TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OROMIA

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።

ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።

ኢሰመኮ ፦

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)

ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ #በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦

* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።

* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።

* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#CentralEthiopia

ትላንትና እሁድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣  በምሥራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ ይጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ 7 ሰዎችን ከጫነ " ባጃጅ " ጋር በመጋጨቱ ነው የደረሰው።

የ5ቱ ተጓዦች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ፤ በሁለቱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ ነበር። ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ከተላኩት መካከል አንደኛው ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ አልፏል።

@tikvahethiopia
#Oromia

ዛሬ ሌሊት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ፤ ዱከም ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተጨማሪም 11 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

መረጃው የቢሾፍቱ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Hadiya

የሀዲያ ዞን አዲስ አስተዳዳሪ ተሾመለት።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዛሬ 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የ6ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባዔ እያካሄደ ነው።

በዚህም #አቶ_ማቴዎስ_አኒዮን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

@tikvahethiopia