TIKVAH-ETHIOPIA
1.49M subscribers
56.5K photos
1.41K videos
203 files
3.84K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ ከትላንት ለሊት አንስቶ ከበድ ያለ ዝናብ ሲጥል ነበር። ዛሬ ንጋት ላይ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ደግሞ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል። @tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የ4 ሰዎች አስክሬን ከተለያየ ቦታ አውጥተናል። ...‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም " - አቶ ንጋቱ ማሞ

ከቀናት በፊት “ ሰዓሊተ ምህረት ጀርባ ያድሩ የነበሩ 13 የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው እንዳለፈ አካባቢው ላይ ተነግሯል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በስፍራው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፣ ዋናተኞች፣ የፌደራል ፓሊስ አባላት ተገኝተው አስክሬን ለማውጣት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደተመለከቱ የገለጹ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመረራር ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ምላሽ፤ “ ባለፈው እንደገለጽነው የ4 ሰዎች አስከሬን አውጥተናል። ‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። ጥቆማ ከሆነ ሊሆን ይችላል ” ብለዋል።

“ ምክንያቱም በየትኛውም ጉዳይ ሕይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖር ወይ እሳት አደጋ ወይ ፓሊስ ነው የሚያነሳው፤ በግለሰብ ደረጃ አስከሬን አንስቶ ቀብር ያለ አይመስለኝም ” ነው ያሉት።

“ በቦታው ነበርን ግን ይሄ አሁን የተጠቀሰው ቁጥር (13) አስከሬን አልተገኘም። ያገኘነው 4 አስከሬን ነው ” ያሉት አቶ ንጋቱ ፣ 4ቱን አስክሬን ለፓሊስ አስረክበናል ሲሉ አስረድተዋል።

4 አስክሬን የት አካባቢ ነው የተገኘው ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሰዓሊተ ምህረትም፤ ከተለያዩ ቦታም ነው የገኘነው። ጎዳና ተዳዳሪ ይሁኑ፣ እዛው አካባቢ ነዋሪ ይሁኑ እኛ መረጃ የለንም። ፓሊስ ነው የሚያረጋግጠው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አሁን የሚሉት ጥቆማ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጥ ከሆነ ከፓሊስ ጋር ሆነን ፍለጋ እናካሂዳለን። አንዳንድ ጊዜ ጥቆማ ትክክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይኖር ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል።

ጎርፉ ተቋማትን ጨምሮ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን፣ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ኑሯቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ወንዝ አካባቢ ባደረጉ ሰዎች እንደሆነ፣ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አደጋ ከደረሰም በ #939  የኮሚሽኑ ስልክ በፍጥነት ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝበዋል። 

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ?

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል።

ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው።

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው።

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

ተማሪዎቹ የትምህርት ጊዜያቸው እያለፈ እንደሆነና አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል።

70% ፈተናው በሰኔ ወር ይሰጣ መባሉ ደግሞ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- የነዚህ ልጆች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
- ከዚህ በኃላ መቼ ተጠርተው ተምረው ለፈተና ይቀርባሉ ?
- ለምን ምቹ ሁኔታ ከሌለ ቀደም ብሎ ሌላ ግቢ አይመደቡም ነበር ?
-  አሁን መፍትሄ ምንድነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች በተደጋጋሚ በድምጽ እና በፅሁፍ ለማናገር ጥረት ቢያደርግም #ቁርጥ ያለ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

በቀጣይም ጥረቱን ይቀጥላል።

ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ካገኘ ያቀርባል።

Via @tikvahUniversity

@tikvahethiopia
#ማኅብረቅዱሳን

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት እንዳልታወቀ የቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ጸሎተ_ሐሙስ

የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።

ዛሬ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ።

በስነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ቆሞሳት ፣ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit - TMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማኅብረቅዱሳን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል…
የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ " #ለጥያቄ_ይፈለጋሉ " በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

ቀደም ብሎ ፥ የሰንበት ት/ ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ከቤታቸው በጸጥታ ኃይል መወሰዳቸውና ቤታቸው ላክ ፍተሻ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዝገቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ጸሎተ_ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብሯል።

በአዲስ አበባ ፒያሳ ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴና የቅባ ቅዱስ ቡራኬ ተካሂዷል።

Photo Credit - FBC & Emdiber Catholic Secretariat

@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር

በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ!

የዘመናዊነት ተምሳሌት!


አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282

👉 Telegram:  https://t.me/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture

👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/