TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ለሌላቸው 1,051 ሴቶች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቴክኖሎጂ እቃዎች ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል።

ድጋፉ የተደረገላቸው በቤት ለቤት በተካሄደ ልየት ነው ተብሏል።

ቢሮው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣  " ሴቶችን ኢኮኖሚ ላይ ስናያቸው ከ153 አገራት 153ኛ ደረጃ ላይ ናት ኢትዮጵያ። ይሄ ማለት ከግማሽ በመቶ በላይ ሴቶች የኢኮኖሚ ተደራሽነታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው " ሲል ገልጿል።

ይህን ታሳቢ ተደርጎ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑና በቢሮው ካፒታል አማካኝነት በተሸፈነ በጀት ከአኗኗራቸው ጋር ይስማማል ብለው ሴቶች የመረጧቸውን ኦቨን፣ የኤሌክትሪክ ምጣድና ሌሎች እቃዎችን ለ1,051 ሴቶች ድጋፍ መደረጉ አሳውቋል።

በቀጣይ 2,000 ያህል ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን ለሴቶች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አመልክቷል።

ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ከ400ዐ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች ድጋፍ መደረጉን፣ ድጋፉ የሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ላላቸው፣ ምንም አይነት ገቢ ለሌላቸው፣ ለአካል ጉዳተኞች ነው ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጊብሰን መካከለኛ ደረጃ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዕውቅና ፍቃድ ታግዷል። ይህን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆነ ወላጆች " ግልፅ አይደለም " ያሉትን ጥያቄ አንስተው ምላሽ እንዲሰጥባቸው መልዕክት ልከዋል። የወላጆች ጥያቄ ... - ይፋ የሆነው ደብዳቤ የዋናው የባለስልጣን መ/ቤቱ ሳይሆን " የጉለሌ ቅርጫፍ ፅ/ቤት " ነው ለዋናው ባለስልጣን መ/ቤት…
#ጊብሰን #GibsonSchool

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጊብሰን ትምህርት ቤት የሚማሩ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከተማ አቀፉን የሚኒስትሪ ፈተና ትምህርት ቤቱ ማስፈተን እንደማይችል እንዳሳወቀው ት/ቤቱ ገልጿል።

ጊብሰን ትምህርት ቤት " ባጠፋቸው ጥፋቶች ምክንያት እግድ ስለተጣለበት ተማሪዎችን ማስፈተን አይችልም " የተባለ ሲሆን ትምህርት ቢሮው ተማሪዎችን ሌላ ትምህርት ቤት ወስዶ በማስፈተን የሚኒስትሪ ካርዱ ላይም " በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስር " የሚል እንደሚፃፍበት ተገልጿል።

ይህን ውሳኔ ወላጆች እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።

ወላጆች ምን አሉ ?
- ልጆቻችን በተማሩበት ት/ቤት ስር ነው መፈተን ያለባቸው
- የተነገርን ነገር የለም
- ባለቀ ሰዓት ነው ይህን የሰማነው
- በተቀመጠው ካሪኩለም እንደሚማሩ ነው እኛ የምናውቀው
- ልጆቻን ካሪኩለሙ የሚፈቅደውን ነው የሚማሩት
- ቋንቋ ችግር አለ ወይ ? የለም
- ሌሎች ት/ቤት የሚተገበረው ነው እዚህም ያለው
- ከሌሎች የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚለየው ሳይንስ እና ሂሳብን በተጨማሪ እንግሊዘኛ ቋንቋ ያንኑ ካሪኩለም ጠብቆ ማስተማሩ ነው። እኛ ትምህርት ቤቱን የመረጥነው ተጨማሪ ቋንቋ ስለሚያስተምር ነው።
- በተቀመጠው አማራጭ ሁለት ቋንቋ እያስተማረ ነው። አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ በትምህርት አይነት ደረጃ እየተማሩ ነው። የቀረ ነገር የለም።
- በመደበኛው ፕሮግራም ምንም የተጣሰ ነገር የለም።

የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ትምህርት ቤቱ ብዙ ጥሰት ፈጽሟል ብለዋል።

አቶ አድማሱ ደቻሳ ምን አሉ ?

° የትምህርት አይነት ጨምሮ ማስተማር
° የክፍለ ጊዜ ጥሰት
° የትምህርት ቋንቋ አለማክበር
° የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሀገራችን " እንግሊዘኛ ነው " ብሎ ስታንዳርድ እስከመያዝ መድረስ፤
° በእንግሊዝኛ አፋቸውን የፈቱ ካሉ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አለ እዛ መማር ይችላሉ ግን በከተማው ፍቃድ የወሰደ ት/ቤት " የአፍ መፍቻ ቋንቋው እንግሊዝኛ ነው " በሚል ማስተማር አይችልም።
° የሀገር በቀል ቋንቋ ጠል መሆን ተገቢ አይደለም።
° ተጨማሪ ቋንቋ በጥናት የተመለሰ ነው ይህንም እንዲታወቅ ብዙ ተሰርቷል ይህ ሆኖ እያለ ' አናውቅም፣ አልሰማንም ፣የሚመጣ ነገር የለም ' የማለት ነገር አለ።

አንድ ወር ለቀረው የትምህርት ጊዜ ይህን ውሳኔ ለምን አሳለፋችሁ ? ለምን አልታገሳችሁም ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦

አቶ አድማሱ ደቻሳ ፦

" እኛ እልህ እየተጋባን አይደለም። የተወሰደው እርምጃ ከ4 ወር በፊት ነው። ነገር ግን ት/ቤቱ ተማሪና ወላጆችን መጠቀሚያ ለማድረግ ጥረት አድርጓል። እርምጃው ከተወሰደ ግን ቆይቷል።

ከፈተና ጋር ተያይዞ ግልጽ ነው አንድ የትህምህርት ተቋም እውቅና ፍቃድ ኖሮት ወደ ፈተና ስርዓት ሲገባ ኮድ ይሰጠዋል ይህ የትምህርት ተቋም የእውቅና ፍቃዱ ቀድሞ የተነሳ ስለሆነ ኮድ ሊሰጠው አይችልም።

ኮድ ባልተሰጠበት ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ይፈተኑ ቢባል ፈተናቸው ሊታረም አይችልም።

ስለዚህ ኮድ ወዳለው ትምህርት ተቋም ወስደን ነው የምናስፈትናቸው።  " ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" በተጣሉ ተተኳሾች እና ፈንጂዎች 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል " - የቆላ ተምቤን ወረዳ

በትግራይ ማእከላይ ዞን የቆላ ተምቤን ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ተተካሾች እና ፍንጂዎች ይገኛሉ።

እጅግ አስከፊውና ደም አፋሳሹን ጦርነት ተከትሎ በአከባቢው የተቀበሩትና የተጣሉት ተተካሾችና ፈንጂዎች በበርካታ ሰዎችና እንስሳት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ በማድረስ ላይ እንደሆኑ ተነግሯል።

በወረዳው በተቀበሩትና በተጣሉት ተተኳሾችና ፈንጂዎች እስካሁን 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል።

አሁን ላይ አደጋውን ለመቀነስ ነዊና ጉያ  በተባሉ የቀበሌ አስተዳደሮች በባለሙያዎች የተደገፈ የማምከን ስራ መጀመሩን የወረዳው አስተዳደር አሳውዋል።

ህዝቡ በአከባቢው ከተለመደው የተለየ ብረት ሲያገኝ ከመንካት እና ከመቀጥቀጥ ተቆጥቦ ለጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ማሳሰቢያ ተለልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ነው ያገኘው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
' 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ '

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር #ዕዳ እንዳለበት ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው በህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይልን የ9 ወራት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት ነው።

የተቋሙ የብድር ጫና በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ  ባቀረቡት ሪፖርት ፤ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር እንዳለበት ተናግረዋል።

የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አስረድተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ ካለበት የዕዳ ጫና ለመውጣት ፦
#የታሪፍ_ማሻሻያዎችን በማድረግ
የውጭ የሃይል ሽያጭ አቅሞችን በማጠናከር
የውስጥ ገቢን በመሳደግ ለዕዳ ቅነሳው ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስቧል።

ኢ/ር አሸብር ፥ በቀጣይ ከጅቡቲ፣ ከኬኒያ እና ከሱዳን በተጨማሪ ለታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የዕዳ ጫናውን ለመቀነስ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በዕቅድ መያዙን  ተናግረዋል።

#HouseofPeoplesRepresentatives #CapitalNewspaper

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

💥በቀን 12 ብር ምን ያደርጋሉ?

አንድ ስኒ ቡና ይገዛሉ?
ፓርኪንግ ይከፍላሉ?
የቀንዎን ትራንስፖርትስ ይችላል?

ለዲኤስቲቪ ግን ይበቃዎታል! 🥳🥳

ተወዳጁን ሀገርኛ ድራማዎችን እና መዝናኛዎችን የምናገኝበት አቦል ቲቪ ከሜዳ ወደ ጎጆ ፓኬጅ መጣ!

ምን ይሄ ብቻ ኒክ ጁኒየር በአማርኛ፥ ዚ-ዓለም የተከታታይ ድራማ ቻናል እና ሌሎችም የዲኤስቲቪ ቻናሎችን በጎጆ ፓኬጅ ያገኛሉ።

አሁን ጎጇችን ሞላ፤ በወር 350... በቀን 12ብር ብቻ

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #AbolTV #NickJrAmh #TraceMuzika #Zeeዓለም
“ ... 1,500 ካ/ሜ ግሪን ኤርያውን 12 ወጣቶች መጥተው አጠሩት ” - ቅሬታ አቅራቢዎች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አካባቢ በሚገኘውና በ1979 ዓ/ም ለ “ አዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ቤት ሥራ ማኀበር ” ተሰጥቶ ነበር የተባለ 1500 ካ/ሜ መሬት የመከነ ማስረጃ ባቀረቡ ሰዎች መታጠሩን ማኅበሩ ገለጸ።

ቦታው በ1979 ዓ/ም ለማኀበሩ ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ “ የአዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ግሪን ኤሪያ ” እየተባለ ይጠራ እንደነበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

“ በፊት የአዲስ አበባ 100ኛ ዓመት ግሪን ኤሪያ ነበረ። በኋላ ‘ የአካባቢው ማህበረሰብ ይጠቀምበት ’ ተባለ ” ብሏል።

በዚህም የማኀበሩ አባላት በግንብ እንዳሳጠሩት ፣ ጥበቃም ቀጥረው ጥበቃ ያስደርጉለት እንደነበር ፣ ቦታው ላይ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት የሚመለከታቸውን አካላት ቢጠየቅም ፣ “ ለጊዜው ቆዩ ስንወስንላችሁ ትሰራላችሁ ” ተብለው እየጠበቁ እንደነበር ገልጿል።

ይህ በሆነበት ግን ወጣቶች መጥተው ቦታውን እንዳጠሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።

ማኀበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ “ ጥበቃውም ሰሞኑን ጥሎ ሄደ አስገድደውት ይሁን ተስማምቶ ይሁን አናውቅም። ልክ እሱ እንደሄደ 1,500 ካሬ ግሪን ኤሪያውን 12 ወጣቶች መጥተው አጠሩት ” ብሏል።

ማኅበሩ እጄ ላይ አሉ ያላቸውን ዶክመንቶችም ልኳል።

“ ‘አረንጓዴው እንዳይሸፈን’ ብለውን እኛ ባጭሩ በግንብ አጥረን ከላይ ብረት አድርገንበት ነበር ” ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች ፥ “ አሁን ግን እነርሱ ሙሉ ለሙሉ #በቆርቆሮ ግጥም አድርገው አጠሩት ” ብለዋል።

አክለው “  2 ጊዜ ፎርጂድ ካርታ አሰርተውበት የማኀበሩ ተጠሪዎች ሂደው አምክነውታል በ2011 እና በ2014 ዓ/ም ” ሲሉ አስታውሰው፣ ቦታውን ያጠሩት ወጣቶች ለደንቦች ያቀረቡት በ2011 ዓ/ም ማኀበሩ ያመከነውን ሰነድ እንደሆነ፣ ማኀበሩ ከቦታው የምስክር ወረቀት ሁሉ እንዳለው አስረድተዋል።

ግሪን ኤሪያው በማኀበሩ አማካኝነት ፦
- መብራትና ውሃ እንደገባለት፣
- ወይራ፣ ፅድ የመሳሰሉ አገር በቀል እፅዋቶች እንደለሙበት፣
- ህጻናትም በየወቅቱ እየገቡ #የሚናፈሱበት አረጓዴ መናፈሻ እንደሆነ የገለጹት ቅሬታ አቅሬቢዎቹ፣ “ ይሄ እያለ ነው ሰዎቹ መጥተው ያጠሩት ” ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ጉዳዩን መንግሥት ትኩረት እንዲሰጠው የጠየቁ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩኩ ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ ለማግኘት ወደ ክፍለ ከተማው ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ሰሞኑን በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ3 ሺህ 80 የሺሻ ዕቃ እና 80 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ ተይዞ መወገዱን ገልጿል።

በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ከተገኙ ቤቶች ነው ይሄ የተያዘው።

ፖሊስ በሰጠው መረጃ በድንገተኛ ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል ፦
- መኖሪያ ቤቶች
-  ፔንሲዮኖች፣
- ማሳጅ ቤቶች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል፡፡

ይህ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይም በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያለው አዋኪ ድርጊት እጅግ ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።

በተለይ ተማሪዎች፣ ህፃናት፣ የወለዱ እናቶች፣ ቀን ስራ ደክመው የሚገቡ በርካታ ዜጎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ብዙ አዋኪ ድርጊቶች በመኖራቸው ትኩረትን ያሻል።

የግል መኖሪያ ቤቶች ለሺሻ ማጬሻ ፣ ለመጠጥ መጠቻ፣ ለሲጋራ ማጬሻ እየዋሉ ማህበረሰቡ እንደሚታወክ ተጠቁሟል።

ምሽት ላይም ቢሆን ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣው ድምጽ ማህበረሰቡን ሰላም የሚነሳ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠይቋል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

" የስፖርት ውርርድ / የቤቲንግ ቤቶች #ሊታገዱ ይገባል " ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለተ/ም/ቤት አቅርቦ ነበር።

በዚህ ወቅት ፤ " የወጣቶች ሱሰኝነት በሀገር ደረጃ እየተባባሰ መጥቷል ፤ በተለይ አሉታዊ መጤ ልማዶች እና አደንዛዥ ዕጽ እንደ ሀገር እየተስፋፋ መጥቷል " ሲል ገልጿል።

ይህም ብዙ ወጣቶችን እያሳጣን ነው ሲል አስረድቷል።

ወጣቶች ሰብዕና ግንባታ ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ ከሚገኘው አንዱ የስፖርት ውርርድ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ " የስፖርት ውርርድ ለሀገሪቱ ከሚያስገባው ገቢ አኳያ ብቻ መታየት የለበትም " ብሏል።

" ' ስፖርት ቤቲንግ ' ላይ ያሉት፣ ካሁን በፊት የወጡት መመሪያዎች፣ ደንቦች፤ ጥናትን መሰረት አድርገው ሊታገዱ ይገባል " ሲል ገልጿል።

ፓርላማውም በዚህ ረገድ እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል።

" ገቢ አንድ ነገር ነው። ሀገር ገቢ ማግኘት አለባት " ያለው መ/ቤቱ ነገር ግን ፦

➡️ በወጣቶቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያስከተለ ስለሆነ፣

➡️ ብዙ ወጣቶች እያሳጣ ስለሆነ፣

➡️ ብዙ ቤተሰብም #እየፈረሰ ስለሆነ ሊታገድ እንደሚገባ ገልጿል።

በህ/ተ/ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ " ብሔራዊ ሎተሪ ከገቢ ጋር አይቶታል። በዚህም በኩል ደግሞ ሌላ ችግር እየፈጠረ ነው " ያለ ሲሆን " ተማሪዎች ዩኒፎርማቸውን እያወለቁ የስፖርት ውርርድ ቤት ይገባሉ። ስለዚህ መቼ ያጥኑ። አእምሮአቸው ሊጎዳ ስለሚችል ጥንቃቄ ተደርጎ መሰራት አለበት " ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስፖርት ውርርድ ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በቅርቡ የወሰደውን እርምጃ " ጥሩ ስራ " ሲል አወድሷል።

በሌሎች አካባቢዎች በተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ሲል ጠቁሟል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ፤ ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ያለውን የወጣቶች ሁኔታ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ እንዲያየው እና ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ መክሯል።

ከዚህ ቀደምም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ' #ቁማር ' ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ እንዲታገድ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን ፤ " ቤቲንግ " ' #ጨዋታ ' እንጂ ' ቁማር ' ነው ብሎ እንደማያምን ገልጾ ነበር። ቤቲንግ አትራፊና ብዙ ወጣቶች ስራ እንዲያገኙ ያደረገና በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ መሆኑንም አስረድቶ ነበር።

በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎች ወጥተውለት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ሲል ነበር የመለሰው።

@tikvahethiopia
#ATTENTION🔔

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ወላይታ ዞን ባሉ ወረዳዎች ያሉ መምህራን ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ስራ እንዳቆሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ፦

" ... ጉዳዩ ስር የሰደደና የቆየ ነው። አሁን ላይ ' በተራበ አንጀታችን መስራት አልችልም ' በሚል መምህራኑ ስራ አቁመዋል።

በፐርሰንት እየተቆራረጠ የሚከፈላቸው ደመወዝ በዚህ ወር ለ16 ቀን ዘግይቷል።

ከደመወዝ በላይ የሌሎች ጥቅማጥቅሞች ፥ የወዝፍ ደሞዝ ፣ ከደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደሞዝ ጭማሪና የእርከን ጭማሪ መቅረት ፈተና ሆኖባቸዋል። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን ይልካል።

ከዚህ ቀደም ወላይታ ዞን ስለሚገኙ መምህራን ቅሬታ የቀረበ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/86484?single

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
📱 ባይትዳንስ ' #ቲክቶክ ' ን #ለአሜሪካ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ #ቢዘጋው እንደሚመርጥ ሮይተርስ ለኩባንያው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ።

ኩባንያው በ' ቲክቶክ ' ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል።

አሁን ' ቲክቶክ ' የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር እንደሚቆጠርና በዚህ አልጎሪዝም መተገበሪያውን የመሸጥ እድሉ እጅግ ሲበዛ አነስተኛ እንደሆነ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል።

በዚህም ፤ ለአሜሪካ ገዢ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ እስከወዲያኛው ድረስ መዝጋትን እንደሚመርጥ ተጠቁሟል።

አሜሪካ ' ቲክቶክ ' እንዲሸጥ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ገደብ አስቀምጣለች ካልሆነ ግን እስከ ወዲያኛው እንዲታገድ ሕግ አጽድቃለች።

በርካታ ጉዳዩን የሚከታተሉ የዘርፉ ሰዎች አሁን ባለው የአሜሪካ አቋም 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ' ቲክቶክ ' እስከ ወዲያኛው ድረስ የመወገዱ ነገር እውን መሆኑ አይቀርም ብለዋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የወራቤ - ቦዠባር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህ መንገድ ግንባታ 2.77 ቢሊዮን ብር በጀት የተመደበለት ሲሆን 41.3 ኪ.ሜ ርዝመት አለው። የተቀመጠው የሙሉ በሙሉ ግንባታ የማጠናቀቀያ ጊዜ ሁለት ዓመት ነው ተብሏል። የአስፓልት መንገዱን የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ እየሰራ ያለው የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ በተያዘለት በጀት ፣ ጊዜ እና የጥራት ደረጃ…
#Update

የመንገዱ ፕሮጀክት እንዴት እየሄደ ነው ?

የወራቤ ቦጆበር አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በፍጥነት እየተከናወነ አይደለም።

ይህ መንገድ የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት በአሁኑ ሰዓት እየገነባቸው ከሚገኙ የአስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው።

የመንገድ ስራው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የሶስተኛ ወገን ችግሮች እና የአየር ሁኔታው ፈተና እንደሆኑ ተገልጿል።

ድርጅቱ መንገዱን ቶሎ ሰርቶ ለማስረከብ ሙሉ ዝግጅት አድርጎ የገባ ቢሆንም የሶስተኛ ወገን ችግሮች ለፍጥነቱ እንቅፋት እንደሆኑ አመልክቷል።

ምንም እንኳን የሶስተኛ ወገን ችግሮችን መፍታት በዋናነት የተቋራጩ ተግባር ባይሆንም ከባለደርሻ አካላት ጋር በመተባበር  የተወስኑ አካባቢዎችን ችግሮች በመፍታት ስራው ማስቀጠል ቢቻልም አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።

እነዚህ የሶስተኛ ወገን ችግሮች ምን እንደሆኑ በዝርዝር አልተገለጸም።

ከዚህ በተጨማሪ መንገዱ የሚገነባበት አካባቢ የበልግ ዝናብ የሚያገኝ መሆኑ ለመንገድ ስራ ምቹ አይደለም ተብሏል።

የመንገዱን ጥራት አስጠብቆ ለመስራት ዝናብ የሌለባቸውን ቀናት እየጠበቁ መስራት የግድ በመሆኑ በፍጥነት ፕሮጀክቱ እንዳይሄድ ማድረጉን አሳውቋል።

#AmharaRoadWorksEnterprise

@tikvahethiopia