TIKVAH-ETHIOPIA
1.37M subscribers
54.3K photos
1.34K videos
188 files
3.59K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን። የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል። የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ…
“ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ? ”

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ አካላት ላይ የሚወሰነው ፍርድ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ወንጀል ፈፃሚዎች ከስህተታቸው ተምረው እንዲታረሙና ድርጊቱ እንዲቆም በማስቻል ፋንታ “ አይዟችሁ በርቱ ” የሚል ይመስላል ፣ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ ? የሚሉ ትችት እና ጥያቄዎችን በተለይም ከሰሞኑን በበርካቶች ዘንድ ሲሰነዘር ተስተውለዋል።

በርካቶችን ካስቆጡ የወንጀል ቅጣቶች መካከል አንዱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ዓርብ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ/ም አንድ የ17 ዓመት ተማሪ ፣ ምንም ነፍስ ያላወቀች የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ ደፈሩን ተከትሎ የወረዳው ፍ/ቤት መጋቢት 9/ 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በወንጀል ፈጻሚው ላይ የ6 ወራት እስራት የፍርድ ቅጣት ማስተላለፉ ተጠቃሽ ነው።

እንዲሁም፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ኬሌ 01 ቀበሌ መጋቢት 2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ተማሪ ፣ የ13 ዓመት ታዳጊ ፣ የአብራካቸው ክፋይ የሆነች #ልጃቸውን አስገድደው ደፈሩ የተባሉትን የ42 ዓመት አባት ላይ የዞኑ ፍርድ ቤት የ10 ዓመታት የእስራት ቅጣት መወሰኑም ሌላኛው ትችት ያጫረ የፍርድ ውሳኔ መሆኑ አይዘነጋም።

ሌሎች ተያያዥ በርካታ ወንጀሎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ አብነት ከላይ በተጠቀሱት የአስገድዶ መድፈር ረገድ በተላለፉ የወንጀል ቅጣት ውሳኔዎች እና የቤንሻንጉል ወንበራውን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ወንጀል የተሰጠውን ቅጣት በተመለከተ ፦
➡️ ምን አይነት ቀልድ ነው ?
➡️ ይሄ ውሳኔ አሁን ቅጣት ነው ?
➡️ እስከ መቼ ነው በሰው ቁስል የሚቀለደው ? በሚል ብዙኅን ጥያቄዎች አንስተዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን #ልጃቸውን ደፈሩ የተባሉትን አባት የቅርብ ጊዜ የፍርድ ቤት ቤት ቅጣት ውሳኔ በተመለከተ፣ “ 10 ዓመት እስራት ብቻ ?፣ ውሳኔው ድርጊቱ እንዲበረታታ እንዲያደርግ ታስቦ የተሰጠ ነው እንዴ ? ” የሚሉ ጥያቄዎችን አጭሯል ተስተውሏል።

በተያያዘ ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአምስት ዓመታት በታች የሆኑ ወንዶችን ሁሉ የደፈሩ ወንጀለኞች ከአምስት ዓመታት በታች በሆኑ የእስራት፣ ከ2,000 ብር ያልበለጡ ቅጣቶች ሲወሰኑባቸው መስተዋሉ በርካቶችን “ ፍትህ የት ናት ? ” ያስባሉ ጉዳዮች ናቸው። 

በወቅቱ አስተያዬታቸውን የሰጡ ምሁራንም፣ ወንድ ልጅ ላይ “ እንዲህ አይነት ወንጀል መፈጸም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሳይሆን፣  የግብረሰዶም ድርጊት ተፈጸመ ነው መባል ያለበት ” ሲሉ ተስተውለው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከሰሞኑ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የአምስት ዓመቷን ህፃን አስገድዶ ደፈረ በተባለው የ17 ዓመት ወጣት የ6 ወራት የእስራት ቅጣት መወሰኑ፣ በአጠቃላይ በዘርፉ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ለሚሰጠውን “ የተለሳለሰ ቅጣት ” በተመለከተ ሕጉን በድጋሚ ማጤን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጽያ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ? ” የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ አካላት ላይ የሚወሰነው ፍርድ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ወንጀል ፈፃሚዎች ከስህተታቸው ተምረው እንዲታረሙና ድርጊቱ እንዲቆም በማስቻል ፋንታ “ አይዟችሁ በርቱ ” የሚል ይመስላል ፣ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ ? የሚሉ ትችት እና ጥያቄዎችን በተለይም ከሰሞኑን በበርካቶች ዘንድ ሲሰነዘር ተስተውለዋል። በርካቶችን ካስቆጡ የወንጀል ቅጣቶች መካከል አንዱ…
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር (ኢሕባማ) በፆታዊ ጥቃት ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲወሰን የሚስተዋለውን ፍፁም ያልተመጣጠነ ቅጣት በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማኅበሩ የቅጣት ዋነኛ ዓላማ ወንጀል ፈጻሚዎች ተጸጽተው እንዲማሩ ፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጊት ላለመፈጸም ትምህርት እንዲወስዱ ለማድረግ ቢሆንም አሁን እየሆነ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው እንደሆነ ገልጿል።

የማኀበሩ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ቤተልሄም ደጉ ምን አሉ ?

“ አሁን አሁን የምንሰማቸው ውሳኔዎች ይበልጥ እንዲያውም የልብ ልብ የሚሰጡና ‘ምንድነው ይህን ያክል ጊዜ ነው ብታሰር’ የሚሉ አይነት አስተሳሰቦችን በሰዎች ላይ Create የሚያደርጉ ናቸው ” ብለዋል።

ሰሞንኛውን የወምበራ ወረዳ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ6 ወራት የቅጣት ውሳኔ በተመለከተ በሰጡት ቃል ፦

“ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ዝቅተኛው ተብሎ የሚቀመጠው እንኳ 5 ዓመታት ነው።

በልዩ ሁኔታዎች ተብሎ የተቀመጠው እንኳ፣ የወንጀለኛ መቅጫ 620ንና ከዚያ ቀጥሎ ያሉትን ብናይ ከ3 ዓመታት በታች የሚያስወስን የወንጀል ጥቃት የለም።

ከ6 ወራት እስከ 4 ዓመታት የሚወሰኑ ቅጣቶች አሉ። ለችግሩ ዋነኛ ክፍተቱ ምን ላይ እንደሆነ የሚያመላክት ጥናት ግን ገና የለም።

የማስረጃ ሕግ አለመኖር፣ ነገር ግን የማስረዳት ሸክም ጋር ተያይዞ ያሉት ከፍተኛ የሆኑ የማስረጃ ስታንዳሮዶች ራሱን በቻለ መልኩ ፆታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች Contribute እያደርጉ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ክፍተት ያለው የቱ ጋር ነው ? ከዳኞች መረዳትና ግንዛቤ ነው ?፣ ከሕግ ማዕቀፎች ነው ? የሚለውን ለመለየት ጥናት ያስፈልጋል።

ቅጣት በሚወሰንበት ጊዜ ዳኞች ሚያስቀምጡት የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎችና ደንቦች አሉ። እዚህን መመሪያዎችና ደንቦችን በደንብ መቃኘት ያስፈልጋል " ብለዋል።

... የ3 ዓመቷን ህፃን ላይ በፈፀመው ወንጀል ተላለፈ የተባለው የ6 ወራት የእስራት ቅጣትን በተመለከተ በመነሻው ምናልባት ጉድለት ሲኖር ፣ የማስረዳት ሸክምን ዐቃቢ ሕግ በአግባቡ ሳይወጣ ሲቀር ዝቅተኛ ቅጣት ሊወሰን ይችላል። ግን ጨቅላ ህፃን የደፈረን ሰው 6 ወራት ሊያስወስን የሚችል የህግ መነሻና መንደርደሪያ የለም።

ቅጣቱ የ3፣ 4 ዓመታት እንኳ ቢሆን ዝቅተኛው መንደርደሪያ ላይ አረፈ ብለን፣ በቂ አይደለም ልንል እንችላለን። ይሄ 6 ወራት የሚለው ግን ቅጣት ነው ወይ ? ራሱ፣ የሚለውን ጥያቄ አብሮ ያስነሳል። ስለዚህ የሕግ ማዕቀፋችን እንደገና ሊታይ ይገባል ” ብለዋል።

መፍትሄውን ምንድነው ?

“ ሁላችንም በዘርፉ ያለን ተቋማት ሁሉ የሕግ ማዕቀፎችን Re evaluate ማድረግና ክፍተቶች ካሉ ደግሞ መንግሥት እንዲያስተካክል የAdvocacy ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ” ብለዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድሬዳዋ❤️

የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው።

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ በከባድ ዝናብ ውስጥ ሆነው ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶች የማበረታቻ የብር ሽልማት ተበረከተላቸው።

ሽልማቱን ያበረከቱት የትራፊክ ፖሊስ አባላቱን ተግባር በማህበራዊ ሚድያ የተመለከቱ የድሬዳዋ ወጣቶች ናቸው።

የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ የትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ ሲያከናውኑት የነበረው ስራ ለሌሎችም ትምህርት ሆኖ ያለፈ ነው። #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
ዒድ ኤክስፖ ትኬትና ሸመታዎን በቴሌብር ያድርጉ!

በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ተዘጋጀው ዒድ ኤክስፖ ጎራ ካሉ የመግቢያ ትኬቱን በቴሌብር http://onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ሲቆርጡና ሲገበያዩ እስከ ብር 2500 ላለው የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት 10% ተመላሽ ያገኛሉ።
#ደመወዝ

" ላለፉት ወራት በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ስንፈተን ቆይተናል " ያሉ የዎላይታ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች " ስራችንን በአግባቡ ለመስራት እንችል ዘንድ መንግሥት በአግባቡ ደሞዝ ሊከፍለን ይገባል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸው ከሰጡት የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ በተለይም #መምህራን እና #የህክምና_ባለሙያዎች ይገኙበታል።

" ጉዳዩን በተዋረድ ለሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ለወረዳ አመራሮች ካሳወቅን ቆየን " የሚሉት እነዚህ ሰራተኞች " ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም ወደ ክልሉ መንግስት መቀመጫ ወደሆነችዉ ወላይታ ሶዶ ከተማ ብናቀናም ሰሚ አላገኘንም " ብለዋል።

በተለይ ይህ የደሞዝ አለመክፈል እና መቆራረጥ ችግር የተከሰተባቸው በዎላይታ ዞን ስር የሚገኙት የኪንዶ ኮይሻ ፣ የሆብቻ ፣ አባላ ፣ አባያ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ፑላሳ ፣ ዳሞት ወይዴ ፣ ኪንዶ ዲዳዬ እና አካባቢዉ ወረዳና ቀበሊያት እንደሆኑ ተገልጿል።

በሆብቻ ወረዳ የሚገኘው የሆብቻ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስራ ካቆመ መሰነባበቱንና ተማሪዎች ቤታቸዉ እየዋሉ መሆኑን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ መምህራን " መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ወስዶ ወደስራችን ይመልሰን " ብለዋል።

ከዚህዉ ጋር ተያይዞ የከልሉን መንግስት ሀሳብ በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አዜብ ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸዉ በመግለጽ ዝርዝር ሀሳብ ከመሰንዘር ተቆጥበዋል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተልን እናሳውቃችኃለን።

መረጃዉን አዘጋጅቶ የላከዉ የሀዋሳው ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት ያላቸዉን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ብሏል።

የወጣቱ ህይዎት ይቀጠፍ ዘንድ ምክኒያት የሆኑ ጉዳዮችን ለማወቅ የስልክ ልውውጦችን ከመመርመር በተጨማሪ በዙሪያው የነበሩ አካላትንም በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነማን ተያዙ ? የምርመራዉ አካሄድስ ምን ይመስላል ? ሲል ለአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የለሆኑት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ጥያቄ አቅርቧል።

" የተጫዋቹ መሞት በተሰማበት ወቅት አጠራጣሪ ጉዳዮች ስለነበሩ ፖሊስ የምርመራ እንቅስቃሴ ጀምሯል " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም " በዚህ ወቅት ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " ብለዋል።

በሶሻል ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለዉን የእናቱ እና ባለቤቱ መያዝ በተመለከተ ላነሳንላቸዉ ጥያቄ " አሁን ላይ ከእህት እና ወንድሙ ዉጭ የተያዘ አካል የለም በማለት ወደፊት ግን ከተያዙት የሚለቀቅ ካልተያዙት ደግሞ የሚያዝ ሊኖር ይችላል " ብለዋል።

" አሁን ላይ ምርመራዉን በፍጥነትና በጥንቃቄ እያካሄድን ነው " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ውጤቱን ለመላ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማድረስ ማሰባቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

“ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን። 2.8 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ አልተለቀቁም ” - እምባ የሚተናኘቃቸው የታጋች እህት

መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ባቱ (ዝዋይ) እየተጓዙ የነበሩና በ “ ሸኔ ” ታጣቂዎች ታገቱ የተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ሁሉም እንዲለቀቁ 2.8 ሚሊዮን ብር ተዋጥቶ ቢላክም 3ቱ ተለቀው 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ የታጋች ቤተሰብ በእንባ እየተናነቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል “ ከአቅሜ በላይ ” ነው እንዳላቸውና በከፋ ጭንቀት ውስጥ እንደሆኑም እንባ አስረትድተዋል።

አንዲት የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ “ ከታጋቾቹ ሥም ዝርዝር የወንድሜም ስም ዝርዝር እንደነበረ ከእገታ የተለቀቁት ነግረውኛል። ብር አምጡ ብለው የመብራት ኃይል ሠራተኞች ሁሉ አዋጥተው 2.8 ሚሉዮን ብር ለ6ቱም ተብሎ ከተላከ በኃላ 3ቱ የኢሬቻ ዕለት ተለቀቁ፣ 3ቱ ግን አልተለቀቁም ” ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል የስራ ኃላፊዎችን ሲጠይቁ “ ከአቅማችን በላይ ነው ” ብለው “ ለፌደራል ፓሊስ አስተላልፈናል ” እንዳሏቸው፣ የፌደራል ፓሊስም አጥጋቢ የሆነ ምላሽ እንዳልሰጣቸው ጠቁመዋል።

በቤተሰብና ወዳጀ ዘመድ በኩል ለታጋቾች ተብሎ 300 ሺህ ብር እንደተላከ፣ ወንድማቸው፣ ሹፌሩ እና አንድ ሌላ ሠራተኛን ጨምሮ ከታገቱ 6 ወራት እንዳስቆጠሩ፣ ቤተሰብም በከፋ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።

“ ወንድሜ ሁለት ልጆች አሉት ፣ ሚስቱ የስኳር ታማሚ ናት። ሹፌሩም 2 ልጆች አሉት፣ ሚስቱ ሞታለች ” ያሉት የታገቹ እህት፣ “መለቀቅ እንኳ የማይቻል ከሆነና በሕይወት ካለ፣ በስልክ እንኳን ‘አለሁ በሕይወት’ እንዲለን ድምጹን ያሰሙን " ሲሉ ተማጽነዋል።

ምንም እንኳን ለማስለቀቂያ 2.8 ሚሊዮን ብር ቢከፈልም ከታገቱት 6 ሰራተኞች ውስጥ 3ቱ ሲለቀቁ 3ቱ ሠራተኞች ግን ከእገታ ያልተለቀቁ ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን አሁን 6 ወራት እንደሞላቸው የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በሀዘን ስሜት ሆነውም መፍትሄ የሚሰጣቸው አካል ካለ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የጠየቅን ሲሆን ምላሹን እናቀርባለን። #TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

መስረከም 19/2016 ዓ/ም ለስራ በወጡበት በታጣቂዎች ከታገቱ 6 የኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኞች ሁሉም እንዲለቀቁ 2.8 ሚሊዮን ብር ቢከፈልም 3ቱ ተለቀው የቀሩት 3ቱ እስካሁን ያልተለቀቁ ሲሆን ያሉበት ሁኔታም አይታወቅም።

የታጋች ቤተሰቦች ዛሬም በሀዘን ውስጥ ሆነው የሚወዷቸውን ሰዎች በተስፋ እየተጠባበቁ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል " እኔ ከአቅሜ በላይ ነው " እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይና አጠቃላይ ስላለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምን ይላል ? የሚለውን ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምን ምላሽ ሰጠ ?

Q. በታጋች ቤተሰብ በኩል ተቋማችሁ ይህ ጉዳይ “ ከአቅማችን በላይ ነው ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ነው የገለጹት እውነት ነው ? ምን ያክል ጥረት አድርጋችኋል ? ከአጋቾቹ በቅርቡ ያገኛችሁት ምላሽስ ምን ነበር ? 3ቱ ታጋቾች ሲለቀቁ 3ቱ የዘገዩበት ምክንያት ምንድን ነው ? ተስፋ አለ ?

የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ፦

“ ያው እኛ ወታደር አናሰማራም ልክ ነው ከአቅም በላይ ነው።

እኛ ልናደርግ የምንችለው አካባቢው ላይ ካሉ የአገር ሽማግሌዎች ጋር በመነጋገር ሰዎቹ ያለምንም ጉዳት ከቤተሰቦቻቸው መቀላቀል የሚችሉበትን ሁኔታ እንዲፈጠር መስራት ነው።

ያንን ደግሞ እገታው ከተፈጸመበት ቀን የመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ያልተቋረጠ ጥረት ሲደረግ ነበር። ይህንንም ደግሞ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር ያውቃሉ።

እኛእንደ ተቋም ባለን አቅም በሙሉ ሠራተኞቻችን ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ጥረት አድርገናል። ይሄ ጥረት አሁንም ቢሆን በሌላ በተሻለ መንገድ ሊፈታ የሚችል ከሆነ ያንን ከመሞከር ወደ ኋላ አንልም። ”

Q. 3ቱ ታጋቾች ለምን ሳይለቀቁ ዘገዩ ተስፋስ አለ ?

የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ፦

“ ይህንን በትክክል ምክንያቱን የሚያውቁት ያገቱት ሰዎች ናቸው። ‘አጣርተን እንለቃቸዋለን’ የሚል ነበር በወቅቱ የተሰጠው ምላሽ እኛም አጣርተው ይለቃሉ የሚል እምነት ይዘን ነበር የቆየነው። ተስፋ አለው የለውም ለማለት ያስቸግራል። ”

Q. ዞሮ ዞሮ አጋቾቹ ታጋቾቹን ለመልቀቅ የጠየቁት ሁሉም ገንዘብ ተሰጥቷቸው ነው ሳይለቋቸው የቀሩት ? ያለዎት መልዕክት ምንድን ነው ?

የተቋሙ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ፦

“ ሠራተኞቻችን ግን ‘ነግ በእኔ’ ብለው ያዋጡ አሉ። እንደ ተቋም ግን ያንን ልናደርግ የምንችልበት ከተያዘ በጀት ውስጥ ገንዘብ ልታወጣ የምትችልበት አሰራር ስሌለ ያንን አላደረግንም።

የጠየቁትን ያክል አልተሰጣቸውም። ሠራተኛው ማወመጣት የሚችለውን ያክል ነው ማዋጣት የሚችለው።

ሠራተኞቹ የአገር ልማት ሥራ ላይ ሲደክሙ ነው ይሄ ችግር የደረሰባቸው። ግለሰቦቹን በማገት የሚመጣ ለውጥ የለም። በተጀመረው መንገድ በሰላም እንዲለቋቸው የሚል ጥሪ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። ”

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
#GlobalBankEthiopia

ማንችስተር ሲቲ ወይስ አርሰናል

በመገመት የሚያሸልም ጥያቄ በኢንስታግራም ገጻችን (https://bit.ly/3NiRHOn ) ብቻ ግምትዎን ይስጡ!

በፕሪሚየር ሊጉ በጉጉት ከሚጠበቁት ጨዋታዎች መካከል አንዱ የፊታችን እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በማንችስተር ሲቲ እና በአርሰናል መካከል ይካሄዳል፡፡ ጨዋታውን በትክክል ለሚገምቱ 3 የኢንስታግራም (https://bit.ly/3NiRHOn) ተከታዮቻችን ለእያንዳንዳቸው የ300 ብር የካርድ ሽልማት አዘጋጅተናል፡፡

1. የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የኢንስታግራም ገጽን https://bit.ly/3NiRHOn ገፅ መከተልዎን አይዘንጉ!
2. ትክክለኛ መላሾች ከ 3 በላይ ከሆኑ አሸናፊዎቹን የምንለየው በዕጣ ይሆናል፡፡

መልካም ዕድል!!
ግሎባል ባንክ