TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ኑም” ሆነ “አትምጡ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ " ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል በሰጡት ቃል፣ “ ዩኒቨርስቲው አሁን አልጠራም ማለትም አይችልም (ምክንያቱም አልጠራም ቢል ከትምህርት ሚኒስቴር ግዳጅ አለበት)። ጠርቶ እንዳያስገባ ደግሞ አካባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች እያደረጉ ያሉትን ነገር በዓይናችን እያዬን ነው ” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

ይህን ተከትሎም፣ የተወሰኑ የተማሪዎቹን ቅሬታና ሀሳብ የወከሉ ተማሪዎች ሰሞኑን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል ሂደው ነበር።

በዚህም ወቅት በ2016 የትምህርት ዘመን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው ስላልጠራ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ባለመሆኑ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንደገና እንዲመድባቸው ጠይቀዋል።

ይህ በተመለከት አንድ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ የጠየቅነው ጥያቄ ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድቡን ነበር። የሰጡን መልስ፣ መጀመሪያ ዩኒቨርሲቲው ‘መቀበል አልችልም፣ ካቅሜ በላይ ነው’ ማለት አለበት ” የሚል ነው ብሏል።

አክሎም ፣ “ ሲቀጥል ደግሞ የክልሉ መንግሥት ‘እነዚህ ልጆች ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ መመደብ አለባቸው’ ብሎ ደብዳቤ መፃፍ አለበት’ አሉን” ያለ ሲሆን ሌሎች ጥያቄውን በአካል ተገኝተን አቅርበናል ካሉት መካከል የሆኑት ሦስት ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር እንደሰጣቸው የተገለጸው ማብራሪያ እውነተኛነት ተጋርተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎቹ ትምህርት ሚኒስቴር ሰጠን ያሉትን ማሳሰቢያ በመጥቀስ፣ ዩኒቨርሲቲው  ለትምህርት ሚኒስቴር ያለው ምላሽ ምንድን ነው ? ሲል ከዚህ በፊት በተሰሩት ዘገባዎች ተማሪዎቹ ሲያነሷቸው ለነበሩት ቅሬታዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ለነበሩ አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል ጥያቄ አቅርቧል።

ጥያቄው የቀረበላቸው አካል በሰጡት አጭር የጽሑፍ ምላሽ፣ “ ከዓርብ ጀምሮ ሁሉም ነገር ተዘግቷል፣  ከተማሪዎቹ ጋር በተያያዘም ከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቋል። ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን እንዴት መጥራት ይችላል? ” ብለዋል።

ጥያቄውን ባቀረብነው መሠረት እንዲብራራ የተፈለገው ጉዳይ ዩኒቨርሲቲው ለምን ተማሪዎችን አይቀበልም ? ሳይሆን ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በድጋሚ እንዲመደቡ ይመቻችላቸው ዘንድ ለምን ተማሪዎቹን አልቀበልም በማለት ለትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ አይሰጥም የሚል በመሆኑ ቀጥተኛ ምላሽ እንዲሰጡ በድጋሚ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

በሰጡት ምላሽም፣ “ አልጠራም ማለት አይችልም። ከዛ ይልቅ አንፃራዊ ሰላም ሲኖር አስገብቶ በ45 ቀን 1 Semister አስተምሮ ሊያካክሰው ይችላል እንጂ like ከአሁን በፊት በነበረው Corona and War እንዳደረገው” ነው ያሉት።

በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ክልሉ መስጠት እንዳለበት ገልጿል የተባለውን ማሳሰቢያ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳለው ለአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ቃላቸውን ማካተት አልተቻለም።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#DrAbrhamBelay

የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትግርኛ ቋንቋ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ምን አሉ ?

- ሁሉም ክልሎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ለትግራይ መልሶ ማቋቋም እንዲረዱ ፣ ትምህርት ጨምሮ ሁሉም የመንግስት አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ያስቻለው የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ነው ፡፡ ስለሆንም የፕሪቶሪያው የሰላም ውል አሁንም በቦታው ነው ያለው።

- ከጦርነቱ በፊት የነበረው #ግጭት_ቆስቋሽ ሁኔታ እና አካሄድ ወደ ጦርነት እንዳይሸጋገር ለማድረግ በፌደራሉ መንግስት ብዙ ጥረት ተደርጓል። ክልሉን ይመሩ የነበሩ ሰዎች ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። ጦርነቱ በትግራይ #አመራሮች እና #ኤሊቶች ገፋፊነት ከተጀመረ በኋላም ጦርነቱ ቆሞ ወደ ውይይት እንዲገባ ጥረት ተደርጓል። ጦርነቱ ውድመቱ እንዳይባባስ በድብቅም ይሁን በግላጭ በርካታ ውይይቶች ቢካሄዱም ሊሳካ አልቻለም።

- ጦርነቱ ተከትሎ በተለይም ከትግራይ ውጪ በመላ አገሪቱ ውስጥ የነበሩ ባለሃብቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና በሌላ ስራ የተሰማሩ ከስራ ውጪ የሆኑበት ፣ የታሰሩበት ፣ ንብረታቸው በርካሽ በመሸጥ እንዲሰደዱ የሚገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። ይህን እንዲቆም የፌደራል መንግስት ባደረገው ሰፊ ጥረት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ብዙ አላሳፈላጊ ነገሮች ማቆም ተችሏል።

- " በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከኔ በላይ ደስተኛ ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱ ስምምነቱ ብዙ ነገሮችን ከማባባስ ታድጓል፡፡ በፌደራል መንግሥት በኩል ስምምነቱን የፈረሙ የመንግስት ልኡካን ጀግኖች ናቸው፡፡ ምክንያቱ እንደ አገር ሊቀጥል የነበረው የስውና የንብረት ኪሳራ እንዲቆም ያደረጉ ናቸውና፡፡ "

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሁሉም የትግራይ ችግሮች ይፈታል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ስምምነቱ እንደ አገርና ትግራይ ብዙ ጥፋቶችን አስቁሞልናል፡፡ ስምምነቱ በመፈረሙ ምክንያት ተኩሶ ቆሞ ህዝቡ የሰላም አየር እንዲተነፍስ ሆኗል፡፡ ትልቁ የስምምነቱ ትሩፋት ይህ ነው።

- ከተወሰኑት በቀር በርካታው የትግራይ አከባቢዎች በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የአከካቢው አስተዳደር ተረክቧል። አሁን የተቀሩት አከራካሪ የሚባሉ ቦታዎች ናቸው። እነዚህም ተጨማሪ ግጭትና ደም መፋሰስ እንዳያስከትሉ በማሰብ በፌደራል መከላከያ ሰራዊት ስር እንዲቆዩ ተደርጓል።

- በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ውጤት ነው። ሁሉም ክልሎችና የፌደራል መንግስት ተቋማት ለክልሉ እንዲረዱ ፣ ትምህርት ጨምሮ ሁሉም የመንግስት አገልግሎት እንዲጀምሩ ያስቻለው የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ነው ፣  ስለሆንም የፕሪቶሪያው የሰላም ውል አሁንም በቦታው አለ።

- ስምምነቱ ከውል በላይ በሁለቱ ተወያዮች በኩል መተማመን እንዲፈጠረ ያበረከተው አስተዋፅኦ ስምምነቱ ከስምምነት በላይ መሆኑ አንድ አመላካች ተደርጎ ይወሰዳል።

- የእርሻ እና የኢንዳስትሪ ስራ እንዲነቃቃ የሚያግዝ የማሽነሪና የውጭ ምንዛሪ መሰጠቱ፣ የክልሉ የትምህርትና የጤና ተቋማት መልሶ የመገንባት ሂደት እንዲፋጠን ያስቻለው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውጤት ነው።

- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፌደራል መንግስት የሚመራውን የብልፅግና ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ ፓርቲዎች የተካተቱበት አሳታፊ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ቢደነግግም ፣ የፌደራል መንግስትና የብልፅግና ፓርቲ በሆደ ሰፊነትና ለሰላም ካለቸው ፍላጎት በሚመነጭ ክልሉ ሃላፊነት ወስዶ በፍጥነት ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲመሰረት እድል መሰጠቱ ሊመሰገንና እውቅና ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

- ከትግራይ ምዕራባዊና ደቡባዊ ዞኖች የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸው የመመለስ ጉዳይ መዘግየቱ አለ የሚባል ቢሆንም የተዘነጋ እንዳልሆነ ግን ሊሰመርበት ይገባል። የፌደራል መንግስት ፍላጎት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው። ይህ አቋሙም ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውል ማግስት ጥረት ከማድረግ ባሻገር 2015 ዓ.ም ክረምት እንዲመለስ ፍላጎት ነበር። ይሁን እንጂ በአፈፃፀም መዘግየት ምክንያት እስከ አሁን አልተሳካም።

- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ጉዳይ ዳግም ወደ ጦርነት በማይመልሰን መልኩ መፈፀም አለበት የሚለው አቅጣጫ ተቀምጦ የፌደራል መከላከያ ሰራዊት ጥያቄዎች በሚነሳባቸው አከባቢዎች ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸው እንዲፈቱ የማድረግ ስራ እየሰራ ነው። ቢሆንም ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ወደ አከባቢው አልተመለሰም የፌደራል መንግስት አቋም ህዝቡ ወደ ቄየው ተመልሶ የራሱ አመራሮች መርጦ በአመቺ ጊዜ በአከባቢው ህዝብ ውሳኔ እንዲካሄድ ማድረግ ነው።

- የፌደራል መንግስት አቋም ግልፅ ነው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ ፣ ራሳቸው በመረጡዋቸው መሪዎች ይተዳደሩ ፣ የህዝበ ውሳኔው ጉዳይ ጊዜ ሲደርስ የሚከናወን ይሆናል። አሁንም አቅጣጫው እንዲፈፀም በመጠባበቅ ላይ ነን ፣ ዳግም ግጭት ሳይፈጠር ከዚህ በላይ የተሻለ አማራጭ አለኝ የሚል ካለ ደግሞ የፌደራል መንግስት ለማዳመጥ ዝግጁ ነው። 

- የሻብዕያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መሬት ስለመውጣት ጉዳይ ምን አሉ ? 👉 "  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊት በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች የሻዕብያ ሃይል ገብቶ ነበር ፣ ከስምምነቱ በኋላ እንዲወጣ ተደርጓል ፣ አሁንም የተቀሩ ቦታዎች ካሉ ቦታዎቹ እና ቀበሌዎች ከፌደራልና ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ቡድን በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲሰጠው እየሰራን ነው ሁሉም ልክና መስመር ይይዛል። "

- በትግራይ የተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ በተለመደው አካሄድ ይፈታል የሚል እምነት የለንም ፣  እርግጥ ነው ወደ አከባቢው መድረስ ያለበት የሰብአዊ ድጋፍ እየደረሰ ነው ፣ እየተላከ ያለው ድጋፍ ወደ ተጠቃሚው መድረሱ ማረጋገጥ እንዳለ ሆኖ ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና የፈደራል የመንግስት ተቋማት እገዛ በማድረግ ችግሩ በመፍታት እንዲረባረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

- በትግራይ የተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ በዘላቂነት የሚፈታ ከፌደራልና ከክልሉ የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ይህንን ግብረ ሃይል የሚያቀርበው ጥያቄ ለመመለስ ሁሉም የትግራይ ተወላጆችና መላ ኢትዮጵያውያን ዝግጁ እንዲሆኑ ከወዲሁ ጥሪ እናቀርባለን።

ቃለ ምልልሱን ተከታትሎና ወደ አማርኛ ትርጉም መልሶ ያቀረበው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው፡፡

#TikvahMekelleFamily

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbrhamBelay የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትግርኛ ቋንቋ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ምን አሉ ? - ሁሉም ክልሎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ለትግራይ መልሶ ማቋቋም እንዲረዱ ፣ ትምህርት ጨምሮ ሁሉም የመንግስት አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ያስቻለው የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ነው ፡፡ ስለሆንም የፕሪቶሪያው የሰላም ውል አሁንም…
#Ethiopia

የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ አሁንም በኢትዮጵያ፣ የትግራይ መሬት ስለሚገኙ የ " ሻብዕያ ሰራዊት " ኃይሎች ተጠይቀው ነበር።

እሳቸውም ፦

" ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊት በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች የሻዕብያ ሃይል ገብቶ ነበር ፣ ከስምምነቱ በኋላ እንዲወጣ ተደርጓል።

አሁንም #የተቀሩ_ቦታዎች ካሉ ቦታዎቹ እና ቀበሌዎች ከፌደራል እና ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ቡድን በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲሰጠው እየሰራን ነው። ሁሉም ልክና መስመር ይይዛል !! " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎቶች ታገዱ። በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ተከናውኖ በአዳስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሠራተኞች የባህሪ እና የቴክኒክ ፈተና ተሰጥቶ ውጤቱ ይፋ መደረጉ ይታወቃል። በዚህም አዲስ በተጠናው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት መሰረት የሰራተኞች ድልድል ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከዛሬ…
" ዓርብ መጋቢት 6 ምሽት ወደ ትግበራ እንዲገባ ይታወጃል " - ዶ/ር ጣሰው ገብሬ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞችና አመራሮች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ወስደው የወደቁ ከ7,500 በላይ ሠራተኞች ከደረጃ ዝቅ ተደርገው የተመደቡበት የሥራ ዕርከን ድልድል መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤  " ፈተና ያላለፉት ከደረጃ ዝቅ ብለው ነው የሚሠሩት። ድልድሉ ስለተጠናቀቀ ደብዳቤው በየተቋሙ ይሰጣል " ብለዋል።

" ከሰኞ የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለ5 ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠናቸው ነው " ያሉት ኃላፊው " 2ኛው ዙር ሥልጠና ከመጪው ሳምንት ሰኞ መጋቢት 2 እስከ ዓርብ መጋቢት 6/ 2016 ዓ.ም. ይሰጣል። ዓርብ መጋቢት 6/ 2016 ዓ.ም. ምሽት ወደ ትግበራ እንዲገባ ይታወጃል፣ ሥልጠናው እንዳለቀ ወደ ትግበራ ነው የሚገባው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሠራተኞች ድልድል እንደ አዲስ ተካሂዶ እስኪጠናቀቅ ድረስ በከተማው ሁሉም ክ/ከተሞች " ማናቸውም የመሬት አገልግሎቶች " ለአጭር ጊዜያት መታገዳቸው ይታወሳል።

ታዲያ በመጪው ሳምንት ድልድሉ ይፋ ሲሆን የመሬት አገልግሎቶች መሰጠት ይቀጥላሉ ወይ ? ተብለው ከጋዜጣው የተጠየቁት ዶ/ር ጣሰው ፤ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። 

ጋዜጣው ግን ከመጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ የሥራ ዕርከን ድልድል በኋላ የመሬት ሥራ አገልግሎት በቅርብ እንደሚጀመር በዘርፉ ከተሰማሩ ምንጮች መስማቱን አመላክቷል። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PurposeBlack የፐርፐርዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሁን ሰዓት #አሜሪካ ሀገር እንደሚገኙ ተነግሯል። " አሜሪካ የሚገኙት ለስራ ነው " ያለው ድርጅቱ የፊታችን ሀሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና መግለጫም እንደሚሰጡ አመልክቷል። ዛሬ መግለጫ ሰጥተው የነበረው የድርጅቱ የቦርድ አባል እና የህግ አማካሪ ዶ/ር ኤርሚያስ ብርሃኑ ናቸው። ፐርፐዝ ብላክ ከቤቶቹ ግንባታ…
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ መግለጫ ሰጠ።

በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን መግለጫዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ውሉ ስለመቋረጡ ከገለጸ በኋላ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ህግ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ነጋ ምህረቴ እንዲሁም የህግ አማካሪ የሆነው "ምህረታብ እና ጌቱ አድቮኬትስ ኤል ኤል ፒ" መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይ የተነሱ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

- የድርድር ሂደቱ 8 ወራት ፈጅቷል። ቀድመን የተፈራረምነው የቀብድ ውል ነው። የቀብድ ውሉ የጊዜ ገደቡ ሦስት ወር ቢሆንም በእኛ በኩል በቅንነት 8 ወራት ጠብቀናል።

- ቀብድ ውሉን ከተፈራረምን በኋላ በእኛ በድርጅታችን ኃላፊ ጭምር እንዲሁም የመክፈል አቅም እንዳላቸው በተደጋጋሚ ማስረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም እንከፍላለን ከሚል ደብዳቤ በስተቀር የሚጠበቅባቸውን ብር ለመክፈል አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም።

- ግብር ለመክፈል ወደኋላ የምንል አይደለንም። የሚሸጠውም ህንጻ እዳ ያለበት አይደለም ቢጂአይ እዳ ያለበት ንብረት ለሽያጭ አያቀርብም።

- ካፒታል ጌን ኪሊራንስ ለማውጣት በቅድሚያ የሽያጭ ውል መሟላት አለበት። ይህ በሌለበት ሁኔታ ክሊራንስ ማውጣት አንችልም። ይህ በህጉ የተቀመጠ የታወቀ አሰራር ነው። ቢጂአይ ክሊራንስ ለማምጣት ዝግጁ ቢሆንም ነን በቀብድ ውሉ በተጠቀሰው መሰረት በቅደም ተከተል በተቀመጠው መሰረት የሽያጭ ውሉ ላይ መስማማት ያስፈልጋል። የተለያዩ ውይይቶች ቢደረግም እሱን መፈረም አልቻሉም።

- በቀብድ ውሉ መሰረት የተከፈለው 1 ቢሊዮን ብር +15 VAT ሲሆን ቀጣዩን ክፍያ ለመክፈል የሽያጭ ውሉን መፈረም እንዲሁም በውልና ማስረጃ ሌሎች የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ቀርቦ እንዲጸድቅ ይጠበቃል። ይህንን ለማድረግ ከሚያስፈልገው አንዱ የሽያጭ ውል ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ይህንን መፈረም ባለመቻሉ ውሉን ለማቋረጥ ተገደናል።

- ከፐርፐዝ ብላክ ጋር ያለን ውል ተቋርጧል። ዳግም ተመልሰን የምንደራደርበት ነገር የለም። ይህ ውል ከተጠናቀቀ በኋላ ህንጻውን የመሸጥ አሁንም ፍላጎት አለን።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ መግለጫ ሰጠ። በቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና በፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መካከል ሲካሄድ የቆየው አ/አ #ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ሽያጭ ድርድር ውል ለማሰር ባለመቻሉ ሂደቱ መቋረጡን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን መግለጫዎች መውጣታቸው ይታወሳል። ቢጂአይ ኢትዮጵያ ውሉ ስለመቋረጡ ከገለጸ በኋላ ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ የቢጂአይ…
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ፤ " ውሉ የተቋረጠው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው " ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

" የመክፈል አቅም እንዳላቸው በተደጋጋሚ ማስረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ' እንከፍላለን ' ከሚል ደብዳቤ በስተቀር የሚጠበቅባቸውን ብር ለመክፈል አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም " ሲልም ገልጿል።

ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ግብር ለመክፈል ወደኋላ የሚል እንዳልሆነና የሚሸጠውም ሜክሲኮ የሚገኘው የዋናው መስሪያ ቤት ህንጻ እዳ እንደሌለበት አስገንዝቧል።

እዳ ያለበት ንብረት ለሽያጭ እንደማያቀርብም ገልጿል።

" ከፐርፐዝ ብላክ ጋር ያለን ውል ተቋርጧል። " ያለው ቢጂአይ-ኢትዮጵያ " ዳግም ተመልሰን የምንደራደርበት ነገር የለም። ይህ ውል ከተጠናቀቀ በኋላ ህንጻውን የመሸጥ አሁንም ፍላጎት አለን " ብሏል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DStv

ቀላል እና ፈጣን መላ ለዲኤስቲቪ ደንበኞች በሙሉ!

ወደ ዲኤስቲቪ የጥሪ ማዕከል ሳይደውሉ በማንኛውም ሰዓት በሞባይልዎ *9299# በመደወል እና My DStv App ስምዎንና የስማርት ካርድ ቁጥርዎን አስገብተው የዲኤስቲቪ ክፍያ መጠንዎንና ቀኑን በቀላሉ ለማወቅ ፓኬጅ ለመቀየር ብሎም በቴሌብር ፣ በሲቢኢ ብር እና በአዋሽ ብር መክፈል ይችላሉ።

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk

የፕሌይ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3qJ95Us 

የአፕ ስቶር ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/45hIwEU

በተጨማሪም ስለ አገልግሎታችን ጥራት በሚደርስዎት የፅሁፍ መልዕክት ላይ ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

ይሞክሩትና የማይጠገብ የመዝናኛ አማራጭ ያለማቋረጥ ያጣጥሙ ፤ የእርስዎንም አስተያየት ያጋሩ!

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET'
 #PretoriaPeaceAgreement

በኢትዮጵያ ሆነ በትግራይ ክልል ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በሙሉነት መተግበር አጅግ አስፈላጊ መሆኑ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ገለፁ።  

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምነት የአተገባበር  ሂደት ያተኮረ ተፈራራሚ አካላትና የአፍሪካ ህብረት ያሳተፈ ግምገማ በአዲስ አበባ መካሄድ መጀመሩን አመልክተዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የፕሪቶሪያ የሰላም ውል በሙሉነት መተግበር የግድ ነው ያሉት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ፡ ስምምነቱ ሕግና ሕገ-መንግስታዊ የትግራይ ህዝብ ጥያቄዎች ባከተተ መልኩ መገምገም ያስፈልጋል ብለዋል። 

ስምምነቱ የጠብመንጃ ላንቃ ህልም በኢትዮጵያና በመላ ትግራይ ክልል በሚያጠፋ  መልኩ ሙሉ በሙሉ መፈፀምና መተግበር ይገባዋል ሲሉ አክለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያው የሰላም የስምምነት መሬት ላይ እንዴት እየተፈፀመና እየተተገበረ  አንደሆነ አስመልክቶ  በጀመረው ስትራቴጂክ ግምገማ ከስምምነቱ ፈራሚዎች በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአውሮፓ ህብረት ፣ ኢጋድ እና አሜሪካ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
                        
@tikvahethiopia            
የግጭት ዳፋ በትምህርት ተቋማት !

(በጋዜጠኛ ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ)

ተማሪ ፀሐይ አፈወርቅ (ለዚህ ዘገባ ስሟ ተቀይሯል) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ታጣቂዎች ሲሰነዝሩት በነበረው ጥቃት በወደመ ትምህርት ቤት በመማር ትምህርቷን ላለማቋረጥ የምትፍገመገም ተማሪ ነች። 

ታዳጊዋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል ምን አለች ?

" ትምህርት ቤቴ ስለፈረሰ የተሟላ አይደለም፣ ግን መማር እፈልጋለሁ።

የምማርበት ትምህርት ቤት በግጭት ምክንያት ከመውደሙ በፊት በተሟላ መቀመጫ ወንበር፣ ላይብረሪ፣ ኮምፒዩተሮች እንማር ነበር።

የምንማርበት ትምህርት ቤት መፈራረሱ ለትምህርት ያለኝን ልዩ ፍላጎት ስላልገደበው ብፍጨረጨርም ፣ ባልተሟላ ትምህርት ቤት መማር ከትምህርት አቀባበል ጀምሮ አንዳች አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል።

ውድድሩ በቴክኖሎጂ በሆነበት ዓለም ከቴክኖሎጅ ርቆ መማር ለአሁኑ ካለመማር ቢሻልም፣ ለችግሩ መፍትሄ ካልተሰጠው ደግሞ ለወደፊት ግን በዚህ መልኩ ከመማር አለመማር ሊሻል የሚችልበት ደረጃ እንዳይደረስ እሰጋለሁ።

በምንማርበት ትምህርት ቤት እንደቀድሞው የመማር ማስተማር ቁሳቁሶች እንዳልነበሩ ሆነዋል። ይህም አንዱ የግጭት አስከፊ ገጽታ የሚያስገነዝብ ነው።

ትምህርቷን ላለማቋረጥ የቻልኩትን እያደረኩ ነው። ቢሆንም ቁሳቁስ ባልተሟላበት ትምህርት ቤት መማራችንን ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች የትምህርት አቀባበላቸው እየተሸረሸረ ይገኛል። "

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/TikvahEthiopia-03-07

@tikvahethiopia
#Wolkite

ለአመታት በውሃ ችግር የሚፈተነው የወልቂጤ ከተማ ህዝብ ዛሬም " የመንግስት ያለህ " እያለ ነዉ።

ችግሩን ለመፍታት ጥረት ላይ እየተደረገ ነዉ የሚለው የከተማው አስተዳደር በበኩሉ " ሩጫ ላይ ነኝ " ይላል።

የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የውሀ ጀሪካኖች በጫኑ ባጃጆችና ጋሪዎች ተሞልተዉ ይታያሉ። ሆቴሎች የሻወር አገልግሎትን ከረሱ የቆዩ ይመስላሉ።

በአጠቃላይ ውሀ ቅንጦት መሆኑ ግለጽ ነዉ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ስለጉዳዩ የጠየቀዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ችግሩ ለአመታት የቀጠለ መሆኑን ተረድቷል።

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ የቧንቧ ውሀ በወር አንዴ በጣም ፈጠነ ሲባል በሁለት ሳምንት አንዴ ያውም ለሰአታት ብትመጣም አንዳንዴ የምትመጣዉ ሌሊት ሲሆን እንደምታመልጣቸዉ ይገልጻሉ።

ለሽንኩርትና ቲማቲም ከሚያወጡት እኩል ለውሀ ግዥ እንደሚያወጡ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ መንግስት ችግራቸዉን ይቀርፍላቸዉ ዘንድ በምሬት ይጠይቃሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ጥያቄ ከሰሞኑ በነበረ የምክር ቤት ጉባኤ የቀረበለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በበኩሉ የውሀ ችግሮች ያለመፈታታቸዉ ምክኒያት በየዞንና ከተሞች የተጀመሩ የውሀ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች እየተጀመሩ በመቆማቸዉ የተከሰተ መሆኑን ገልጾ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በሙሉ ሀይሉ እንደሚሰራ ገልጾ ነበር።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የህዝብ ጥያቄ  የቀረበላቸዉ የወልቂጤ ከተማ የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ቢሮ ሀላፊዉ  አቶ ዳዊት ሀይሌ በበኩላቸዉ ችግሩ መኖሩን በመግለጽ አሁን ላይ የቅሀ አጥረቱ ከተማዉን እየፈተነ መሆኑና ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉና ከሚጠበቁ መፍትሄዎች አንዱ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራው ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ዳዊት አክለዉም ፤ በቅርቡ የጉራጌ ዞን የውሀና መአድን ቢሮ ጋር በመሆን ሁኔታዎች እንደሚገመገሙና ለህዝብ አስፈላጊዉ መረጃ እንደሚሰጥ በመግለጽ ሁኔታዉን ከከተማዉ ባለስልጣናት ባለፈ የዞኑም ሆነ የበላይ አካላት በትኩረት እየሰሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።

መረጃው ወደ ወልቂጤ ተጉዞ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው አዘጋጅቶ የላከው።

ፎቶ ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የደብረ ብርሃን 2 - ሸዋ ሮቢት - ኮምቦልቻ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ ማምሻውን ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

በሸዋ ሮቢት አቅራቢያ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገኑ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የአፋር መዲና ሠመራን ጨምሮ በሰሜን ምሥራቅ የሚገኙ ከተሞች ዳግም ኃይል አግኝተዋል ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የቆዩት ሁሉም የሰሜን ምሥራቅ ከተሞች ኤሌክትሪክ ዳግም አግኝተዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia