን መታየትና #ሰብሰብ ብሎ መሄድ መጀመራቸው እንዳስገረማቸው ገልጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የቡሽሎ ቀበሌ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማርቆስ ቡታ ፤ " በእኛ ቀበሌ ብቻ 3 ህጻናት በጅቦች ተበልተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

2ቱ መሞታቸውን ፤ አንዷ ህጻን በወቅቱ በተደረገ ርብርብ ተርፋ በተደረገላት ህክምና መዳኗን ገልጸዋል።

በአጎራባች ቀበሌያት ውስጥ በ2 አዋቂ ሰዎች ላይ አሰቃቂ አደጋ ቢደርስም ለመትረፍ እንደቻሉ የጠቀሱት አቶ ማርቆስ ችግሩ አሳሳቢ በመሆን የጸጥታ አካላት እየተነጋገረበት ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ በጊዜ በመግባት የሚሰጠዉን የጥንቃቄ መልእክት በአግባቡ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለ Big 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ይዘጋጁ! በሃገሪቱ ግንባታ ዘርፍ ትልቁ ዝግጅት፤ ከግንቦት 22 እስከ ግንቦት 24፣ 2016 በሚሊኒየም አዳራሽ ይዘጋጃል።

- ከ 150 በላይ ከሚሆኑ ተሳታፊዎች የሚቀርቡ አዳዲስ ምርቶችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይጎብኙ!

- ከ 15 በላይ ሃገራት ከሚመጡ ተሳታፊዎች ጋር ይገናኙ!

- በግንባታው ዘርፍ ከበቁ 9000 ባለሙያዎች ጋር ትስስር ይፍጠሩ!

- ከ 20 በላይ በሚሆኑ፣ በዋጋ በማይተመኑ መረጃ ሰጪ መድረኮች ላይ የመሳተፍና የ Continuous professional development ነጥብዎን የማሳደግ ዕድሉን ያግኙ!

በሁነቱ ላይ ልናገኝዎ በጉጉት እንጠብቃልን!
በነጻ ለመጎብኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ : https://bit.ly/3UsrL5I
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ2 ሰዎችን አስክሬን እየፈለግን ነው " - የዞኑ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከሰው ህይወት መጥፋት ባለፈ በአዝእርትና በብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ  መፍጠሩ ተነግሯል። በጉዳዩ…
#Update

" በጎርፍ የተወሰዱ አስክሬኖች #አልተገኙም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ መምሪያ

ከሰሞኑን በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃ እንደሰጠናችሁ ይታወሳል።

በወቅቱ 5 ሰዎች መሞታቸዉንና ከነዚህ ዉስጥ የ2 ሰዎች አስከሬን አለመገኘቱ መግለጹ አይዘነጋም።

አስክሬን ፍለጋው ከምን ደረሰ ? ከአደጋው ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? ስንል የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊን አቶ ሙደስር ጉታጎ ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊው አስከሬኖቹ አሁን ድረስ አለመገኘታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ አንድ አስክሬን በዞኑ መገኘቱን  በተደረገው ማጣራት አስከሬኑ ከስልጤ ዞን በጎርፍ ምክንያት የመጣ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የጎርፍ አደጋው እስካሁን መሬት ላይ የነበረዉን ሰብል ሙሉ በሙሉ እንዳወደመ ገልጸዋል።

በዞኑ ውስጥ ባለው የሀላባ ቁሊቶ ሆስፒታል  ላይ ከ6 ሚሊየን 500 ሺህ ብር በላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተናግረዋል። ነገር ግን ሆስፒታሉ አሁንም በስራ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም የተገለጸው ዌራ ወረዳ ሆስፒታል ግን በአደጋው ምንም ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ጎርፉ ያስከተለዉ አደጋ በህዝብና ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ እና የንብረት ውድመት ያስከተለ ሲሆን ዞኑ አሁንም አስክሬን እና የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ስራ እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁንም የአየር ትንበያ ዘገባዎች በደቡቡ ኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ዝናብ እንደሚኖር ስለሚጠቁሙ ማህበረሰቡ ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መጋቢት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? - ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም - ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም - ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም - ቀላል…
የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

- ነጭ ናፍጣ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ብር 61.16 በሊትር ሆኖ ባለበት ይቀጥላል።

የቤንዚን ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ በሊትር 78 ብር 67 ሳንቲም ገብቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

ትላንትና ማክሰኞ #ከሀዋሳ ወደ #አዲስ_አበባ በመብረር ላይ እያለ የደኅንነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ክስተት በገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር #ET154 ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥልቅ የሆነ የደኅንነት ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ትላንት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከፍተኛ ጭስ መከሰቱን፣ ነገር ግን በመንገደኞች ላይም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ ምን ዓይነት እክል ሳይፈጠር ቦሌ ኤርፖርት በሰላም ማረፉ መገለጹ ይታወሳል።

አውሮፕላኑ ውስጥ ለጊዜው በምን ምክንያት እንደተነሳ ያልታወቀው ጭስ መንገደኞችን ከፍተኛ ድንጋጤና ፍርኃት ውስጥ አስገብቷቸው ነበር።

የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ባስተላለፉት የደኅንነት ጥንቃቄ ዕርምጃ መሠረት ሁሉም ተሳፋሪዎች በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመውን የአየር መሳቢያ የፊት ጭምብል (oxygen mask) እስከማድረግ ደርሰው ነበር።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የበረራ ደኅንነት ክፍል እክል የገጠመው አውሮፕላን ቀጣይ በረራ እንዳያደርግ በማገድ በበረራ ወቅት ያጋጠመውን የደኅንነት ክስተት እንደሚያጣራ ሪፖርተር ጋዜጣ ስማቸው ያልተገለጹ የተቋሙን ምንጮች ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

እኚሁ ምንጮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አየር መንገዱ በሚሰጠው የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት ላይ የደኅንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ክስተቶች ደጋግመው መከሰታቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን አጠቃላይ የደኅንነት ፍተሻ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ/ም ላይ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ሲበር የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት ከማረፊያው አስፋልት ውጪ የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል።

ሌላው የመንገደኞች አውሮፕላን በተመሳሳይ በአርባ ምንጭ አውሮፓላን ማረፊያ ከማረፊያ መስመሩ (ራንዌይ) የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ተስምቷል።

በአጠቃላይ በአንድ ዓመት 4 የደኅንነት እክሎች የተመዘገቡ መሆኑን ጋዜጣው ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ጠቁሟል።

ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲበር የነበረውን ጨምሮ እክል ያጋጠማቸው አውሮፕላኖች ' #Q400 ' በመባል የሚታወቁት አየር መንገዱ በአገር ውስጥ እና ወደ ጎረቤት አገሮች ለሚደረጉ በረራዎች የሚገለገልባቸው ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካሉት 178 አውሮፕላኖች መካከል 33 የሚሆኑት Q400 በመባል የሚታወቁት ለመካከለኛ ርቀት የሚጠቀምባቸው አውሮፕላኖች ናቸው። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
📱 ባይትዳንስ ' #ቲክቶክ ' ን #ለአሜሪካ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ #ቢዘጋው እንደሚመርጥ ሮይተርስ ለኩባንያው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ። ኩባንያው በ' ቲክቶክ ' ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል። አሁን ' ቲክቶክ ' የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር…
ቲክቶክ ወደ ፍርድ ቤት አመራ።

ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ በመላ አሜሪካ ለመታገድ ተቃርቧል።

እግዱ ተግባራዊ እንዳይደረግ ወይም ውድቅ እንዲሆን ቲክቶክ ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት አምርቷል፤ ሙግትም ከፍቷል።

መተግበሪያው ለፍ/ቤት ባቀረበው የአቤቱታ መዝገብ " ከ9 ወር - 1 ዓመት ባለው ጊዜ ቲክቶክ ካልተሸጠ #ይታገድ " የሚለው ሕግ ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው ብሎታል።

" ሕጉ የአሜሪካውያንን የመናገር ነጻነትን የሚያደናቅፍ እና ሕጋዊ መረጃን እንዳያገኙ የሚከለክል ነው " ሲል አክሏል።

አሜሪካ እርምጃውን ለመውሰድ " ግምታዊ ስጋቶችን " ብቻ እንዳቀረበች የገለጸው ቲክቶክ ፍርድ ቤት እግዱን እንዲያስቆምለት ጠይቋል።

ባይትዳንስ ኩባንያ 'ቲክቶክ'ን አሁን ባለው አልጎሪዝም ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ #መዘጋትን እንደሚመርጥ የኩባንያው ምንጮች መናገራቸው ይታወሳል።

አሜሪካም ከሀገር ደህንነት ጋር በተያያዘ " ካልተሸጠ ይታገድ " በሚለው ሕግ ላይ አቋሟ ፍጹም የጸና ነው ተብሏል።

በቀሩት ጥቂት ወራት ውስጥ #ካልተሸጠ በመላው አሜሪካ መታገዱ የማይቀርለት ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹን ያጣል።

@tikvahethiopia
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የዳግመ ትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ ይቀርባል፡፡

እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እንዲሁም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከወዲሁ ተዘጋጅተው ይጠብቁን !

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ     
 የስኬትዎ አጋር!   

[Telegram]  [Facebook]

https://t.me/LionBankSC

#LIB #lioninternationalbank #anbesabank #keytosuccess
" በ5ቱ ኮሪደር ልማት ስራ 16 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ከተማ  ፦
° መንገዶችን የማስፋት ፣
° የመንገድ ዳሮችን የማሳመር ፣
° የእግረኛና የሳይክል ብስክሌት መሄጃዎችን መስራት
° የቴሌ፣ የመብራት ኬብሎችን ወደ መሬት መቅበር
° የውሃ ፍሳሽ መሄጃዎችን መስራት
° ፕላዛዎችን መስራት የሚያጠቃልለው የኮሪደር ልማት ስራ በ5 ኮሪደሮች በመሰራት ላይ ይገኛል።

48.7 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል የተባለው የኮሪደር ስራ ፥
➡️ ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ፣
➡️ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ ፣
➡️ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣
➡️ ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይ ቦሌ ድልድይ ፣
➡️ ከቦሌ ድልድይ በመገናኛ እስከ አፍሪካ ኮንፌሽንን ያካልላል።

ስራዎቹ በሳምንት ለ7 ቀናት በቀን ለ24 ሰዓት የሚሰሩ ሲሆን ብዙ ቦታ ላይ መሰረታዊ ስራዎች ተሰርተው መጠናቀቃቸው ታውቋል።

የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ በአምስቱ የኮሪደር ልማት ስራ " 16,000 ሰዎች ስራ እድል አግኝተዋል " ብለዋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-08-4
TIKVAH-ETHIOPIA
ቲክቶክ ወደ ፍርድ ቤት አመራ። ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ በመላ አሜሪካ ለመታገድ ተቃርቧል። እግዱ ተግባራዊ እንዳይደረግ ወይም ውድቅ እንዲሆን ቲክቶክ ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት አምርቷል፤ ሙግትም ከፍቷል። መተግበሪያው ለፍ/ቤት ባቀረበው የአቤቱታ መዝገብ " ከ9 ወር - 1 ዓመት ባለው ጊዜ ቲክቶክ ካልተሸጠ #ይታገድ " የሚለው ሕግ ኢ-ሕገመንግስታዊ…
'ቲክቶክ' ን ሙሉ በሙሉ / በከፊል ያገዱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?

1ኛ. ህንድ

ቲክቶክን ያገደችው በ2020 ላይ ነው። በድንበር አካባቢ ከቻይና ጋር የተፈጠረው #ግጭትን ተከትሎ ነው ለደህንነት በሚል ቲክቶክን እና ሌሎች ከቻይና ጋር የተገናኙ መተገበሪያዎችን ያገደችው።

በወቅቱ በሀገሪቱ 200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩ።

2. አፍጋኒስታን

ቲክቶክን በ2022 ያገደች ሲሆን ምክንያቷ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዳይሄድ ለመከላከል ነበር።

3.  አውስትራሊያ

በፌዴራል መንግሥት ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ ማሳሪያ ላይ እንዳይሰራ ተደርጓል። ከደህንነት ጋር በተያያዘ

4. ቤልጂየም

ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ቲክቶክን በፌደራል የህዝብ አገልግሎት መሳሪያዎች ላይ እንዳይሰራ ጊዜያዊ እገዳ ጥላለች።

5. ካናዳ

ከደህንነት ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግሥት መሳሪያዎች ላይ ታግዷል።

6. ዴንማርክ

የሀገር መከላከያው ሚኒስቴር ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ስልኩ ቲክቶክ እንዳይጠቀመ ያገደ ሲሆን ሁሉም ሰራተኛ ጭኖት የነበረውን መተግበሪያ እንዲያጠፋ አስደርጓል።

7. የአውሮፓ ህብረት

ሰራተኞች ሚጠቀሙበት መሳሪያ ላይ ታግዷል። የፓርላማው ህግ አውጭዎች እና ሰራተኞችም ከኤሌክትሮኒክ መሳሪያቸው ላይ እንዲያስወግዱ ተደርጓል።

8. ፈረንሳይ

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ቲክቶክና ሌሎች እንደ X ፣ ኢንስታግራም ያሉ መተግበሪያዎችን የመንግስት ሰራተኞች ስልካቸው ላይ ለ 'መዝናኛ' በሚል እንዳይጠቀሙ ታግደዋል።

9. ላቲቪያ

ከደህንነት ጋር ተያይዞ በሁሉም የላቲቪያ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ እንዳይሰራ ታግዷል።

10. ኔዘርላንድስ

ማዕከላዊ መንግሥት ቲክቶክ ጨምሮ ሌሎችንም መተግበሪያዎች ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከሰራተኞች ስልክ ላይ እንዲታገዱ አድርጓል።

11. ኔፓል

ማህበራዊ መስተጋብር በመሸርሸር፣ ወጣቶችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በመውሰድ በሚል ሙሉ በሙሉ ነው ያገደችው።

12. ኒውዚለንድ

የፓርላማው ህግ አውጪዎችና ሰራተኞች በሙሉ ስልካቸው ላይ ቲክቶክ እንዳይኖር ታግደዋል፤ ይህ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው።

13. ኖርዌይ

ከመላው የኖርዌይ ፓርላማ የስራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እንዲታገድ ተደርጓል። የመንግስት ሰራተኞች ስልካቸው ላይ እንዳይጭኑ ታዟል።

14. ፓኪስታን

ከ2020 ጀምሮ ቢያንስ ለአራት ጊዜ በጊዜያዊነት አግዳለች ይህም ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ይዘትን ያስተዋውቃል በሚል ነው።

15. ሶማሊያ

መንግሥት ቲክቶክ፣ ቴሌግራምና 1 የቁማር ድረገጽ እንዳይሰሩ እንዲያደርጉ አዟል። መተግበሪያዎቹ የጽንፈኝነት መፈንጫ ሆነዋል በሚል ነው።

16. ታይዋን

ከደህንነት ጋር ተያይዞ ከሁሉም መንግሥታዊ መሳሪያዎች ከስልክ ፣ ታብሌት ፣ ኮምፒዩተር ፣ እንዳይሰራ ተደርጓል።

17. ዩናይትድ ኪንግደም

የመንግስት ሚኒስትሮችና የመንግስት ሰራተኞች ከሚጠቀሙባቸው የሞባይል ስልኮች እንዳይሰራ ታግዷል። ፓርላማው ከኦፊሴላዊ መሳሪያዎችና ኔትዎትክ ላይ አግዷል። ይህ ከደህንነት ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ ነው።

18. ኪርጊስታን

የልጆች አእምሯዊ፣ መንፈሳዊ እና ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም በሚል ቲክቶክን በሙሉ አግዳለች።

19. አሜሪካ

ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከፌደራል ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እንዲታገድ ተድርጓል። ከ50 ግዛቶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መተግበሪያውን ከይፋዊ የመንግስት መሳሪያዎች ላይ አግደዋል።

አሁን ሙሉ በሙሉ ልታግድ ጫፍ ደርሳለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፤ መረጃውን ያሰባሰበው ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነው።

@tikvahethiopia
#ጎጆብሪጅ #ጤናባለሙያዎች

➡️ " ውላችን ይቋረጥ ፣ #ገንዘባችንም_ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች

➡️ " ከጤና ሚኒስቴር፣ ከዳሽን ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ

ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ #የጤና_ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ ብሪጂ ሀውሲንግ ፦
➡️እጣውን በወቅቱ እያወጣ ባለመሆኑ፣
➡️እጣ የወጣላቸውም ግንባታ ባለመጀመሩ፣ 4,000 ቆጣቢዎች ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢጠይቁም እንዳልተመለሰላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ጠይቀዋል።

የቆጣቢዎቹ ኮሚቴ በጉዳዩ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " በየሶስት ወሩ ለማውጣት እጣው ሳይሰጥ 2 ዙር አልፏል። ለምን ? ተብለው ሲጠየቁ ' #የመሬት_አስተዳደር_ችግር_ስላለብን_ነው ' እያሉ እስካሁን ቆዩ " ብሏል።

" ውላችን ይቋረጥ ፤ ገንዘባችንም ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 የቤት ቆጣቢዎች አሉ " ሲል የገለጸው ኮሚቴው በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተሰጠው አስረድቷል።

ለተነሳው የቤቶች እጣ መዘግየት ቅሬታ በ ' ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ' በኩል ምላሽ እንዲሰጡን የተጠየቁት አቶ አልማው ጋሪ ፤ " የገጠመን ችግር በአደረጃጀት ላይ #መዘግየቶች ስለነበሩ ነው " ብለዋል።

" የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የሚባለው ነው " ያሉት አቶ አልማው፣ " ሌላ ሳይት ላይ በተፈጠረ ክስ ትንሽ ሥራው ስለቆመ እስኪ ውጤቱን እንየው የሚል ሀሳብ ተነስቶ ስለነበረ የመዘግየት ጉዳይ አጋጥሟል " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የቤት ቆጣቢዎቹ ከጠየቁ ለምን ገንዘባቸውን አልመለሳችሁም ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ውሉ የሚያስቀምጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ይህን ደግሞ ለብቻችን ሳይሆን ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " ብለዋል።

" የመጀመሪያው እጣ ማውጣት ተደርሶ ወደ 300 ሰዎች እጣ የደረሳቸው አሉ። እነርሱን ለማደራጀት በሂደት ላይ ነው ያለነው " ያሉት አቶ አልማው " አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ አላቸው እየመጡ ይጠይቃሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጉዳይም ባለፈው ሳምንት ጤና ሚኒስቴር የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ አቀረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ምናልባት በዚህ ሳምንት አንድ ደረጃ ላይ ይደርሳል " ብለዋል።

#TikvahEthinpiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM