TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia

ዛሬ ሌሊት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ፤ ዱከም ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተጨማሪም 11 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

መረጃው የቢሾፍቱ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Hadiya

የሀዲያ ዞን አዲስ አስተዳዳሪ ተሾመለት።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዛሬ 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የ6ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባዔ እያካሄደ ነው።

በዚህም #አቶ_ማቴዎስ_አኒዮን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ወደ ሐዋሳ እያመራ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ። በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ ማምሻውን አስከፊ የትራፊክ አደጋ ደርሷል። በዚህም አደጋ የ8 ሰው ሕይወት መቀጠፉ ተሰምቷል። አደጋው የደረሰው በዛሬው ዕለት ምሽት 12:30 ገደማ መነሻውን ከአርባምንጭ ከተማ አደርጎ ወደ ሐዋሳ ከተማ በመጓዝ ላይ…
" የሟቾች ቁጥር ከ8 ወደ 11 ከፍ ብሏል " - ኢስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ

ወደ ሐዋሳ ጉዞውን እያደረገ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ትላንት ማምሻውን መነሻውን ከአርባ ምንጭ አድርጎ ወዘ ሐዋሳ እያመራ የነበረ ተሽከርካሪ በዎላይታ ዞን በዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ዞንጋ " በተባለው ቦታ አስከፊ አደጋ እንደደረሰበት ይታወቃል።

በዚህም አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ8 ወደ 11 ከፍ ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊዉ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ዛሬ ጥዋት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በመኪናው ውስጥ ከነበሩት ውስጥ አብዛኛው ወጣት የጤና ቡድን አባላት መሆናቸዉን ገልጸው የደረሰዉ አደጋ ከፍተኛ ሀዘን መፈጠሩን ገልጸዋል።

ትናንት ከተገለጸዉ 8 ሰዎች በተጨማሪ ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ 3ቱ ማለፋቸዉን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 11 መድረሱን ገልጸዋል።

ኢስፔክተር ተስፋዬ ፤ " የጤና ቡድኑን ይዞ ይጓዝ የነበረዉ መኪና የፍሬን ችግር እንደነበረበት መረጃ ደርሶኛል " ያሉ ሲሆን አደጋው የደረሰው በዎላይታ ዞን ስር በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

አሁን ላይ በሐዋሳ ያኔት ሆስፒታል ውስጥ 2 ሰዎች በጽኑ ህክምና ክትትል ዉስጥ ሲሆኑ ከ5 በላይ ሰዎች ቀላል ጉዳት በማስተናገዳቸዉ ህክምና ተደርጎላቸዉ መሄዳቸው ተሰምቷል።

አስከፊ በተባለው በዚህ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው የጤና ስፖርት ቡድን አባላት ወጣቶች በሐዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑና ከማህበረሰቡ ጋር ተግባቢ ፣ በፀባያቸው በስራቸው ፣ በማህበራዊ ኑሯቸው በነዋሪዎች ዘንድ እጅግ የሚወደዱ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

በተከሰተው አደጋ እና በጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት ከተማዋ የሀዘን ማቅ ለብሳለች ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

መረጃዉን አዘጋጅቶ የላከዉ የሐዋሳው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ወጋገን_ባንክ

በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ወጋገን  ሞባይል መተግበሪያን ከፕለይስቶር ወይም ከአፕስቶር በማውረድ ምቾትዎ ተጠብቆ ሂሳብዎን ያንቀሳቅሱ። አገልግሎቱን ለማግኘት የወጋገን ባንክ ሂሳብ  በመክፈት የወጋገን የሞባይል ባንክ አገልግሎት *866# ይመዝገቡ፡፡

ከዚያም ቀጣዩን ሂደት ይከተሉ፤
(ሀ) መተግበሪያውን ከአፕስቶር ወይም ጎግል ፕሌይስቶር በማውረድ ስልክዎ ላይ ይጫኑ፤
(ለ) ወደ *866#  በመደወል “Activate Your Mobile Application” የሚለውን ይምረጡ፤
(ሐ) በአጭር ፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቱን ማስጀመሪያ  የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል  (Activation Code) ሲደርስዎት መተግበሪያው ላይ ይህንኑ ሚስጥራዊ ቁጥር ያስገቡ፤
(መ) የሚስጥር ቁጥር በመቀየር አገልግሎቱን መጠቀም መጀመር ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በ 866 ነፃ የስልክ መስመር  ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ፡፡

Download now:

Android:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.act.wegagen&hl

IOS:https://apps.apple.com/in/app/wegagen-mobile/id6472656143
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 ከእድሳትና የማስፋፋት ሥራ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር አሳውቋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት በረራዎች በተርሚናል 1 ይደረጋሉ።

በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በሳምንት 3 በረራዎችን ዛሬ መልሶ አስጀምሯል፡፡

ይህ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት አንዱ አካል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

በመቐለ የታገተ የ9 ዓመት ህፃን ልጅ ለማስለቀቅ 4 ሚሊዮን ብር ቢጠየቅም ልጁ ከ1 ሳምንት እግታ በኃላ በፓሊስና ህብረተሰብ ትብብር ነፃ ሊወጣ ችሏል።

ለመሆኑ እግታው እንዴት ተፈፀመ ? 

ልጁ ሳሚኤል መሓሪ ከበደ ይበላል። ገና 9 ዓመቱ ነው። ነዋሪነቱ በዓይደር ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ቀበሌ ነው።

ይኸው ልጅ አገር አማን ብሎ ቅዳሜና እሁድ በመንደሩ ከጓደኞቹ በመጫወትና በመቦረቅ ላይ እያለ በባጃጅ የመጡ ሰዎች አፍነው ወሰዱት።

ወላጆቹ ልጃችን ይመጣል ብለው ቢጠብቁም ብርሃን በጨለማ ተተክቶ የውሃ ሽታ ሆነባቸው።

ወደ ፓሊስ ቢያመለክቱም ፤ ወደ መንግስትና የግል የጤና ተቋማትና አብያተ ክርስትያናትም ጭምር ቢያፈላልጉ የሚወዱት ህፃን ልጃቸውን ማግኘት አልቻሉም።

ከቀናት ፍለጋ በኃላ የህፃኑ ቤተሰቦች ስልክ ተደወለላቸው።

አጋቾቹ ልጃቸው መታገቱንና እንዲለቀቅ ከተፈለገ 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ጠየቁ።

በዚህ መሀል ፓሊስ ብርቱ የክትትል እያደረገ ስለነበር ከሳምንት እልህ አስጨራሽ ፍለጋ በኃላ አጋቾቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ህፃኑም ለህክምና ምርመራ ወደ ጤና ተቋም እንዲላክ ሆኗል።

በድርጊቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መረጃው የመቐለ ፓሊስ ዛሬ ለጋዜጠኛች የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ዋቢ በማድረግ ያደረሰን የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵይም ቤተሰብ አባል ነው።
                      
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
" በፈንጂ እና በድማሚት ቢሞከረም ሊሳካ አልቻለም " - የከበሩ ማዕድናት አምራች ማህበር ከ12 ቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፤ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች የሚወጡበት መፍትሔ አሁንም ድረስ አለመገኘቱን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እና የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ተናግሯል። ትላንት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በመገኘት የዋሻውን የላይኛው…
#Update

" አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት ፈፅመዋል " - የደላንታ ወረዳ አስተዳደር

በናዳ ከተቀበሩ 18 ቀን የሞላቸው ወጣቶች ዛሬም አልተገኙም፡፡

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገል ጤና አካባቢ በማዕድን ቁፋሮ ላይ እንዳሉ ጉድጓድ ከገቡ 18ኛ ቀን የሆናቸውን ወጣቶች እጣፋንታ ለማወቅ የተደረጉ የህዝብና የመንግስት ጥረቶች እስካሁን እንዳልተሳኩ የደላንታ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።

አንዳንድ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ የለቅሶ ስነ ስርዓት መፈፀማቸው ተነግሯል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ወጣቶቹን ከተቀበሩበት ጉድጓድ ለማውጣት በሰው ኃይል ሲያደርጉት የነበረው ሙከራ ባለመሳካቱ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ለቁፋሮ እንቅፋት የሆነውን የአለት ክፍል በከባድ መሳሪያ ለማስወገድ የተለያዩ ሙከራዎች ሲደረጉ ቢቆይም የተገኘ ምንም ውጤት እንደሌለ ወረዳው ገልጿል።

ወረዳው ፤ በባባህላዊ መንገድ ቁፋሮዎች ለተከታታይ አንድ ሳምንት ያክል ሲካሄድ መቆየቱን ግን ሌላ ናዳ በቆፋሪዎች ላይ ሊያስከትል የሚችል ስጋት በመፈጠሩ በሰው ጉልበት ሲደረግ የነበረው ቁፋሮ መቆሙን አመልክቷል።

ከዚህ ቀጥሎ ዞን፣ ክልልና ፌደራል መንግስት በጋራ ተነጋግረው በባለሙያዎች ተጠንቶ ተራራውን የሚንድ መሳሪያ እንዲመጣ ተደርጎ 35 ቶን የሚመዝን ተተኳሽ ተጠምዶ ተንጠልጣይ ቋጥኙን በፍንዳታ ለማስወገድ ቢሞከርም ሳይቻል ቀርቷል ብሏል።

ዛሬም የአካባቢው የመከላከያ ኃላፊ፣ የዞን የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች በተገኙበት ቋጥኙን በተለያዩ ተተኳሾች ለማስወገድ የተደረገው ሙከራ እንዳልተሳካ ተገልጿል።

ዛሬ ብቻ ቋጥኙን 10 ጊዜ ያክል በታንክ ቢመታም ቋጥኙን ማስወገድ እንዳልተቻለ ወረዳው አሳውቋል።

የደቡብ ወሎ ዞን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በናዳው 20 ያክል ወጣቶች መቀበራቸውን ከዚህ ቀደም ቢያሳውቅም ወረዳው ግን በተጨባጭ አደጋው የደረሰባቸው 9 ወጣቶች ናቸው ብሏል፡፡

ተስፋ የቆረጡ አንዳንድ ቤተሰቦች ለቅሶ መቀመጣቸውን ያሳወቀው ወረዳው ፤ እስካሁን የተደረጉ ሙከራዎች ባይሳኩም የቤተሰብ ፍላጎት እስካለ ድረስ ወጣቶቹን በህይወት የማገኘት እድሉ በእጅጉ የጠበበ ቢሆንም አስከሬንም የሚገኝ ከሆነና በወግና በስርዓት የቀብር ስነስርዓት ለመፈጸም ፍለጋው በሰው ኃይልም ቢሆን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ፎቶ፦ የደቡብ ወሎ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Infinix_Hot40

በአጭር ደቂቃ ስልኮን ፉል ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አዲሱን ኢንፊኒክስ ‘Hot 40 pro’ የግሎ ያድርጉ!

#InfinixEthiopia #InfinixMobile #Infinix_Hot40 #Infinix_HotSeries
ከቴሌብር አካውንት ወደ ሌላ የቴሌብር ደንበኛ አካዉንት ገንዘብ መላኪያ ታሪፍ ላይ እስከ 80% ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በአዲሱ የታሪፍ ቅናሽ እስከ ብር 5,000 ሲልኩ 0.1% እንዲሁም ከብር 5,001-75,000 ለመላክ 5 ብር ብቻ የአገልግሎት ክፍያ ይፈጽማሉ።

የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ http://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ ወይም *127# ይደውሉ!

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia